Telegram Web Link
#AddisAbaba

የትግርኛ እና የአፋን ኦሮሞ የቋንቋ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩ አመራሮች የማጠቃለያ ፈተና እንደወሰዱ ተነገረ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ለ5 ተከታታይ ወራት የትግርኛ እና አፋን ኦሮሞ ቋንቋ ትምህርት ሲሰጥ እንደቆየ ተነግሯል።

ትላንትና የማጠቃለያ ፈተና እንደተሰጠ ተገልጿል።

ከክ/ከተማው በተገኘ መረጃ ፥ ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ የሚገኙ 371 አመራሮች በትግርኛ እና በአፋን ኦሮሞ የቋንቋ ትምህርት ለ5 ወራት ሲከታተሉ ቆይተዋል።

አመራሮቹ ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ተጨማሪ ቋንቋ ተምረው ትላንት የማጠቃለያ ፈተና መውሰዳቸው ተገልጿል።

የቋንቋ ትምህርቱ ሲሰጥ የነበረው ከጋራ ጉሪ 1ኛ ደረጃ  ትምህርት ቤት ጋር በመቀናጀት እንደነበረ ተነግሯል።

ክ/ከተማው ፤ ብልፅግና ፓርቲ በሀገሪቱ አምስት የስራ ቋንቋዎች እንዲሆኑ ትኩረት በመስጠት እየሰራ ይገኛል ብሏል።

#AddisAbaba
#LamiKuraCommunication

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gambella ንፁሃንን " መረጃ ሰጥታችኋል " በሚል በአቃቂ ሁኔታ #እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ፤ ግድያው ላይም ተሳትፈዋል ከተባሉ ተከሳሾች ውስጥ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞ ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ በተከሰሱበት ክስ #ነጻ መባላቸው ተሰምቷል። ሌሎች የቀድሞ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና የልዩ ኃይል አዛዦችን ጨምሮ 12 ተከሳሾች ግን የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል። …
#EHRC #Gambella

“ ቪዲዮው የቆየ ነው ፤ ከሁለት ዓመት በፊት ነው ” - የኢሰመኮ ጋምቤላ ክልል ጽሕፈት ቤት

ባለፉት ሳምንታት ውስጥ አንድ እጅግ በጣም አሰቃቂ ቪድዮ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወር ቆይቷል።

እውነት ለመናገር በቪድዮ ላይ የሚታየው የጭካኔ ተግባር በቃላት የሚገለጽ አይደለም።

ቪድዮው የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ልብስ የለበሱ አካላት ሰዎችን እጅግ በአሰቃቂ ሁኔታ በድንጋይ ጭምር ጭንቅላታቸውን እየፈጠፈጡ በጅምላ ሲገድሏቸው የሚያሳይ ለማየት የሚከብድ ዘግናኝ ቪዲዮ ነው።

ይህን ቪዲዮ የተመለከቱ በርካቶች ፣ “ እውነት እኛ ሀገር ነው ? እኛ ሀገር ከሆነስ ለዚህ ተግባር ተጠያቂነት እና ፍትሕ ተረጋግጧል ? ” በማለት በእጅጉ አዝነው ጠይቀዋል።

አብዛኛዎቹ ሰዎችም ቪዲዮው ከሰሞኑን የተፈጸመ ጥቃት አድርገውም የወሰዱ ነበሩ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ለጉዳዩ ቅርብ ናቸው ያላቸውን አካላት ስለቪድዮው ጠይቋል።

ይህንን ቪዲዮ ኮሚሽናችሁ ተመልክቶት ነበር ? በማለት የጠየቃቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጋምቤላ ክልል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አቤል አዳነ፣ “ ቪዲዮው የቆየ ቪዲዮ ነው። ከሁለት ዓመታት በፊት የነበረ ቪዲዮ ነው ” ብለዋል።

ሰኔ 7 / 2014 ዓ/ም “ የሸኔና ጋነግ ” ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ገብተው ጥቃት እንደፈጸሙ አስታውሰዋል።

በኋላ “ የክልሉ ልዩ ኃይሎች ‘ ኦነግ ሸኔ ቀርተዋል ’ ብለው የጠረጠሯቸውን ሰዎች በየቤታቸው እየሄዱ፣ እዛው ፓሊስ ኮሚሽን አካባቢ ወስደው ግድያ ፈጽመውባቸዋል ” ነው ያሉት።

“ ይህንን ቪዲዮ ጨምረን ሌሎችንም ምርመራ አድርገን የምርመራውን ሪፓርት ይፋ አድርገናል በሰዓቱ ” ብለዋል።

የኮሚሽኑ አስተያዬት የተካተተበትን ሪፓርትም ልከዋል። 

ግድያውን የፈጸሙት አካላት በሕግ ፊት ተጠያቂ ተደርገው ይሆን ? በማለት ላቀረብንላቸው ጥያቄ “ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎች አሉ ” ብለዋል።

ከፌደራል ፓሊስ ፣ ከፍትህ ሚኒስቴር የተውጣጣ አጣሪ መርማሪ ቡድንም ጋምቤላ መጥቶ ጉዳዩን እንደመረማረና ‘በጉዳዩ ላይ ተጠይቂ ናቸው’ ብሎ የሚያስባቸውን ሁሉ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ የፍርድ ሂደታቸው እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል።

ከነዚህም ውስጥ በወቅቱ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር የነበሩትና ምክትላቸውን ጨምሮ ሌሎችም እንዳሉበት አክለዋል።

ትላንትና ከሰኔ 7 ቀን 2014 የጋምቤላ ክስተት ጋር በተያያዘ ንፁሃንን " መረጃ ሰጥታችኋል " በሚል በአቃቂ ሁኔታ #እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ፤ ግድያው ላይም ተሳትፈዋል የተባሉ ፦
➡️ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞ አመራሮች ፣
➡️ የልዩ ኃይል አዛዦች (ዋናውና ምክትሉ)
➡️ የተለያዩ የጸጥታ አባላት
የጥፋተኝነት ፍርድ እንደተላለፈባቸው ፤ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞ ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ ግን በተከሰሱበት ክስ #ነጻ መባላቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

አዲስ አበባ ፖሊስ ከሰኔ 5 እስከ ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ/ም ለ15 ቀናት በሁሉም ክ/ከተሞች ኦፕሬሽን ማካሄዱን አሳውቋል።

በርካታ የወንጀል ተጠርጣሪዎችንና ኤግዚቢቶችን በቁጥጥር ስር እንዳዋለም ገልጿል።

በተደረገው ኦፕሬሽን ፦
➡️ ከዚህ ቀደም የተሰረቁ 8 የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ማስመለሱን ፤
➡️ ለወንጀል ፈፃሚዎቹ ሀሰተኛ የተሽከርካሪ ሰሌዳ በተለጣፊ እስቲከር ሲያዘጋጁ የነበሩ ግለሰቦች ሀሰተኛ ሰሌዳ ለማዘጋጀት ከሚጠቀሙበት ኮምፒውተር ፣ ላፕቶፕ ፣ ፍላሽ እና ካሜራ ጋር በቁጥጥር ስር እንዳዋለ፤
➡️ የመኪና መያቸውን
➡️ ሞተር ብስክሌት በመጠቀም የቅሚያ ወንጀል የፈፀሙ ተጠርጣሪዎችን ይዞ ከ700 በላይ ሞባይል ስልኮች ማስመለሱን፤
➡️ የተሰረቀ እቃ ከሚገዙ ህገወጦች ላይ 108 ላፕቶፕ ߹6 ኮምፒዩተር ߹11 ካሜራዎች ߹ 2 ቴሌቪዥንና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ከሸሸጉበት ቦታ መያዙን
➡️ 2 ክላሽ ከመሰል 120 ጥይቶች ጋር፣ 67 ልዩ ልዩ ሽጉጦች ከ568 መሰል ጥይት ጋር እንዲሁም 2 ኋላ ቀር መሳሪያ ከእነ ተጠርጣሪዎቹ በኦፕሬሽኑ መያዙን አመልክቷል።

ከዚህ በተጨማሪ ኮንትሮባንድ ፣ ሀሰተኛና ሰነዶችን እና መድኃኒቶች በኦፕሬሽኑ መገኘታቸውን ገልጿል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው 24 ኮንደሚኒዬም ውስጥ መድሃኒት የማከፋፈልም ሆነ የመሸጥ ፍቃድ የሌላቸውና በህገ-ወጥ መንገድ መድሃኒት እያዘጋጁ ሲያከፋፍሉ የተገኙ ግለሰቦች ተዘዋል፡፡

ግለሰቦቹ ያዘጋጇቸውና ለገበያ ሊያቀርቧቸው የነበሩ ፦
° 169 ብልቃጥ መድሃኒቶች ፣
° 40 ግሉኮስ ፣
° በርካታ የመድሃኒት ብልቃጦች እና ህገ-ወጥ ስራቸውን ለመስራት የሚገለገሉበት አንድ ማሽንን ጨምሮ ፕሪንተር እና ላፕቶፕ በኤግዚቢትነት መያዙን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ " ሰልባጅ ተራ / አሸዋ " ከጥዋት አንስቶ እስካሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ያልተቻለ ከባድ የእሳት አደጋ ደርሷል።

አደጋው ጥዋት 1:45 የተነሳ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ለመቆጣጠር ማስቸገሩን ድሬ ቲቪ የሶማልኛ ቋንቋ ክፍል ዘግቧል።

በቃጠሎ እስካሁን በሰዎች ሕይወት ላይ የደረሰ የሞት አደጋ ባይኖርም ከፍተኛ የንብረት ውድመት መድረሱ ግን ተጠቁሟል።

አሁንም እሳቱን የመቆጣጠር ሥራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

#DireDawa
#DireTVSOMALI

Via @tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ  ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12:00 በፌዴራል ፖሊስ " #ለጥያቄ_ይፈለጋሉ " በሚል ከቤታቸው ተወስደው መታሠራቸውን ቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግቧል። ቀደም ብሎ ፥ የሰንበት ት/ ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን…
#Update

መሪጌታ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ከእስር ተፈቱ።

የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ  መሪጌታ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ከእስር መለቀቃቸውን የማሕበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ነበር ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ለእስር የተዳረጉት።

ከሁለት ወራት በኋላ ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2016  ዓ.ም  ከእስር  መለቀቃቸውን  ከቤተሰቦቻቸው ማረጋገጥ ተችሏል።

#MahibereKidusanTV

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#BiniyamGirmay🇪🇷

ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ቢንያም ግርማይ በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ ስፍራ የሚሰጠውን ቱር ደ ፍራንስ የተሰኘውን የፈረንሳዩን የብስክሌት ውድድር ‘ስቴጅ 3’ በማሸነፍ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ በመሆን ለኤርትራ እና ለአፍሪካ ታሪክ ሰርቷል።

ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ የውድድሩ ተሳታፊዎች ወደ ቢኒያም በመሄድ " እንኳን ደስ አለህ ! አንተ በጣም ምርጡ ነበርክ ፤ በጣምም ጠንካራ ነህ፤ ለአፍሪካ እና ለዓለም ታሪክ ሰርተሃል ፤ እንኮራብሃለን " ሲሉ አወድሰውታል።

ቢኒያም ፤ " ሁሉንም ጥንካሬ እና ድጋፍ ስለሰጠኝ ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪ ይመስገን " ሲል ተናግሯል።

ኤርትራዊው ቢኒያም በተለያዩ ጊዜያት ባስመዘገበው ስኬት " የአፍሪካ የብስክሌት ንጉሥ " የሚል ስም ተሰጥቶታል።

ኤርትራውያን በተለይ በብስክሌት ግልቢያ በዓለም መድረክ በእጅጉ ይታወቃሉ።

#Eritrea
#NBC_Sport
#BBC
@tikvahethiopia
2024/11/18 15:28:14
Back to Top
HTML Embed Code: