Telegram Web Link
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕግ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በኑረምበርግ ዓለም አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር እየተሳተፉ ነው።

በታዋቂው ውድድር በመጀመሪያው ዙር 600 ዩኒቨርሲቲዎች የተሳተፉ ሲሆን፤ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 40 ዩኒቨርሲቲዎች በጀርመን ኑረምበርግ ከተማ ለሚካሄደው የመጨረሻው ዙር ውድድር አልፈዋል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕግ ትምህርት ቤት አፍሪካን በመወከል በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉት አራት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ሲሆን፤ኢትዮጵያን በመከል በውድድሩ ላይ የሚሳተፈው ብቸኛ ቡድን ነው።

መካሻው ጫኔ፣ እሱባለው ሞላ እና ትዕግስት ደርብ በውድድሩ ላይ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን በመወከል የሚወዳደሩ ሲሆን፤ የቡድኑ አሰልጣኝ እንድሪያስ ጌታቸው እና የቡድኑ አስተባባሪ ተገኘ ዘርጋው በመሆን በውድድሩ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ታሪካዊቷ ኑረምበርግ ከተማ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃትን ተከትሎ የናዚ የጦር ወንጀለኞች የተዳኙበት ከተማ ናት።

@tikvahuniversity
#KUE

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ 'የአደጋ ጊዜ ትምህርት' ስርዓተ ትምህርት ቀርጿል፡፡


ስርዓተ ትምህርቱ በባለድርሻ አካላት እና በገምጋሚዎች ማረጋገጫ ተሰጥቶታል፡፡

በዚህም ዩኒቨርሲቲው በ2017 የትምህርት ዘመን በማስተርስ ደረጃ ትምህርቱን መስጠት እንደሚጀምር ይጠበቃል፡፡

የትምህርቱ መጀመር ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በዘርፍ የሚያስፈልጉ በርካታ ሙያተኞችን ለማፍራት እንደሚያስችለው ተገልጿል፡፡

ስርዓተ ትምህርቱ በፀጥታ ችግር ምክንያት ከትምህርት የራቁ ዜጎች ወደ ትምህርት ተቋማት እንዲመለሱ እንዲሁም በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ሆነው ትምህርት እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው፡፡ በተጨማሪም የስነ-ልቦና ድጋፍ መስጠት በስርዓተ ትምህርቱ መካተቱም ታውቋል፡፡

@tikvahuniversity
#ነፃ_የፌሎውሺፕ_ዕድል

ከዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ተመርቀዋል? የማኅበረሰብ ለውጥ ለማምጣት ፍላጎት አለዎት?

እንግዲያውስ ለዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ምላሽ የአመራር ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ያመልክቱ።

ለሁለት ዓመት የሚቆየው ፌሎውሺፕ ፕሮግራሙ የአደጋ ተጋላጭነት አስተዳደር ክህሎትና ልምድ እንዲያጎለብቱ ያስችልዎታል።

በዘርፉ ባለሙያዎች ስልጠና የሚያገኙ ሲሆን፤ በፕሮጀክቶች ላይ በመስራት ከዘርፉ ሙያተኞች ጋር ትስስር እንዲፈጥሩ ይደረጋል።

ስለፌሎውሺፕ ፕሮግራሙ መረጃ ለማግኘት 👇
https://drive.google.com/file/d/12fK_rTrR37tfEasG7tPd4Sm--4L2jkeu/view?usp=drive_link

ኦንላይን ለማመልከት 👇
https://docs.google.com/forms/d/1QJflHITYBmP_dxSQRTWhUsGZoHRQashTNqMsIOd2zZI/edit

የማመልከቻ ጊዜው የሚያበቃው 👇
ነሐሴ 5/2016 ዓ.ም

@tikvahuniversity
ከM-PESA Safaricom app ፈጣን የኢንተርኔት ጥቅል በመግዛት እስከ 50% ተጨማሪ ጥቅል እናግኝ!

M-PESA ላይ እንመዝገብ! በM-PESA እንገበያይ!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉 https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether
Tikvah-University
#WachemoUniversity ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ተመድቦለታል። ዳዊት ሃየሶ (ዶ/ር) ከሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ጀምሮ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው እንደተወከሉ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ ያሳያል። የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) እና ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት…
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመደቡት ዳዊት ሀዬሶ (ዶ/ር) ከዩኒቨርሲቲው የማኔጅመንት ካውንስል እና ሌሎች ሠራተኞች ጋር ትወውቅ አድርገዋል።

በዩኒቨርሲቲው የተጀመሩ ጠንካራ ሥራዎችን በማስቀጠል፣ ተቋሙን ተወዳዳሪ ለማድረግ እንደሚሰሩ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።

ተቋማዊ አስራሮችን በመገንባት የአካዳሚክ አካባቢ የልህቀት አቅጣጫዎችን ለማጠናከር ይሰራል ብለዋል።

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2.7 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የኤሌክትሮኒክስ መጽሄት፣ ኤሌክትሮኒክስ መጻሕፍት፣ የምርምር መመዘኛ እና የፕላጃሪዝም ማሳወቂያ ቴክኖሎጂ ገዝቷል።

የተገዙት የኤሌክትሮኒክስ መጽሄት፣ መጻሕፍት እና ቴክኖሎጂው የዩኒቨርሲቲውን የመማር ማስተማር እና የጥናትና ምርምር ሥራዎች በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ያስችላል ተብሏል።

የኤሌክትሮኒክስ መጻሕፍቱ እና መጽሄቶቹ ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት እንደሚያገለግሉ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ጀይሉ ዑመር (ዶ/ር) ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የክረምት ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚሰጡ የአሰልጣኞች ስልጠና (ToT) ዛሬ ተጠናቋል።

የአሰልጣኞች ስልጠና ከሐምሌ 17/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተሰጥቷል።

የአሰልጣኞች ስልጠናው በትምህርት አመራርነት፣ በእንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ የትምህርት መስኮች በማስተማር ስነ-ዘዴ ላይ ትኩረት በማድረግ መሰጠቱ ታውቋል።

የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የክረምት ስልጠና የፊታችን ሰኞ ይጀምራል።

ስልጠናው ለትምህርት ቤት አመራሮች ለአስር ቀናት፤ ለመምህራን ለ20 ቀናት ይሰጣል።

ምስል፦ ወሎ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
የክረምት ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና የፊታችን ሰኞ ይጀምራል።

የአቅም ግንባታ ሰልጣኞቹ ሰኞ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም እስከ ቀኑ 6፡00 ብቻ ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ መግባት ይጠበቅባቸዋል።

ስልጠናውን የሚሰጡ የተመረጡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሰልጣኞቹ ጥሪ እያደረጉ ነው።

ሰልጣኞች ወደየተመደባችሁበት ተቋም ስትሔዱ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ መያዝ ይኖርባችኋል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሰልጣኞች የምዝገባ ቦታ፦ ፔዳ ግቢ

(ወልድያ፣ ባሕር ዳር እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ያደረጉት ጥሪ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
በ2015 ዓ.ም ተቋርጦ የነበረው የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክረምት ትምህርት መርሐግብር በዚህ ዓመት መቀጠሉ ይታወቃል።

ባለፉት ዓመታት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዲሁም በፀጥታ ችግር ምክንያት ጫና ውስጥ የቆየው የክረምት ትምህርት ዘንድሮ መሰጠት ጀምሯል።

የ2016 ዓ.ም የክረምት መርሐግብር ትምህርት ከሐምሌ ወር ሁለተኛ ሳምንት ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል።

ምስል፦ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ሳምንት ከ1 ሺህ በላይ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ የክረምት መርሐግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ፡፡

ብሪቲሽ ካውንስል ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የ IELTS ፈተና ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ በመከናወን ላይ ይገኛል።

ሁለት አይነት የ IELTS ፈተናዎች (IELTS Academic and IELTS General Training) ይሰጣሉ፡፡

የብሪቲሽ ካውንስል ድረ-ገፅ ላይ በመግባት ኦንላይን መመዝገብ ይችላሉ 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts/dates-fees-locations

ለፈተናው ዝግጅት የሚያስፈልግዎትን ስልጠና እና ምክር ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማግኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ፦ 0925629589

@tikvahuniversity
2024/10/02 14:15:49
Back to Top
HTML Embed Code: