Telegram Web Link
በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የተቋሙ ተማሪዎች 80.75 በመቶዎቹ ፈተናውን እንዳለፉ ዩኒቨርሲቲው አሰውቋል፡፡

በአምስት የትምህርት ክፍሎች እና የትምህርት ፕሮግራሞች ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች እንደዩኒቨርሲቲ 80.75 በመቶዎቹ ማለፋቸውን የዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ገልጿል፡፡

በመደበኛ እና በክረምት ፕሮግራሞች የፋርማሲ ትምህርት ቤት እና የኤሌክትሪክና ኮምፒውተር ምህንድስና ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ሙሉ በሙሉ (100%) እንዳለፉ ጽ/ቤቱ አረጋግጧል።

@tikvahuniversity
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 1,658 የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራንን አስመርቋል፡፡

መምህራኑ በደብረ ብርሃን እና አሰላ የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች ለሁለት ዓመታት ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው፡፡

ሰልጣኞቹ በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል።

ቢሮው በ2014 ዓ.ም ሁለት ሺህ የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራንን አሰልጥኖ ማስመረቁን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት ገፅ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

@tikvahuniversity
#RayaUniversity

ራያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 76 ተማሪዎች ያስመርቃል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ባካሔደው መደበኛ ስበሰባ በአራት ኮሌጆችና በ13 የትምህርት ክፍሎች ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ 76 ተማሪዎች እንዲመረቁ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

ራያ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች 96.47 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ፈተናውን እንዳለፉ መገለፁ አይዘነጋም፡፡

@tikvahuniversity
#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም. የተመደባችሁ አዲስ የአንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም. በሪሚዲያል ፕሮግራም በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን የካቲት 20 እና 21/2016 ዓ.ም. እና በቅጣት ምዝገባ የካቲት 22/2016 ዓ.ም. መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➢ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት፣
➢ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➢ 3x4 መጠን ያለው አራት ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

@tikvahuniversity
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 457 ተማሪዎች የፊታችን እሑድ ያስመርቃል።

ከተመራቂዎቹ 101 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ሲሆን ቀሪዎቹ 356 ተማሪዎች ደግሞ የመጀመሪያ ዲግሪ ሰልጣኞች ናቸው፡፡

በቅርቡ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ነጥብ ያመጡ 246 የዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎችም በዕለቱ ይመረቃሉ፡፡

@tikvahuniversity
በኮሌራ የተያዙ ተማሪዎች በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ

በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተከስቷል በተባለ የኮሌራ በሽታ ከ400 የማያንሱ ተማሪዎች መያዛቸውን በተቋሙ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ከተከሰተ አንድ ሳምንት ሆኖታል ስለተባለው በሽታም ሆነ ስለደረሰ ጉዳት ከዩኒቨርሲቲው እንዲሁም ከክልሉ ጤና ቢሮ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱን ሬዲዮ ጣቢያው ገልጿል። 

ይሁን እንጂ አስተያየት የሰጡ ተማሪዎች በበሽታው ተይዘው ህክምና ሲደረግላቸው ከነበሩት መካከል አንዳንዶቹ እያገገሙ ይገኛሉ ብለዋል።

በዩኒቨርሲቲው ተከሰተ ስለተባለው ወረርሽኝ ለተማሪዎች በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። በሽታው "በውኃ ብክለት" ወይም "የግል ንፅህና ባለመጠበቅ" የመጣ ነው የሚሉ አስተያየቶች ተሰምተዋል።

በዚህም ምክንያት ተማሪዎች ወደ መመገቢያ አዳራሾች ሲገቡ ለጥንቃቄ እንዲታጠቡ ሲደረግ ነበር ተብሏል።

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች የፊታችን እሑድ እንደሚያስመርቅ ይጠበቃል። #ዶይቼ_ቬለ

@tikvahuniversity
ወሎ ዩኒቨርሲቲ 21 የእንሰሳት ሕክምና ዶክተሮችን አስመረቀ።

ተመራቂዎቹ (13 ወንድ እና 8 ሴት) ባለፉት ሰባት ዓመታት ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

የዩኒቨርሲቲው የእንሰሳት ሕክምና ትምህርት ቤት በተጨማሪም አንድ የእንሰሳት ሕክምና ዶክተር በስፔሻሊቲ ፕሮግራም አስመርቋል።

@tikvahuniversity
#ተጨማሪ

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በስፔሻሊቲ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 27 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ ላለፉት አራት ዓመታት በቀዶ ጥገና እንዲሁም በማህጸንና ጽንስ በስፔሻሊቲ ፕሮግራም ስልጠናቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ከተመራቂዎች መካከል ሦስቱ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#WallagaUniversity

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ወደ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አድጓል።

ሆስፒታሉ ተርሺየሪ ሆስፒታሎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶችን ማሟላቱን ተከትሎ ወደ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ማደጉን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#AmboUniversity

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ለሦስት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ሰጥቷል።

በዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ የሙሉ ፕሮፌሰርነት የተሰጣቸው ምሁራን፦

1. ዶ/ር ሙሉጌታ ነገሪ ቱሉ - በግብርና ኢንቶሞሎጂ
2. ዶ/ር አጫሉ ቺምዲ ያሪሞ - በአፈር ሳይንስ
3. ዶ/ር ብዙነሽ ሚደቅሳ ቦረና - በተላላፊ የእንሰሳት በሽታዎች ጥናት

@tikvahuniversity
#WolkiteUniversity

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 463 ተማሪዎች አስመረቀ።

ከተመራቂዎቹ 101 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

በዛሬው ዕለት ከተመረቁት መካከል በቅርቡ የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ነጥብ ያመጡ 246 የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎችም ይገኙበታል፡፡

@tikvahuniversity
2024/10/01 07:16:24
Back to Top
HTML Embed Code: