Telegram Web Link
Tikvah-University
#AAU #GAT በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) በመጀመሪያ ዙር ለመውሰድ አመልክታችሁ ፈተናውን ሳትወስዱ የቀራችሁ ቀጣይ ፈተናውን የምትወስዱበት ቀን በቅርቡ እንደሚገለፅ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። የተራዘመው የሁለተኛ ዙር GAT ፈተና የማመልከቻ ግዜ ዛሬ መስከረም 8/2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይታወቃል፡፡ እስካሁን ካላመለከቱ በቀሩት ሰዓታት በኦንላይን…
AAUGAT_Schedule neww.xls
146 KB
#AAU #GAT

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) በመጀመሪያ ዙር ለመውሰድ አመልክተው ፈተናውን ሳትወስዱ ለቀሩ አመልካቾች ፈተናውን መስከረም 15/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ረዕቡ መስከረም 15/2017 ዓ.ም ጠዋት ለሚሰጠው ፈተና የተፈታኞች ኮድና ስም ዝርዝር፣ የመፈተኛ ካምፓስ፣ የመፈተኛ ላብ እንዲሁም የኮምፒውተር ክፍል ከላይ ከተያያዘው ኤክሴል ይመልከቱ፡፡

@tikvahuniversity
#AssosaUniversity

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ትምህርት ዘመን የመደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ጊዜ መስከረም 27 እና 28/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

የዕረፍት ቀናት ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቀን መስከረም 25 እና 26/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#Update

የመፈተኛ ጣቢያዎች ማስተካከያ ያድርጉ!

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም ለመማር ያመለከታችሁ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና (UAT) ለመውሰድ የፈተና ቦታዎችን መምረጣችሁ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ፈተናው በተወሰኑ ጣቢያዎች ብቻ እንዲሰጥ መወሰኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

በዚህም አመልካቾች የመፈተኛ ቦታችሁን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዩኒቨርሲቲዎች ከሚገኙ ጣቢያዎች ብቻ በመምረጥ ማስተካከያ ቅያሪ እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።

- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ካምፓስ
- አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ
- መቐለ ዩኒቨርሲቲ
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ
- የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
- ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
- ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስኮላርሺፕ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ውጤት ላስመዘገቡ 200 ተማሪዎች በውድድር ነፃ የትምህርት ዕድል ሊሰጥ ነው።

በውድድር ነፃ የትምህርት ዕድሉን የሚያገኙ ተማሪዎች የዶርሚታሪ እንዲሁም የካፌ አገልግሎት ተጠቃሚም ይሆናሉ ተብሏል።

ዩኒቨርሲቲው በውድድሩና ነፃ የትምህርት ዕድሉ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን በቀጣይ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

@tikvahuniversity
#ArsiUniversity

አርሲ የኒቨርሲቲ የመደበኛ ነባር ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ. ም ወደ አርሲ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መረሐግብር የተመደባችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ እና የመመዝገቢያ ቀናት መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው የነባር ተማሪዎች የካምፓስ ሽግሽግ ያደረገ ሲሆን፤ የሜዲሲን 1ኛ እና 2ኛ ዓመት፣ የኮምፒዩተር ሳይንስ 1ኛ እና 2ኛ ዓመት እንዲሁም የህግ 1ኛ እና 2ኛ ዓመት ዲንሾ ካምፓስ የተመደባችሁ መሆኑ ተገልጿል። የ2014 ዓ.ም ባች የፋርማሲ፣ የሜዲካል ላቦራቶሬ እና የነርሲንግ ተማሪዎች ጤና ኮሌጅ ካምፓስ ተመድባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስኮላርሺፕ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ውጤት ላስመዘገቡ 200 ተማሪዎች በውድድር ነፃ የትምህርት ዕድል ሊሰጥ ነው። በውድድር ነፃ የትምህርት ዕድሉን የሚያገኙ ተማሪዎች የዶርሚታሪ እንዲሁም የካፌ አገልግሎት ተጠቃሚም ይሆናሉ ተብሏል። ዩኒቨርሲቲው በውድድሩና ነፃ የትምህርት ዕድሉ ዙሪያ ተጨማሪ…
#Update

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ውጤት ላስመዘገቡ 200 ተማሪዎች በውድድር ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ ዛሬ መግለፁ ይታወቃል።

እንዴት ማመልከት ይችላሉ?

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ከ500 በላይ ውጤት ያመጡ የተፈጥሮ እና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪ ከሆኑ ያመልክቱ።

https://portal.aau.edu.et በመግባት Apply for Admission የሚለውን በመጫን መሰረታዊ መረጃዎች ከሞሉ በኋላ Sponsorship ለሚለው Government Scholarship የሚለውን በመምረጥ Other Reason ለሚለው “more than 500 and above” በማለት በክፍት ቦታው ላይ በመፃፍ የ12ኛ ውጤት ያስመዘገባችሁበትን የሚያሳይ ማስረጃ ማያያዝ ያስፈልጋል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ 👇
ሐሙስ መስከረም 9/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ

ይህ ጥሪ ከዚህ ቀደም ያመለከቱት አመልካቾች አያካትትም።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#Update የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና መርሐግብር የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከመስከረም 8-10/ 2017 ዓ.ም ይሰጣል። የብቃት ምዘና ፈተናው መርሃሐግብር፦ መስከረም 8/2017 ዓ.ም Medicine, Pharmacy, Anesthesia, Dental Medicine, Environmental Health, Psychiatric Nursing and Surgical Nursing. መስከረም 9/2017…
የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ዛሬ መስከረም 8/ 2017 ዓ.ም መሰጠት ጀምሯል። ፈተናው እስከ መስከረም 10/ 2017 ዓ.ም ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።

የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ Addis Ababa Science and Technology Institute (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት) የመፈተኛ ጣቢያ የመረጣችሁ ተመዛኞች ፈተናው የሚሰጠው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (5 ኪሎ ካምፓስ) መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ከቡሉምበርግ ሚዲያ ኢኒሼቲቭ አፍሪካ ጋር በመተባበር የፋይናሻል ጋዜጠኝነት ስልጠና ሊሰጡ ነው፡፡ ስልጠናውን በተመለከተ የፕሮግራም ትውውቅ በዛሬው ዕለት የተካሔደ ሲሆን፤ ስልጠናው በዩኒቨርሲቲዎቹ የጋዜጠኝነት ተማሪዎች እንዲሁም በሥራ ላይ ላሉ ጋዜጠኞች የፋይናሻል ዘገባ ግንዛቤያቸውን የሚያሳድግ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፣ የካፒታል ገበያ ሌሎች…
ብሉምበርግ ሚዲያ ኢኒሼቲቭ አፍሪካ (BMIA) የፋይናንሺያል ጋዜጠኝነት ስልጠና ፕሮግራም በኢትዮጵያ መስጠት ጀመረ።

55 ከመገናኛ ብዙሃን፣ ከፋይናንስ ዘርፍ እና ከመንግስት ሴክተሮች የተውጣጡ ሰልጣኞች በመጀመሪያው ዙር ስልጠና ይሳተፋሉ ተብሏል።

የንግድ እና የፋይናንስ ጋዜጠኝነትን ለማሳደግ ያለመው ፕሮገራሙ፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ እና ከኬንያው ስትራትሞር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ይሰጣል።

ተሳታፊዎች በመረጃ ትንተና፣ ካፒታል ገበያ፣ ኢኮኖሚክስ እና ፐብሊክ ፖሊሲ ​​ላይ ስልጠና ይወስዳሉ ተብሏል።

@tikvahuniversity
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በአቅራቢያው ለሚገኙ ዞኖች ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ ይታወቃል።

አሪ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ እና ባስኬቶ ዞኖች የዕድሉ ተጠቃሚ የሆኑ ስምንት ዞኖች ናቸው።

ዞኖቹ የዕድሉ ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን መልምለው በአካል ተገኝተው እንዲያመለክቱ ጠይቆ የነበረ ቢሆንም፤ በዩኒቨርሲቲው የመደበኛ ተማሪዎች ጥሪ ላልተወሰነ ጊዜ በመራዘሙ ምክንያት ለነፃ ትምህርት የተመለመሉ አመልካቾች ምዝገባም ተራዝሟል።

ሌላ ጥሪ እስከሚደረግ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።

@tikvahuniversity
#ተራዝሟል

የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ ለሚጀምረው የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም በአራት የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን አወዳድሮ መቀበል ይፈልጋል፡፡

የሚሰጡ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች፦

► MSc & PhD in Remote Sensing
► MSc & PhD in Space Science
► PhD in Geodesy
► MSc & PhD in Astronomy and Astrophysics

አመልካቾች የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በተጨማሪም ለማስተርስ ዲግሪ ለማመልከት የመጀመሪያ ዲግሪ CGPA 3.00 እንዲሁም ለፒኤችዲ ፕሮግራም ለማመልከት የማስተርስ ዲግሪ CGPA 3.00 እና የመመረቂያ ፅሁፍ 'በጣም ጥሩ' ሊኖራችሁ ይገባል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የድኅረ ምረቃ ቢሮ 2ኛ ፍሉር በመገኘት ወይም የትምህርት ሰነዶችን በPDF ፎርማት በማዘጋጀት በ [email protected] የኢ-ሜይል አድራሻ ማመልከት ይቻላል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም

(የኢንስቲትዩቱ ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል።

በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ውጤት ተለቋል።

ተማሪዎች ውጤታችሁን በተከታዩ ሊንክ አማካኝነት መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል 👇

https://result.ethernet.edu.et/

@tikvahuniversity
🌼 አዲስ ቅመም ለአዲስ ዓመት!

ለምንወዳቸው የበዓል ስጦታ Itel Proን ዛሬውኑ ገዝተን በሽ በሽ እናድርጋቸው! ዛሬውኑ ወደ ሳፋሪኮም ሱቆች በማቅናት ለ90 ቀናት በሚቆይ 5ጊባ ወር​ሃዊ ጥቅል እና በ1000 የሳፋሪኮም ደቂቃ ስጦታ እንንበሽበሽ!

የቴሌግራም ቦታችንን https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
#SPHMMC

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ህክምና ኮሌጅ የ Hematology and Oncology ፌሎውሺፕ ፕሮግራም አስጀምሯል።

ይህ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ሠልጣኞች ዘመናዊና ጥራት ያለው የካንሰር ህክምና፣ ትምህርት እና ምርምር እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል።

ፕሮግራሙ የሁለት ዓመት ቆይታ የሚኖረው ሲሆን፤ ኮሌጁ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኝ የሚሆኑ ሦስት ፌሎውስ በዚህ ወር እንደሚቀበል ይጠበቃል።

@tikvahuniversity
የቻይናው First Highway Engineering Company (CFHEC) ለ102 ወጣት ኢትዮጵያውያን የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

የግዙፉ CCCC ኩባንያ እህት ተቋም የሆነው CFHEC፤ ስልጠናውን ለአንድ ወር የሚሰጥ ሲሆን፤ ሰልጣኞቹ ከCCCC የኢትዮጵያ ፕሮጀክት ሳይቶች የተመረጡ መሆናቸው ተገልጿል።

ግንባታ፣ ሰርቬዪንግ፣ የግንባታ ቁሳቁስ ፍተሻ እና የቻይንኛ ቋንቋ በስልጠናው የተካተቱ ጉዳዮች መሆናቸው ተመላክቷል።

Seagull Talent Nurturing Project በሚል የሚሰጠው ስልጠና፤ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት፣ በሉባን ወርክሾፕ በኢትዮጵያ እና በ CFHEC በጋራ የተዘጋጀ ነው። #Xinhua

@tikvahuniversity
#DebreBerhanUniversity

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ከ2ኛ-6ኛ ዓመት ያሉ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ተማሪዎችን ዛሬ መቀበል ጀምሯል፡፡

ካምፓሱ ለ2017 ትምህርት ዘመን በመደበኛው ፕሮግራም ከ 1,200 በላይ ነባር እና አዲስ ገቢ የህክምናና የጤና ሳይንስ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ይጠበቃል፡፡

@tikvahuniversity
#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!

የአዲስ ዓመት ልዩ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ! ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮዎት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማኅበራዊ ገፅዎት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮች እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡

የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገፆችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማኅበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስትዎት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡

Tag ሲያደርጉን
ለ Facebook @TecnoEt https://www.facebook.com/share/KpViroSyJgPe1bML/?mibextid=qi2Omg
ለ Instagram @TecnoMobileEthiopia https://www.instagram.com/tecnomobileethiopia?igsh=cjdwdjQzbGlvaDV1
ለ TikTok @TecnoEt
https://www.tiktok.com/@tecnoet?_t=8pQuOpSYlGP&_r=1 ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
በተጨማሪም #TecnoEt2017 ኪወርድን መጠቀም እንዳይረሱ!
ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ትምህርት ዘመን ጥሪ የተደረገላቸው ነባር ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል።

ዩኒቨርሲቲው ነባር የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 09 እና 10/2017 እንደሚከናወን መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
2024/10/04 11:32:55
Back to Top
HTML Embed Code: