Telegram Web Link
የትምህርት ማስረጃዎችን የማጥራት ሥራ በክልሎች ደረጃ ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡

በፌደራል ተቋማት ላይ የተጀመረው ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን የመመርመር ሥራ በክልሎች ደረጃ እንደሚጀመርም የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ም/ዋ/ዳይሬክተር ቢኒያም ሔሮ ለአሐዱ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ማስረጃዎችን የመመርመር ሥራው በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ እንደሚመራ ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ የትምህርት ማስረጃዎችን በዲጂታል አማራጭ ብቻ ለመስጠት ሙከራ እየተደረገ እንደሆነም ኃላፊው አብራርተዋል፡፡

ማስረጃዎችን በመፈተሽና በማረጋገጥ የህግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እየተሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡ #AhaduFM

@tikvahuniversity
ባለ ብዙ ሙያ ተመራቂው

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ባሳለፍነው ቅዳሜ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል ባለ ብዙ ሙያ ተመራቂ የሆኑት ዶ/ር በዛብህ ብርሃኑ ይገኝበታል።

የቴሌቪዥን ድራማዎች ፅሁፍ ዝግጅት እና መፃሕፍት ማሳተም ዶ/ር በዛብህ የሚታወቅባቸው ሌሎች ጉዳዮች ናቸው፡፡

ዶ/ር በዛብህ በቅርቡ የሚያሳትመውን ጨምሮ አራት መፃሕፍትን የፃፈ ሲሆን፤ ስድስት ሲትኮም ድርሰቶችን በመድረስ ለህዝብ አድርሷል፡፡

በጥርስ ህክምና የዶክትሬት ዲግሪ ተመራቂው በዛብህ፤ በሀገራችን በተለያዩ ቴሌቪዥን የሚተላለፉ ተከታታይ ድራማዎች ላይ በደራሲነት ተሳትፏል፡፡

ዘጠነኛው ሺ ከ35 ክፍል በላይ፣ መስሪያ ቤት፣ ሳሎኑ፣ ዶክተሮቹ፣ ፊሽካዎቹ እና አንድ ላይ የተሰኙ ድራማዎች ላይ በደራሲነትና በዳይሬክተርነት ተሳትፏል። በርካታ የቴሌቪዥን እና የራዲዮ ማስታወቂያዎችንም አዘጋጅቷል።

ደራሲ እና የጥርስ ሐኪም ዶ/ር በዛብህ ብርሃኑ፤ በቅርቡ ለህትመት የሚበቃ "የአፍ ጤና አጠባበቅ ለልጆች እና ለወላጆች" የሚል መማሪያ መፅሐፍ አዘጋጅቶ ማጠናቀቁንም ገልጿል።

@tikvahuniversity
#AddisAbabaUniversity

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ከአምስት ዓመታት በኋላ ዳግም ወደ ህትመት ሥራ መመለሱ ተሰምቷል።

ለዘመናት የተለያዩ የህትመት ውጤቶችን ለአንባብያን ሲያበረክት የቆየው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ፤ በግብርና፣ በኢኮኖሚ፣ በትምህርት እና በፓን አፍሪካኒዚም ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ስምንት መፃሕፍትን በማተመ ዳግም ሥራ መጀመሩን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በሌላ መረጃ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመፃሕፍት አውደ ርዕይ በ 6 ኪሎ ካምፓስ (ዋናው ግቢ) ትናንት ተከፍቷል፡፡

በርካታ መፃሕፍት የቀረቡበት አውደ ርዕዩ፤ እስከ እሁድ ሚያዝያ 13/2016 ዓ.ም ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል።

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ጥቆማ

የመሬት ሕግ እና ፖሊሲ ቅኝት በኢትዮጵያ የተሰኘ መፅሐፍ አርብ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም ይመረቃል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ለህትመት የበቃው መፅሐፉ፤ በዳንኤል በሀይሉ የተፃፈ መሆኑ ታውቋል፡፡

መፅሐፉ አርብ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 በራስ መኮንን አዳራሽ ይመረቃል፡፤

@tikvahuniversity
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቼ ይሰጣል?

2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መቼ እንደሚሰጥ በርካቶች ጥያቄ አድርሰውናል።

12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል።

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ እንዳደረጉ መገለፁም ይታወሳል፡፡

ለሦስተኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በቀርከሃ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ያካሒዳል፡፡

"Climate-smart Bamboo Forest Economy for Sustainable Development” በተሰኘ ጭብጥ ላይ የሚመክረው ጉባኤው፤ ሚያዝያ 11 እና 12/2016 ዓ.ም ይካሔዳል፡፡

ቀርክሃ ከምግብነት እስከ ቤት ውስጥ መገልገያ እቃ፣ ለቢሮ እና ለመኖሪያ እንዲሁም ለቢዝነስ፣ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው አረንጓዴ ወርቅ ነው፡፡

ኢትዮጵያ አንድ ሚሊዮን ሄክታር የተፈጥሮ ቀርክሃ ሃብት እንዳላት የሚገመት ሲሆን በቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የቀርክሃ ሃብት ይገኛል፡፡

ለሁለት ቀናት በሚካሔደው ጉባኤ፤ በርካታ የዘርፉ ተዋናዮች እና ተመራማሪዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡

@tikvahuniversity
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ከዚህ በታች በተገለፀው የትምህርት መስክ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ በመምህርነት በቋሚ ኮንትራት ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡

➤ የሥራ መደብ፦ መምህርነት
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 16
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ በህክምና የመጀመሪያ ዲግሪ
➤ የሥራ ቦታ፦ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ
➤ የመመዝገቢያ ጊዜ፦ ከሚያዝያ 8/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ብቻ
➤ የምዝገባ ቦታ፡- አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የሰው ሃብት አስተዳደር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 5

Note:

አመልካቾች ለምዝገባ ስትሔዱ የ8ኛ እና 10ኛ/12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት፣ የመጀመሪያ ዲግሪ ማስረጃ ሰርቲፊኬት እንዲሁም የሙያ ፍቃድ ምዝገባ የታደሰ ዋናውና የማይመለስ አንድ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

አመልካቾች የመጀመሪያ ዲግሪ ውጤታችሁ 3.00 እና ከዚያ በላይ ሊሆን ይገባል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ “የባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎች” በተሰኘ ጭብጥ ላይ የፓናል ውይይት መድረክ አዘጋጅቷል፡፡

ውይይቱ ዛሬ ሚያዝያ 10/2016 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ መታሰቢያ አዳራሽ ይካሔዳል፡፡

መርሐግብሩን የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በኢትዮጵያ ከሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ክፍል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ ዘርፉ ታዋቂ የሆኑ ምሁራን በመድረኩ በአቅራቢነትና ተወያይነት ይሳተፋሉ፡፡ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡

@tikvahuniversity
በሰኔ 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ የርቀት እና ተከታታይ መርሐግብር ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር በወሰነው መሰረት የአገልግሎት ክፍያ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) እስከ ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም ድረስ እንዲከፍሉ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አሳስቧል።

ክፍያውን ያልፈፀመ ተማሪ የመውጫ ፈተና መውሰድ የማይችል መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

“ኢትዮጵያ:- ከግብርናና ከምግብ ቀውስ ነጻ ስለ መውጣት” በሚል ርዕስ ለህትመት የበቃ መፅሐፍ ተመረቀ፡፡

“ኢትዮጵያ:- ከግብርናና ከምግብ ቀውስ ነጻ ስለ መውጣት” የተሰኘው የአቶ ጌታቸው ድሪባ የጥናት ውጤት የሆነው መፅሐፉ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ለህትመት መብቃቱ ታውቋል፡፡

በሀገሪቱ የግብርና ዘርፍ ልማት ላይ ጥልቅና ሳይንሳዊ ዕይታን ያቀረበው መፅሐፉ፤ በዘርፉ ለሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች ማጣቀሻ ሆኖ ያገልግላል ተብሏል፡፡

መፅሐፉ ETHIOPIA: OVERCOMING AGRICULTURAL AND FOOD CRISES በሚል ርዕስ በእንግሊዘኛ መታተሙም ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፈው ወር ያጋጠመውን ችግር ተከትሎ ገንዘብ ያወጡ ወይም ያዘዋወሩና እስካሁን ገንዘቡን ያልመለሱ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እስከ ዛሬ ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም ድረስ ገንዘቡን እንዲመልሱ ዩኒቨርሲቲው ለመጨረሻ ጊዜ አሳስቧል፡፡

የወሰዱትን ገንዘብ ተመላሽ ያላደረጉ 55 ተማሪዎችን ሙሉ ስም፣ የተማሪ መለያ ቁጥር እና የትምህርት ክፍል ይፋ ያደረገው ዩኒቨርሲቲው፤ ለመጨረሻ ጊዜ በተሰጣቸው ዕድል ገንዘቡን በማይመልሱ ተማሪዎች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው በጥብቅ አሳስቧል፡፡

@tikvahuniversity
Tikvah-University pinned Deleted message
#Update

የመውጫ ፈተና መቼ ይሰጣል?

ትምህርት ሚኒስቴር ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ፤ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎችን መረጃ በማሰባሰብ በትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በኩል አረጋግጠው ባሳለፍነው ሳምንት ለትምህርት ሚኒስቴር መላካቸውን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
2024/09/30 13:19:30
Back to Top
HTML Embed Code: