Telegram Web Link
ታዳጊዎቹ የድረ-ገፅ አበልፃጊዎች

ጎዶሊያስ ሙሉጌታ እና ሰላዲን መራዊ በአቤም ዩዝ አካዳሚ የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ናቸው።

ታዳጊዎቹ የግለሰብ መረጃን ወይም 'CV' የሚያደራጅ ድረ-ገፅ አበልፅገዋል።

ድረ-ገፁ፤ ሰዎች ሥራን ለመቀጠር የሚያስገቡት የራስ መግለጫ 'CV'' በእጅ ስልካቸው ላይ እንዲያገኙና በማንኛውም ሰዓት ለሚፈልጉት ቀጣሪ ማስገባት የሚያስችል ነው።

ድረ-ገፁ የግለሰቡን የትምህርት ደረጃ፣ አድራሻ፣ ክህሎቶች እና የሰዎችን ምስክርነትን ማካተት የሚያስችል መሆኑን ታዳጊዎቹ ተናግረዋል።

ድረ-ገፁ የሰዎችን ብቻ ሳይሆን የድርጅቶችን መረጃ እንዲያስቀምጥ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑንም ታዳጊዎቹ አስረድተዋል።

ታዳጊዎቹ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም በተከፈተው የ'ስታርት አፕ' አውደ-ርዕይ ላይ ፈጠራቸውን አቅርበዋል። #ENA

@tikvahuniversity
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሶሻል ወርክ ትምህርትን በሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም መስጠት ሊጀምር ነው።

የዩኒቨርሲቲው ሶሻል ወርክ ትምህርት ክፍል ፕሮግራሙን ለመክፈት በሀገር አቀፍ ደረጃ የፍላጎት የዳሰሳ ጥናት ማካሔዱ ተገልጿል።

ፕሮግራሙን ለማስጀመር አዲስ ስርዓተ ትምህርት በማዘጋጀት በባለሙያዎች ሲያስገምግም ቆይቷል።

በዚህም የተሰጡትን ማስተካከያዎች በማካተት የማረጋገጫ አውደ ጥናት አካሒዷል፡፡

@tilvahuniversity
#MoE

በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተፈታኝ ተማሪዎች እያንዳንዳቸው የአገልግሎት ክፍያ 500.00 (አምስት መቶ) ብር ብቻ የሚከፍሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

በዚህም #ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች የሚከፍሉትን ብር ሰብስበው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000553176097 በመጠቀም እስከ ማክሰኞ ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም ድረስ ለትምህርት ሚኒስቴር ገቢ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

ተፈታኞች የከፈሉበትን ደረሰኝ ኮፒ በኢሜይል አድራሻ [email protected] እና [email protected] መላክ ይኖርባቸዋል።

(ተጨማሪ መረጃ ከተያያዘው ደብዳቤ ይመልከቱ።)

@tikvahuniversity
ትምህርት ሚኒስቴር ለ 50,000 መምህራን እና የትምህርት አመራሮች የብቃት ስልጠና ሊሰጥ ነው፡፡

በመጪዎቹ ሐምሌ እና ነሐሴ ወራት የሚሰጠው ስልጠናው፤ የቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን አቅም ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

42,000 መምህራን ለ120 ሰዓት እንዲሁም 8,000 የትምህርት አመራሮች ለ60 ሰዓት ስልጠና እንደሚሰጣቸው በሚኒስቴሩ የመምህራንና የትምህርት አመራር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ለኤፍቢሲ ተናግረዋል።

መምህራኑ በሚያስተምሩበት ትምህርት ውጤታማነታቸውን የሚጨምር የማስተማር ስነ-ዘዴ (ፔዳጎጂ) ስልጠና የሚሰጣቸው ሲሆን፤ ስልጠናቸውን ሲያጠናቅቁ ፈተና እንደሚወስዱ መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገልፀዋል፡፡

ስልጠናው በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡

@tikvahuniversity
የራያ ዩኒቨርሲቲ አሰራርን የሚያዘምኑ ሦስት መተግበሪያዎችን የተቋሙ መምህራን እና ባለሙያዎች አበልፅገው ሥራ አስጀመሩ፡፡

የበለፀጉት መተግበሪያዎች የንብረት አስተዳደር መረጃ ስርዓት፣ የፈተና አስተዳደር ስርዓት ፖርታል እና የራያ ዩኒቨርሲቲ ድረ-ገፅ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

መተግበሪያዎቹ ብክነት ለመቀነስ፣ ደህንነት ለማስጠበቅ፣ እንዲሁም ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ያግዛሉ ተብሏል፡፡

የፈተና አስተዳደር ስርዓት ፖርታሉን በመጠቀም ባሳለፍነው ጥር ለዩኒቨርሲቲው የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች ውጤታማ የሞዴል ፈተና ተሰጥቶ እንደነበር ተነስቷል።

@tikvahuniversity
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የተቋሙ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች በሰኔ 2016 ዓ.ም ወይም በጥር 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመውሰድ በግለሰብ ደረጃ እንዲወስኑና በውሳኔያቸው መሰረት ለፈተው እንዲቀመጡ ዩኒቨርሲቲው ዕድል እንዲፈጥር
ወስኗል፡፡

በዚህም በሰኔ ወር የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ፍላጎቱ ያላቸው ተመራቂ ተማሪዎች ስም ዝርዝር በአስቸኳይ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር መላክ ሰላለበት ተፈታኞች እስከ ሚያዝያ 17/2016 ዓ.ም መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

በተጠቀሰው ግዜ ውስጥ ስማቸውን ያላስመዘገቡ ተመራቂ ተማሪዎች በጥር 2017 ዓ.ም ፈተናውን ለመውሰድ እንዳቀዱ ተደርጎ እንደሚወሰድ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

በአዲስ አበባ ትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ፍቃዱ የታገደበት የጊብስን አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መውሰድ እንዲችሉ ምዝገባ እንዲያደርጉ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ጥሪ አድርጓል፡፡

በዚህም የትምህርት ቤቱ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ ዛሬ ሚያዝያ 15/2016 ዓ.ም በጊብሰን የጉለሌ ብራንች መድኃኔዓለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና በጊብሰን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ብራንች ብስራተ ገብርኤል ኢስት ዌስት አዳራሽ የሚካሔድ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጠቀሱት ቦታዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች ተማሪዎችን በመያዝ ምዝገባ በዛሬው ዕለት እንዲያካሒዱ ቢሮው አሳስቧል፡፡

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ጥቆማ

ጤና ሚኒስቴር የሚያስተዳድራቸውን አዲስ የህክምና ትምህርት ኢንሼቲቭ (NMEI) ትምህርት ቤቶች መቀላቀል የምትፈልጉ ዕጩዎች ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

ሚኒስቴሩ በNMEΙ ስርዓተ ትምህርት የቅበላ ፖሊሲ መሰረት፣ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ አዲሱን የህክምና ትምህርት ኢንሼቲቭ (NMEI) ለመቀላቀል ፍላጎት ያላቸውን ዕጩዎች እንዲመለምል፣ የመግቢያ ፈተና እንዲሰጥ እና ውጤት እንዲያሳውቅ ውክልና ሰጥቶታል። ውጤት ከተገለፀ በኋላ ቀሪ ጉዳዮች በሚኒስቴሩ የሚከናወን ይሆናል፡፡

ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፦

➤ የመጀመሪያ ዲግሪ በጤና ሳይንስ እንዲሁም በባዮሎጂ እና በኬሚስትሪ

➤ CGPA ለሴቶች 2.75 እና ለወንዶች 3.0 ፤ ለአዳጊ ክልሎች ለሴቶች 2.5 እና ለወንዶች 2.75

➤ ከምርቃት በኋላ ቢያንስ ሁለት ዓመት የሥራ ልምድ

➤ ዕድሚያችሁ ከ35 ያልበለጠ

➤ የፖንሰርሺፕ ደብዳቤ ከምትሰሩበት የመንግሥት ተቋም ማምጣት የምትችሉ

➤ ራሳችሁን ስፖንሰር ማድረግ የምትችሉ ማመልከት ትችላላችሁ

የፅሁፍ ፈተና 60% የሚይዝ ሲሆን ከፍተኛ ውጤት የሚያመጡ 260 አመልካቾች 30% ለሚይዘው ቃለመጠይቅ ይመረጣሉ፡፡

ተከታዩን ሊንክ በመጫን ያመልክቱ፦
https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement/List?studyLevel=Undergraduate&instructionId=dc716240-4408-46d0-8da6-4ea0bf659bae

Note:

➧ ማመልከት የሚቻለው በኦንላይን ብቻ ነው፡፡
➧ የምዝገባ ጊዜ፦ ከሚያዝያ 10-22/2016 ዓ.ም
➧ የፅሁፍ ፈተና፦ ግንቦት 4/2016 ዓ.ም
➧ ቃለመጠይቅ፦ ግንቦት 11/2016 ዓ.ም
➧ ውጤት የሚገለፀው፦ ግንቦት 14/2016 ዓ.ም

@tikvahuniversity
እስካሁን ጥሪ ያልተደረገላቸው የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ተማሪዎች

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል።

ተማሪዎቹ ከታህሳስ ወር ጀምሮ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የአቅም ማሻሻያ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡

ይሁን እንጂ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የተመደቡ ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ አልተደረገላቸውም።

ዩኒቨርሲቲው በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ የጀማሪ መርሐግብር እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ለተከታተሉ ተማሪዎች መጋቢት 14/2016 ዓ.ም ጥሪ ሲያደርግ፤ በ2016 ዓ.ም ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ አዲስ የሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ ሳያደርግ ቀርቷል።

እነዚህ ተማሪዎች በቀጣይ ጥሪ ይደረግልናል በሚል በተስፋ ሲጠብቁ ቆይተዋል። ይሁን እንጂ ከአንድ ወር በኋላም ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አላደረገላቸውም።

"የትምህርት ጊዚያቸው እየባከነባቸው እንደሆነ"ና "አስቸጋሪ ጊዜያትን እያሳለፉ እንደሚገኙ" ለቲክቫህ አስተያየታቸውን የሰጡ ተማሪዎች፤ መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ጠይቀዋል።

የሪሚዲያል ፈተናው ይሰጣል ተብሎ በመንግሥት የተቀመጠው ጊዜ 45 ቀናት የቀሩት መሆኑ ሌላው ተማሪዎቹን እያሳሰበ ያለ ጉዳይ ነው።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎቹ መቼ ጥሪ እንደሚደረግ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችን በስልክ እና በአጭር መልዕክቶች የጠየቀ ቢሆንም ምንም አይነት ምላሽ ማግኘት አልቻለም።

ተማሪዎቹ ወደሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተዘዋውረው የሚማሩበት ዕድል ካለ፣ አማራጭ የፈተና ጊዜ የሚዘጋጅላቸው ከሆነ እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ወይም/እና ትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጡትን ምላሽ ወደናንተ እናደርሳለን።

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎቻቸው የሞዴል ፈተና እየሰጡ ነው፡፡

ሞዴል ፈተናው ከትላንት ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት እንደሚሰጥ የተገለፀ ሲሆን፤ ተማሪዎቹን በቀጣይ በሰኔ ወር ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ ፈተና ማዘጋጀት የሞዴል ፈተናው ግብ መሆኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#MoE

በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተፈታኝ ተማሪዎች እያንዳንዳቸው የአገልግሎት ክፍያ 500.00 (አምስት መቶ) ብር ብቻ እንደሚከፍሉ ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

የዚህን ደብዳቤ ትክክለኛነትና ከደብዳቤው ጋር በተያያዘ ያላቸውን ጥርጣሬ በርካታ ተፈታኝ ተማሪዎች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አድርሰዋል፡፡

ደብዳቤው ትክክለኛ መሆኑን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል፡፡ የተገለፁትም የኢሜይል አድራሻዎች ህጋዊ የተቋሙ አድራሻዎች እንደሆኑ ለማወቅ ችለናል፡፡

Note:

#ዩኒቨርሲቲዎች ተፈታኝ ተማሪዎች የከፈሉትን ብር ሰብስበው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000553176097 ለትምህርት ሚኒስቴር ገቢ ማድረግ እንዳለባቸው ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

በተመሳሳይ ተቋማቱ ተፈታኞች የከፈሉበትን ደረሰኝ ኮፒ በኢሜይል አድራሻ [email protected] እና [email protected] መላክ ይኖርባቸዋል።

@tikvahuniversity
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሁለት ካምፓሶች በፀጥታ ችግር ተዘግተው ተማሪዎች እንዲሸጋሸጉ መደረጋቸው ተሰማ፡፡

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሥር የሚገኙት ዘንዘልማ እና ሰባታሚት ካምፓሶች በፀጥታ ችግር ምክንያት መዘጋታቸውን ሪፖርተር ዩኒቨርሲቲውን በመጥቀስ ዘግቧል።

በሁለቱ ካምፓሶች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ የግብርና፣ የጤና፣ የጂኦሎጂ እና የዲዛስተር ማኔጅመንት ተማሪዎች የፀጥታው ችግር እስኪቀረፍ ከተማ ውስጥ ባሉ ካምፓሶች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ማድረጉን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ብርሃኑ ገድፍ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በዘንዘልማ እና በሰባታሚት ካምፓሶች ውስጥ ይማሩ የነበሩ በርካታ ተማሪዎች ከተማ ውስጥ ያሉ ካምፓሶች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው፡፡

ዘንዘልማ እና ሰባታሚት ካምፓሶች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የተኩስ ድምፅ በየጊዜው እንደሚሰማ የገለፁት ም/ፕሬዝዳንቱ፤ በተማሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከአንድ ወር በፊት ወደተለያዩ የተቋሙ ካምፓሶች እንዲዘዋወሩ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

በከተማዋ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች ውስጥ በቂ ቦታ በመኖሩ ተማሪዎቹ ምንም ዓይነት መጉላላት ሳይደርስባቸው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ከሁለቱ ካምፓሶች ውጪ በሌሎች ካምፓሶች ላይ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንደሌለ ም/ፕሬዝዳንቱ ገልጸው፤ በባህር ዳር ከተማ ካለው አንፃራዊ ሰላም አኳያ በርካታ ተማሪዎች ምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡

ከሁለቱ ካምፓሶች ውጪ አለመረጋጋቱ የተሻሻለ ቢሆንም፤ አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰሙ ተማሪዎቹ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ የዘንድሮ ተመራቂዎች የምረቃ ቀን መቼ እንደሆነ እስካሁን እንዳልተነገራቸውም አክለዋል፡፡ #ሪፖርተር

@tikvahuniversity
ገቢራዊ እየሆነ የሚገኘው አዲሱ የትምህርት ፖሊሲ የምልክት ቋንቋን አለማካተቱ በክፍተትነት ሊታይ እንደሚገባ ተገለፀ።

መንግሥት አዲስ የትምህርት ፖሊሲ በማዘጋጀት ሥራ ላይ ማዋሏ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ፖሊሲው የምልክት ቋንቋን ሳያካትት ቀርቷል።

ይህም በሰነዱ አካታችነትን ላይ ጥያቄ የሚያስነሳ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ትምህርት፣ ቋንቋና መስማት የተሳናቸው ባህል ጥናት ክፍል ኃላፊ ጳውሎስ ካሱ (ዶ/ር) ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በምልክት ቋንቋ ከቅድመ መደበኛ እስከ መሰናዶ ደረጃ የመምህራን መመሪያና የተማሪዎች መማሪያ መፃሕፍት ቢዘጋጁም፤ በስርዓተ ትምህርቱ የምልክት ቋንቋን አለመካተቱ በትምህርት ስርዓቱ ላይ የሚፈጥረው ክፈተት ከፍ ያለ ነው ብለዋል፡፡

የዘርፉ ባለሙያዎች የምልክት ቋንቋ በኢትዮጵያ ተጨማሪ የሥራ ቋንቋ ሆኖ ዕውቅና እንዲያገኝ ጥያቄ እያቀርቡ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ #መናኸሪያ_ሬዲዮ

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና ፈተና (IELTS Test) በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይውሰዱ፡፡

የብሪቲሽ ካውንስል IELTS የፈተና ማዕከል የIELTS ፈተና ግንቦት 17/2016 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይሰጣል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ የአመልካቾች ምዝገባ በመከናወን ላይ ይገኛል።

ሁለት አይነት የ IELTS ፈተናዎች (IELTS Academic and IELTS General Training) መውሰድ ለሚፈልጉ አመልካቾች እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡

የብሪቲሽ ካውንስል ድረ-ገፅ ላይ በመግባት ኦንላይን መመዝገብ ይችላሉ 👇
https://ethiopia.britishcouncil.org/exam/ielts/dates-fees-locations

ለፈተናው ዝግጅት የሚያስፈልግዎትን ስልጠና እና ምክር ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማግኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ፦ 0925629589

@tikvahuniversity
2024/09/30 11:34:03
Back to Top
HTML Embed Code: