Telegram Web Link
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ አድርጓል።

በአስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል ፈተና የማለፊያ ነጥብ ለወንድ ተማሪዎች 50%፣ ለሴት ተማሪዎች 47% እንዲሁም ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች 45% እንደሆነ ቢሮው አሳውቋል።

በዚህም በአስተዳደሩ በ2016 ዓ.ም ለፈተና ከቀመጡ 9,085 ተማሪዎች መካከል 5,673 ተማሪዎች ወይም 62.43 በመቶዎቹ ማለፋቸውን ቢሮው ገልጿል።

ውጤት ለመመልከት 👇
https://www.geight.diresrms.org/View_Result/get_result

@tikvahuniversity
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለክረምት ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና የተመደባችሁ ወደ ተቋሙ መግቢያ ቀን ነገ ሐምሌ 21/2016 ከጠዋት 2፡00-6፡00 በዋናው ሬጅስትራር ሕንጻ መሆኑ ተገልጿል፡፡

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተሞች በሚገኙ 18 ካሞፓሶቹ ያስተማራቸውን 9,000 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በጤና፣ በቢዝነስ፣ በማኅበራዊ ሳይንስና ቴክኖሎጂ መስኮች በቴክኒክና ሙያ፣ በመጀመሪያ እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸው።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ
#MoE

መንግሥት አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን  'ኮደሮችን' ለማሰልጠን ያለመ ኢኒሼቲቭ አስጀምሯል።

ለሦስት ዓመት የሚቆየው ኢኒሼቲቩ፤ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ (UAE) ጋር በመተባባር የሚተገበር ነው።

የፕሮግራሚንግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኮርሶች #ከክፍያ_ነፃ ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

የትምህርት ይዘቶቹን በኦንላይን ተምረው የሚያጠናቅቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው የምስክር ወረቀት ያገኛሉ።

ከ6-7 ሳምንታት በሚፈጀው የኦንላይን ስልጠና ለመሳተፍ እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል የሚያሳይ ቪዲዮ በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ 👇  https://youtu.be/-zSmhhD5qE4

@tikvahuniversity
#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለስምንት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት የማዕረግ ዕድገት ሰጥቷል።

ሙሉ ፕሮፌሰር የሆኑ ምሁራን፦

1. ዶ/ር አህመድ ዘይኑዲን ➧ ፕ/ር በፓራሲቶሎጂ ህክምና
2. ዶ/ር ቤይራ ሀይሉ ➧ ፕ/ር በኔማቶሎጂ
3. ዶ/ር ሌሊሳ ሴና - ፕ/ር በኅብረተሰብ ጤና ኢፒዴሚዮሎጂ
4. ዶ/ር ሙባረክ አበራ ➧ ፕ/ር በአዕምሮ ጤና
5. ዶ/ር ሙሉመቤት አበራ ➧ ፕ/ር በኅብረተሰብ ጤና
6. ዶ/ር ስራውድንቅ ፍቅረየሱስ ➧ ፕ/ር በምግብ ሳይንስና ድኅረ-ምርት ቴክኖሎጂ
7. ዶ/ር የትናየት በቀለ ➧ ፕ/ር በምግብ ሳይንስና ቴክኖሎጂ
8. ዶ/ር ዘሪሁን አየነው ➧ ፕ/ር በሰው ሃብት አስተዳደር

@tikvahuniversity
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ነባር የክረምት ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 27 እና 28/2016 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል።

በዚህም በ2011 ዓ.ም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራቹሁ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ነባር የክረምት ተማሪዎች በተገለፁት ቀናት ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

ለምዝገባ ወደ ተቋሙ ስትሔዱ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ መያዝ ይኖርባችኋል።

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የክረምት ስቴም ሰልጣኝ ተማሪዎችን ተቀብሏል።

ዩኒቨርሲቲው 347 አዲስ የክረምት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ (STEM) ሰልጣኞችን ተቀብሏል።

@tikvahuniversity
አድማስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው 771 በድኅረ-ምረቃ፣ 1,931 በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም ከ3 ሺህ በላይ በቴክኒክና ሙያ መርሐግብር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

አድማስ ዩኒቨርሲቲ 10 ካምፓሶች እና በርካታ የርቀት ትምህርት መስጫ ማዕከላት ያሉት ሲሆን፤ ከኢትዮጵያ ውጪ በሶማሊላንድ እና በፑንትላንድ ካምፓሶች በመክፈት እያስተማረ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሞላ ፀጋይ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የገጠር እና የከተማ ቀበሌዎች የግብርና ናሙና ቆጠራ ያከናውናል።

አገልግሎቱ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ የሚያሟሉ #መረጃ_ሰብሳቢዎችን አወዳድሮ በኮንትራት መቅጠር ይፈልጋል።

በዚህም በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በኩል በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (ሌበር ማርኬት ፖርታል - E-LMIS) በመጠቀም ከመላ የሀገሪቱ ክፍሎች 43,500 ሰራተኞች ይፈልጋል።

በዚህ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን lmis.gov.et ላይ በመግባት በመመዝገብና አቅራቢያችሁ ወደሚገኝ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሔድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር ይዛችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

የሥራ መደብ፡-
የስታቲስቲክስ መረጃ ሰብሳቢ 1
ብዛት፡- 43,500
ፆታ፡- አይለይም
ሊንኩን በመጫን ይመዝገቡ፦
https://lmis.gov.et

@tikvahuniversity
#National_GAT

ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተፈታኞችን ለ3ኛው ዙር አገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና ለማዘጋጀት ቲቶሪያል እየሰጡ ይገኛሉ።

የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ለመቀጠል "ወጥ የሆነ" ፈተና በትምህርት ሚኒስቴር እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ተማሪዎቹ ለመማር የሚያመለክቱበት የትምህርት ክፍል የተለያዩ በመሆናቸው ወጥ ፈተና መሰጠቱ አግባብነት የለውም የሚሉ ባለሙያዎች አሉ፡፡

ተፈታኞች "የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተናው ከባድ ነው፣ የማለፊያ ነጥቡም በጣም ተሰቅሏል" ሲሉ ይደመጣሉ።

ምሁራን በበኩላቸው "ፈተናውን ማቅለል ይቻላል፣ ይህ ግን መፍትሔ አይደለም" ይላሉ። ይልቁንም "ሌሎች አገራት እንደሚያደርጉት የመግቢያ ነጥቡን ቀነስ ማድረግ የተሻለ አማራጭ እንደሆነ" ምሁራኑ ይመክራሉ፡፡

የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና ወስደዋል? በፈተናው ላይ ያለዎትን አስተያየት ለቲክቫህ ያድርሱ። ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከብሔራዊ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ያደርሳችኋል።

@tikvahuniversity
የክረምት ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና ዛሬ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም ይጀምራል።

እስከ ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም በተመረጡ 28 የስልጠና ማዕከላት የሚሰጠውን የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚወስዱ ሰልጣኞቹ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

60 ሺህ የሚሆኑ ሰልጣኞች የሚከታተሉት ስልጠናው፤ ለትምህርት ቤት አመራሮች ለ10 ቀናት እንዲሁም ለመምህራን ለ20 ቀናት እንደሚሰጥ መርሐግብር ተይዞለታል፡፡

ስልጠናውን የተከታተሉ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ከ100% ፈተና የሚፈተኑ ሲሆን፤ 75% እና ከዚያ በላይ የሚያመጡ የምስክር ወረቀት በሙያቸው ይሰጣቸዋል።

ምስል፦ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
የክረምት ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና የመክፈቻ ስነ-ስርዓት በበይነመረብ ተካሒዷል፡፡

ስልጠናውን በሚሰጡ 28 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የመክፈቻ መርሐግብሩን ታድመዋል፡፡

ስልጠናው ለትምህርት ቤት አመራሮች ለአስር ቀናት እንዲሁም ለመምህራን ለሃያ ቀናት ይሰጣል፡፡

@tikvahuniversity
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ከግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ጋር በፈቃድ እና ፈቃድ ዕድሳት አሰጣጥ መመሪያ፣ ስታንዳርዶች እና ዳግም ምዝገባ መምሪያ ላይ ውይይት አካሒዷል፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባለቤቶች/አንድ ተወካይ በውይይቱ ተሳትፈዋል፡፡

@tikvahuniversity
#Exit_Exam

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ባለፈው ወር የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው ተማሪዎች መካከል 13 በመቶ ብቻ ማሳለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ ላይ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ተገኝተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውስጥ 87 በመቶዎቹ መውደቃቸውን ጠቁመዋል። 22 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ  አለማሳለፋቸውን ገልፀዋል።

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ካስፈተኗቸው ተማሪዎች 58 በመቶ ማሳለፋቸውን  ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ ሊያደርግ መሆኑ ተሰምቷል።

ዳግም ምዝገባው ያስፈለገው እንደ  ሀገር ወጥነት ያለው የፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ እና በመንግሥት እና በግል ተቋማት መካከል ያለውን የፈቃድ አሰጣጥ የአሰራር ስርዓት ልዩነት ለማስቀረት መሆኑን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሽፈራው ሽጉጤ ገልፀዋል። #ETA

@tikvahuniversity
2024/10/02 08:14:50
Back to Top
HTML Embed Code: