Telegram Web Link
ሁዋዌ በ8ኛው ዓለም አቀፍ የ2023/24 አይሲቲ ውድድር የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን ሸልሟል።

ዘጠኝ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ባለፈው ዓመት በአገር አቀፍ እና በአህጉር አቀፍ የፍጻሜ ውድድሮች በክላውድ ትራክ፣ በኮምፒውቲንግ ትራክ እና በኔትወርክ ትራክ መወዳደራቸው ይታወሳል።

120 ተማሪዎች ለአገር አቀፍ የፍጻሜ ውድድር አልፈው የተሳትፎ ሰርተፍኬት መውሰዳቸውን ሁዋዌ ገልጿል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ ዘጠኝ ተማሪዎች ኢትዮጵያን ወክለው በቱኒዚያ በተካሄደው ክፍለ አህጉራዊ ውድድር የሦስተኛ ደረጃን ሽልማት ማግኘታቸውና ሦስት ተማሪዎች ያሉት ቡድን ደግሞ፣ በቻይና ሼንዘን ከተማ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የፍጻሜ ውድድር መሳተፋቸው አይዘነጋም፡፡

@tikvahuniversity
#ይመዝገቡ

የሁዋዌ አይሲቲ ውድድር 2024/25 ፕሮግራም ይፋ ሆኗል፡፡

በ9ኛው ዓለም አቀፍ የ2024/25 አይሲቲ ውድድር ለመሳተፍ የምትፈልጉ እስከ ታህሳስ 2017 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ መመዝገብ ይኖርባችኋል፡፡

ኔትዎርኪንግ፣ ክላውድ ኮምፒውተር እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ውድድሩ ከሚደረግባቸው የአይሲቲ ዘርፎች መካከል ይጠቀሳሉ።  

በሁዋዌ የICT ውድድር (Huawei ICT Competition 2024-2025) ለመሳተፍ በቅድሚያ የሁዋዌ ICT አካዳሚ አባል ይሁኑ።

የአካዳሚው አባል ለመሆን 👇
https://e.huawei.com/en/talent/portal/#/

ለውድድሩ ምዝገባ ለማድረግ 👇
https://bit.ly/SAR2024-2025

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ፡፡

ብሪቲሽ ካውንስል ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ IELTS ፈተና ኅዳር 21/2017 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ፈተናውን መውሰድ የሚፈልጉ አመልካቾች ምዝገባ ማድረግ ጀምሯል።

የፈተና ቦታ፦ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ

ሁለት አይነት የ IELTS ፈተናዎች (IELTS Academic and IELTS General Training) ይሰጣሉ፡፡

ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts

በአካል ለመመዝገብ፦ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ህንፃ ቁ. 130፣ ቢሮ ቁ. 408

ለበለጠ መረጃ፦ 0925629589

@tikvahuniversity
የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ምደባችሁን ለማየት

በድረ ገጽ፦
https://placement.ethernet.edu.et

በቴሌግራም፦
https://www.tg-me.com/moestudentbot

ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ #የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahuniuversity
የፊታችን ሰኞ ህዳር 2/2017 ዓ.ም 17ኛ እና 18ኛ ዙር የድረ-ገፅ እና ሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (Full-Stack Website and Mobile Application Development) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ይጀምራል።  

👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ የኮምፒውተር እና ፕሮግራሚንግ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 Front-end እና Back-end በአንድ ላይ እስከ Deployment ያካተተ
👉 በተግባር ድረ-ገፅ እና ሞባይል መተግበሪያ እያበለፀጉ የሚሰለጥኑበት
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️    0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: https://www.tg-me.com/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።

ላፕቶፕ ከመገዛትዎ በፊት ማወቅ ያለባችሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። በላፕቶፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844

0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ለአስር የሀገር ውስጥ የምርምር ጆርናሎች ዕውቅና ሰጥቷል፡፡

በ2016 ዓ.ም ዕውቅና ለማግኘት ካመለክቱ የአገር ውስጥ የምርምር ጆርናሎች መካከል መስፈርቱን ላሟሉ አስር (10) የምርምር ጆርናሎች ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የሚቆይ ዕውቅና መስጠቱን ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡

ዕውቅና የተሰጣቸው ጆርናሎች፦

1. Berhan International Research Journal of Sciences and Humanities
2. Choke Journal of Science and Technology
3. Ethiopian Journal of Applied Sciences and Technology
4. Ethiopian Journal of Biological Sciences
5. Science, Technology and Arts Research Journal
6. Ethiopian Journal of Business and Social Science
7. Ethiopian Journal of Economics
8. Ethiopian Journal of Language, Culture and Communication
9. Ethiopian Journal of Sport Science
10. RADA Multidisciplinary Research

@tikvahuniversity
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ኀዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
- የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግቢ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➭ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➭ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➭ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➭ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
➭ የስፖርት ትጥቅ

@tikvahuniversity
#RayaUniversity

በ2017 ዓ.ም በራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች እና በ2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የማጠናከሪያ ትምህርት (Remedial Program) ወስዳችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 2 እና 3/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት ህዳር 9/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

Note:
በ 2017 ዓ.ም ወደ ራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

(የዩኒቨርሲቲው ጥሪ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
💫 ከዳር እስከ ዳር አስተማማኙን ኔትወርካችንን እያሰፋን ወደ እናንተ እየቀረብን ነው! 🙌 ከአስተማማኙ ኔትወርካችን ጋር አሁንም በአብሮነት ወደፊት!

አስተማማኙን ኔትወርክ ዛሬውኑ እንቀላቀል!

የቴሌግራም ቦታችንን https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia
#1Wedefit #Furtheraheadtogether
ክቡር ኮሌጅ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ነጥብ ያላሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ መርሐግብር (Remedial Program) ለመስጠት ምዝገባ ጀምሯል!

👉 በትምህርት ሚኒስቴር የመግቢያ መስፈርት መሠረት
👉 በተጨማሪ የጥናትና የፈተና አወሳሰድ ክህሎት ስልጠናን ያካተተ
👉 የበይነ መረብ የፈተና አሰጣጥ ስልጠናን ያካተተ
👉 ትምህርቱ ብቃት ባላቸው መምህራን እንዲሁም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አሰጣጥ ልምድ ባለው ተቋም በመታገዝ ይሰጣል፡፡

Website: https://kibur.edu.et
አድራሻ፦ ጀሞ ሚካኤል ከአፍሪካ ህንፃ አጠገብ
☎️ 0113854042 / 0904848586

https://www.tg-me.com/kiburcollege
#HaramyaUniversity

በ2017 ትምህርት ዘመን ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የፍሬሽማን ቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ከህዳር 9 እስከ 11/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ምዝገባ ለማድረግ የሚያስፈልጉ፦
- የ8ኛ ክፍል ካርድ፣
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
- የ12ኛ ከፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
- 6 ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
- ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

ከላይ የተዘረዘሩትን የትምህርት ማስረጃዎች እና ፎቶግራፍ ስካን አድርጋችሁ በሶፍት ኮፒ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
#OdaBultumUniversity

በ2016 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያስመዘገባችሁ እና በ2017 ዓ.ም ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 4 እና 5/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ምዝገባ ለማድረግ የሚያስፈልጉ፦

- የ8ኛ ክፍል ስርትፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

@tikvahuniversity
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የብሪክስ+ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበር መስራች አባል ሆነ።

ማኅበሩ በዘጠኙ የብሪክስ+ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት የተመሰረተ ሲሆን፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመስራች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱ ሆኗል።

የብሪክስ+ ቡድንን ለመቀላቀል ፍላጎት ያላቸው የ 34 ሀገራት ዩኒቨርሲቲውዎችም የማኅበር አባል መሆናቸውን ከማኅበሩ ድረ-ገፅ ላይ የተገኘ መረጃ ያሳያል።

ዓለም አቀፍ ድጋፍ ማጠናከር፣ ልምድ ልውውጥ፣ የትምህርት ትብብርና ኔትወርኪንግ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የአቅም ግንባታ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማጎልበት ማኅበሩ የሚያከናውናቸው ተግባራት ናቸው።

@tikvahuniversity
2024/11/05 23:20:30
Back to Top
HTML Embed Code: