Telegram Web Link
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን 434 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በሕክምናና ጤና ሳይንስ፣ በኪነ-ህንፃ ምህንድስና እንዲሁም በተለያዩ የሁለተኛ ዲግሪ ፕርግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ከአጠቃላይ ተመራቂዎቹ 58 ተማሪዎች የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ተመራቂዎች መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#WallagaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን 1,347 ተማሪዎች አስመርቋል።

ሰሞኑን የመውጫ ፈተና በድጋሜ ወስደው ያለፉ 709 ተማሪዎች ከተመራቂዎቹ መካከል ይገኙበታል።

ከአጠቃላይ ተመራቂዎቹ ዘጠኝ የሦስተኛ ዲግሪ እንዲሁም 422 የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ተመራቂዎች መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#WachemoUniversity

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 2,668 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሐግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል 43 የሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎች ሲሆኑ 141 ተመራቂዎች ደግሞ በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#HawassaUniversity

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የሕክምና የሙያ መስኮች ያስተማራቸውን 493 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በሁለተኛ ዲግሪ፣ በስፔሻሊቲ፣ በመጀመሪያ ዶክትሬት ዲግሪ እንዲሁም በሌሎች የጤና መስኮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

የመውጫ እና የሙያ ፈቃድ ፈተና ከወሰዱ የኮሌጁ ተመራቂዎች መካከል 99.5 በመቶ ፈተናውን ማለፋቸው ይታወቃል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 61 በመቶ የሚሆኑት በማዕረግ እና በከፍተኛ ማዕረግ መመረቃቸውም ተገልጿል።

ዶ/ር ሶስና ሸለመ 3.95 CGPA በማምጣት የሜዳልያና የልዩ ሽልማት ባለቤት ሆናለች። #ኢዜአ

@tikvahuniversity
#HaramayaUniversity

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 627 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው

ዩኒቨርሲቲው በጤናና ህክምና ሳይንስ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ እንዲሁም በኮምፒዩተር ሳይንስ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

ከተመራቂ ተማሪዎቹ መካከል 327 ተማሪዎች በጤናና ህክምና ሳይንስ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#ArsiUniversity

የአርሲ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 214 የሕክምና ባለሙያዎችን አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ 13ቱ የስፔሻሊቲ ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

በቅርቡ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና በአራት የትምህርት መስኮች የወሰዱ የህክምናና ጤና ሳይንስ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ፈተናውን ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው መግለፁ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 95.41 በመቶ ተፈታኞች የማለፍያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ 524 የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 70 በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመደበኛ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ይገኙበታል።

ካምፓሱ በተከታታይ መርሐግብር ስልጠናቸውን የተከታተሉ 454 የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችንም አስመርቋል።

@tikvahuniversity
#DireDawaUniversity

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 386 ተማሪዎች አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 29 ተማሪዎች በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የበለፀገ ‘’የቤንሻንጉል-እንግሊዝኛ-አማርኛ መዝገበ ቃላት መተግበሪያ’’ ይፋ ሆኗል፡፡

Tri-lingual Mobile App Dictionary የሆነው መተግበተሪያው፤ በዩኒቨርሲቲው የኮምፒዉቲንግና ኢንፎርማትክስ ኮሌጅ መምህራን መበልፀጉ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ መምህራን የሽናሻ እና ጉሙዝ ቋንቋዎችን ጨምሮ የተለያዩ መተግበሪያዎች በልፅገው ለአገልግሎት መብቃታቸው ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

የሞባይል መተግበሪያው ለአጠቃቀም ቀላልና ምቹ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን መተግበሪያው የመጀመሪያ ስሪት (First Version) እንደመሆኑ በቀጣይ እየተሻሻለ እንደሚሔድ ተመላክቷል፡፡

@tikvahuniversity
#WolkiteUniversity

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያውን አካዳሚያዊ ጆርናል በይፋ አስጀምሯል።

"JEFORE Ethiopian Journal of Applied Sciences" የተሰኘው ጆርናሉ፤ የአካዳሚክ ልህቀት ማምጣት እና ምሁራዊ ውይይትን ማጎልበት ግብ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሁለገብ በሆነው ጆርናል፤ በተፈጥሮ ሳይንስ፣ ማህበራዊና ስነ-ሰብ ሳይንስ፣ ጤናና ሕክምና ሳይንስ፣ ግብርና ሳይንስ፣ ምህንድስናና ቴክኖሎጂ፣ ኮምፒውተርና ኢንፎርማቲክስ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ እንዲሁም በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የምርምር ግኝቶች፣ ግምገማዎች እና ፅሁፎች እንደሚወጡበት ተመላክቷል፡፡

@tikvahuniversity
#Update

የ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ውጤት ተለቋል፡፡

በቅርቡ የተሰጠውን የመውጫ ፈተናው የወሰዱ #የግል እና #የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ የካቲት 18/2016 ዓ.ም ጀምሮ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

የመውጫ ፈተና የወሰዱ #የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ ውጤታቸውን ሲመለከቱ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

ውጤት ለማየት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ 👉 https://result.ethernet.edu.et

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ2016 ዓ.ም በጨቅላ ህፃናት ነርሲንግ ፖስት ቤዚክ ስፔሻሊቲ ለመማር የምትፈልጉና መስፈርቱ የምታሟሉ እስከ የካቲት 23/2016 ዓ.ም በተቋሙ ሬጅስትራል ቢሮ በመገኘት መመዝገብ ትችላላችሁ።

የመመዝገቢያ መስፈርቶች፦

- በነርሲንግ ዲፕሎማ ደረጃ 4 የተመረቁ፣
- በሚድዋይፍሪ ዲፕሎማ የተመረቁ፣
- የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ ማምጣት የሚችል/የምትችል ወይም ከፍለው መማር የሚችሉ፣
- ኮሌጅ የሚያዘጋጀውን የቃል እና የፁሑፍ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል፣
- ሙሉ ጤነኛ የሆነ/የሆነች፣
- አንድ ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ያላት።

የቃል እና የፁሑፍ ፈተና የካቲት 24/2016 ዓ.ም ይሰጣል የተባለ ሲሆን አስፈላጊ ዶክመንት ያላሟሉ ፈተናው ላይ እንደማይቀመጡ ተገልጿል።

Note:

- ኮሌጁ ማደሪያ እና ምግብ አያዘጋጅም።
- የትምህርት ማስረጃ online መግባት አለበት፡፡

ለበለጠ መረጃ፦ 0112756089

@tikvahuniversity
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ተመርቆ ከፊል አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሉን በ2011 ዓ.ም በባለቤትነት ተረክቦ ቀሪ ግንባታዎችን በማጠናቀቅ ለአገልግልት ክፍት እንዲሆን አድርጓል፡፡

የሆስፒታሉን ቀሪ የግንባታ ሥራዎች ለማከናወን 500 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 400 የህሙማን አልጋዎች እንደተገጠሙለት ተገልጿል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል ለአጎራባች ክልሎችም አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።

@tikvahuniversity
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች የፊታችን እሑድ ያስመርቃል።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ሲያስተምራቸው የቆዩ ተማሪዎችን እሑድ የካቲት 24/2016 ዓ.ም ያስመርቃል፡፡

በቅርቡ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ውስጥ 97.6 በመቶዎቹ ፈተናውን እንዳለፉ ተቋሙ መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች የፊታችን እሑድ ያስመርቃል።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ሲያስተምራቸው የቆዩ ተማሪዎችን እሑድ የካቲት 24/2016 ዓ.ም ያስመርቃል፡፡

በቅርቡ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና የወሰዱ 160 የዩኒቨርሲቲው የህክምናና ጤና ሳይንስ ተማሪዎች ሁሉም ፈተናውን እንዳለፉ ተቋሙ መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
2024/10/01 09:19:43
Back to Top
HTML Embed Code: