Telegram Web Link
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ልዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች መካከል 98 በመቶ የሚሆኑት የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሆሞሻ ወረዳ የሚገኘው 'ፋሮ የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት' ዘንድሮ ያስፈተናቸውን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በመሉ ማሳለፍ መቻሉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

@tikvahuniversity
ቤተሰብ አካዳሚ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች ውስጥ በጅማ ካምፓስ ያስፈተናቸውን ተማሪዎች በሙሉ አሳልፏል።

በአዲስ አበባ ካምፓስ ካስፈተናቸው ተማሪዎች መካከል 97 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን አካዳሚው ለቲክቫህ ገልጿል፡፡

አካዳሚው በአጠቃላይ 197 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና አስፈትኗል።

@tikvahuniversity
በራያ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ፕሮግራም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 14 ተማሪዎች መካከል 13ቱ የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል በ2016 ዓ.ም ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያስቀመጣቸው ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ አልፈዋል፡፡

በማዕከሉ የተመዘገበው የዓመቱ ከፍተኛ ውጤት 557 ሲሆን፤ ትንሹ ደግሞ 395 መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። ሌሎች ተማሪዎች ከ419 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

ዘንድሮ በማዕከሉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከተፈተኑት ውስጥ 42.55 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስቲም ማዕከል በዚህ ዓመትም ለ3ኛ ጊዜ በተደጋጋሚ ሁሉንም ያስፈተናቸውን ተማሪዎች ማሳለፍ መቻሉን ገልጿል።

@tikvahuniversity
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ሁሉም የጤና ሳይንስ ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 11 እና 12 /2017 ሲሆን ትምህርት መስከረም 13 ይጀምራል።

@tikvahuniversity
#MekelleUniversity

በ2016 ዓ.ም የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቅያ ፈተና ምክንያት የተቃረጠው ሰሚስተር ለማስጨረስ እና የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ለማስጀመር ዘንድ ሁለተኛ እና ከሁለተኛ ዓመት በላይ የሆኑ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መስከረም 04 - 05 /2017 ዓ.ም ባለው ግዜ ውስጥ በግቢ ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

ሃገራዊ የስታቲስቲክስ ስልጠና በ ኣይናለም ግቢ, (MIT Campus) እየተሰጠ በመሆኑ የኣይናለም ግቢ (MIT Campus) ተማሪዎች ከላይ በተጠቀሰው ግዜ ሳይሆን መስከረም 11-12/ 2017ዓ.ም ወደ ግቢ ገብተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል።

በተካሄደው የሰላም ሚኒስቴር በጎ ኣድራጎት ዘመቻ ለመሳተፍ የኣንደኛ ዓመት የመጨረሻ ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ጥቅምት 06-07/ 2017 ዓ.ም በየግቢያቸው ሪፖርት እንዲያደርጉ ተብሏል። ሆኖም ግን ፈተናውን የወሰዱ (ያጠናቀቁ) የኣንደኛ ኣመት ተማሪዎች ጥቅምት 22-23/2017 ዓ.ም በየግቢያቸው ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደረጉ ተብሏል።

የሪሜዳል ትምህርት መረሃግብር ሲከታተተሉ የነበሩ ተማሪዎች የ2017 ዓ. ም ኣዲስ ተማሪዎች ( Fresh Man) ቅበለ ጊዜ ወደፊት ስለሚገለጽ ከነሱ ጋር ይገባሉ ተብሏል።

@tikvahuniversity
የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያስፈተናቸውን ተማሪዎች በሙሉ አሳልፏል።

ትምህርት ቤቱ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያስፈተናቸው 65 ተማሪዎች ሁሉም ከ458 በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

በትምህርት ቤቱ ከተፈተኑ 65 ተማሪዎች 45 ተማሪዎች ከ500 በላይ ነጥብ አስመዝግበዋል። ቀሪዎቹ 20 ተማሪዎች ከ458 እስከ 499 ነጥብ አምጥተዋል፡፡

በትምህርት ቤቱ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 574 ሲሆን፤ ዝቅተኛው ውጤት 458 እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ተማሪ ጌታቸው እያዩ 574 ነጥብ በማምጣት ከፍተኛውን ውጤት ማስመዝገቡን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በለጠ ኃይሌ ለአሚኮ ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡

በዚህም የሁሉም ነባር መደበኛ ተማሪዎች (ቅድመ-ምረቃ እና ድኅረ-ምረቃ) የ2017 ዓ.ም የመግቢያ ጊዜ መስከረም 10 እና 11/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

መስከረም 13/2017 ዓ.ም ትምህርት የሚጀመር መሆኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለሁሉም ነባር እና አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም በዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት ጀምራችሁ ሳታጠናቅቁ ከግቢ የወጣችሁ የ1ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች በአካል ሪፖርት የማድረጊያ ቀናት መስከረም 6 እና 7/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የሌሎች ነባር የድኅረ ምረቃ እና የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት መስከረም 19 እና 20/2017 ዓ.ም እንደሆነ ተገልጿል።

በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም በዲላ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በፍሬሽማን ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር ዲላ ዩኒቨርሲቲ የምትመደቡ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 19 እና 20/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል።

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
ቲክቫህ ለመላው ኢትዮጵያውያን በተለይም ለተማሪዎች ፣ መምህራን ፣ ከትምህርት ጋር ተያያዥ ስራዎች ላይ ለሚሰሩ ሠራተኞች በሙሉ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የደስታ እና የስኬት እንዲሆን ይመኛል።

@tikvahuniversity
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለመደበኛ ተማሪዎች ጥሪ አደርጓል።

የ2017 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስቴር ምዝገባ/የተማሪዎች ቅበላ/ የሚካሄደዉ ከመስከረም 10 እስከ 11/2017 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

@tikvahuniversity
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለመደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አቅርቧል።

ነባር ቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው መስከረም 27 እና 28/2017 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት መስከረም 30/2017 ዓ.ም ይጀምራል።

ነባር የድህረ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት መስከረም 19 እና 20 ሲሆን መስከረም 23/2017 ዓ.ም ትምህርት የሚጀምር ይሆናል።

በ2016 ዓ.ም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን የተከታተሉ የማለፊያ ውጤት ያመጡ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም አዲስ በትምህርት ሚኒስቴር ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሚመደቡ ፍሬሽማን ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ጥቅምት 4 እና 5/2017 ዓ.ም ይከናወናል።

@tikvahuniversity
ዓዲግራት ዪኒቨርሲቲ በሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ፕሮግራም ካስተማራቸውና በ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 21 ተማሪዎች 17ቱ (80.95 በመቶ) የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ልዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካስተማራቸውና በ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 57 ተማሪዎች 54ቱ (95 በመቶ) የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ልዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካስተማራቸውና በ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 95.2 በመቶ የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ተማሪ ራጂ ተስፋዬ የትምህርት ቤቱን ከፍተኛ ውጤት ማለትም 568 ከ600 ማምጣቱ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#HarariEducationBureau

በ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተሻለ ውጤት በሀረሪ ክልል መመዝገቡን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።

በሀረሪ ክልል ሁሉም ትምህርት ቤቶች ተማሪ ማሳለፍ መቻላቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ጌቱ ነገዎ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም በክልሉ ሁለት ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ሳያሳልፉ መቅረታቸውን ያስታወሱት የቢሮው ኃላፊ፤ ዘንድሮ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን አሳልፈዋል።

በ2015 ዓ.ም 7.1 በመቶ ተማሪዎች ማለፊያ ውጤት አስመዝግበው የነበረ ሲሆን፤ በ2016 ዓ.ም 13.3 በመቶ ተማሪዎች በክልሉ ማለፍ መቻላቸውን ጠቁመዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገቡ ከፍተኛ ውጤቶች መካከል አራቱ በሀረሪ ክልል የተመዘገቡ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ የተመዘገበው ውጤት አጥጋቢ አይደለም ያሉት ኃላፊው፤ በ2017 የትምህርት ዘመን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የበለጠ ይሠራል ብለዋል።

@tikvahuniversity
#UniversityOfKabridahar

ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ ለነባር ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን የመግቢያ ቀናት መስከረም 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ላመጣችሁና በ2017 ዓ.ም ወደ ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ ለምትመደቡ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች በቅርቡ ጥሪ የሚደረግ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
2024/10/04 19:31:13
Back to Top
HTML Embed Code: