Telegram Web Link
#AssosaUniversity

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከ 1,500 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ፣ በኤክስቴንሽን እና በክረምት መርሐግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 1,538 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 140 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የተመረቁ ናቸው፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#JimmaUniversity ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ 1,700 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል 20 በሦስተኛ ዲግሪ፣ 253 በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም ከ 1,400 በላይ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው። @tikvahuniversity
ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ውጤት የተመረቁት መንትዮቹ

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል መንትዮቹ ዮሴፍ ሞላወርቅ እና ሰለሞን ሞላወርቅ ይገኙበታል።

መንትዮቹ ከመዋለ ህጻናት ጀምሮ በአንድ ክፍል የተማሩ ሲሆን፤ በጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባዮ-ሜዲካል ምህንድስና ትምህርት ክፍል ትምህርታቸውን ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ተመሳሳይ የአጠቃላይ ውጤት (CGPA) እና ተቀራራቢ የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ውጤት (71 እና 73) በማምጣት ተመርቀዋል።

@tikvahuniversity
#DireDawaUniversity

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ 42 የትምህርት መስኮች በቅድመ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

ተማሪዎቹ በመደበኛ፣ በኤክስቴንሽን እና በእረፍት ቀናት መርሐግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁና አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በኦንላይን ለሚወስዱ ተፈታኞች #ሞዴል_ፈተና ዛሬ ተሰጥቷል።

የሙከራ ፈተናው አብርሆት ቤተ-መፃሕፍትን ጨምሮ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የኦንላይን መፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠቱን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

ከሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን አገር አቀፍ ፈተና፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስኬት ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ቢሮው ጠቁሟል።

ቢሮው ከኢትዮ ቴልኮም እና ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ቅድመ ዝግጅት ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን የቢሮው ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
#BahirDarUniversity

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ግዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 93.3 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጿል።

@tikvahuniversity
#DebreTaborUniversity

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 544 ተማሪዎች አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው 11ኛ ዙር ተመራቂዎች፣ በቅድመ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ተመራቂዎቹ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ከ92 በመቶ በላይ በማምጣት ለምረቃ መብቃታቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አነጋግረኝ ጋሻው (ዶ/ር) ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
#WallagaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ 2,300 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል።

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ነቀምቴ ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 2,335 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ስልጠናቸውን የተከታተሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#RayaUniversity

ራያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 497 ተማሪዎች አስመረቀ።

ከተመራቂዎቹ መካከል 141 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 356 ደግሞ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች ናቸው፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታና የራያ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ፤ የፌዴራል መንግሥት የዩኒቨርሲቲውን አቅም ማጎልበት የሚያስችል ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
#SalaleUniversity

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1,197 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity
የግል የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት መቼ ይፋ ይሆናል?

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ውጤት ሰኔ 21/2016 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤት እስካሁን ይፋ አልተደረገም። ይህንንም ተከትሎ የግል ተፈታኞች በርካታ ጥያቄዎችን ለቲክቫህ አድርሰዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልገሎት ዴስክን ጠይቀናል።

"ከግል ተፈታኞች ውጤት ጋር በተያያዘ ያልተጠናቀቁ ነገሮች በመኖራቸው ውጤቱ ይፋ አለመደረጉን" የዴስኩ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ለቲክቫህ ተናግረዋል።

"ቀሪ መጠናቀቅ ያለባቸው ጉዳዮች እንዳለቁ የግል ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ይደረጋል" ብለዋል።

የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ገበየሁ በበኩላቸው፤ "ከግል ተፈታኞች አጠቃላይ መረጃ እና ክፍያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሲጠናቀቁ ውጤቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚለቀቅ" ለቲክቫህ ተናግረዋል።

ማኅበሩ 178 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በአባልነት ይዟል፡፡

ዘንድሮ 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ማስፈተናቸው ይታወቃል።

@tikvahuniversity
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በቡና ሳይንስና ኢኮኖሚክስ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስመርቃል።

ዩኒቨርሲቲው ነገ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ያካሒዳል።

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከ 2,800 በላይ ተማሪዎችን የሚያስመርቅ ሲሆን፤ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 127 ተማሪዎች ይገሀኙበታል፡፡

@tikvahuniversity
Active and graduate UG and PG student datasheet.xlsx
21.9 KB
#ETA

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2015 ዓ.ም እና በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎችን ዝርዝር እንዲልኩ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳስቧል።

ተቋማቱ ፈቃድ በተሰጣችሁ የትምህርት መስኮች፣ የትምህርት ደረጃ፣ መርሐግብር እና ካምፓስ ያስመረቋቸውንና ከዚህ በፊት ያልተላኩ የተመረቁ ተማሪዎች መረጃንም እንዲልኩ ተብሏል።

በዚህም መረጃዎቹን እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም በሶፍት እና በሀርድ ኮፒ እንድትልኩ ባለሥልጣኑ አሳስቧል።

የተመራቂ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ መላኪያ ቅፅ ለውጥ ማድረጉን ባለሥልጣኑ ገልጿል።

(አዲሱ መረጃ መላኪያ ቅፅ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#MizanTepiUniversity

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 279 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ቴፒ ካምፓስ በ 16 የትምህርት ክፍሎች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል ሰባቱ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ (ሚዛን ካምፓስ) በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነገ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

@tikvahuniversity
በዲላ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ግዜ የወሰዱ የአንስቴዥያ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ውጤት አስመዝግበዋል።

በተመሳሳይ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ግዜ የወሰዱ የአንስቴዥያ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸው ተሰምቷል። #HakimEthio

@tikvahuniversity
2024/10/01 16:41:55
Back to Top
HTML Embed Code: