Telegram Web Link
የመውጫ ፈተና መቼ ይሰጣል?

የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መረጃ ማሰባሰብ ሥራ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተከናወነ ይገኛል።

ተቋማቱ ለፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎች የተሟላ መረጃ እስከ ሚያዚያ 5/2016 ዓ.ም ድረስ በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል ተረጋግጦ እንዲላክ ትምህርት ሚኒስቴር ማሳሰቡ ተሰምቷል።

የመውጫ ፈተናው በሰኔ ወር አጋማሽ እንደሚሰጥ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahuniversity
#BahirDarUniversity

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) ወደ ሌላ የመንግሥት ኃላፊነት መመደባቸው ተሰምቷል።

በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዛሬው ዕለት ተፈርሞ የወጣ የውክልና ደብዳቤ፤ ፕ/ር እሰይ ከበደ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተወከሉ መሆናቸውን ያሳያል።

"በቀጣይ ውድድር ተደርጎ በቋሚነት ፕሬዝዳንት እስኪመደብ ድረስ ካለዎት የሥራ ኃላፊነት በተጨማሪ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ስራን እንዲሰሩ ውክልና የተሰጠዎት መሆኑን" እገልፃለሁ ይላል በሚኒስትሩ የተፃፈው የውክልና ደብዳቤው።

ፕ/ር እሰይ ከበደ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙ ሲሆን ባለፈው በኅዳር 2016 ዓ.ም ነበር በባዮ-ስታትስቲክስ መስክ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በዩኒቨርሲቲው የተሰጣቸው።

ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል።

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Tikvah-University pinned Deleted message
#MoE

የአገር ውስጥ የምርምር ጆርናል አርታኢዎች እና አሳታሚዎች ለ Plagiarism ችግር ልዩ ትኩረት በመስጠትና ቅድመ ፍተሻ በማድረግ የምርምር ጆርናል ጥራትን እንዲያስጠብቁ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ።

በርካታ በአገር ውስጥ የሚታተሙ የምርምር ጆርናሎች ፅሁፎች (Manuscripts) የPlagiarism መጠናቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ከሚሰጠው ነጥብ በላይ መሆኑን በዚህ ዓመት ባደረገው የፍተሻ ሥራ ማረጋገጡን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በመሆኑም ከመጋቢት 30/2016 ዓ.ም. ጀምሮ የPlagiarism መጠኑ ከ 30% በላይ የሆነ የምርምር ጆርናል ለፍተሻ ብቁ የማይሆንና ዕውቅና የማይሰጠው መሆኑ ተገልጿል።

ለዚህም ሚኒስቴሩ የተሻሻለ መመሪያ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መላኩ ታውቋል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
Photo
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል።

የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸው ሥራ መጀመራቸውም ታውቋል፡፡

ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በእንስሳት እርባታ እና አመጋገብ ከ Humboldt-Universität zu Berlin አጊኝተዋል፡፡

@tikvahuniversity
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከ STEMpower ጋር በመተባበር በሰሜኑ ጦርነት ውድመት የደረሰበትን ዩኒቨርሲቲውን ስቴም ማዕከል በድጋሜ በማቋቋም ሥራ ለማስጀመር እየሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡

ማዕከሉ የ STEM ትምህርት እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስልጠና ይሰጥ የነበረ ሲሆን በተጨማሪ የቤተ-ሙከራ ማዕከል እንዲኖረው ለማድረግ ይሠራል ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 778 ተማሪዎች ነገ ሚያዝያ 5/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

ከተመራቂዎቹ 26ቱ በሦስተኛ ዲግሪ እንዲሁም 350 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁቀ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 402 ተማሪዎች ደግሞ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች ናቸው፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል ብሔራዊ የመውጫ ፈተና ወስደው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ 379 የዩኒቨርስቲው ጤና ኢንስቲትዩት የህክምና ተማሪዎች እንደሚገኙበት ታውቋል።

@tikvahuniversity
2.5 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሕንጻዎች እና መሠረተ ልማቶች ግንባታ እያካሔደ መሆኑን ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ገለፀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በበጀት ዓመቱ 25 የተለያዩ ሕንፃዎች እና መሠረተ ልማቶች በማስገንባት ላይ ይገኛል።

ግንባታዎቹ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና የተማሪ ቅበላ አቅምን ለመጨመር የሚረዱ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ግንባታ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ተስፋሁን ገብሩ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

የአስተዳደር እና የተማሪዎች አገልግሎት ሕንጻዎች፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ የተማሪዎች ዶርሚተሪዎች፣ ቤተ-ሙከራዎች፣ አይ.ሲ.ቲ. ታወሮች እና ሌሎች መሠረተ ልማቶች በግንባታው መካተታቸውን ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
#የሥራ_ቅጥር_ጥቆማ

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በስምንት የጤና ሙያ መስክ የሥራ መደቦች ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 48
➤ የትምህርት ደረጃ፦ ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ
➤ የሥራ ልምድ፦ ዜሮ ዓመት
➤ የሥራ ቦታ፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
➤ የማመልከቻ ጊዜ፦ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት
➤ የምዝገባ ቦታ፦ አዲስ አበባ ቦሌ ርዋንዳ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው የዲላ የኒቨርሲቲ ጉዳይ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ወይም ዲላ ዩኒቨርሲቲ በኦዳያአ ግቢ የሰው ኃብት አስተዳደር ቢሮ ቁ. G1/012

Note:
በድረ-ገጽ የተመዘገባችሁ አመልካቾች ለፈተና ስትጠሩ የትምህርት ማስረጃችሁንና ተያያዥ ስነዶችን ዋናውና የማይመለስ ኮፒ ይዛችህ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

የትምህርት ማስረጃችሁ ከአገር ውስጥ ትምህርት ተቋማት ከሆነ ዋናውና ኮፒ እንዲሁም በውጭ አገራት ትምህርታችሁን የተከታተላቹ የአቻ ግመታ ሰነድ ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦ 0926208813

@tikvahuniversity
#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃ መርሐግብር ያሰለጠናቸውን 54 ተማሪዎች ነገ ሚያዝያ 5/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

ተማሪዎቹ ነገ በተቋሙ ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ በሚካሔድ የምረቃ ስነ-ስርዓት እንዲመረቁ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

በዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስና ህክምና ኮሌጅ በቅድመ ምረቃ መርሐግብር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁና የመውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች እንደሚመረቁ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University pinned Deleted message
#MizanTepiUniversity

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አመራር ተመድቦለታል።

ዋቆ ገዳ (ዶ/ር) የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበዋል።

ተረፈ ጌታቸው (ዶ/ር) ተጠባባቂ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት፣ ግርማ ጥላሁን (ዶ/ር) ተጠባባቂ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት እንዲሁም ይደግ ማሞ ተጠባባቂ የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ እና የቢዝነስ ልማት ም/ፕሬዝዳንት ሆነው መመደባቸው ተገልጿል።

አዲስ የተመደቡት አመራሮች ለአንድ ዓመት ተቋሙን እየመሩ እንደሚቆዩና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ምልመላ መመሪያ መሠረት ወደፊት በሚወጣ የውድድር ማስታወቂያ የቋሚ አመራሮች ምርጫ ይደረጋል ተብሏል።

@tikvahuniversity
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 778 ተማሪዎች አስመረቀ።

ከተመራቂዎቹ 26 በሦስተኛ ዲግሪ፣ 350 በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም 402 በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

በህክምና፣ በጥርስ ህክምና፣ በነርሲንግ፣ በሚድዋይፈሪ እና በፊዚዮቴራፒ የትምህርት መስኮች የሰለጠኑ የህክምና ተማሪዎች ከተመራቂዎቹ መካከል ይገኙበታል።

@tikvahuniversity
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ በመደበኛ መርሐግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም በህብረተሰብ ጤና የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 54 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ያጠናቀቁና የመውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያመጡ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
2024/09/30 11:41:47
Back to Top
HTML Embed Code: