Telegram Web Link
#ASTU

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር መደበኛ የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን የምዝገባ ቀናት መስከረም 21 እና 22/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት የሚጀመርበት ቀን መስከረም 23/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

በቅጣት ለመመዝገብ 👇
መስከረም 23 እና 24/2017 ዓ.ም

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
#Update

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና መርሐግብር

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከመስከረም 8-10/ 2017 ዓ.ም ይሰጣል።

የብቃት ምዘና ፈተናው መርሃሐግብር፦

መስከረም 8/2017 ዓ.ም
Medicine, Pharmacy, Anesthesia, Dental Medicine, Environmental Health, Psychiatric Nursing and Surgical Nursing.

መስከረም 9/2017 ዓ.ም
Medical Laboratory Science, Midwifery, Pediatric and Child Health Nursing, Medical Radiology Technology and Public Health.

መስከረም 10/2017 ዓ.ም
Nursing 

@tikvahuniversity
የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና የጥንቃቄ መልዕክት

የብቃት ምዘና ፈተናው ከመስከረም 8-10/ 2017 ዓ.ም ይሰጣል።

► እያንዳንዱ ተፈታኝ ከሚፈተንበት ቀን አንድ ቀን ቀደም ብሎ ጠዋት 3፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለፃ መከታተል፣ የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራት እና የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል።

► በፈተናው ዕለት ተፈታኞች ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ሕጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡

► ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀት፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ወደመፈተኛ ማዕከል ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡

► በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት) አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረም ይኖርባችኋል።

► ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲሔድ ሲስተሙ የሚሰጠውን QR Code ያለው የፈተና መግቢያ (ስሊፕ) Print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ አይችልም፡፡

► የመፈተኛ ጣቢያ ኦንላይን በመረጣችሁት መሰረት ስም ዝርዝራችሁን https://drive.google.com/drive/folders/17QzuVtjm4Uh3yQhA-teNFt7PRDqBc0Ft?usp=sharing በመጫን መመልከት ይኖርባችኋል፡፡

► ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት ተቋም ውጪ ፈተናውን መውሰድ አትችሉም፡፡

► ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (ቴዎድሮስ ካምፓስ) የመፈተኛ ጣቢያ የመረጣችሁ ተመዛኞች ወደ ዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተዘዋወራችሁ መሆኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#SalaleUniversity

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም 1ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ነባር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን የምዝገባ ቀናት መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

@tikvahuniversity
#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!

የአዲስ ዓመት ልዩ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ!
ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮዎት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማኅበራዊ ገፅዎት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮች እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡

የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገፆችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማኅበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስትዎት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡

Tag ሲያደርጉን
ለ Facebook @ TecnoEt https://www.facebook.com/share/KpViroSyJgPe1bML/?mibextid=qi2Omg
ለ Instagram @ TecnoMobileEthiopia https://www.instagram.com/tecnomobileethiopia?igsh=cjdwdjQzbGlvaDV1
ለ TikTok @ TecnoEt
https://www.tiktok.com/@tecnoet?_t=8pQuOpSYlGP&_r=1 ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።
በተጨማሪም #TecnoEt2017 ኪወርድን መጠቀም እንዳይረሱ!
የ $2,000 ተሸላሚው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የቬተርናሪ ሳይንስ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነው ዶ/ር ድነግዴ ቱሉ የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሥራ ፈጠራ ልማት ሽልማት ውድድር አሸናፊ ሆኗል፡፡

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ብሩክ ኢትዮጵያ ከተባለ ተቋም ጋር በመተባበር ተማሪዎችን የማሰልጠን እና የማብቃት ሥራ ሲያከናውን መቆየቱን ገልጿል፡፡ የተቋሙ ድጋፍ ለዶ/ር ድነግዴ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደነበረውም ተጠቁሟል፡፡

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የቬተርናሪ ሳይንስ ተማሪ የሆነው ዶ/ር ድነግዴ ቱሉ፣ በሀገር አቀፍ ውድድሩ አሸናፊ ከሆኑት መካከል አንዱ በመሆኑ 2,000 የአሜሪካን ዶላር ተሸላሚ ሆኗል፡፡

@tikvahuniversity
#ArbaMinchUniversity

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለነባር መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም የኮሌጁ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን የመግቢያ ቀን መስከረም 9/2017 ዓ.ም፣ የመመዝገቢያ ቀን መስከረም 10/2017 ዓ.ም እና ትምህርት የሚጀምርበት ቀን መስከረም 11/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#JinkaUniversity ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የነባር መደበኛ ተማሪዎች፣ በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም በጂንካ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ መርሐግብር ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በፍሬሽማን ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው መስከረም 7 እና 8/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።…
#JinkaUniversity

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የነባር ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 7 እና 8/2017 ዓ.ም ይከናወናል ብሎ የነበረ ቢሆንም፤ ምዝገባው ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን አሳውቋል፡፡

በቀጣይ ሌላ የጥሪ ማስታወቂያ እስከሚደረግ ድረስ ተማሪዎቹ በትዕግስት እንድትጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል፡፡

@tikvahuniversity
ለቻርጀር መሯሯጥ ድሮ ቀረ!
ገና ቀኑ ሳይጋመስ የሚያልቅ ባትሪ አላማረራችሁም? እንግዲያውስ ቅመም Itel Pro ለእናንተ ነው! ባለ የ4000mAh የባትሪ አቅም ያለው ቅመም Itel በአንድ ጊዜ ቻርጅ ብቻ ለሁለት ቀናት እንደልባችሁ ስልካችሁን መጠቀም ያስችላችኋል! ቅመም Itel Pro በሄዳችሁበት ሁሉ አብሯችሁ ነው!
ሁለት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም የብሩህ ኢትዮጵያ የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር አሸናፊ ሆነዋል፡፡

በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒዩቲንግ ኮሌጅ ተማሪዎች የሆኑት በእምነት ጥላሁን እና ቶማስ ግዛው የ2016 ዓ.ም የብሩህ ኢትዮጵያ የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ተማሪዎቹ በሠሯቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች (Mesob እና Pain የተባሉ የሞባይል መተግበሪያዎች) እያንዳንዳቸው የ 2,000 የአሜሪካ ዶላር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

@tikvahuniversity
#SamaraUniversity

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለሁሉም ነባር መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

ነባር መደበኛ ተማሪዎች (ቅድመ ምረቃ እና ድኅረ ምረቃ) የ2017 ትምህርት ዘመን የመመዝገቢያ ጊዜ መስከረም 09 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 13/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በፍሬሽማን ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የምትመደቡ አዲስ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደፊት በሌላ ማስታወቂያ የሚገለፅ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#ASTU አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል። በዚህም የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር መደበኛ የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን የምዝገባ ቀናት መስከረም 21 እና 22/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ትምህርት የሚጀመርበት ቀን መስከረም 23/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡ በቅጣት ለመመዝገብ 👇 መስከረም 23 እና…
#ASTU

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች ከመስከረም 04/2017 ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው በመገኘት ሪፖርት አድርጉ ተብሏል፡፡

የ2016 ዓ.ም የሁለተኛ ሴሚስቴር ማጠናቀቂያ ፈተና የሚሰጠው ከመስከረም 07-14/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

በመሆኑም ሁሉም የዩኒቨርሲቲው የ2ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች ከመስከረም 04/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሪፖርት እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም ሊሰጠው የነበረውን የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ትምህርት ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም መግቢያ ፈተና (NGAT) ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መስጠት አለመቻሉን ገለፀ። ተፈታኞች ለደረሰባችሁ መጉላላት ይቅርታ የጠየቀው ዩኒቨርሲቲው፤ ፈተናውን መስከረም 3 እና 4/2017 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል። @tikvahuniversity
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም ሳይሰጥ የቀረውን የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ትምህርት ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም መግቢያ ፈተና (NGAT) ነገ አርብ መስከረም 3/2017 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ይሰጣል፡፡

በመሆኑም ተፈታኞች ከዚህ ቀደም በተመደባችሁበት የኮምፒውተር ላብራቶሪ ተገኝታችሁ ፈተናችሁን እንድትወስዱ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#AAU #GAT አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) መስከረም 3/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡  በተቋሙ የሚሰጠውን ፈተና ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 1/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል፡፡ @tikvahuniversity
#AAU #GAT Schedule.xls
203 KB
#AAU #GAT

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነገ አርብ መስከረም 3/2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) መርሐግብር ይፋ አድርጓል፡፡

መስከረም 3/2017 ዓ.ም ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ለሚሰጠው ፈተና የተፈታኞች ዝርዝር፣ የመፈተኛ ካምፓስ፣ የመፈተኛ ላብ እንዲሁም የኮምፒውተር ክፍል ከላይ ከተያያዘው ኤክሴል ይመልከቱ፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#AAU #GAT አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) መስከረም 3/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ አሳውቋል፡፡  በተቋሙ የሚሰጠውን ፈተና ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 1/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል፡፡ @tikvahuniversity
#AAU #GAT Afternoon Schedule .xls
40.5 KB
#የቀጠለ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነገ አርብ መስከረም 3/2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) መርሐግብር ይፋ አድርጓል፡፡

መስከረም 3/2017 ዓ.ም ከሰዓት ከ7፡30-11፡00 ሰዓት ለሚሰጠው ፈተና የተፈታኞች ዝርዝር፣ የመፈተኛ ካምፓስ፣ የመፈተኛ ላብ እንዲሁም የኮምፒውተር ክፍል ከላይ ከተያያዘው ኤክሴል ይመልከቱ፡፡

@tikvahuniversity
2024/10/04 21:15:45
Back to Top
HTML Embed Code: