Telegram Web Link
#AAU #GAT

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) ዛሬ መስከረም 3/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ፈተናው በጠዋት እና ከሰዓት ክፍለጊዜ እንደሚሰጥ ዩኒቨርሲቲው ያወጣው መርሐግብር ያሳያል።

ነገ መስከረም 4/2017 ዓ.ም ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ዝርዝር እና የመፈተኛ ካምፓስ ዛሬ ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።

ስማችሁ በዝርዝሩ ያልተካተተ አመልካቾች በቅርቡ ቀጣይ ዙር ፈተና እንደሚሰጥ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

@tikvahuniversity
ለመስከረም 3 እና 4/2017 ዓ.ም የተዘዋወረው ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በሰባት ማዕከላት ይሰጣል።

ይህ ፈተና የሚሰጠው ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም በተሰጠው የNGAT ፈተና፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን እንደ ፈተና ማዕከል መርጠው ለነበሩ ተፈታኞች መሆኑ ይታወቃል።

ፈተናው የሚሰጥባቸው ሰባት ተቋማት፦

1. በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣
2. በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
3. በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣
4. በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት፣
5. በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ፣
6. በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና
7. በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ፡፡

(የፈተናው ፕሮግራም ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
#WallagaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለነባርና አዲስ ገቢ መደበኛ እና ተከታታይ መርሐግብር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም የሁሉም የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም የመደበኛ እና የተከታታይ መርሐግብር ነባር እንዲሁም አዲስ የሚመደቡ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ምዝገባው በዩኒቨርሲቲው ሦስቱም ካምፓሶች (ነቀምቴ፣ ጊምቢ እና ሻምቡ) የሚካሔድ ይሆናል።

ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 22/2017 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

Note: ወደዩኒቨርሲቲው አዲስ የምትመደቡ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የካምፓስ ምደባ በማስታወቂያ በቀጣይ ይገለፃል ተብሏል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#AAU #GAT አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) ዛሬ መስከረም 3/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ ፈተናው በጠዋት እና ከሰዓት ክፍለጊዜ እንደሚሰጥ ዩኒቨርሲቲው ያወጣው መርሐግብር ያሳያል። ነገ መስከረም 4/2017 ዓ.ም ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ዝርዝር እና የመፈተኛ ካምፓስ ዛሬ ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል። ስማችሁ በዝርዝሩ ያልተካተተ አመልካቾች በቅርቡ…
#AAU #GAT Sep 14 Morning Schedule.xls
136 KB
#AAU #GAT

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነገ ቅዳሜ መስከረም 4/2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) መርሐግብር ይፋ አድርጓል፡፡

መስከረም 4/2017 ዓ.ም ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ለሚሰጠው ፈተና የተፈታኞች ዝርዝር፣ የመፈተኛ ካምፓስ፣ የመፈተኛ ላብ እንዲሁም የኮምፒውተር ክፍል ከላይ ከተያያዘው ኤክሴል ይመልከቱ፡፡

@tikvahuniversity
M-PESA ጋር አዳዲስ ሽልማቶችን እያፈስን፣ ከነፃ ያልተናነሱ ቅናሾችን እያገኘን፣ ከ M-PESA ጋር በአዲሱ ዓመት እንጓዝ!

የ M-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #Furtheraheadtogether
#ETA

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚሰጧቸው የትምህርት ፕሮግራሞች ዕውቅና መስጠት ሊጀምር መሆኑን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ገለፀ።

ባለሥልጣኑ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እንደገና መዝግቦ በጥራት እንዲሠሩ ለማድረግ የሚያግዝ መመሪያ እና አሰራር ሲያወጣ መቆየቱን ገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር ተቋማቱ በተመዘገቡበት የትምህርት ዘርፍ ማስተማር እንደሚችሉ ብቻ ታይቶ ፈቃድ ይሰጣቸው እንደነበረ የተነገረ ሲሆን፤ በአዲሱ የጥራት መመዘኛ መመሪያ መሠረት አስፈላጊውን የጥራት ደረጃ ማሟላታቸው እየተመዘነ ዳግም እንዲመዘገቡ ይደረጋል ተብሏል፡፡

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የሚነሳውን የትምህርት ጥራት መጓደል ለማሻሻል ይረዳል የተባለው ይህ አሰራር፣ ከ2017 የትምህርት ዘመን አጋማሽ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ምዝናው በሒደት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችም ላይ ገቢራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡ #ShegerFM

@tikvahuniversity
#WoldiaUniversity

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለሁሉም ነባር እና አዲስ ገቢ መደበኛ የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡

በዚህም የሁሉም ነባር መደበኛ ተማሪዎች፣ በ2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችው የማለፊያ ውጤት አምጥታችሁ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የምትገቡ አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት መስከረም 27 እና 28/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የመማር ማስተማር ሥራ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

(የዩኒቨርሲቲው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
#AAETQRA

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የሁለት የግል ኮሌጆች ካምፓስን የዕውቅና ፍቃድ ሰረዘ፡፡

ባለስልጣኑ ያደረገውን ድንገተኛ ኢንስፔክሽን ተከትሎ በ44 የግል ኮሌጆች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል፡፡

በዚህም ሸገር ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ እና አልፋ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ግሎባል ካምፓስ "ያለባቸውን ክፍተት ለማስተካከል ፍቃደኛ ባለመሆናቸው" የዕውቅና ፍቃዳቸው የተሰረዘ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡

ልቀት ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ "የተወሰነ ማስተካከያ ያደረገ ቢሆንም፤ ሙሉ በሙሉ ለማስተካከል በጠየቀው መሰረት የአንድ ወር ተጨማሪ ጊዜ" በባለስልጣኑ ተሰጥቶታል፡፡

የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ከነበሩ ተቋማት መካከል ስምንት ኮሌጆች ያለባቸውን ክፍተት ማስተካከላቸውን ባለስልጣኑ በምልከታ ማረጋገጡን አሳውቋል፡፡ እነዚህም፦

1. ያኔት ኮሌጅ 6 ኪሎ ካምፓስ፣
2. ዳማት ኮሌጅ ጊዮርጊስ ካምፓስ፣
3. ያኔት ኮሌጅ ሰፈረ ሰላም ካምፓስ፣
4. ኤክስፕረስ ኮሌጅ፣
5. ቅድስት ሀና ኮሌጅ፣
6. ግራንድ ማርክ ኮሌጅ፣
7. ኩዊንስ ኮሌጅ ሀና ካምፓስ እና
8. ሀራምቤ ኮሌጅ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የዕውቅና ፍቃዳቸው ታግዶ የነበሩና ያለባቸውን ክፍተት በተሰጣቸው ጊዜ ማስተካከላቸው በባለስልጣኑ በምልከታ የተረጋገጠላቸው 15 ተቋማት የዕውቅና ፍቃድ እገዳው ተነስቶላቸዋል፣ የመጨረሻ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነዚህም፦
1. ብራይት ኮሌጅ ልደታ ካምፓስ፣
2. ብራይት ኮሌጅ ጀሞ ካምፓስ፣
3. ልቀት ኮሌጅ 4 ኪሎ ካምፓ'ስ፣
4. ላየን ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ፣
5. ኩዊንስ ኮሌጅ መድኃኒዓለም ካምፓስ፣
6. ሳትኮም ኮሌጅ፣
7. ሀርመኒ ኮሌጅ ሀና ማርያም ካምፓስ፣
8. ኩዊንስ 5 ኪሎ ካምፓስ፣
9. ሃርመኒ ቅሊንጦ ካምፓስ፣
10. አፍሪካ ቤዛ ኮሌጅ፣
11. አረና ኮሌጅ፣
12. ጌጅ ኮሌጅ ሾላ ካምፓስ፣
13. ሀጌ ኮሌጅ፣
14. ኩዊንስ ኮሌጅ ዮሃንስ ካምፓስ እና
15. ኪያሜድ ኮሌጅ እንቁላል ፋብሪካ ካምፓስ እንደሆኑ ባለስልጣኑ ጠቁሟል፡፡

የመጨረሻ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው የነበሩ 18 ተቋማት በተሰጣቸው ጊዜ ያለባቸውን ክፍተት ያስተካከሉ መሆኑን ባለስልጣኑ በምልከታ አረጋግጧል፡፡ እነዚህም፦

1. ዌልነስ ኮሎጅ፣
2. ግሬት ኮሌጅ ቡልቡላ ካምፓስ፣
3. ቢኤስቲ ኮሌጅ 18 ካምፓስ፣
4. ክቡር ኮሌጅ፣
5. ፋርማ ኮሌጅ፣
6. ቅድስት ልደታ ኮሌጅ፣
7. ኤግል ኮሌጅ፣
8. አፍሪካ ጤና ኮሌጅ፣
9. ናሽናል ኮሌጅ፣
10. ካርቫርድ ኮሌጅ፣
11. ሰቨን ስታር ኮሌጅ፣
12. ራዳ ኮሌጅ፣
13. ሪፍት ቫሊ ኮሌጅ ካራ አሎ ካምፓስ፣
14. ኬቢ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ፣
15. ያጨ ኮሌጅ፣
16. ኪያሜድ ኮሌጅ 22 ካምፓስ፣
17. ናይል ሳይድ ኮሌጅ እና
18. ኪያሜድ ኮሌጅ አየር ጤና ካምፓስ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University
#MizanTepiUniversity ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው መስከረም 06 እና 07/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡ (የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡) @tikvahuniversity
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለ3ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል፡፡

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 06 እና 07/2017 ዓ.ም ይከናወናል ብሎ የነበረ ቢሆንም፤ "በተቋሙ ውስጥ እየተሰጡ ያሉ ስልጠናዎች ባለመጠናቀቃቸው ምክንያት" የምዝገባው ቀን ወደ መስከረም 13/2017 ዓ.ም የተቀየረ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት መስከረም 14/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

@tikvahuniversity
#DambiDolloUniversity

ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ነባር ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት መስከረም 22 እና 23/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በ2017 ዓ.ም አዲስ ወደ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችው እና በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን ወደ ፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
በፈረንሳይ ሊዮን ከተማ እየተካሔደ በሚገኘው 47ኛው የዓለም የክህሎት ውድድር ኢትዮጵያ በሦስት መስኮች እየተሳተፈች ትገኛለች፡፡

ጽዮን አዳነ በአይ.ቲ.፣ ብሩክ መኮንን በእንጨት ሥራ እና የሮምነሽ ዋሬ በማምረቻ ዘርፎች ኢትዮጵያን ወክለው እየተወዳደሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በውድድሩ ከ70 ሀገራት የተወጣጡ 1,400 ወጣቶች በ60 የሙያ መስኮች እየተሳተፉ ነው።

@tikvahuniversity
#AksumUniversity

አክሱም ዩኒቨርሲቲ የመደበኛ ነባር ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት መስከረም 7 እና 8/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በመሆኑም ከዚህ ቀደም ስትማሩበት በነበራችሁበት ግቢ በአካል በመገኘት በተጠቀሱት ቀናት ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

በ2016 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁ ተከታትላችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም አዲስ ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ የምትመደቡ ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/10/04 19:25:25
Back to Top
HTML Embed Code: