Telegram Web Link
#AAETQRA

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የሁለት የግል ኮሌጆች ካምፓስን የዕውቅና ፍቃድ ሰረዘ፡፡

ባለስልጣኑ ያደረገውን ድንገተኛ ኢንስፔክሽን ተከትሎ በ44 የግል ኮሌጆች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል፡፡

በዚህም ሸገር ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ እና አልፋ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ግሎባል ካምፓስ "ያለባቸውን ክፍተት ለማስተካከል ፍቃደኛ ባለመሆናቸው" የዕውቅና ፍቃዳቸው የተሰረዘ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡

ልቀት ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ "የተወሰነ ማስተካከያ ያደረገ ቢሆንም፤ ሙሉ በሙሉ ለማስተካከል በጠየቀው መሰረት የአንድ ወር ተጨማሪ ጊዜ" በባለስልጣኑ ተሰጥቶታል፡፡

የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ከነበሩ ተቋማት መካከል ስምንት ኮሌጆች ያለባቸውን ክፍተት ማስተካከላቸውን ባለስልጣኑ በምልከታ ማረጋገጡን አሳውቋል፡፡ እነዚህም፦

1. ያኔት ኮሌጅ 6 ኪሎ ካምፓስ፣
2. ዳማት ኮሌጅ ጊዮርጊስ ካምፓስ፣
3. ያኔት ኮሌጅ ሰፈረ ሰላም ካምፓስ፣
4. ኤክስፕረስ ኮሌጅ፣
5. ቅድስት ሀና ኮሌጅ፣
6. ግራንድ ማርክ ኮሌጅ፣
7. ኩዊንስ ኮሌጅ ሀና ካምፓስ እና
8. ሀራምቤ ኮሌጅ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የዕውቅና ፍቃዳቸው ታግዶ የነበሩና ያለባቸውን ክፍተት በተሰጣቸው ጊዜ ማስተካከላቸው በባለስልጣኑ በምልከታ የተረጋገጠላቸው 15 ተቋማት የዕውቅና ፍቃድ እገዳው ተነስቶላቸዋል፣ የመጨረሻ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነዚህም፦
1. ብራይት ኮሌጅ ልደታ ካምፓስ፣
2. ብራይት ኮሌጅ ጀሞ ካምፓስ፣
3. ልቀት ኮሌጅ 4 ኪሎ ካምፓ'ስ፣
4. ላየን ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ፣
5. ኩዊንስ ኮሌጅ መድኃኒዓለም ካምፓስ፣
6. ሳትኮም ኮሌጅ፣
7. ሀርመኒ ኮሌጅ ሀና ማርያም ካምፓስ፣
8. ኩዊንስ 5 ኪሎ ካምፓስ፣
9. ሃርመኒ ቅሊንጦ ካምፓስ፣
10. አፍሪካ ቤዛ ኮሌጅ፣
11. አረና ኮሌጅ፣
12. ጌጅ ኮሌጅ ሾላ ካምፓስ፣
13. ሀጌ ኮሌጅ፣
14. ኩዊንስ ኮሌጅ ዮሃንስ ካምፓስ እና
15. ኪያሜድ ኮሌጅ እንቁላል ፋብሪካ ካምፓስ እንደሆኑ ባለስልጣኑ ጠቁሟል፡፡

የመጨረሻ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው የነበሩ 18 ተቋማት በተሰጣቸው ጊዜ ያለባቸውን ክፍተት ያስተካከሉ መሆኑን ባለስልጣኑ በምልከታ አረጋግጧል፡፡ እነዚህም፦

1. ዌልነስ ኮሎጅ፣
2. ግሬት ኮሌጅ ቡልቡላ ካምፓስ፣
3. ቢኤስቲ ኮሌጅ 18 ካምፓስ፣
4. ክቡር ኮሌጅ፣
5. ፋርማ ኮሌጅ፣
6. ቅድስት ልደታ ኮሌጅ፣
7. ኤግል ኮሌጅ፣
8. አፍሪካ ጤና ኮሌጅ፣
9. ናሽናል ኮሌጅ፣
10. ካርቫርድ ኮሌጅ፣
11. ሰቨን ስታር ኮሌጅ፣
12. ራዳ ኮሌጅ፣
13. ሪፍት ቫሊ ኮሌጅ ካራ አሎ ካምፓስ፣
14. ኬቢ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ፣
15. ያጨ ኮሌጅ፣
16. ኪያሜድ ኮሌጅ 22 ካምፓስ፣
17. ናይል ሳይድ ኮሌጅ እና
18. ኪያሜድ ኮሌጅ አየር ጤና ካምፓስ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#MizanTepiUniversity ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው መስከረም 06 እና 07/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡ (የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡) @tikvahuniversity
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለ3ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል፡፡

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 06 እና 07/2017 ዓ.ም ይከናወናል ብሎ የነበረ ቢሆንም፤ "በተቋሙ ውስጥ እየተሰጡ ያሉ ስልጠናዎች ባለመጠናቀቃቸው ምክንያት" የምዝገባው ቀን ወደ መስከረም 13/2017 ዓ.ም የተቀየረ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት መስከረም 14/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

@tikvahuniversity
#DambiDolloUniversity

ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ነባር ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት መስከረም 22 እና 23/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በ2017 ዓ.ም አዲስ ወደ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችው እና በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን ወደ ፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
በፈረንሳይ ሊዮን ከተማ እየተካሔደ በሚገኘው 47ኛው የዓለም የክህሎት ውድድር ኢትዮጵያ በሦስት መስኮች እየተሳተፈች ትገኛለች፡፡

ጽዮን አዳነ በአይ.ቲ.፣ ብሩክ መኮንን በእንጨት ሥራ እና የሮምነሽ ዋሬ በማምረቻ ዘርፎች ኢትዮጵያን ወክለው እየተወዳደሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በውድድሩ ከ70 ሀገራት የተወጣጡ 1,400 ወጣቶች በ60 የሙያ መስኮች እየተሳተፉ ነው።

@tikvahuniversity
#AksumUniversity

አክሱም ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ነባር ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት መስከረም 7 እና 8/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በመሆኑም ከዚህ ቀደም ስትማሩበት በነበራችሁበት ግቢ በአካል በመገኘት በተጠቀሱት ቀናት ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

በ2016 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁ ተከታትላችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም አዲስ ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ የምትመደቡ ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#ይመዝገቡ

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በ13 የትምህርት መስኮች የማስተርስ ፕሮግራም አመልካቾችን ለመቀበል ላወጣው ጥሪ የአመልካቾች የምዝገባ ጊዜን እስከ መስከረም 10/2017 ዓ.ም አራዝሟል፡፡

በሕክምና ትምህርት ቤት (በመደበኛ)
- MS in Respiratory Therapy
- MS in Medical Microbiology
- MS in Medical Radiologic Technology

በማኅበረሰብ ጤና ትምህርት ቤት
(በመደበኛ እና በእረፍት ቀናት)
- MPH in General Public Health
- MPH in Nutrition
- MPH in Epidemiology
- MPH in Health Communication and Promotion

በነርሲንግ ትምህርት ቤት (በመደበኛ)
- MS in Critical Care Nursing
- MS in Cardiovascular Nursing
- MS in Neonatal Nursing
- MS in Clinical Oncology Nursing
- MS in Paramedics Science
- MS in Cardiothoracic Nursing

ኦንላይን ለመመዝገብ 👇
https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement

Note:
► አመልካቾች መንግሥት የሚሰጠውን ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ያለፉ ሊሆኑ ይገባል፡፡
► የምዝገባ ክፍያ ብር 400 በኢ/ን/ባ ሂሳብ ቁ. 1000006577192 መክፈል ይጠበቅባችኋል፡፡
► ያመለከታችሁበት ትምህርት ክፍል የፅሑፍ እና የቃል ፈተና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

@tikvahuniversity
#RayaUniversity

ራያ ዩኒቨርሲቲ የነባር መደበኛ የቅድመ ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት መስከረም 13 እና 14/2017 ዓ.ም ብቻ መሆኑን አሳውቋል።

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በራያ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም አዲስ ለምትመደቡ ተማሪዎች በቀጣይ ጥሪ እንደሚደረግ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#WerabeUniversity

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለነባር የቅድመ ምረቃ መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም የ2014 እና 2016 ባች (3ኛ እና 1ኛ ዓመት) የቅድመ ምረቃ መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። በቅጣት ለመመዝገብ መስከረም 22/2017 ዓ.ም ብቻ።

የ2013 ባች (5ኛ ዓመት) የቅድመ ምረቃ መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 5 እና 6/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል። በቅጣት ለመመዝገብ ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም ብቻ።

በ2016 ትምህርት ዘመን የሪሚዲያል ፕሮግራም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ያጠናቀቃቹ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ወደፊት ይገለፃል ተብሏል።

@tikvahuniversity
ነፃ የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ዕድል #ለሴቶች

አክሱም ዩኒቨርሲቲ በ2017 የትምህርት ዘመን ለሴት አመልካቾች ነፃ የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ዕድል ለመስጠት ዕቅድ ይዟል፡፡

የማመልከቻ ቦታ፦
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ሬጅሰትራር ፅ/ቤት እና ሽረ ግቢ ሬጅስትራር ማስተባበርያ ፅ/ቤት

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
መስከረም 07/2017 ዓ.ም

መስፈርቶች፦
► የተቀመጡ የመግቢያ ነጥብ አሟልተው ሲገኙ፣
► አመልካቾች ከዚህ በፊት በመንግስት ወጪ የትምህርት ዕድል ተሰጥቷቸው የተማሩ ከሆነ የወጭ መጋራት ክፍያቸውን መፈፀም ይጠበቅበቸዋል፣
► ዕድሜያቸው ከ35 ዓመት በታች የሆኑ (Exceptions ይኖራሉ)፣
► በመንግስት ዕውቅና ከተሰጠው ዩኒቨርሲቲ የተመረቁና የመጀመሪያ ዲግሪ ውጤታቸው 3.00 እና ከዚያ በላይ (ለአካል ጉዳተኞች 2.75 እና ከዚያ በላይ) የሆነ፣
► የድኅረ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች የመግቢያ ፈተና (GAT) የማለፍያ ውጤት ያገኙ፣

Note: ነፃ የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ዕድል የተሰጠባቸው የትምህርት ፕሮግራሞች እና ሌሎች መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡

@tikvahuniversity
#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!

የአዲስ ዓመት ልዩ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ!
ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮዎት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማኅበራዊ ገፅዎት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮች እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡

የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገፆችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማኅበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስትዎት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡

Tag ሲያደርጉን
ለ Facebook @ TecnoEt https://www.facebook.com/share/KpViroSyJgPe1bML/?mibextid=qi2Omg
ለ Instagram @ TecnoMobileEthiopia https://www.instagram.com/tecnomobileethiopia?igsh=cjdwdjQzbGlvaDV1
ለ TikTok @ TecnoEt
https://www.tiktok.com/@tecnoet?_t=8pQuOpSYlGP&_r=1 ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
በተጨማሪም #TecnoEt2017 ኪወርድን መጠቀም እንዳይረሱ!
ትግራይ ክልል ውስጥ ውድመት የደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች አሁንም ድረስ እየተጠገኑ እንዳልሆነ ተገለፀ፡፡

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ትግራይ ክልል ውስጥ የነበሩ 2,492 ትምህርት ቤቶች ወድመዋል፣ በክልሉ ከነበሩ 46,598 መምህራን ውስጥ 14 ሺህ የሚሆኑት በሞት፣ በአካል ጉዳት እና መሰል ችግሮች ምክንያት በመምህርነት አልቀጠሉም፡፡

በ2016 ዓ.ም ትግራይ ክልል ውስጥ 2.4 ሚሊዮን ተማሪዎች ለመመዝገብ ታቅዶ የተሳካው ግን 1.2 ሚሊዮን ብቻ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

መሰረተ ልማቶቹን ጠግኖ ወደ ሥራ ለማስገባት ጥናት ቢደረግም ዛሬም ድረስ ከፌዴራል መንግስት እና ከሌሎች ረጂ ተቋማት በቂ ድጋፍ እየተደረገ አለመሆኑን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

አሁንም ድረስ ሙሉ ለሙሉ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ሥርዓቱ ማስገባት አለመቻሉን የገለፁት ኃላፊው፤ ዛሬም ድረስ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የተፋናቃይ እና ስደተኛ መጠለያ ናቸው፣ ሌሎች ትምህርት ቤቶች ደግሞ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ስር እየተዳደሩ አይደሉም ብለዋል፡፡

በክልሉ ውስጥ ያሉ ህፃናት ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ መገንባትና መሰረተ ልማቶችን የማሟላት ሥራ ሊሠራ እንደሚገባ ኃላፊው ጥሪ አድረገዋል፡፡ #ShegerFM

@tikvahuniversity
2024/10/01 07:14:45
Back to Top
HTML Embed Code: