Telegram Web Link
#2024_Commencement

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ማስመረቅ ጀምረዋል፡፡

ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ -ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ - ሰኔ 27/2016 ዓ.ም

@tikvahuniversity
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የ2016 ዕጩ ተመራቂዎች አገር አቀፍ የመውጫ ፈተናን ሙሉ በሙሉ ማለፋቸውን ካምፓሱ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#WolloUniversity

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ግዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 83.27 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ዩኒቨርሲቲው ገለፀ።

የዩኒቨርሲቲው አምስት ትምህርት ክፍሎች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ እንደቻሉ ከተቋሙ የተገኘ መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
#TVTI_Exit_Exam

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለዕጩ ተመራቂ ተማሪዎቹ የመውጫ ፈተና እየሰጠ ነው፡፡

በዛሬው ዕለት እየተሰጠ የሚገኘውን የመውጫ ፈተና፣ በኢንስቲትዩቱ ለአራት ዓመታት ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ እንዲሁም ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ ሰልጣኞች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመተባበር እየተሰጠ በሚገኘው በዚህ ፈተና 2,135 ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተናውን እየወሰዱ ይገኛሉ።

በኢንስቲትዩቱ እንዲሁም በተቋሙ ሳተላይት ካምፓሶች አቅራቢያ የሚገኙ ዩኒቨርሲዎችን ጨምሮ በ11 የተለያዩ የፈተና ማዕከላት ፈተናው እየተሰጠ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ም/ዋ/ዳይሬክተር ሀፍቶም ገ/እግዚአብሄር ገልፀዋል፡፡

ከመውጫ ፈተናው አስቀድሞ ሰኔ 21/2016 ዓ.ም ለመስጠት ታቅዶ የነበረው #ሞዴል የመውጫ ፈተና አለመሰጠቱን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል፡፡

@tikvahuniversity
🎓🎓 ፕሮፌሰሮቹ አባት እና ልጅ

ፕሮፌሰር ባዬ ይማም (አባት) እና ፕሮፌሰር ቃለአብ ባዬ ይማም (ልጅ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሙያቸው እያገለገሉና ተተኪ ምሁራንን እያፈሩ የሚገኙ ፕሮፌሰሮች ናቸው።

ፕሮፌሰር ባዬ ይማም 44 ዓመታትን እንዲሁም ፕሮፌሰር ቃለዓብ ባዬ 15 ዓመታትን በመምህርነት፣ በተመራማሪነት እና በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች ያገለገሉና እያገለገሉ የሚገኙ ምሁራን ናቸው።

ሁለቱም የፒኤችዲ ዲግሪያቸውን በሰሩ በ10ኛው ዓመት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አገኝተዋል።

ፕሮፌሰር ቃለዓብ ባዬ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ከሰጣቸው ምሁራን መካከል አንዱ ናቸው። #AAU

@tikvahuniversity
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ 1,700 በላይ ተማሪዎችን ነገ ያስመርቃል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 20 በሦስተኛ ዲግሪ እንዲሁም 253 በሁለተኛ ዲግሪ  ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ3,500 በላይ ተማሪዎች ያስመርቃል።

በቅድመ እና ድኅረ ምረቃ መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁት ተማሪዎቹ፤ ሰኔ 26/2016 ዓ.ም በሳውላ ካምፓስ እና ሰኔ 27/2016 ዓ.ም በአባያ ካምፓስ እንደሚመረቁ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#WoldiaUniversity

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ግዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 93.1 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ዩኒቨርሲቲው ገለፀ።

ዩኒቨርሲቲው በ11 የትምህርት ክፍሎች ተማሪዎችን ያስፈተነ ሲሆን፤ አራት የትምህርት ክፍሎች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ እንደቻሉ ከተቋሙ የተገኘ መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው ተማሪዎች መካከል የ15ቱ ተማሪዎች ውጤት በድጋሚ እንዲታይ ጠይቀዋል፡፡

በትምህርት ክፍሉ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ 40 ተማሪዎች መካከል 25 ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ያገኙ ሲሆን የቀሩቱ 15 ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣት አልቻሉም፡፡

ተማሪዎቹ ውጤታቸው በድጋሜ እንዲታይላቻው ትምህርት ክፍሉ ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

ተማሪዎቹ የተሻለ ውጤት ያላቸው በመሆናቸው ውጤታቸው በድጋሜ እንዲጣራላቸው የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ ለቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ጽ/ቤት ዱራሜ ካምፓስ በፃፈው ደብዳቤ ጠይቋል።

@tikvahuniversity
#RayaUniversity

ራያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን የመጀመርያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ነገ ሰኔ 25/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

@tikvahuniversity
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ለ5ኛ ዓመት የህክምና ተማሪዎች በውጪ ፈታኞች የብቃት ምዘና ሰጥቷል።

በህክምና ትምህርት ቤት ስር የሚገኙ 35 የህክምና ተማሪዎች ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና የፌደራል ሆስፒታሎች በመጡ ሲኒየር ሀኪሞች የብቃት ፈተናውን ወስደዋል።

በውጪ ፈታኞች (External Examiners) ከተፈተኑ 35 ተማሪዎች መካከል 29ኙ በተሻለ ውጤት ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ ሲሆን ቀሪዎች ለሦስት ወራት ያክል የጎደላቸውን በመሙላት ቀጣዩን ዙር እንደሚቀላቀሉ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በበይነ መረብ ለሚወስዱ ተማሪዎች ሞዴል ፈተና እየተሰጠ ነው።

ሞዴል ፈተናው በክልሉ በሚገኙ አምስት ማዕከላት ማለትም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዋና ጊቢና ዱራሜ ካምፓስ፣ በወራቤ እና በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም  ሆሳዕና ሊች ጎጎ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየተሰጠ ነው።

በክልሉ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሚወስዱ ከ 47 ሺህ በላይ ተማሪዎች ውስጥ 1,401 ተማሪዎች በበይነ መረብ ይፈተናሉ ተብሏል።

ሞዴል ፈተናው እስከ ሰኔ 28/2016 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
#DebreMarkosUniversity

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ግዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 96 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ዩኒቨርሲቲው ገለፀ።

@tikvahuniversity
#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ 1,700 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 20 በሦስተኛ ዲግሪ፣ 253 በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም ከ 1,400 በላይ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity
2024/10/01 18:32:59
Back to Top
HTML Embed Code: