Telegram Web Link
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው ጆርናል ማሳተም ጀምሯል፡፡

የመጀመሪያ ሀገር አቀፍ ዓመታዊ የትምህርት ምዘና ጉባኤውን ያደረገው አገልግሎቱ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተና ጆርናል (Journal of Educational Assessment and Examinations) የመጀመሪያ ዕትምን አስመርቋል።

ምዘናና ፈተናን በምርምር ማሳደግና የምርምር ግኝቶችን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ማድረግ የጆርናሉ ተልዕኮዎች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

ጆርናሉ በዘርፉ ምሁራን የሚመራ፣ ገለልተኛ የሆነና ለተመራማሪዎች እና የትምህርት ማኅበረሰብ አባላት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚኖረው ነው ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
ወጣቶች እንዲሁም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የፋይናንስ ማስተማሪያ ሞጁል በብሔራዊ ባንክ ይፋ ሆኗል፡፡

ባለፈው ሳምንት ይፋ የሆነው ሞጁሉ፤ ፍላጎት ላላቸው ሰልጣኞች የግልና ሙያዊ ክህሎት ስልጠና በባንኮች እና አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ባለሙያዎች ለመስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ሞጁሉ የፋይናንስ ትምህርት ጥረቶችን ማዕከላዊ ለማድረግ እና ወጣቶችን እንዲሁም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በመረጃ ላይ የተመሰረቱ የገንዘብ ውሳኔዎችን እንዲወስኑ አስፈላጊው ዕውቀትና ችሎታ እንዲኖራቸዉ ለማድረግ የሚያስችል ነው።

First Consult እና BRIDGE ከተባሉ ተቋማት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የስልጠናው ሞጁል፤ ብድር፣ ኢንሹራንስ እና ዲጂታል የገንዘብ አገልግሎትን ጨምሮ የተለያዩ የፋይናንስ ትምህርቶች ማካተቱ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 283 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በማታ እና በዕረፍት ቀናት መርሐግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity
ይመዝገቡ!

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ የፊታችን ቅዳሜ ይጠናቀቃል።

የተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ ነገ ቅዳሜ የካቲት 30/2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

በ2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ870 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሚፈተኑ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነገ የካቲት 30/2016 ዓ.ም ያስመርቃል።

የዩኒቨርሲቲው 15ኛ ዙር ተመራቂዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ እንደሚከናወን ተገልጿል።

ባለፈው ወር የተሰጠውን የመውጫ ፈተና የወሰዱ የተቋሙ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ተማሪዎች ከፋርማሲ ተማሪዎች በስተቀር (97 %) ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ዩኒቨርሲቲው መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ2016 ዓ.ም በ Maxillofacial Surgery ስፔሻሊቲ መርሐግብር አመልካቾችን አወዳድሮ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

ተከታዮቹን መስፈርቶች የምታሟሉ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

- ከታወቀ የመንግሥት ተቋም የ Dental Medicine (DDS or DDM) ያለው/ያላት
- ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያለው/ያላት
- በጥሩ የጤና ሁኔታ የሚገኝ/የምትገኝ
- እድሜ ከ40 ዓመት በታች
- ስፖንሰርሺፕ ማምጣት የሚችል/የምትችል

የምዝገባ ቀናት፦ ከየካቲት 27 እስከ መጋቢት 17/2016 ዓ.ም.

የፈተና ቀናት፦ መጋቢት 23 እና 24 /2016 ዓ.ም.

ለበለጠ መረጃ፦ 0911563284

@tikvahuniversity
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#SPHMMC

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ አዲስ የተመረጡ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ መጋቢት 4 እና 5/2016 ዓ.ም. መሆኑን አሳውቋል፡፡

በቅጣት ለመመዝገብ፦ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም.

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

• ዲግሪ/ቴምፖራሪ/ማጠናቀቅን የሚገልፅ ደብዳቤ ዋናውና ኮፒው፣
• ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
• የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ፣
• ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
• የምዝገባ ክፍያ 100 ብር በኮሌጁ የኢ/ን/ባ አካውንት በኩል መክፈል፡፡

@tikvahuniversity
#MizanTepiUniversity

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ እና ድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 361 ተማሪዎች አስመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው ሕክምናን ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎችም አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸውን በተቋሙ ሲከታተሉ የቆዩ የደቡብ ሱዳን ተማሪዎችንም አስመርቋል።

@tikvahuniversity
#AmboUniversity

አምቦ ዩኒቨርሲቲ በጤና ሳይንስ እንዲሁም በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 714 ተማሪዎች አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 322 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ሲሆኑ ቀሪዎቹ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎቹ በሙሉ ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ መሆናቸውን የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ባይሳ ለታ (ዶ/ር) በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለየዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 809 ተማሪዎች አስመረቀ።

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ ዲግሪ (483)፣ በሁለተኛ ዲግሪ (331)፣ በስፔሻሊቲ (10) እና በፒ.ኤቺ.ዲ. (5) መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahuniversity
ተማሪ ዳዊት ኮርጋሌ - የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የዓመቱ የዋንጫ ተሸላሚ

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 809 ተማሪዎች ትላንት ማስመረቁ ይታወቃል።

ተማሪ ዳዊት ኮርጋሌ ከጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ፋርማሲ ትምህርት ቤት እጅግ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የዓመቱ ተሸላሚ ሆኗል።

CGPA 3.98 ውጤት በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ የሜዳልያ ተሸላሚ ሆኗል።

@tikvahuniversity
የቦረና ዩኒቨርሲቲ ሞያሌ ካምፓስ ግንባታ ለማስጀመር የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

የሚገነባው ካምፓስ የዩኒቨርሲቲውን የማስተማር እና የምርምር አገልግሎት ለማስፉፋት እንደሚያስችል የተቋሙ ፕሬዝዳንት ቦኩ ጠቼ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ቦረና ዩኒቨርሲቲ በሰኔ 2013 ዓ.ም. ተመርቆ ሥራ የጀመረ የመጨረሻው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ መሆኑ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
#AddisAbabaUniversity

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ጠዋት 2:30 አካባቢ በተቋሙ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ካምፓስ ወንዶች ዶርሚተሪ የእሳት አደጋ ተነስቶ እንደነበር ገልጿል።

የእሳት አደጋው በሰው እና በንብረት ላይ "የከፋ ጉዳት ሳያደርስ" በቁጥጥር ስር መዋሉን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

አደጋው ሲቀሰቀስ ከህንጻው ያልወጡ አራት ተማሪዎች የነበሩ ሲሆን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተማሪዎቹ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው እንዲወጡ ማድረጋቸው ተሰምቷል፡፡

የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር አራት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች እና ሁለት አምቡላንስ ከ32 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር ተሰማርተው እንደነበር የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ሰጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል፡፡

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ እሳቱን በፍጥነት መቆጣጠር መቻሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ኤፍ.ኤም. ተናግረዋል፡፡

በሰው ላይ ምንም ጉዳት አለማድረሱን የገለፁት ባለሙያው፤ የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን ጠቁመዋል።

@tikvahuniversity
2024/10/01 07:28:44
Back to Top
HTML Embed Code: