Telegram Web Link
በአማራ ክልል የ2017 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ቀን ትምህርት ዛሬ ተጀምሯል፡፡

በክልሉ በዚህ ዓመት 7 ሚሊዮን ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እየሩስ መንግስቴ ገልፀዋል።

እስካሁን ባለው የምዝገባ ሒደት 24 በመቶ ተማሪዎች እንደተመዘገቡ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ ቀናት ሁሉም እድሚያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናትን ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ኃላፊዋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

@tikvahuniversity
የ2017 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሒደት በተለያዩ ክልሎች ተጀምሯል።

የመማር ማስተማር ሒደቱ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በጋምቤላ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በሐረሪ ክልል እና በድሬዳዋ አስተዳደር በይፋ ተጀምሯል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 ትምህርት ዘመን በድኅረ-ምረቃ መርሐግብር በ Extension (ቅዳሜና እሁድ) ፕሮግራም አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

የትምህርት መስኮች

- General Public Health,
- Health Care Quality,
- Reproductive Health and
- Epidemology

የምዝገባ ጊዜ፦
ከመስከረም 8-30/2017 ዓ.ም


የምዝገባ ቦታ፦
በኮሌጁ ሬጅስትራር ቢሮ

መስፈርቶች
- ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በጤና ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ
- የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) ያለፈ/ች

@tikvahuniversity
#GambellaUniversity

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ትምህርት መስከረም 22/2017 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል።

አዲስ ገቢ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም አመልካቾች የመግቢያ ፈተና ውጤት እንደተለቀቀ ጥሪ እንደሚደረግ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የሪሚዲያል ተማሪዎች እና የ2017 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥሪ በጋራ ወደፊት ይደረጋል ተብሏል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#AddisAbabaUniversity በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም #በቀን_መደበኛ መርሐግብር በመንግስት ስኮላርሽፕ እና በግል ከፍላችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ለመማር የምታመለክቱ ዝርዝር መስፈርቶችን በማሟላት በ https://portal.aau.edu.et ወይም www.aau.edu.et ላይ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል። አመልካቾች የዩኒቨርሲቲውን የመግቢያ ፈተና (UAT) እና ዩኒቨርሲቲው…
Application Procedure :For Addis Ababa University Undergraduate Programs

1. Open the portal of Addis Ababa University https://portal.aau.edu.et 

2. Click on 'Apply for Admission' on the left side

3. On the top bar, you will find the undergraduate drop-down menu. You can click on the Programs button to view Undergraduate programs

4. After reviewing the programs, Click on Apply.

5. You will find the general information and the application steps on the front page of the apply button. Once you read it, click on the 'Continue' button and it will direct you to the programs for choosing.

6. Once you decide on the program of your choice, click on the program and press the 'Continue' button to create an applicant account.

7. Fill out the required information on the Create Undergraduate Applicant Account page. Use a valid email and phone number and record the password you entered on the page for future use. Once finished, click the 'CREATE ACCOUNT' button.

8. Log in using the 'LOG IN' button on the top-right corner of the page with the email address and password you used to create the account.

9. Fill out the required information on the Your Academic Profile page, Click on UPDATE, and then click NEXT.

10. Select admission Type(Regular/Extension)

11. Choose Government Scholarship/Self-Sponsorship on the Financing Your Study form

12. If you choose a Government Scholarship, upload an official letter from your regional Woreda or Sub-City in Addis Ababa resident indicating your family’s financial status. Then  Select your Program of Choice and Click on Continue

13. If you select Self-Sponsored, select the four options provided on the Program Choice form and Click Continue.

14. Upload your 12th-grade result certificate and transcript for the grades 9 to 12

15. Undergraduate Admission Test (UAT) Exam Location Select the location of the entrance exam from the options provided

16. Read the Consent Statement, select Accept and Click CONTINUE.

17. To pay the amount specified for the registration and UAT test, Click on Continue to Payment and then Click on Proceed.

18. Complete your payment through Telebirr

19. Click on UAT ADMISSION TICKET to get UAT exam ticket

20. Click on EXAM SCHEDULE to review your UAT exam schedule

21. Click on EXAM RESULT to review your UAT results once available.

22. Open SEE ADMISSION STATUS to know the final result of admission

(Addis Ababa University)

@tikvahuniversity
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2017 የመጀመሪያ ሴሚስትር ምዝገባ ቀናት ይፋ አድርጓል።

የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ፕሮግራምና ሁሉም የድህረ ምረቃ ተማሪዎች (መደበኛ እና የእረፍት ቀናት) ምዝገባ መስከረም 20-21 /2017 ነው።

የማታና የእረፍት ቀናት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 23 -25/2017 ዓ/ም ነው።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ለሚገኙ ትምህርት ፈላጊዎች የ2ኛ ዲግሪ የትምህርት ዕድል አመቻችቷል።

ኢንስቲትዩት በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ በተከታታይ እና በማታ መርሐግብር ማስተማር ይፈልጋል፡፡

የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት መስኮች

- በፋሽን ዲዛይን
- በጨርቃጨርቅ ማኑፋክቸሪንግ
- በፋሽን ቴክኖሎጂ
- በፋይበር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ
- በቴክስታይል ኬምስትሪ
- በቆዳ ውጤቶች ዲዛይንና ኢንጂነሪንግ

የምዝገባ ጊዜ፦
እስከ መስከረም 14/2017 ዓ.ም

የማመልከቻውን ቅፅ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ ላይ ማግኘት ይቻላል።

@tikvahuniversity
#AAU #GAT

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) በመጀመሪያ ዙር ለመውሰድ አመልክታችሁ ፈተናውን ሳትወስዱ የቀራችሁ ቀጣይ ፈተናውን የምትወስዱበት ቀን በቅርቡ እንደሚገለፅ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የተራዘመው የሁለተኛ ዙር GAT ፈተና የማመልከቻ ግዜ ዛሬ መስከረም 8/2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይታወቃል፡፡

እስካሁን ካላመለከቱ በቀሩት ሰዓታት በኦንላይን https://portal.aau.edu.et ያመልክቱ።

@tikvahuniversity
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል በመደበኛ የትምህርት መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 21 የተፈጥሮ ሳይንስ የህግ ታራሚ ተማሪዎች መካከል ሰባቱ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣት መቻላቸው ተገለፀ።

የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ሳምሶን ወንድሜነህ የህግ ታራሚ ተማሪዎች ምንም እንኳ በህግ ጥላ ስር ቢሆኑም ትምህርታቸውን በአግባቡ ሲከታተሉ መቆየታቸውንና ለውጤት እንደበቁ ገልፀዋል፡፡

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ያመጡት የህግ ታራሚ ተማሪዎች ያመጡት ውጤት ለመታረማቸው ማሳያ በመሆኑ የፍትህ ሚኒስቴር በይቅርታና ምህረት መልቀቅ የሚችልበትን ዕድል እንዲያገኙ፣ ካልሆነም ትምህርታቸውን በርቀት እንዲከታተሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲያመቻችሏቸው ጠይቀዋል፡፡ #ebc

@tikvahuniversity
Tikvah-University
Photo
#Update
#AASTU #ASTU

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታችሁን መከታተል ለምትፈልጉ ተቋማቱ መስፈርቶችን ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል።

ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች ለመግባት ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም በኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://stuoexam.astu.edu.et/registrationnew.php

@tikvahuniversity
#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!

የአዲስ ዓመት ልዩ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ! ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮዎት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማኅበራዊ ገፅዎት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮች እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡

የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገፆችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማኅበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስትዎት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡

Tag ሲያደርጉን
ለ Facebook @ TecnoEt https://www.facebook.com/share/KpViroSyJgPe1bML/?mibextid=qi2Omg
ለ Instagram @ TecnoMobileEthiopia https://www.instagram.com/tecnomobileethiopia?igsh=cjdwdjQzbGlvaDV1
ለ TikTok @ TecnoEt
https://www.tiktok.com/@tecnoet?_t=8pQuOpSYlGP&_r=1 ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
በተጨማሪም #TecnoEt2017 ኪወርድን መጠቀም እንዳይረሱ!
#Update

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎችን ለመቀበል የማመልከቻ ግዜን አራዝሟል።

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥባቸውን ቀናትም ይፋ አይርጓል፡፡

በዚህም የቅድመ ምረቃ #መደበኛ መርሐግብር የማመልከቻ ቀን እስከ ነገ መስከረም 9/2017 ዓ.ም የተራዘመ ሲሆን የመግቢያ ፈተና (UAT) መስከረም 11/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

የቅድመ ምረቃ #የማታ መርሐግብር የማመልከቻ ቀን እስከ መስከረም 13/2017 ዓ.ም የተራዘመ ሲሆን የመግቢያ ፈተና (UAT) መስከረም 15/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

የድኅረ ምረቃ መርሐግብር የማመልከቻ ቀን እስከ መስከረም 13/2017 ዓ.ም የተራዘመ ሲሆን የመግቢያ ፈተና (GAT) መስከረም 15/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

(ተጨማሪ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
2024/10/04 09:32:13
Back to Top
HTML Embed Code: