Telegram Web Link
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1,381 ተማራዎች አስመረቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ያስመረቃቸው ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ እና በሁለተኛ ዲግሪ መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ በልዩ ሁኔታ በጤና ስፔሻሊቲ ዘርፍ አምስት የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስቶችን አስመርቋል። #SMMA

@tikvahuniversity
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከ 800 በላይ በቅድመ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ያስተማራቸውን ተማሪዎች ያስመርቃል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ነገ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም በሚያካሒደው 16ኛ ዙር የምረቃ ሥነ-ስርዓት፤ 446 የድኅረ ምረቃ እና 409 የቅድመ ምረቃ ዕጩ ምሩቃን በድምሩ 855 ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅ ይጠበቃል።

@tikvahuniversity
#BoranaUniversity

ቦረና ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት አካሒዷል።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 135 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ አስመርቋል።

ቦረና ዩኒቨርሲቲ በሰኔ 2013 ዓ.ም ተመርቆ፥ በ2014 የትምህርት ዘመን በ15 የትምህርት ዘርፎች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መጀመሩ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
#WallagaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በጊምቢ እና በሻምቡ ካምፓሶች ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

ጊምቢ ካምፓስ 385 ተማሪዎችን ሲያስመርቅ፥ ሻምቡ ካምፓስ 449 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና ተከታታይ መርሐግብር ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ነቀምቴ ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 2,335 ተማሪዎችን ትናንት ማስመረቁ ይታወቃል፡፡

@tikvahuniversity
#SamaraUniversity

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1,478 ተማሪዎች አስመረቀ።

15ኛ ዙር ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity
#InjibaraUniversity

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ያስተማራቸውን ተማሪዎች ነገ ያስመርቃል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ነገ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም በሚያካሒደው 5ኛ ዙር የምረቃ ሥነ-ስርዓት፥ 268 የድኅረ ምረቃ እና 428 የቅድመ ምረቃ ዕጩ ምሩቃን በድምሩ 696 ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅ ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
* National Exam

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን በኦንላይን የሚፈተኑ ተማሪዎች ልምምድ እያደረጉ እንደሚገኙ ይታወቃል።

ተማሪዎች እና ወላጆች / መምህራን ሲስተሙን እንዴት አገኛችሁት ? ለዋናው ፈተና ምን አሳሳቢ ጉድለት ተመለከታችሁ ? ምን ጥሩ ነገር ተመለከታችሁ ?

በአስተያየት መስጫው አጋሩን።

@tikvahuniversity
🎓🏥 ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሐኪሞችን አስመርቋል።

16ኛ ዙር የምረቃ ስነ-ስርዓቱን ትናንት ያከናወነው ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፤ በውስጥ ደዌ ህክምና የስፔሻሊቲ ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ስድስት ስፔሻሊስት ሐኪሞችን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አስመርቋል።

ስፔሻሊስቶቹ (Internal Medicine Specialists) በዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት ሼክ ሐሰን ያባሬ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስልጠናቸውን ተከታትለው ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

ይህም ለዩኒቨርሲቲው እንዲሁም ለአካባቢው ማኅበረሰብ ትልቅ ትርጉም ያለውና በዘርፉ የሚሰጠውን ሕክምና ክፍተቶች መሙላት የሚችል ነው ተብሏል።

@tikvahuniversity
#HarariEducatiomBureau

የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ አድርጓል፡፡

ተፈታኝ ተማሪዎች ከዚህ በታች በተቀመጠው ሊንክ በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት የሚችሉ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል፡፡

ውጤት ለማየት 👇
https://harari.ministry.et/

በክልሉ የ8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 4 እና 5/2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ

የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት የህክምና ዶክተሮችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 12
➤ የሥራ ቦታ፦ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ
➤ የማመልከቻ ጊዜ፦ ከሰኔ 24/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት
➤ የምዝገባ ቦታ፦ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የሰው ሀብት አስተዳደር ቢሮ ቁ. 2 ወይም በኢሜል አድራሻ [email protected]

ለተጨማሪ መረጃ፦ 0575553618 / 0575553628

(የተቀመጡ መስፈርቶችና አስፈላጊ ሰነዶችን የተመለከተ መረጃ ከላይ ተያይዟል፡፡)

@tikvahuniversity
#2024_Commencement

19 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ያስመርቃሉ፡፡

ዛሬ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች የትኞቹ ናቸው?

አምቦ ዩኒቨርሲቲ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
ወሎ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
#JinkaUniversity

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 871ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 85ቱ ዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም አሰልጥኖ ያስመረቃቸው መሆኑ ተገልጿል።

ነፃ የትምህርት ዕድል አጊኝተው በዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ የደቡብ ሱዳን ዜጎችም በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀዋል።

@tikvahuniversity
#DillaUniversity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በቡና ሳይንስ ኢኮኖሚክስ በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ድግሪ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 2,356 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል ከ 120 በላይ የሚሆኑት በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

@tikvahuniversity
#ArbaMinchUniversity

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 2,544 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

ተመራቂዎቹ በቅድመ እና በድኀረ ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ ናቸው፡፡

@tikvahuniversity
#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 859 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

ምሩቃኑ 4 በዶክትሬት ዲግሪ፣ 446 በማስተርስ ዲግሪ እንዲሁም 409 በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 814 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

ተመራቂዎቹ በቅድመ እና በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም በመደበኛ፣ በርቀት እና በተከታታይ መርሐግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity
2024/10/01 18:35:02
Back to Top
HTML Embed Code: