Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኬንያ ምንም እንኳን ትላንትና የኬንያ ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ በፋይናንስ ረቂቅ ሕጉ ላይ ፊርማቸውን እንደማያኖሩ እና ሙሉ በሙሉ ውድቅ እንደተደረገ ቢያሳውቁም ዛሬም ተቃዋሚዎች አደባባይ ወጥተው ነበር። ናይኖቢ ውስጥ የመንግስት ጸጥታ ኃይሎች አደባባይ በወጡ ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጪስ ተኩሰዋል። ወደ ፕሬዜዳንቱ ቤተመንግስት የሚወስደውን መንገድ ዘግተውታል። ዛሬም በከተማይቱ በርካታ የንግድ ተቋማት…
#Kenya

በኬንያ ሰሞነኛውን ተቃውሞ እና ሰልፍ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በርካቶች ዝርፊያ ላይ መሰማራታቸው ተሰምቷል።

የሀገሪቱ የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዝርፊያ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች " ዋጋቸውን ያገኛሉ " ብሏል።

በኬንያ ከፋይናንስ ሕጉ ጋር የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አልቆመም።

ምንም እንኳን ፕሬዜዳንት ሩቶ " ትቼዋለሁ ፤ አልፈርምም፣ ተሰርዟል " ቢሉም ተቃዋሚዎቻቸው " ረፍዷል ስልጣን ይልቀቁ " በሚል ተቃውመ ቀጥለዋል።

ተቃውሞውን ተከትሎ ግን በርካታ ዘረፋዎች እየተፈጸሙ ነው።

እነዚህ የዝርፊያ ተግባራት በዜጎች የእጅ ስልክ እና በደህንነት ካሜራዎች ተቀርጸው እየተሰራጩ ነው።

የኬንያ የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ተቃውሞ እና ሰልፉን በመጠቀም የወሮበሎች ቡድን ንጹሃንን ሲዘርፉ መታየታቸውን እና እነዚህን ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ እንደሆነ አመልክቷል።

ዘራፊዎች የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ ዋጋቸውን ያገኛሉም ብሏል።

ሌሎችም ከሰልፉ ጋር በተያዘ ህገወጥ ተግባር ላይ ተሳትፈዋል ያላቸውን ተፈላጊ ተጠርጣሪ ሰዎችንም በፎቶ አሰራጭቷል።

@tikvahethiopia
አንጋፋው ገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ከ ' አዲስ አድማስ ጋዜጣ ' መሥራች አንዱ እና በዋና አዘጋጅነትም ጋዜጣዋን ተወዳጅ ያደረጋት ገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን ባደረበት ህመም ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ዛሬ ረቡዕ ረፋድ ላይ ድንገት ህይወቱ አልፏል።

ነቢይ ተርጓሚ ፣ ገጣሚ ወግ አዋቂ የጥበብ ሰው ነበር።

Via @tikvahethmagazine
#Ethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ አቶ ካሳሁን ጎፌን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አድርገው ሾሙ።

ወ/ሮ ሽዊት ሻንካን ደግሞ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አድርገው ሾመዋቸዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር የነበሩት አቶ ቀጀላ መርዳሳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጣቶች እና ስፖርት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ከዛሬ ሰኔ 26 /2016 ዓ/ም ጀምሮ እንደ ተሾሙ ታውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፓለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 “ መንግስት እንደ መንግስት ሥራውን እየሰራ አይደለም ” ሲል ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ተቸ። የፓርቲው ሊቀመንበር ፤ ዶክተር አብዱልቃድር አደም ስለወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች የፓርቲያቸውን ምልከታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርተዋል። ሊቀመንበሩ በነበራቸው ቆይታ  ፦ - የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል ጉዳይ - የኑሮ ውድነት - የሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ - ከሰሞኑን…
" ሁለት ወራት ከ18 ቀናት ነው መተከል የቆየሁት አንድም ቀን መብራት አልበራም " - ዶክተር መብራቱ አለሙ

የኢትዮጵያ ፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሥራ አስፈፃሚ ፣ የቦሮ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ቦሮ) የውጪ እና ዓለም አቀፍ ዘርፍ ኃላፊ ፣ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር መብራቱ አለሙ የቦሮ ዲሞክራሲ ፓርቲን ወክለው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በዚህ ቆይታቸው ፦
- ስለ ሰሞነኛው ምርጫ
- ስለ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የደህንነትና ሰላም ሁኔታ
- ከምርጫ ሲመለሱ ስላጋጠማቸው ነገር
- ስለ መሰረተ ልማት ጉዳይ ... ሌሎችም ጉዳዮች ተነስተውበታል።

ዶ/ር መብራቱ አለሙ ከተናገሩት ፦

" በዚህ ምርጫ ላይ ህዝባችን በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ለማየት ሞክረናል።

2 ወራት ከ18 ቀናት ነው መተከል የቆየሁት አንድም ቀን መብራት አልበራም።

ኤሌክትሪክ ከተዘረጋ ወደ 10 ዓመታት ይሆነዋል ፤ ግን ከግጭቱ በኋላ መሠረተ ልማቶች ተመልሰው አልተገነቡም። ጨለማ ውስጥ ነው መተከል ያለው።

ገዢው ፓርቲ (ብልጽግና) ደግሞ የሚበራ አምፓል ነው ያቀረበው ለምርጫ እንኳ ምልክት አድርጎ።  ‘ የቆመ ፓል እንጂ ሚበራ አምፓል የለም ’ እያሉ መፈክር ያሰሙ ነበር የኛ የፓርቲ ደጋፊዎች።

የሚጠጣ ንጹህ ውሃ የለም፤ መንገድ የለም።

መተከል ዞን ማለት የህዳሴው ግድብ፣ ብዙ ብሔር ብሔረሰቦች ፣ ሰፋፊ መሬት ፣ ከሱዳንም ጋር ረጅም ድንበር ያሉበት ዞን ነው።

ይህ ዞን እንግዲህ የመልካም አስተዳደር ፣ የመንገድ እጦት አይገባውም። የተማረ የሰው ኃይል አለው። ይሄ ማለት በክልሉ የLeadership ክፍተት አለ። ይሄንን የገዢው ፓርቲም ቢሆን አይቶ እልባት እንዲሰጠው እንደ ፓርቲ ሰላማዊ ትግል እናደርጋለን።

የክልሉ መንግስት በተለይ በተለይ በመሠረተ ልማት ላይ ኮሚቴ አቋቁሞ በደንብ መስራት እንዳለበት ይሰማኛል።

በተረፈ ብዙ ችግሮች አሉ። በመልካም አስተዳደር ፣ በሙስና (በተለይም ማዕድን ያለበት አካባቢ ላይ)፣ የወርቅ ኮንትሮባንድ ንግድ በጣም ከፍተኛ ነው። ይሄ ሁሉ ችግር ተደማምሮ ህዝቡ ችግር ላይ ነው። "

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-03

#የፖለቲካፓርቲዎችምንይላሉ? #ቦሮፓርቲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sidama #Hawassa ° " በሀዋሳ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ነዳጅ በመቋረጡ ለከፋ ችግር ተጋልጠናል " - የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ° " በእጃችን ምንም ነዳጅ ባለመኖሩ ተጠቃሚው ለተወሰነ ጊዜ ይታገሰን " - የሀዋሳ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2016 በሀዋሳ ከተማ ያሉ ማደያዎች መዘጋታቸውን ተከትሎ በርካታ የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች መቆማቸውን በመግለጽ ቅሬታቸዉን…
#Sidama

በሀዋሳ ከተማ 1 ሊትር ቤንዚን በድብቅ እስከ 180 ብር እየተሸጠ ነው።

በከተማይቱ ያሉ ሁሉም ማደያዎች ውስጥ ቤንዚን የለም ተብሏል።

ይህን ተከትሎ 1 ሊትር ቤንንዚን ከ150 ብር እስከ 180 ብር በድብቅ እየተሸጠ ይገኛል።

ቀድሞውም ቢሆን በከተማዋ በድብቅ ነዳጅ ይሸጥ ነበር። ዋጋውም 100 ብር የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በመላ ከተማይቱ ነዳጅ መጥፋቱን ተከትሎ እስከ 180 ብር ደርሷል።

የከተማ ውስጥ ታክሲዎች በተለይ በከተሞች ዳርቻ ዋጋቸዉን እጥፍ ከማድረግ በዘለለ ኮንትራት ካልሆነ አንጭንም እያሉ መሆኑን ሰምተናል።

አንድ የሀዋሳ ከተማ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል  " ዛሬ በሀዋሳ 1 ሊትር ቤንዚል ከ170 ብር ጀምሮ እየተሸጠ ነው። በየትኛውም ነዳጅ ማደያ ዛሬ ቤንዚል የለም " ብሏል።

" አንዳንድ ታክሲዎች ዝም ብለን ከምንቀመጥ ብለው 2 ሊትር ከ320 ብር ጀምሮ እየገዙ ፤ የ5 ብር መንገዶችን በ10 ብር እየጫኑ ነው ፤ ከዛ ውጭ ሌሎች በተለይ ባጃጆች በየጥሻው ቆመው ነው ያሉት " ብለዋል።

የከተማው ትራንስፖርት ቢሮም ሆነ የነዳጅ ጉዳይ የሚመለከተዉ የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ትናንት ስብሰባ ላይ እንደነበሩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረዳት ችሏል።

ስብሰባውን ተከትሎ እስካሁን ምንም አዲስ ነገር አልተፈጠረም።

በትላንትናው ዕለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡት  የከተማዉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ችሎት " ጉዳዩ አገር አቀፍ ችግር ነው " ብለዋል።

በማደያዎች ነዳጅ አለመኖሩን እና መንገድ የጀመረ የነዳጅ ጫኝ ቦቴ እንደሌለ በመግለጽም ማህበረሰቡ እንዲታገስ ጥሪ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
#የጤናባለሞያዎች

" የ5 ወር የትርፍ ሰአት ክፍያ አልተከፈለንም !  አፋጣኝ ምላሽ እንፈልጋለን " - በዋቻሞ ዩኒቨርስቲ የንግስት እሌኒ መሐመድ ሆስፒታል ሰራተኞች

" በጀቱ ስለተለቀቀልን ክፍያዉን በሁለት ቀን ውስጥ እናጠናቅቃለን ተረጋጉ " - የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ


በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሀመድ ሆስፒታል ውስት የሚሰሩ ሰራተኞች 5 ወር ሙሉ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዳልተከፈላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" ለወራት የትርፍ ሰአት ክፍያ ስንጠይቅ ነበር " ያሉት ሰራተኞቹ ከሰሞኑ ድምጻቸዉን ለማሰማት ሰልፍ ለመውጣት መገደዳቸውን አመልክተዋል።

" የዘገየዉ ገንዘባችን ይሰጠን  !! " ሲሉም ለሚመለከተዉ አካል መልእክታቸዉን አሰምተዋል።

" የኑሮ ዉድነት ምን ያክል ፈተና እንደሆነብን እየታወቀ የትርፍ ሰአት ክፍያችን በጠየቅን ቁጥር ቀጠሮ መስጠት የማይሰለቸዉ የሆስፒታሉ አስተዳደር ትእግስታችን ተፈታትኖታል " የሚሉት ሰራተኞቹ " ከዚህ በላይ መታገስ የምንችልበት ሁኔታ ላይ ባለመሆናችን ጥያቄያችን በቶሎ ይመለስ " ሲሉ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰራተኞቹን ጥያቄ ይዞ የሆስፒታሉን ስራ አስኪያጅ ዶክተር አያኖ ሻንቆን አነጋግሯል።

" ምንም እንኳን ችግሩ የታወቀ ቢሆንም የ5 ወር መዘግየት ሰልፍ የሚያስወጣ አልነበረም " ብለዋል።

አሁን ላይ ክፍያዉን ለማጠናቀቅ ቢበዛ 2 ቀናት ብቻ እንደሚበቃቸዉ ገልጸዋል።

የገንዘብ እጥረቱ የተከሰተዉ የነበረውን የበጀት እጥረት ለማስተካከል ዩኒቨርሲቲው ቅድሚያ ለተማሪ በማለቱ እንደሆነ አስረድተዋል።

" አሁን ላይ በጀቱ ተለቋል " ብለዋል።

ለክፍያው የተፈቀደው ገንዘብ በጽሁፍ እንጅ በካሽ አለመለቀቁን ተከትሎ ክፍያዉ በቶሎ አለመጀመሩን የገለጹት ስራ አስኪያጁ ፥ " አሁን ገንዘቡ በመድረሱ በ2 ቀን ውስጥ ክፍያዉ ይጠናቀቃል " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
" እኔ ያያሁት 3 ሰዎች ሞተዋል እና የቆሰሉ ሰዎችም ነበሩ " - ነዋሪ

በአዳማ ከተማ ፤ በቦኩ ሸነን ክፍለ ከተማ ሀሮሬቲ ወረዳ እና ቶርበን ኦቦ ወረዳ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የሰው ሕይወት ማለፉና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን ለመስማት ችለናል።

በነዋሪዎች ዘንድ ተቃውሞ እንዲቀሰቀሰ ምክንያት የሆነው የከተማ አስተዳደሩ በወረዳዎቹ የሚገኙ ቤቶችን ሕገ-ወጥ ናቸው በሚል የማፍረስ ሂደት ሊጀምር ሲል መሆኑን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም ይፈርሳሉ ያሏቸውን ቤቶች በቀይ ቀለም " X " እያረጉ እንደነበር እና ዛሬ ለማፍረስ ሲመጡ ነዋሪዎች ተቃውሞ እንዳነሱ ይህን ተከትሎም የጸጥታ ኃይሎች ተኩስ መክፈታቸውን አንድ የዐይን እማኝ አስረድተዋል።

ቦታዎቹ ላለፉት ዓመታት ግብር ሲከፈልባቸው የነበሩ እንደሆኑም ጠቁመዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የአከባቢው ነዋሪ እንዳሉት " በተቀሰቀሰው ግጭት እኔ ያያሁት 3 ሰዎች ሞተዋል እና የቆሰሉ ሰዎችም ነበሩ። በዛ አከባቢ ከሰዓት በኋላ እንቅሰቃሴ አልነበረም። ሁሉም ሰው በቤቱ ውስጥ ተቀምጧል እና በአጠቃላይ ያለውን ነገር ማወቅ አልቻልንም " ሲሉ ገልጸዋል።

ከማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ያገኘናቸው ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩት የኢትዮጵያ እና የኦሮሚያ ክልል ባንዲራ የያዙ በርካታ ሰዎች ተቃውሞቸውን ለማሰማት መንገድ በመዝጋት እና " ፈረሳው ይቁም !! " የሚሉ መፈክሮች እየሰሙ እንደነበር ነው።

በሌላ አንድ ቪዲዮ ላይ ነዋሪዎቹ በዱላ እንዲሁም በድንጋይ መንገድ ዘግተው እንደነበር ተመልክተናል።

ነዋሪው ተቃውሞውን ማሰማት በጀመረበት ወቅት ተኩስ መጀመሩና በሰልፍ ላይ የነበሩ ሰዎች ሲበታተኑም ተመልክተናል።

በዚህ ውስጥ የሰዎች ሕይወት ማለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዐይን እማኞች መስማት የቻለን ቢሆንም ምን ያህል ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ ማረጋገጥ አልተቻለም።

ከከተማው አመራርና የጸጥታ አካላት ጉዳዩን ለማጣራት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

#TikvahEthiopiaFamilyAdama

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፥ " በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በሽረ እንዳስላሰ ከተማ የነበሩ ተፈናቃዮች ከሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቄያቸው ሰሜን ምዕራብ ዞን ፀለምቲና ማይ ፀብሪ እንዲመለሱ የማድረግ ስራ ተጀምሯል " ሲል አሳውቋል። ከ3 ዓመት በላይ በእንዳስላሰ ሽረ ከተማ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው ለመጓዝ ዝግጁ እንዲሆኑ አርብ ማታ ተነግሯቸው…
#Update

የሀገር መከላከያው ስለ ትግራይ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የማድረግ እንቅስቃሴ ምን አለ ?

የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌ/ጄነራል ብርሃኑ በቀለ ከብሄራዊ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ አድርገው ነበር።

የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነትን መሰረት በማድረግ በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

ሀገር መከላከያው ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ እንዲያስተባብር አቅጣጫ ተሰጥቶ እየሰራ እንዳለ አመልክተዋል።

የፀለምት እና አካባቢው ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው የመመለስ ስራ ኃላፊነት የተሰጠው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ መሆኑን ተናግረው " ስራው እጅግ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው " ብለዋል።

ዛሬን ረቡዕ ጨምሮ ባለፉት ቀናት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቄያቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ሌ/ጄነራሉ ፥ ተፈናቃዮች እየተመለሱ ያሉት አስፈላጊና መሟላት አለባቸው የተባሉ ቅድመ ሁኔታዎች ከጎን እየተሰሩ ነው ብለዋል።

ስራው በፍጥነት እየሄደ ያለው አብዛኛዎቹ አርሶ አደር የክረምቱ ወቅት ሳያልፍ እርሻውን እንዲሰራና ህይወቱን እንዲመራ በማሰብ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በፀለምት ካሉ 25 ቀበሌዎች አብዛኛው ተፈናቃይ ከ22 ቀበሌዎች ነው አሁን ባለው ሁኔታ በአስራዎቹ ቀበሌዎች ተፈናቃይ ተመልሷል ፤ እስከዚህ ሳምንት መጨረሻ ቀሪ 11 ቀበሌዎች  አብዛኛው እንዲገባ ይደረጋል ሲሉ አሳውቀዋል።

የቀረውም ስራ በቀጣይ ይሄዳል ብለዋል።

ስለ ታጣቂዎች መውጣት ምን አሉ ?

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የትግራይ ታጣቂዎች በኃይል ገብተዋል " ስለሚባለው ጉዳይ ሌ/ጄነራሉ ፥" ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኃላ በፀለምትም ይሁን በወልቃይት በኃይል የገባባቸው ቦታዎች የሉም " ሲሉ መልሰዋል።

ፀለምት ካሉት ቀበሌዎች 3 ቀበሌዎች ላይ የትግራይ ታጣቂዎች እንዳሉ እነዚህም ጦርነት ሲቆም ባሉበት የቆሙ ናቸው ሲሉ አስረድተዋል።

ባለው መግባባት ከሁለቱም ክልል ጋር የሁለቱም ክልል ታጣቂ መውጣት ስላለበት ተፈናቃዮችን በመመለስ ታጣቂዎቹን የማስወጣት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም ፀለምት ያለው የትግራይ ታጣቂ እንዲወጣ እየተደረገ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ከተፈናቃይ ጋር ታጣቂ እንዳይመለስ ስለሚሰራ ስራ ምን አሉ ?

በአማራ በኩል " ከተፈናቃይ ጋር ታጣቂ ይገባል " የሚል ስጋት እንዳለ ያልሸሸጉት አዛዡ ፥ በትግራይ በኩልም " ታጣቂዎች (በአማራ በኩል ያሉ) እንደ አዲስ ተደራጅተዋል ስጋት ናቸው " የሚል ነገር እንዳለ ገልጸዋል።

" የሀገር መከላከያው ከሁለቱም በኩል ከተፈናቃዮች እና እዛው ከነበሩት ነዋሪዎች ( ካልተፈናቀሉት ) ሽማግሌዎች እንዲውጣጡ አድርጎ የተፈናቃዮችን ዝርዝር ለመከላከያ ተሰጥቶ ከዛም መከላከያው ከሽማግሌዎቹ ጋር አብሮ ሰዎቹ የዛ ቦታ ነዋሪ መሆናቸውን እየጠየቀና እያረጋገጠ ተፈናቃዮች ይመለሳሉ " ብለዋል።

' ይሄ ታጣቂ ነው ፣ ይሄ ሚሊሻ ነው ' የሚል ክርክር በሽማግሌ ደረጃ ከተነሳ ወደ ህዝብ ተወስዶ ህዝቡ እራሱ ይፈርዳል ሲሉ ተናግረዋል።

" እንግዳ ሰው ሲገባ ይታወቃል ይህ ጉዳይ አሳሳቢ አይደለም " ያሉት አዛዡ ፥ ገጠር ይሁን ከተማ መሬት ከሌላቸው / ሊገቡበት የሚችሉበት ቤት ከሌላቸው ተለይቶ ይታወቃል ብለዋል።

#Ethiopia
#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሀገር መከላከያው ስለ ትግራይ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የማድረግ እንቅስቃሴ ምን አለ ? የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌ/ጄነራል ብርሃኑ በቀለ ከብሄራዊ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ አድርገው ነበር። የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነትን መሰረት በማድረግ በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን የመመለስ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል። ሀገር መከላከያው ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ እንዲያስተባብር አቅጣጫ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ ፦ በጦርነት ከፀለምት እና አካባቢው ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉትን ወገኖች ወደ ቄያቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ ይገኛል።

በርካታ የህዝብ ማመላለሻ መኪናዎች ተፈናቃዮችን እያደረሱ ነው።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የማስተባበር ኃላፊነት እየተወጣ ነው።

በፀለምት ውስጥ ካሉ 25 ቀበሌዎች በአብዛኛው ከ22ቱ ዜጎች ተፈናቅለዋል።

እነዚህን ዜጎችን ነው በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የተገለጸው።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በቀጣይም የሌሎች አካባቢዎች ተፈናቃዮች እንደሚመለሱ አሳውቋል።

Video Credit - DW

@tikvahethiopia
የአሜሪካ ኤምባሲ ነገ ለምን ተዘግቶ ይውላል ?

በአዲስ አበባ የአሜሪካ አሜባሲ ነገ ሀሙስ ሙሉ ቀን ተዘግቶ ይውላል።

የሚከፈተውም በነጋታው አርብ ዕለት ነው።

ኤምባሲው ተዘግቶ የሚውለው የሀገሪቱን የነጻነት ቀን ለማክበር ነው።

አሜሪካ በየአመቱ እኤአ ሃምሌ 4 ላይ የነጻነት ቀኗን ታከብራለች።

ሀገሪቱ እኤአ በ1776 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ደግሞ በ1769 ዓ.ም ነው ከብሪታንያ ቅኝ ግዛትነት ነጻነቷዋን ያወጀችው።

@tikvahethiopia
#CHAPA

የይለፍ ቁጥሮን ባለማጋራት ራስዎን ካጭበርባሪዎች ይጠብቁ!

🚫አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎች ሲኖሩ ወደ 📞8911 በመደወል ሪፖርት ያድርጉ

🌐 ለበለጠ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ፡ https://chapa.co/

#chapa #chapapayments #Fraudawareness #Digitalpayment
#HoPR

ዛሬ የህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ተገኝተዋል።

በስብሰባው የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

በአሁን ሰዓት የምክር ቤት አባላት ጥያቄ እያቀረቡ ናቸው።

@tikvahethiopia
#የጤናባለሙያዎች

° “ የ3 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተሰጠንም ” - የጤና ባለሙያዎች

° “ ለጉዳዩ ምላሽ መስጠት ያለበት ወረዳው ነው ” - የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ

° “ የጀበት ችግር ገጥሞን ነው ” - የኪንፋዝ በገላ ጤና ጽ/ቤት
  

በአማራ ክልል፤ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኪንፋዝ በገላ ወረዳ የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች ከሚያዚያ 2016 ዓ/ም ጀምሮ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረዋል።

የጤና ባለሙያዎቹ፣ “ የ3 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተሰጠንም። ስንጠይቃቸውም ‘ አንከፍልም ’ ነው የሚሉት ” ብለው፣ ክፍያው እንዲፈጸምላቸው ጠይቀዋል።

የቅሬታ አቅራቢዎቹ ብዛት ከ30 በላይ እንደሆነ፣ የክፍያ መጠኑ እንደዬደረጃቸው እንደሚለያይ ገልጸው፣ ይህ ቅሬታ የተፈጠረው ፦ 
- በስላሬ 
- በጭቅቂ 
- በሮቢት በገላ በተሰኙ 3 የወረዳው ጤና ጣቢያዎች መሆኑን አስረድተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የጸጥታ ችግር ባለባቸው ቦታዎች የጤና ኤክስቴንሽን፣ ጤና ሙያተኞች ደህንነታችን ዋስትና ሳይሰጠው ‘ የክትባት ዘመቻ ካልዘመታችሁ ’ እየተባልን በስጋት ውስጥ ነው ያለነው ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎቹን ቅሬታ ይዞ የዞኑን ጤና መምሪያ አነጋግሯል።

ለምን ብራቸውን አትከፍሏቸውም ? ስንል ለጠየቅነው ጥያቄ ፤  “ለጉዳዩ ምላሽ መስጠት ያለበት ወረዳ ነው። በወረዳው በጀት ዞን ጤና መምሪያው የሚመለከተው ስላልሆነ ” ብሏል።

ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መላኩ ገ/ህይወት በሰጡት ቃል፣ “ የበጀት እጥረት ገጥሞን ነው ” ብለዋል።

ታዲያ ችግሩን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግራችሁ ነበር ? ለሚለው ጥያቄ፣ “ በሚቀጥው በአዲሱ በጀት ተይዞ ይከፈላቸዋል ” ነው ያሉት።

“ ለዚህም ደግሞ አስተዳደሩ ደብዳቤ ጽፏል። ‘በቀጣይ እከፍላለሁ’ የሚል ” ሲሉ አክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ባለሙያዎቹ ' የጸጥታ ችግር ባለበት ለክትባት ውጡ ተብለናል ' የሚል ቅሬታ አላቸው፤ ለመሆኑ ይህን ስታደርጉ ለደህንነታቸው ከለላ ታደርጉላቸዋላችሁ ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

ኃላፊው በምላሻቸው፣ “ የጸጥታ ችግር የሌለበት የለም። ዞሮ ዞሮ ግን በሚቻለው አግባብ የአገር ሽማግሌዎችን ይዘን እንሰራለን ” ነው ያሉት።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR ዛሬ የህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ተገኝተዋል። በስብሰባው የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ በአሁን ሰዓት የምክር ቤት አባላት ጥያቄ እያቀረቡ ናቸው። @tikvahethiopia
የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?

" አጠቃላይ የሀገራችን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች በዋና ዋና አመላካቾች በምን ደረጃ  ላይ ናቸው ?

በተለይ የኑሮ ውድነት እየከፋ ነው።

የዋጋ ንረትን ደግሞ ማረጋጋት አልተቻለም።

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለው ማህበረሰብ እና የመንግሥት ሰራተኛው መኖር አቅቶታል።

መኖር የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው።

ስለሆነም እንደ መንግሥት በቀጣይ አመታት እነዚህን ተግዳሮቶች ለመወጣትና የህዝቡን ጥያቄ ለመፍታት በምን ደረጃ ታቅዷል። "

(አቶ አቤነዘር በቀለ - የተ/ም/ቤት አባል)

@tikvahethiopia
2024/09/30 16:36:25
Back to Top
HTML Embed Code: