Telegram Web Link
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 551 ተማሪዎች አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው በጤና ሳይንስ ኢንስቲቲዩት እና በፔትሮሊየም ምህንድስና ትምህርት ክፍል በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም እንዲሁም በተቋሙ የድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ተማሪዎችን አስመርቋል። 

ተቋሙ ለመጀመሪያ ጊዜ በፔትሮሊየም ኢንጂነሪንግ የሰለጠኑ 56 ተማሪዎች ማስመረቁን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በሺር አብዱላሂ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
በመቱ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት ተማሪ የነበረው ወጣት ራሱን ማጥፋቱን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በዩኒቨርሲቲው የእንግሊዘኛ ቋንቋና ስነ-ፅሁፍ ትምህርት ክፍል የ4ኛ ዓመት ተማሪ የነበረው ቃለአብ አውዴ ትኩ ራሱን አጥፍቶ መገኘቱን ዩኒቨርሲቲው ጠወቁሟል።

መላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተማሪ ቃለአብ ህልፈት የተሰማውን መሪር ሀዘን ይገልፃል ያለው ዩኒቨርሲቲው፤ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጆቹ እና ለጓደኞቹ መፅናናትን ተመኝቷል።

@tikvahuniversity
ይመዝገቡ!

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ቀርተዋል።

የተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ የካቲት 30/2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል።

የመደበኛ እና ማታ መርሐግብር ተማሪዎች ምዝገባ 👉 በትምህርት ቤቶች

የግል | የርቀት | የበይነመረብ ተማሪዎች ምዝገባ 👉 በክፍለ ከተማ፣ በወረዳ እና በትምህርት ጽ/ቤቶች

በ2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ870 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ይጠበቃል።

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዲጂታል ትምህርት መስጠት የሚያስችለውን መልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ አስመርቋል።

ዘመናዊ ስቱዲዮው የዲጂታል ትምህርት አብዮት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለማምጣት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ፕሮጀክቱ በትምህርት ሚኒስቴር፣ በአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ እና በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ትብብር ገቢራዊ መሆኑ ተገልጿል።

800,000 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና 35,000 መምህራን ለአምስት ዓመት በሚቆየው ፕሮግራም ተደራሽ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

ፕሮግራሙ ተፈፃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ዘመናዊ መልቲ ሚዲያ ስቱዲዮዎች በአዲስ አበባ፣ ባሕር ዳር፣ ጅማ፣ ድሬዳዋ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች መቋቋማቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በመቱ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት ተማሪ ለነበረውና ራሱን ላጠፋው ተማሪ ቃለአብ አውዴ የሻማ ማብራት ስነስርዓት በዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ተካሒዷል።

ተማሪ ቃለአብ በዩኒቨርሲቲው የእንግሊዘኛ ቋንቋና ስነ-ፅሁፍ ትምህርት ክፍል የ4ኛ ዓመት ተማሪ ነበር።

ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጆቹ እና ለጓደኞቹ መፅናናትን እንመኛለን።

@tikvahuniversity
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለሦስተኛ ካምፓሱ የስያሜ ለውጥ አድርጓል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለወሎ ተሪሸሪ ኬር ካምፓሱ ስያሜ ለመቀየር ኮሚቴ በማቋቋም ከመከረ በኋላ ስያሜውን አስመልክቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህም የዩኒቨርሲቲው ሦስተኛ ካምፓስ “ወሎ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ወሎ ልዕለ ህክምና እና ማስተማሪያ ሆስፒታል" ልዕለ ህክምና ካምፓስ በሚል ስያሜ እንዲጠራ ወስኗል፡፡

ካምፓሱ "Wollo University College of Medicine and Health Science, Wollo Tertiary Care and Teaching Hospital" Tertiary Care Campus በሚል የሚጠራ ይሆናል፡፡

@tikvahuniversity
#SalaleUniversity

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች የፊታችን ሐሙስ የካቲት 28/2016 ዓ.ም. ያስመርቃል፡፡

ባለፈው ወር የተሰጠውን የመውጫ ፈተና የወሰዱ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ፈተናውን ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል 25 የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን አሰልጥኗል፡፡

ተማሪዎቹ መሰረታዊ የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ እና የኤሌክትሮኒክስ ክህሎት ስልጠናዎችን ወስደዋል፡፡

በዩነቨርሲቲው አካባቢ ለሚገኙ ተማሪዎች በዕረፍት ቀናት መርሐግብር ለሁለት ወራት የተሰጠው ስልጠናው፤ በዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ ነው፡፡

@tikvahuniversity
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለሚያከናውናቸው ሥራዎች አስፈላጊ የሆኑ የተለያዩ መመሪያዎች ፀድቀው ሥራ ላይ መዋላቸውን አሳውቋል፡፡

ሥራ ላይ የዋሉት መመሪያዎች የትኞቹ ናቸው?

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፕሮግራም የዕውቅና አሰጣጥ መመሪያ፣
የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥና የአቻ ግመታ መመሪያ፣
የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ የክትትል እና ቁጥጥር መመሪያ፣
የቴክኒክና ሙያ የትምህርትና ስልጠና የተቋምና የፕሮግራም ዕውቅና አሰጣጥ መመሪያ፣
የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ፡፡

መመሪያዎቹን የባለሥልጣኑ ድረ-ገጽ www.neta.gov.et በመግባት Resources የሚለውን በመጫን ያገኟቸዋል፡፡

@tikvahuniversity
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ 2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ነባር የቅድመ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ምዝገባ መጋቢት 05 እና 06/2016 ዓ.ም. መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎችም በተገለፁት ቀናት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/10/01 09:16:03
Back to Top
HTML Embed Code: