Telegram Web Link
የመምህራንና የትምህርት አመራሮች የክረምት ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚሰጡ የአሰልጣኞች ስልጠና (ToT) በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ዛሬ መሰጠት ጀምሯል።

የአሰልጣኞች ስልጠና ከሐምሌ 17-19/2016 ዓ.ም ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው መርሐግብር ያሳያል።

የአሰልጣኞች ስልጠናው በትምህርት አመራርነት፣ በእንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ የትምህርት መስኮች በማስተማር ስነ-ዘዴ ላይ ትኩረት በማድረግ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና ከሐምሌ 22 እስከ ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች እንዲሁም ዳግም ተፈታኞች ሰኔ 24/2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና መውሰዳቸው ይታወቃል።

በርካታ ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤት ሳይገለፅ ዘገየ ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ አድርሰዋል።

በጉዳዩ ላይ የኢንስቲትዩቱን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ጠይቀናል።

"ኢንስቲትዩቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመውጫ ፈተናው ላይ እየተወያየ መሆኑን" ዳይሬክቶሬቱ ለቲክቫህ ተናግሯል። ምንም እንኳን የመወያያ ጉዳዮቹን ዝርዝር ባይገልፁም።

"የሁለቱ ተቋማት ውይይት በቅርቡ መቋጫ እንደሚያገኝና የተፈታኞች ውጤትም እንደሚገለፅ" ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከኢንስቲትዩቱ ሰምቷል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለ 2,135 ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና በኦንላይን መስጠቱ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለክረምት የ STEM ማጠናከሪያ ትምህርት ተማሪዎች አቀባበል አድርጓል።

ተማሪዎቹ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡና የተሻለ ውጤት ያላቸው መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
የዲላ ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል ለክረምት መርሐግብር ሰልጣኞች ቅበላ አድርጓል።

የሳይንስ ዝንባሌ ያላቸውና ከጌዴኦ ዞን ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 240 ከ7-12ኛ ክፍል ተማሪዎች ስልጠናውን ይወስዳሉ ተብሏል።

ተማሪዎች ለሁለት ወራት በዩኒቨርሲቲው በሚኖራቸው ቆይታ፤ የምግብ፣ የህክምና እና የመኝታ አገልግሎት እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#ማስታወሻ

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ለመከታተል ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ሐምሌ 22 እና 23/2016 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ጥሪውን ባለፈው ወር ሰኔ 8/2016 ዓ.ም ያደረገ ሲሆን፤ ጥሪው አለመቀየሩን እንድናረጋግጥላቸው በርካታ ተማሪዎች ጠይቀውናል።

ጥሪው #አለመቀየሩን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከአንድ የተቋሙ ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል።

ሪፖርት ማድረጊያ ቦታዎች፦

- የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በፖሊ ካምፓስ
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በግሽ ዓባይ ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው
➧አራት ጉርድ ፎቶግራፍ
➧ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ

@tikvahuniversity
ዩኒቨርሲቲዎች ለክረምት ልዩ ሰልጣኝ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ጥሪ እያደረጉ ነው።

ልዩ የክረምት የአቅም ግንባታ ሰልጣኞቹ ሰኞ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም እስከ ቀኑ 6፡00 ብቻ ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ/ተቋም መግባት ይጠበቅባቸዋል።

ሰልጣኞች ወደየተመደባችሁበት ተቋም ስትሔዱ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ መያዝ ይኖርባችኋል።

(የደብረ ብርሃን እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
AAU 2017 E.C. Academic Calendar.pdf
1.2 MB
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2024/25 አካዳሚክ ካላንደር
#AAU_Academic_Calendar

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2024/25 አካዳሚክ ካላንደሩን ይፋ አድርጓል፡፡

► መስከረም 3/2017 ዓ.ም፦
በ2016 ዓ.ም የገቡ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ወደየካማፓሶቻቸው ይመለሳሉ፡፡
► መስከረም 4-5/2017 ዓ.ም፦
የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የማታ ተማሪዎች ምዝገባ፡፡
► መስከረም 7-8/2017 ዓ.ም፦
የ3ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ፡፡
► መስከረም 14/2017 ዓ.ም፦
የ2017 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት ይጀምራል (በ2016 ዓ.ም ከገቡ ተማሪዎች በስተቀር፡፡)

(ሙሉው የ2024/25 አካዳሚክ ካላንደር ከላይ በፒዲኤፍ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ነባር የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም የክረምት ትምህርት ምዝገባ ሐምሌ 22 እና 23/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦ በዩኒቨርሲቲው ዋና ሬጅስትራር ህንጻ ቁ. 121

በ2016 ዓ.ም በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እንድትሰለጥኑ የተመደባችሁ አዲስ ሰልጣኝ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች መግቢያ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የጤና ኢኒስቲትዩት እና እንስሳት ህክምና ሳይንስ ተማሪዎች መግቢያ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከላይ ጥሪ የተደረገላችሁ ተማሪዎች በሙሉ ወደ ተቋሙ ስትሔዱ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
*400,000 ብር??* በዛ ላይ ደግሞ አስቡት የእናንተ ሙዚቃ በመላው ኢትዮጵያ ሲደመጥ ... እናንተ ችሎታው ይኑራችሁ የቀረውን በእኛ ጣሉት! አሁኑኑ የአንድ ደቂቃ ቪዲዮአችንን እንላክ!

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፦

🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትን ከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳትረሱ
📲 የTikTok ቻናል @Safaricomet ታግ እናድርግ

እንዝፈን! ፖስት እናድርግ! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!
እንዳያመልጣችሁ!


#SafaricomEthiopia #1Wedefit #FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለክረምት ልዩ ሰልጣኝ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ጥሪ እያደረጉ ነው።

ልዩ የክረምት የአቅም ግንባታ ሰልጣኞቹ ሰኞ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም እስከ ቀኑ 6፡00 ብቻ ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ/ተቋም መግባት ይጠበቅባቸዋል።

ሰልጣኞች ወደየተመደባችሁበት ተቋም ስትሔዱ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ መያዝ ይኖርባችኋል።

(ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እና ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ያደረጉት ጥሪ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
የመምህራንና የትምህርት አመራሮች የክረምት ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚሰጡ የአሰልጣኞች ስልጠና (ToT) በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ ይገኛል።

የአሰልጣኞች ስልጠና ከሐምሌ 17-19/2016 ዓ.ም ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው መርሐግብር ያሳያል።

የአሰልጣኞች ስልጠናው በትምህርት አመራርነት፣ በእንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ የትምህርት መስኮች በማስተማር ስነ-ዘዴ ላይ ትኩረት በማድረግ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ምስል፦ ዋቸሞ፣ ወልቂጤ እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች

@tikvahuniversity
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ

በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

➧ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 13
➧ የሥራ ቦታ፦ መቐለ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ
➧ የሥራ ልምድ፦ ከዜሮ ዓመት ጀምሮ
➧ የማመልከቻ ጊዜ፦ ከሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት

አመልካቾች የማይመለስ የትምህርት ማስረጃ እና CV እንዲሁም የሙያ ፍቃድ በመያዝ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ከሐምሌ 12/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት (እስከ ሐምሌ 25/2016 ዓ.ም ድረስ) በሰው ሃብት ልማት አስተዳደር ኮሌጅ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
2024/10/02 12:33:40
Back to Top
HTML Embed Code: