Telegram Web Link
#InjibaraUniversity

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ዕጩ ተመራቂዎች መካከል 83 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ገልጿል።

@tikvahuniversity
#BongaUniversity

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ከወሰዱ ዕጩ ተመራቂዎች መካከል 87.47 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ካስፈተናቸው 1,269 ተማሪዎች 1,110 (87.47 በመቶ) ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸው ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#WolkiteUniversity

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ መርሐግብር በ50 ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው ዕጩ ተመራቂዎች 85.07 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን አሳውቋል።

በተከታታይ ፕሮግራም የተፈተኑ ተማሪዎች ጨምሮ የ2016 አማካይ ውጤቱ 82 በመቶ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahuniversity
#WachemoUniversity

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና ከወሰዱ ዕጩ ተመራቂዎቹ መካከል 86.13 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ገልጿል።

@tikvahuniversity
#DebreBerhanUniversity

በደብረ ብረሃን ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ግዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 90.8 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ዩኒቨርሲው ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ ፕሮግራም በ13 የትምህርት ክፍሎች የመውጫ ፈተና ያስፈተነ ሲሆን በአምስት ትምህርት ክፍሎች ሙሉ በሙሉ ያሳለፈ ሲሆን፤ በሌሎች ትምህርት ክፍሎች ደግሞ ከ80-95 በመቶ የማለፊያ ውጤት መመዝገቡን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

@tikvahuniversity
#DebreTaborUniversity

በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ግዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 92 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ዩኒቨርሲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#SalaleUniversity

በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ግዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 86.07 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ዩኒቨርሲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ሰሞኑን የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና በሁለት የትምህርት መስኮች ያስፈተነ ሲሆን፤ ካስፈተናቸው ዕጩ ተመራቂዎች የአነስቴዢያ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ እንዲሁም የሕክምና ተማሪዎች 90 በመቶ ማለፋቸውን ገልጿል።

@tikvahuniversity
#MaddaWalabuUniversity

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ1,400 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን የተከታተሉ 1,489 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

@tikvahuniversity
#BongaUniversity

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸው 34 ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1,250 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

ከአጠቃላይ ተመራቂዎቹ መካከል 142ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በቡና ሳይንስ በድኅረ ምረቃ መርሐግብርም 11 ተማሪዎችን እያሰለጠነ እንደሚገኝ የተቋሙ ፕሬዝዳንት ጴጥሮስ ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በቀጣይ በዘርፉ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ለማሰልጠን ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
#AksumUniversity

አክሱም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ1 ሺህ በላይ ተማሪዎች አስመርቋል።

በሰሜኑ ጦርነት ከፍተኛ ውድመት ያስተናገደው ዩኒቨርሲቲው፤ 1,050 ተማሪዎችን አስመርቋል።

በነሐሴ 2015 ዓ.ም ዳግም የማስተማር ሥራውን የጀመረው ዩኒቨርሲቲው፤ 14ኛ ዙር ሰልጣኝ ተማሪዎቹን በዛሬው ዕለት ማስመረቁ ታውቋል።

@tikvahuniversity
#SamaraUniversity

በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ግዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 93 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ዩኒቨርሲቲው ገለፀ።

የዩኒቨርሲቲው ሁለት ኮሌጆች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ እንደቻሉ ተቋሙ ያደረሰን መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
#National_GAT

ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) መቼ ይሰጣል?

የ2016 ዓ.ም የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) መቼ እንደሚሰጥ በርካቶች ለቲክቫህ ጥያቄያቸውን አድርሰዋል።

በጉዳዩ ላይ አንድ የትምህርት ሚኒስቴር አመራርን የጠየቅን ሲሆን፤ 3ኛ ዙር አገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) በሐምሌ ወር የመጨረሻ ሳምንት እንደሚሰጥ ለማወቅ ችለናል።

2ኛው ዙር የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና በህዳር 2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
በወሎ ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ትምህርት ቤት አገር አቀፍ የመውጫ ፈተናን የወሰዱ የ2016 ዕጩ ተመራቂዎች ሙሉ በሙሉ ማለፋቸውን አሳውቋል፡፡

የህክምና ትምህርት ቤቱ ደግሞ ካስፈተናቸው 97.5 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/10/01 16:25:08
Back to Top
HTML Embed Code: