Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዕለታዊ

ዛሬ ንግድ ባንክ የዶላር መግዣ ላይ ጭማሪ በማድረግ ወደ 108 ብር ከ0728 ሳንቲም አስገብቷል።

መሸጫው 119 ብር ከ9608 ሳንቲም ነው።

በአቢሲኒያ ባንክ አንዱ ዶላር 108 ብር ከ0729 ሳንቲም መግዣ ፤ 121 ብር ከ0416 ሳንቲም መሸጫ ተቆርጦላታል።

በወጋገን ባንክ የዶላር መግዣው 115 ብር ከ0121 ሳንቲም ነው።

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ደግሞ አንዱን የአሜሪካ ዶላር በ107 ብር ከ8383 ሳንቲም እየገዛ በ120 ብር ከ7789 ሳንቲም ለመሸጥ ቆርጧል።

(የዛሬ ጳጉሜን 2 ቀን 2016 ዓ/ም የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ከላይ ይመልከቱ)

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ምን አሉ ? የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩትና ም/ፕሬዜዳንት ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ የሚገኙበት የአመራሮች ቡድን ከሰሞኑን ህዝባዊ ውይይቶችን እያደረገ ነው። ትላንት ማይጨው ላይ በነበረ ውይይት ጀነራል ፃድቃን ስለ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ዙሪያ ሃሳቦች ሰጥተዋል። " የሚታየውን ዋናው የልዩነት ነጥብ በፕሪቶሪያ ውል ላይ ያለ የአመለካለት…
#Tigray

አቶ ጌታቸው ረዳ የጤና አክል ገጥሟቸዋል።

ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ዛሬ ጳጉሜን 2/2016 ዓ.ም የወጣ መግለጫ እንዳመለከተው ፥ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ዛሬ በአክሱም ሊካሄድ የታቀደው ህዝባዊ ውይይት ተሰርዟል።

ፅ/ቤቱ ፕሬዜዳንቱ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ከአክሱም ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ሊካሄድ እቅድ የተያዘለት ህዝባዊ ውይይት ሳይካሄድ በመቅረቱ ይቅርታ ጠይቋል።

ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ያጋጠማቸው የጤና እክል ቀላል ይሁን ከባድ በመግለጫው የተጠቀሰ የለም ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

ከሰሞኑን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ምክትላቸው ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ያሉበት የአመራሮች ቡድን በየከተማው ህዝባዊ ምክክር እያደረገ እንደነበር ይታወቃል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray አቶ ጌታቸው ረዳ የጤና አክል ገጥሟቸዋል። ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ዛሬ ጳጉሜን 2/2016 ዓ.ም የወጣ መግለጫ እንዳመለከተው ፥ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ዛሬ በአክሱም ሊካሄድ የታቀደው ህዝባዊ ውይይት ተሰርዟል። ፅ/ቤቱ ፕሬዜዳንቱ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ከአክሱም ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ሊካሄድ እቅድ የተያዘለት…
#UPDATE

" የጤናዬ ሁኔታ ብዙ የሚያሳስብ አይደለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ 

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ጳጉሜን 2/2016 ዓ.ም በ X ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሑፍ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት በማስቀደም " የጤንነት ሁኔታየና ድህንነቴ ያሳሰባችሁና ያስጨነቃችሁ ሁላችሁም ደህና ነኝ " ብለዋል። 

" ተደጋጋሚ ረጅም መንገድ በመኪና መጓዝና ደካም ተደራርቦ የፈጠረው ጊዚያዊ ችግር እንጂ በሚያሳስብ ሁኔታ እንዳልሆንኩ በፈጣሪና በፅዮን ማርያም ስም እገልፅላችኃለሁ " ሲሉ ፅፈዋል።   

ቀጣይ ህዝባዊ መድረኮች ከተወሰኑ ቀናት በኋላ እንደሚቀጥሉ የገለፁት አቶ ጌታቸው " በመድረኩ ለመሳተፍ አክሱም ድረስ ለተንገላቱ ተሳታፊዎች ደግሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ " በማለት አክለዋል።   

ዛሬ ጳጉሜን 2/2016 ዓ.ም ከጊዚያዊ  አስተዳደሩ የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት የወጣ መግለጫ ፕሬዜዳንቱ የጤና እከለ እንደገጠማቸው በመግለፅ በአክሱም ከተማ ሊካሄድ እቅድ የተያዘለት ህዝባዊ ውይይት ለሌላ ጊዜ መተላለፉና ይቅርታ መጠየቁን መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
Calling all aspiring entrepreneurs

The Jasiri Talent Investor Program is your opportunity to kickstart your journey! Join a community of visionary leaders and become a changemaker.

Apply now and make a difference
👉🏾 https://bit.ly/3A8rxtV

For more information, Join our telegram channel 👉🏾 @Jasiri4africa
#MPESASafaricom

ከቤተሰብ ጋር እንቁጣጣሽን በአንድ ቦታ በM-PESA:: የሀገር ዉስጥ በረራ ትኬታችንን
በM-PESA ስንቆርጥ የ5% ተመላሻችን ጉዟችንን አፍጥኖ ካሰብንበት ያደርሰናል ::

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!

የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
  #FurtherAheadTogether
#flyethiopian
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 “ ... ያለፉትን ዘመናት እኮ #እንደ_ቅንጦት እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው ” - ጎጎት ፓርቲ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ' #የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ ? ' በሚል በህጋዊ መንገድ ተመዝገበው ለሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች እያቀረበ ያለውን ወቅታዊ ሀገራዊ ጥያቄዎች በመቀጠል ጎጎት ፓርቲን አነጋግሯል። የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጀሚል ሳኒ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ…
🇪🇹 የፓለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

“ ሰው በጣም እየተሰቃዬ ነው ያለው መንግስት ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ” - ወህዴግ

የወላይታ የህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ወህዴግ) ፓርቲ አመራር አባል አቶ ተክሌ ቦረና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

Q. በተለይ የእርስዎ ፓርቲ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ ከደመወዝ አለመከፈልና መቆራረጥ ጋ በተያያዘ ሠራተኞች ተማረዋል። ችግሩ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ? ያላችሁ ግምገማስ ምንድን ነው ?

አቶ ተክሌ፦

“ የደመወዝ ቅሬታ ቅሬታ ሆኖ እስከሚቀርብ መጠበቅ የሌለበት አግባብነት የሌለው ጉዳይ ነው።

ምክንያቱም በዓመቱ መጀመሪያ የደመወዝ በጀት በሠራተኞች ልክ ተሰልቶ ይመደባል በመንግስት።

ግን አዲስ የሰው ኃይል ሳይጨመር በነበረው ሆኖም የተወሰነ ርቀት እንደተሄደ ‘ ደመወዝ የለም ’ የሚያሰኝ ነገር ምን እንደሆ አሳማኝ ነጥብ የለም።

ምናልባት ከደቡብ የክልል አከላለል ጋር ተያይዞ ሠራተኞች ከቦታ ቦታ ይዘዋወራሉና ደመወዝ ከፋዮቹ በዚያ ለማሳበብ ይሞክሩ ይሆናል። 

እሱም ቢሆን ሠራተኞች የሚያገኙትን ደመወዝ ይዘው ይሄዳሉ እንጂ አዲስ ስጡን ብለው አይጠይቁም።

በመሆኑም እንዲህ አይነት ችግር የሚያስከትሉ ሰዎች ምክንያታቸው አጥጋቢ አይደለም።

አንዳንዴ ‘ ከማዳበሪያ ዋጋ ጋር ተገናኝቶ ’ የሚባል ነገር አለ። በምንም ተዓምር የደመወዝ በጀት ቆርሶ ለሌላ ጥቅም ማዋል አይገባም በአገሪቱ ህግ መሠረት። 

ለምን እንደዚህ እንደሚደረግ አይገባንም። ”

Q. የደመወዝ መቆራረጥ ድሮውንም የናረውን የኑሮ ውድነት ለሠራተኞቹ ይበልጥ ፈታኝ እንዳደረገው ስሞታ ይቀርባል። የፓርቲዎ ግምገማና መልዕክት ምንድን ነው ?

አቶ ተክሌ፦

“ በህጉ መሠረት ሠራተኛው ሳይስማማ፣ ፈርሞ ሳያጸድቅ ከደመወዙ አንድ ሳንቲም አይነካም። ደመወዝ ከፋይ እኔ ነኝ እንደፈለኩ አደርጋለሁ የሚል ኃይል አይኖርም።

ያለ ፈቃድ የሚደረግ ነገር በሙሉ ህገወጥ፤ እንደ ወንጀል የሚቆጠር ነው። የሰውን ገንዘብ ቀምቶ እንደመውሰድ ነው።

ደመወዝ ባይቆረጥም የኑሮ ውድነቱ ከደመወዝ ጋር የሚመጣጠን ባለመሆኑ ሠራተኛው ሊቋቋመው አልቻለም። በየሰዓቱ የዋጋ ጭማሪ አለ።

ሰው በጣም ተቸግሮ ነው ያለው። በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ፍላጎቶች በማሟላት ብቻ እያብቃቃ ነው የሚኖረው። 

የዋጋ ንረትና የደመወዝ ሁኔታ በምንም ተዓምር ለጎን ለጎን የሚሄዱና ንግግር ውስጥ የሚገቡ ነገሮች አይደሉም። ሰው በጣም እየተሰቃዬ ነው ያለው መንግስት ኃላፊነቱን መወጣት አለበት። ”

Q. ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል አለመወሰን ለኑሮ ውድነቱ መባባስ እንደ መንስኤ ይነሳል። ፓርቲዎስ ያለው ምልከታ ምንድን ነው ?

አቶ ተክሌ ፦

“ ይሄ የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ነው። መንግስት በጣም በተለዬ ሁኔታ ትኩረት ሊሰጠው፣ ሊጸድቅ ይገባል።

ከዚህም ባሻገር መንግስት ምርት መጋዘን እያከማቹ በአንድ ወቅት በማውጣት ዋጋ የሚጨምሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰድ አለበት።

ችግሩ የ120 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ስለሆነ መንግስት በዬአካባቢው የራሱን ሱቅና መጋዘን ሊከፍት ይገባል። ያኔ ተመጣጣኝ ዋጋ ይኖራል። ”

Q. የተሟላ መሠረተ ልማት አለመኖር ፈታኝ እንደሆነባቸው ነዋሪዎች ሲገልጹ ይስተዋላል። የፓርቲዎ ግምገማ ምን ይመስላል ?

አቶ ተክሌ፦

“ መሠረተ ልማት ይጀመርና ይተዋል። እንደገና 5፣ 6 ዓመታት ከበሰበሰ በኋላ ብዙ ሲገለጽ ይሰማል።

እንዲህ አይነት ችግር በመንገድ፣ በህንፃ ግንባታ በብዙ ቦታዎች  ይስተዋላል።

የመሠረተ ልማት ግንባታ እየተስተጓጎለ ነው። በጀትም በትክክል ሥራ ላይ አይውልም። ስለዚህ ቆምና አሰብ አድርጎ ማስኬድ ያስፈልጋል። ”

Q. እንደ ፓርቲ የሚደርስባችሁ ጫና አለ? ካለ ምንድን ነው?

አቶ ተክሌ፦

“ ጫናው አለ። ለምን ኖረ? የሚለውን ስናይ በተለይ ታች ያሉት የመንግስት ካድሬዎች የሰለጠኑ አይደሉም። 

የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት መኖር ለዴሞክራሲ ስርዓት መዳበር ፋይዳ እንዳለው አያውቁም። ተፎካካሪ ፓርቲዎችን እንደ ጠላት እያዩ ችግር ይፈጥራሉ።

ችግር የሆነብን ይሄ ነው። ስለዚህ መንግስት ታች ወርዶ ከወረዳ እስከ ዞን መስራት አለበት።”

Q. ስለሙስና የፓርቲዎ ግምገማ ቢያጋሩ?

አቶ ተክሌ፦

“ የሙስና ጉዳይ በጣም እድሜ ያስቆጠረ ነው። 
በኢትዮጵያ በኮሚሽን ደረጃ ተቋም ተደራጅቶ ኃላፊነት ወስዶ በመስራት ላይ እንዳለ ነው የምንሰማው ነገር ግን ችግሩ አልተቀረፈም።

አሁንም ጠንካራና የተሻለ ሲስተም መዘርጋትና መቆጣጠሮ ያስፈልጋል። በሌላ በኩል የህዝቡ የኑሮ ውድነት ቢቀረፍ ሁሉም ስለሚዋጋ ችግሩ እየሟሸሸ ይሄዳል ” ብለዋል።

#የፓለቲካፓርቲዎችምንይላሉ? #ወህዴግ

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA🇪🇹

የሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች እና የህብረተሰብ ተወካዮች በአፍሪካ ቀንድ እየተስተዋሉ ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።

የሀገር ሽማግሌ ገራድ ኩልሚዬ ገራድ መሐመድ ምን አሉ ?

" ኢትዮጵያን የሚጎዳ ነገር ሁሉ የሶማሌ ክልል ህዝብ ጉዳት በመሆኑ ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመሆን የሀገርን ጥቅም ለማስከበር መሰራት አለበት።

የተለያዩ ሀይሎች ወደ ሶማሊያ መጥተው የአፍሪካ ቀንድን ለማበጣበጥ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴን እንቃወማለን።

ሀይሎቹ ለጎረቤት ሶማሊያ ህዝብ ጥቅም የሚያመጡ ሳይሆኑ ጦርነት በመክፈት ችግር የመፍጠር ዓላማ ያላቸው በመሆናቸው ህዝቡ ሊቃወማቸው ይገባል።

የሶማሌ ክልል ህዝብ እና የሶማሊያ ህዝብ ድንበር ቢለያቸውም ወንድማማቾች በመሆናቸው የአብሮነት ታሪካቸውን ሊጠብቁት ይገባል።

ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት መብቷን ለማረጋገጥ የምትሰራቸውን ስራዎች የሶማሌ ክልል ህዝብ ይደግፋል።

የባህር በር ጥያቄ አብረን የምናድግበት እንጂ የሚያራርቀን አጀንዳ እንዳልሆነ ለጎረቤቶቻችን ሶማሊያውያን ማሳወቅ እንወዳለን " ብለዋል።


የሀገር ሽማግሌ ኡጋዝ አሊ ምን አሉ ?

" ሶማሊያ ከሩቅ ሀገራት ይልቅ ከጎረቤቶቿ ጋር በመወያየት የሚፈጠሩ ችግሮችን ሰላማዊ በሆነ አግባብ ልትፈታ ይገባል።

ከውጭ የሚመጡ ኃይሎች የኢትዮጵያንና የሶማሊያን ጉርብትና ከማበላሸት ያለፈ ዓላማ አይኖራቸውም " ብለዋል።


ሌላ በውይይቱ ምን ተባለ ?

- ሶማሊያውያን ችግር በገጠማቸው ጊዜ ሁሉ ቀድማ የምትደርሰው ኢትዮጵያ ናት። ይህ አጋርነት እንዲቀጥል የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል።

- የኢትዮጵያ ህዝብና የሶማሊያ ህዝብ ሽብርተኝነትን አብሮ እንደተዋጋ፣ ሰላምን የሚያደፈርስ ሌላ ኃይል በመካከል ሊገባና ሊጎዳቸው አይገባም፤ ይህን ሁሉም ሊረዳው ይገባል።

- የአፍሪካ ቀንድን በእጅ አዙር ችግር ውስጥ ለማስገባት የሚጥሩ ኃይሎች ዕድል እንዳያገኙ ጎረቤታሞቹ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አንድነታቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል።

- ሳማሊያውን የራሳቸው ያልሆኑን ጦርነት ወደ ሀገራቸው በመጋበዝ ቀጠናውን ወደ ቀውስ እንዳይከቱ።

በውይይት መድረኩ ፥ በአሁኑ ወቅት ከ500 ሺህ በላይ የሶማሊያ ስደተኞች በኢትዮጵያ መኖራቸው ፤ ባለፋት ዓመታትም በሚሊየን የሚቆጠሩ ስደተኞች መጠለያቸው ኢትዮጵያ እንደነበረችና ሀብት ንብረትም ማፍራታቸው ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ እና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲዎች በርካታ ሶማሊያውያን በኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ እየተማሩ እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡

#SomaliRegionCommunication

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የመመዝገቢያ ቀናት ከጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም - መስከረም 8/2017 ዓ.ም ድረስ ነው " - የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

አንጋፋዉ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017 ዓ /ም  ለቅድመ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች ለመቀበል መዘጋጀቱን አሳውቆናል።

ዩኒቨርሲቲው ለ2017 ቅድመ ምረቃ ትምህርት በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሺፕ እና በግል ከፍለዉ ለሚማሩ እንዲሁም በማታ በተከታታይ መርሃ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች መማር የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ገልጾልናል።

ከማክሰኞ ጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 8/2017 ዓ.ም የመመዝገቢያ ቀናት እንደሆኑ ይፋ አድርጓል።

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ወደፊት በራሱ በተቋሙ ማህበራዊ ሚዲያ ይገለጸል።

www.aau.edu.et

@tikvahethiopia
2024/11/05 18:49:49
Back to Top
HTML Embed Code: