Telegram Web Link
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታቸውን በተቋሙ ከተከታተሉ ተማሪዎች 𝟗𝟔.𝟗 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ገልጿል።

1,507 ተማሪዎች የሪሚዲያል ትምህርታቸውን በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው 1,461 ተማሪዎች (𝟗𝟔.𝟗 በመቶ) የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው ጠቁሟል።

@tikvahuniversity
ቦረና ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል እና አዲስ ለሚመደቡ ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል።

በ2016 ዓ.ም በቦረና ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ቦረና ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 23 እና 24/2017 ዓ.ም ይከናወናል በማለት ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች ምዝገባው ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድ እና በባትሪ ቆይታ እጅግ አስተማማኝ የሆኑ ላፕቶፕች በተለያዩ ሞዴሎችና በፈለጉት ስክሪን መጠን ኮር እና ጀነሬሽን አሉን።

ላፕቶፕ ከመገዛትዎ በፊት ማወቅ ያለባቹሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳዎታለን።

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለጌመሮች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ወ.ዘ.ተ ሁሉም አሉን! በላፕቶፖቻችን ጥራት አንደራደርም!

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራም ማየት ይችላሉ።

@sww2844
0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
በሦስቱም ቅርንጫፎቻችን (መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸው  ስልጠናዎች ባሉን ውስን ቦታዎች አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለውጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕውቅና ካለው ሰርተፊኬት ጋር! የብዙ ዓመት ልምድና ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች ይማሩ!

🌼 Graphics Design
🌼 Video Editing
🌼 Digital Marketing
🌼 Adobe Photoshop
🌼 English Language
🌼 Website Design
🌼 Programming
🌼 Interior Design
🌼 Database
🌼 Basic Computer
🌼 Accounting Softwares
🌼 SPSS & STAΤΑ
🌼 MS-Project
🌼 Foreign & Local Languages

አድራሻ፦
ቁ.1:
መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)
ቁ.2: ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 639 (ሊፍት ይጠቀሙ) (ትንሹ ኬኬር)
ቁ.3: ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ

☎️    0991929303 / 0991929304 /
         0991926707


Telegram: https://www.tg-me.com/topinstitutes
ዲላ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎቹን በመቀበል ላይ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ለነባር የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ባደረገው ጥሪ መሠረት ተማሪዎቹን በመቀበል ላይ ይገኛል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ Climate Change and Environmental Management የማስተርስ ፕሮግራም ከፍቷል።

የገበያ ተፈላጊነት ባለው የትምህርት ፕሮግራም አመልካቾች እንዲመዘገቡ ጥሪ አድርጓል።

በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና (NGAT) ያለፉ ተማሪዎች ማመልከት ይችላሉ ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው 1ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ነባር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎቹን እየተቀበለ ነው፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከኖርዌዩ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በSocial Anthropology የማስተርስ ፕሮግራም ለአመልካቾች ክፍት አድርጓል።

ለሁለት ዓመታት ለሚቆየው ፕሮግራም፤ በሶሻል አንትሮፖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸውና ብቁ አመልካቾች ማመልከት ይችላሉ ተብሏል።

በፕሮግራሙ የመጀመሪያ ሴሚስተር ኮርሶች ላይ የኖርዌይ ፕሮፌሰሮች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

ለፕሮግራሙ በውድድር የሚመረጡ አምስት አመልካቾች ይፈለጋሉ።

አመልካቾች የአንድ ወር የፊልድ ወጪያቸው በፕሮግራሙ ይሸፈናል። አመልካቾች የኑሮ ወጪ እና የትምህርት ወጪ (ለግል አመልካቾች) እንዲሸፍኑ ይጠበቃል።

መስፈርቶች፦

► የመጀመሪያ ዲግሪ በአንትሮፖሎጂ ወይም በሶሻል አንትሮፖሎጂ ያላት/ያለው
► CGPA 3.00 ወይም B ያላት/ያለው
► በሶሻል አንትሮፖሎጂ ረዳት መምህራን ይበረታታሉ

የተመረጡ አመልካቾች ለፅሁፍ እና የቃል ፈተና እንደሚጠሩ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የምዝገባ ጊዜ፦
ከመስከረም 20-27/2017 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ፦
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

ለተጨማሪ መረጃ፦
[email protected] / [email protected]

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 3,271 ተማሪዎች ቅዳሜ መስከረም 25/2017 ዓ.ም ያስመርቃል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት ተከፍቷል። ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን በውስጡ ያካተተው የቱሪዝም ሳምንቱ በዛሬው ዕለት በስካይላይት ሆቴል በኤግዚቢሽን ሲከፈት፣ በርካታ ተጋባዥ እንግዶች ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት ተገኝተዋል፡፡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከቪዚት ኦሮሚያ ጋር በመተባበር የዚህ ትልቅ ዝግጅት የክብር የወርቅ ስፖንሰር መሆኑን በታላቅ ደስታ ይገልፃል፡፡ በኤግዚቢሽኑ እንዲሁም በፓናል ውይይቶቹ ላይ በመገኘት የዝግጅቱ ተካፋይ እንድትሆኑ ስንጋብዝ በታላቅ አክብሮት ነው!

ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስካይላይት ሆቴል በማቅናት ስለ ሳፋሪኮም ምርቶችና አገልግሎቶች በሰፊው እንወቅ! ከዳር እስከ ዳር በሚገኘው በሳፋሪኮም ኔትወርክ እንገናኝ! አስተማማኙን ኔትወርክ አሁኑኑ እንቀላቀል! ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit #FurtherAheadTogether #OromiaTourismWeek #VisitOromia #Oromia
#KiburCollege #DigitalID #Hackathon

በርዋንዳ ኪጋሊ በተካሔደ የምስራቅ አፍሪካ ሪጅናል #ዲጂታል_መታወቂያ #ሀካቶን ውድድር የክቡር ኮሌጅ ተማሪዎች 4ኛ ደረጃን በማግኘት አጠናቀዋል፡፡

ከዘጠኝ ሀገራት የተወጣጡ 18 ቡድኖች በተሳተፋበት ውድድር፤ የክቡር ኮሌጅ ሦስት ተማሪዎች ኢትዮጵያን በመወከል በውድድሩ የመጨረሻ ፍፃሜ ዙር ተወዳድረዋል፡፡

ተማሪ ያሬድ ኪሮስ፣ ተማሪ ሚኪያስ ተስፋዬ እና ተማሪ ዮርዳኖስ ከፈለኝ፣ የጤና መታወቂያ ላይ ትኩረት ያደረገ የቡድን ፕሮጀክት አቅርበዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ለጤና ችግሮች የዲጂታል መታወቂያ መፍትሔዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።

በአዲስ አበባ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና መስሪያ ቤት በተካሔደ ሰነ-ስርዓት ተማሪዎቹ ሽልማታቸውን የተቋሙ ሳይበር ሰኩሪት ኃላፊ ከሆኑት አቶ ካሳዬ ታፈሰ ተቀብለዋል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ የብሔራዊ መታወቂያ #ፋይዳ እንቅስቃሴ ጎብኝተው ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

የሀካቶን ውድድሩ በካርኔጊ ሜሎን ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ሳይላብ-አፍሪካ/ኡፓንዚ ኔትወርክ እና በማይክሮ ሴቭ ኮንሰልቲንግ (MSC) በጋራ የተዘጋጀ ነው፡፡

@tikvahuniversity
#ይመዝገቡ

ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ይውሰዱ።

አምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ በአራት የስልጠና ዘርፎች የኦንላይን ስልጠና ይሰጣል፦

► በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣
► በአንድሮይድ ማበልፀግ፣
► በዳታ ሳይንስ እና
► በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ።

ስልጠናውን በተሰጠው ጊዜ (ስምንት ሳምንት) ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይበረከትላቸዋል።

ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በ2017 ዓ.ም በደረጃ እና በመጀመሪያ ዲግሪ በቀን መርሐግብር (Regular) ሰልጣኞችን ይቀበላል።

በመጀመሪያ ዲግሪ የስልጠና መስኮች፦
- Hotel Management
- Tourism Management

በመጀመሪያ ዲግሪ ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ፦

- የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያላት/ያለው
- የ8ኛ እና የ12 ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው
- ኢንስቲትዩቱ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና ማለፍ

የምዝገባ ጊዜ፦
ከመስከረም 27 እስከ ጥቅምት 01/2017 ዓ.ም በሥራ ሰዓት

(የኢንስቲትዩቱ ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
#AASTU

በ2017 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የተፈተናችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ውጤታችሁ ተለቋል፡፡

ፈተናውን የወሰዳችሁ ተማሪዎች ተከታዩን ሊንክ በመጠቀምና አድሚሽን ቁጥራችሁን በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ውጤት ለማየት፦ https://stu.ethernet.edu.et

@tikvahuniversity
2024/10/02 02:01:18
Back to Top
HTML Embed Code: