Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#DireDawa በድሬዳዋ ከተማ " ሰልባጅ ተራ / አሸዋ " ከጥዋት አንስቶ እስካሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ያልተቻለ ከባድ የእሳት አደጋ ደርሷል። አደጋው ጥዋት 1:45 የተነሳ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ለመቆጣጠር ማስቸገሩን ድሬ ቲቪ የሶማልኛ ቋንቋ ክፍል ዘግቧል። በቃጠሎ እስካሁን በሰዎች ሕይወት ላይ የደረሰ የሞት አደጋ ባይኖርም ከፍተኛ የንብረት ውድመት መድረሱ ግን ተጠቁሟል። አሁንም እሳቱን…
#Update #DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ አሸዋ የገበያ ስፍራ የተከሰተው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

በተለምዶ ' አሸዋ ' በመባል በሚጠራው የገበያ ስፍራ ዛሬ ጠዋት ተነስቶ የነበረው የእሳት አደጋ፥ በርካታ የመሸጫ ሱቆችና ማሽላ ተራ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በስፍራው ተገኝተው ሁኔታውን ተመልክተዋል።

የአደጋውን መንስኤና የጉዳት መጠን በምርመራ በማጣራት ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

የእሳት አደጋው ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስ ከፍተኛ ርብርብ ላደረጉ ነዋሪዎች የጸጥታ ኃይል ምስጋና አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከድሬ ቴሌቪዥን ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
ዓመታዊ ግብር በገላግሌው ቴሌብር !

ጊዜዎን ቆጥበው ድካምዎን ቀንሰው ግብርዎን በቴሌብር ሱፐርአፕ http://onelink.to/fpgu4m ወይም *127# ባሉበት ሆነው በምቾት ይክፈሉ!

ሥራን በክብር
ግብርዎን በቴሌብር !

ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ !

ለማንኛውም ጥያቄ ወይም አስተያየት በ https://www.tg-me.com/EthiotelecomChatBot 24/7 ያግኙን!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
#Sidama #Hawassa

° " በሀዋሳ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ነዳጅ በመቋረጡ ለከፋ ችግር ተጋልጠናል " - የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች

° " በእጃችን ምንም ነዳጅ ባለመኖሩ ተጠቃሚው ለተወሰነ ጊዜ ይታገሰን " - የሀዋሳ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ


ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2016 በሀዋሳ ከተማ ያሉ ማደያዎች መዘጋታቸውን ተከትሎ በርካታ የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች መቆማቸውን በመግለጽ ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

" ከሰሞኑ በሰልፍና በጎን በሚገቡ ህገወጥ ቀጅዎች ስንማረር መሰንበታችን ሳያንስ ዛሬ ደግሞ በየቀኑ በቴሌግራም የሚለቀቀዉ የነዳጅ ፕሮግራም ተቋርጦ በከተማው ውስጥ ያሉ ማደያዎች ሁሉ ዝግ ሆኑብን "  የሚሉት አሽከርካሪዎች በዚህም በእጅጉ ተቸግረናል ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአሽከርካሪዎቹን ቅሬታ ይዞ የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ችሎትን አነጋግሯል።

እሳቸውም ፤ " እንደከተማ አንድ ማደያ ብቻ አገልግሎት እየሰጠ ነው " በማለት በከተማዉ ምንም አይነት ነዳጅ አለመኖሩን ገልጸውልናል።

የቴሌግራሙ ፕሮግራም አለመውጣቱም ከዚህ የመጣ መሆኑን አስረድተዋል።

አሁን ላይ ችግሩ በጣም አሳሳቢ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ስብሰባ መቀመጣቸውን ገልጸው "  ማህበረሰቡ እና አሽከርካሪዎች ይህን አውቀው እንዲታገሱ " ሲሉ ጠይቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ህፃን ሶሊያን ዳንኤል ተገኝታለች። • " 40 ሺህ ብር ይከፈልሻል ብለው ሰዎች ስላግባቧት ህፃኗን ሰርቃ ልትሰወር መቻሏል ተጠርጣሪዋ ገልጻለች " - የአዲስ አበባ ፖሊስ ከቀናት በፊት በሞግዚቷ ተሰርቃ የተወሰደችው የ2 ዓመቷ ህፃን ሶሊያና ዳንኤል ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ባደረገው ጠንካራ ክትትል ሱሉልታ ከተማ ላይ መገኘቷን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።…
#AddisAbaba

የሁለት ዓመቷን ሶሊያና ዳንኤል የተባለችውን ህፃን በመጥለፍና በከባድ ስርቆት ወንጀል የተከሰሰችው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥታለች።

የፍርድ ውሳኔ የተላለፈባት ቤዛዊት በቀለ የተባለችው ግለሰብ በሰራተኝነት ተቀጥራ ስትሰራበት ከነበረበት ቤት (ሳሪስ አዲስ ሰፈር) መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ/ም ህጻን ሶሊያናን ይዛ በመሰወር ሱሉልታ ከተማ " ኖኖ መና አቢቹ " ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ህፃኗን ሸሽጋ በተቀመጠችበት በአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሏን ይታወሳል።

ግለሰቧ በቁጥጥር ስር ከዋለች በኃላ የአ/አ ፖሊስ ምርመራ የማስፋት ስራ በመስራት ከዚህ ቀደም በቤት ሰራተኝነት ከተቀጠረችባቸው አምስት የተለያዩ ቤቶች ልዩ ልዩ ንብረቶችን መስረቋን አረጋግጧል።

ከሰረቀቻቸው ንብረቶች መካከልም 2 ላፕቶፕ ፣ 1 ሞባይል ስልክ እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎች ፖሊስ ባደረገው ጥረት ከሸጠችበት በምሪት እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡

በግለሰቧ ላይ ምርመራ ተጣርቶ በከባድ ስርቆት እና ህፃን ልጅ መጥለፍ በሚል ወንጀል በአቃቤ ህግ ክስ ከተመሰረተ በኋላ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ልዩ ልዩ ወንጀል ችሎት ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ቤዛዊት በቀለ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#Tigray #Mekelle

ባለፉት 11 ወራት ብቻ በመቐለ 12 ሴቶች ሲገደሉ 80 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል።

የመቐለ ፓሊስ ከሀምሌ 2015 ዓ/ም እስከ ሰኔ 2016 ዓ/ም ባሉት 11 ወራት ግድያ ጨምሮ 4,340 ከባድና ቀላል የወንጀል ተግባራት በከተማዋ እንደተፈጸሙ አሳውቋል።

የተፈፀሙት ከባድና ቀላል ወንጀሎች በቁጥር ፦
 
➡️ የሴቶች ግድያ 12 

➡️ አስገድዶ መድፈር 80

➡️ ስርቆት 1,953

➡️ ድብደባ  583

➡️ ዝርፍያ 349

➡️ የመገደል ሙከራ 178

➡️ እገታ 10 

ፖሊድ ወንጀል ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዙ 170 የፓሊስ ኮሚኒቲዎች መቋቋማቸውን ገልጿል።

እየተፈፀሙ ያሉ የወንጀል ተግባራት ያልተለመዱ ናቸው ያለው ፖሊስ የሚፈጸሙትን ወንጀሎች ለመቆጣጠር ከወትሮው በተለየ የህብረተሰብ ተሳትፎ እጅግ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በአዲስ አበባ ፤ እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ የክረምት ወቅቱ ሳይጠናከር ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ከተማው አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። እስካሁን ባለው የፒያሳ እና የአራት ኪሎ መስመር እንዲሁም ከሜክሲኮ እስከ ሳር ቤት ያለው ተጠናቆ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተመርቋል። ከዚህ ቀደም ፦ - ከ4 ኪሎ - ፒያሳና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ…
#AddisAbaba

" በትልቅ ቁጠባ በ33 ቢሊዮን ነው እየተተገበረ ያለው " - ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፥ የከተማው 5ቱ ኮሪደር ስራ እየተተገበረ ያለው በ33 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህን የተናገሩት ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ነው።

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ፥ መጀመሪያ ላይ የ5ቱም ኮሪደር ስራ ሲጠና ኮንሰልታንቶችና አጥኚው ቡድን መንገድ እና የመንገድ መሰረተ ልማት የሚፈጀው ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ እንደገለጹ አስረድተዋል።

" ይህ እንግዴ በወቅቱ ጥናት ነው በዚህ ተለዋዋጭ ገበያ " ያሉት ከንቲባዋ " እስካሁን ድረስ የተጠኑትን 5 ኮሪደሮች እየተገበርን ያለነው በ33 ቢሊዮን ነው " ብለዋል።

በ33 ቢሊዮን ብር እየተተገበረ ያለው ስራም " ትልቅ ቁጠባ የተተገበረበት ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

ስራው ብክነትን በመከላከል፣ የሚወጣውን ወጪም አስፈላጊ ነገር ላይ ብቻ እንዲሆን እየተደረገ ነው ብለዋል።

አንዳንድ በከተማው አስተዳደር የሚሰሩ ስራዎችም ለኮንትራክተሮች እንዳልተሰጡ የተናገሩት ከንቲባዋ ፥ ለአብነት የሜክሲኮ መንገድ በኮንትራክተር ሳይሆን በራስ አቅም መሰራቱን ገልጸዋል።

#TikvahEthiopia
#AddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኳል። የተማሪዎቹ ውጤት ዛሬ ለተቋማቱ መላኩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል። በዚህም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። የዘንድሮው የመውጫ ፈተና ለ57 የመንግሥት እና ለ124 የግል ከፍተኛ የትምህርት…
#ExitExam

የግል የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት መቼ ይፋ ይሆናል ?

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2016 ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ውጤት ሰኔ 21/2016 ዓ.ም ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

በተመሳሳይ ጊዜ በአንድ ላይ የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤት ግን እስካሁን ይፋ አልተደረገም።

ይህን ተከትሎ የግል ተፈታኞች በርካታ ጥያቄዎችን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አድርሰዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልገሎት ዴስክን ጠይቀናል።

" ከግል ተፈታኞች ውጤት ጋር በተያያዘ ያልተጠናቀቁ ነገሮች በመኖራቸው ውጤቱ ይፋ አለመደረጉን " የዴስኩ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" ቀሪ መጠናቀቅ ያለባቸው ጉዳዮች እንዳለቁ የግል ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ይደረጋል " ብለዋል።

የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ገበየሁ በበኩላቸው ፥ " ከግል ተፈታኞች አጠቃላይ መረጃ እና ክፍያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ሲጠናቀቁ ውጤቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚለቀቅ " ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ማኅበሩ 178 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በአባልነት ይዟል፡፡

የግል ተቋማት ተማሪዎች የፈተና ውጤት ለተቋማቱ አለመላኩን ከተቋማት በኩል ባገኘነው መረጃ የተረዳን ሲሆን ከሰሞኑን የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ተልኳል፣ እየተላከ ነው ፣ ውጤት ሊለቀቅ ነው " የሚሉ መረጃዎች ሀሰተኛ እንደሆነ ተገንዝበናል።

በሌላ በኩል ፥ በዚሁ ጉዳይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተማሪዎች ተወካይ አነጋግሯል።

ይኸው ተወካይ በውጤት ጉዳይ ከተማሪዎች ጫና ሲበዛ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር እንደሄደና አንድን ኃላፊ እንደጠየቀ የተሰጠው ምላሽም ፥ " ለመፈተኛ ይከፈል የተባለውን በክፍያ (በተማሪ 500 ብር) አጠቃለው ያልፈጸሙ ተቋማት አሉ " የሚል እንደሆነ ገልጿል።

ክፍያውን ሙሉ በሙሉ የከፈሉ እንዳሉ ሁሉ ያልከፈሉ በመኖራቸው ውጤቱ እንደዘገየ እንደተነገረው አስረድቷል።

ተማሪዎች የፈተናው ውጤት መዘግየቱ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳሳደረባቸው ተረድተናል።

ተማሪዎቹ ፥ " ያልከፈለውን አለማስፈተን ነው እንጂ የሚጠበቀውን ክፍያ ከፍሎ የተፈተነን ተማሪ ውጤት ማዘግየት እና ተማሪውን በጭንቀት ማሰቃየት ፍጹም ተገቢ አይደለም " ብለዋል።

ውጤታቸው በፍጥነት እንዲላክና እንዲገለጽ ሌላው ጉዳይ እነሱን የሚመለከት ባለመሆኑ ይህን ያህል ውጤት በመጠበቅ ለጨነቁ እንደማይገባቸው አስገንዝበዋል።

ዘንድሮ 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ማስፈተናቸው ይታወቃል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DireDawa

የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ዛሬ በድሬዳዋ በደረሰው ከፍተኛ የሆነ የእሳት አደጋ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ከንቲባ አቶ ከድር ፥ ከጥዋት 1 ሰዓት ጀምሮ በተለምዶ ' አሸዋ ' በሚባለው አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ ፦
ሩዝ ተራ
ማሽላ ተራ
ሰልባጅ ተራ ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ አሳውቀዋል።

ሌሎች በከፊል የተረፉ እንዳሉ ጠቁመዋል።

እሳቱ አሁን ላይ ካደረሰው ጉዳት ባለፈ እጅግ በጣም የከፋ ጉዳት ሊያደርስ ይችል እንደነበር ጠቁመው እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብር ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

Credit : DireTV

@tikvahethiopia
ግሎባል ባንክ እየሸለመ ነው !

መልዕክቱን ያጋሩ፣ ከ1ሺህ ብር ጀምሮ ተሸላሚ ይሁኑ !
የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ 5ኛ ዙር ሽልማት

1. በመጀመሪያ ቀጣዩን የቦት ሊንክ ይጫኑ፡- https://www.tg-me.com/global_bank_referral_bot?start=476862805
2. START የሚለውን ይጫኑ፣
3. JOIN CHANNEL የሚለውን ይጫኑ፣
4. ወደ መጀመሪያው ቦት ይመለሱ፣
5. CONTINUE የሚለውን ሲጫኑ የመጋበዣ ሊንክዎን ያገኛሉ፣
6. መልዕክቱን ቢያንስ ለ30  እና ከዚያ በላይ ወዳጅ ዘመድዎ ሼር ሲያደርጉ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በየሳምንቱ ከአንድ ሺ ብር ጀምሮ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ያበረክታል፡፡
ሽልማቱ በመጪው ሰኞ ለተሸላሚዎች ይደርሳል፡፡
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ናቸው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የጥሪ ማዕከል ቁጥራችን ☎️ 8118 ☎️ ይደውሉ፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!
#ደራ🚨

" የደራ ወረዳ ነዋሪዎች በሁለት ታጣቂዎች መካከል እየተሰቃዩ ናቸው " - ነዋሪዎች

በሰሜን ሸዋ ደራ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ በታጣቂዎች እየተፈጸመ ባለው ጥቃት አሁንም የዜጎች ህይወት እየጠፋ፣ ነዋሪውም ቄዬውን ለቆ ለመሸሽ እየተገደደ ይገኛል።

አንዴ በፋኖ ታጣቂዎች አንዴ ደግሞ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎች መከራቸውን እያዩ እንደሆነ ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በወረዳው በተለይ በ13 ቀበሌዎች ከሁለት ሳምንት ወዲህ ተቀስቅሷል በተባለ የጸጥታ መደፍረስ የሰዎች ህይወት መጥፋቱ ተሰምቷል።

አንድ የጅሩዳዳ ነዋሪ ፥ አራት አርሶ አደሮች በእርሻ ስራቸው ላይ እያሉ መገደላቸውን ገልጸዋል።

ከወረዳው 44 ቀበሌዎች በ18ቱ የታጣቂዎች እንጂ የመንግሥት መዋቅር እንደሌለ ጠቁመዋል።

ሌላ ነዋሪ ፤ " የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ሲመጣ መኪና አስቁሞ የአማራ ተወላጆችን አግቶ ይወስዳል።  የፋኖ ኃይል ደግሞ የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት በኦሮሞ ተወላጆች ላይ እርምጃ ይወስዳል። የደራ ወረዳ ነዋሪዎች በሁለት ታጣቂዎች መካከል እየተሰቃዩ ናቸው። ነዋሪዎች ሰላም ፍለጋ ቄያቸውን እና ንብረታቸውን ጥለው በኤጄሬ በኩል እያቋረጡ ወደ ፍቼ እየሸሹ ነው። ጓደኛዬ የ15 ቀን አራስ ሚስቱን ይዞ ሸሽቷል። ህዝቡ ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ነው። መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ መስጠት አለበት " ብለዋል።

ሌላኛው ነዋሪ ፤ " እየተሰቃየን ይኸው ሁለት ዓመት አሳልፈናል የመንግስት ዝምታ አልገባንም " ያሉ ሲሆን ከቀናት በፊት በቱቲ ቀበሌ በኩል የፋኖ ኃይል ተኩስ መክፈቱን ጠቁመዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪው አቶ ከፍያለው አዳሬ ፤ በደራ ወረዳ የጸጥታ ችግር መኖሩን አረጋግጠዋል።

" የደራ እና ሂዳቡ አቦቴ ነዋሪዎች ብዙ ጊዜ በፋኖ እና ሸኔ ታጣቂዎች ጥቃት ይደርስባቸዋል። ታጣቂዎቹ የነዋሪዎችን ቤት ያቃጥላሉ፣ ሰዎችንም ያግታሉ። ሁለቱም ኃይሎች ህዝቡን በብሄር እና በሃይማኖት ለማጋጨት በተደጋጋሚ ይጥራሉ። ለምሳሌ ፦ ' ፋኖ ነኝ ' ባዩ አካል የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን ንብረት ያወድማል ፤ የሸኔ ታጣቂም እንደዛው የአማራ ብሄር ተወላጆችን ንብረት ያወድማል " ብለዋል።

" የመንግስት የጸጥታ ኃይል በሁለቱም ታጣቂ ኃይሎች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው " ሲሉ አክለዋል።

" ደራ ወረዳ አልፈረሰችም የመንግሥት ማዋቅርም አለ "  ያሉት አስተዳዳሪው " የመንግስት ኃይል በማይደርስባቸው ቦታዎች ሰላም ለማስፈን አስቸጋሪ ሆኗል " ብለዋል።

" ታጣቂው ኃይል በእነዛ ቀበሌዎች ነው ያለው ግን ሌላም ቦታ ገብቶ አያጠፋም ማለት አይቻልም ፤ ይህ ታጣቂ ኃይል ከሌላ አካባቢ የመጣ ሳይሆን ከዚሁ አፋና ኦሮሞ እና አማርኛ ተናጋሪ ህብረተሰብ ውስጥ የወጣ ነው ገሚሱ ተገዶ ሌሎቹ ፈቅደው ነው  የታጣቂውን ቡድን ተልዕኮ ተቀብለው ለሰላም ጠንቅ ሆነዋል " ሲሉ አክለዋል።

አቶ ከፍያለው የደራ ጸጥታ ጉዳይ ሰራዊት / የጸጥታ ኃይል በማስለፍ ብቻ መፍትሄ እንደማያገኝ ገልጸው ነዋሪዎች ለሰላም መስራት አለባቸው ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዚህ መረጃ ባለቤት የቪኦኤ ሬድዮ አማርኛው ክፍል (ጸሐይ ዳምጠው) መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia🕊

ቅዱስነታቸው ሁሉም ለሰላም በአንድነት እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ።

" የሃይማኖት ተቋሞቻችን ለዘላቂ ሰላማችን " በሚል ርእስ በአዲስ አበባ አንድ መድረክ ተካሂዷል።

በዚህም መድረክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወክጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው ፤ " ጥላቻ፣ ጦርነት፣ ጠብ፣ ክርክር፣ ሞኝ መሆኑን እያወቅን እዚያ ላይ እንንከባለላለን። የሰው ልጅ ህልውናውን ለመጠበቅ ሰላምን መምረጥ እና መከተል ይኖርበታል " ብለዋል።

" የሰላምን እጦት ያመጣነው ራሳችን ነን። ማንም አምጥቶ አልጫነብንም " ያሉ ሲሆን " ሰላም ከሌላ መንፈሳዊም ሆነ ዓለማዊ ተቋማት ምንም መሰራት እንደማይችሉ አውቀን ለሰላም በአንድነት መቆምና ሰላምን መከተል ይኖርብናል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ለዚህም ሁላችንም ከቀደመው እየተማርን መጪውን ሰላማዊ ለማድረግ መጣር ይኖርብናል " ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ፥ " የሔድንበት መንገድ ጎድቶናል ስለሆነም ወደ ሰላም እንመለስ ብለን መወሰን አለብን። ለዚህም ሁላችንም ወደ አእምሮችን ተመልሰን ሰላምን እንከተላት " ሲሉ አባታዊ ጥሪ አቅርበዋል።

#EOTC
#Ethiopia

@tikvahethiopia
2024/09/30 14:25:35
Back to Top
HTML Embed Code: