#ማያ ምርጥ ሀገርኛ የቪዲዮ ስትሪሚንግ!!!
📺#ማያ ያሻዎትን የቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ፕሮግራሞች እንዲሁም የልጆች ፕሮግራሞችን ጨምሮ በርካታ የመዝናኛ እና የመረጃ አማራጮችን ይዞ ቀርቧል፡፡
📻 አገልግሎቱን በማያ መተግበሪያ https://onelink.to/7bv4u9 ወይም ወደ 863 Ok ብለው በመላክ ይመዝገቡ! በቀን 5 ብር ብቻ!
📦ዘወትር ማያን ብቻ የሚያስጠቅም #ነጻ 2 ጊ.ባ ዕለታዊ የዳታ ጥቅል ይበረከትልዎታል!
ለማንኛውም ጥያቄ፣ አስተያየት ወይም ቅሬታዎ በ https://www.tg-me.com/EthiotelecomChatBot ያግኙን!
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #SmartAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

#Somaliland
" የአስገድዶ መድፈር ጉዳዮችን በባህላዊ መንገድ የመፍታት ዘዴ በአስገድዶ መድፈር ሰለባዎች ላይ ኢ-ፍትሃዊነትን ያሰፍናል " - ፕሬዜዳንቱ
የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሳ ቢሂ አብዲ፥ ማንኛውም የአስገድዶ መድፈር ጉዳይ በፍርድ ቤት እንዲታይ እና የፍትሕ ተቋማት እንዲከታተሉ ማዘዛቸው ተሰምቷል።
ፕሬዜዳንቱ ከካቢኔያቸው አባላት ጋር ምክክር ካደረጉ በኋላ የአስገድዶ መድፈር ጉዳዮችን የፍትህ አካላት እንዲከታተሉት / በፍርድ ቤት ብቻ እንዲዳኝ አዘዋል።
" አስገድዶ ደፋሪዎች ወደ ህግ ፊት መቅረብና በፍርድ ቤት መዳኘታቸው አስፈላጊ ነው " ብለዋል።
የፖሊስ ኮሚሽነር እና የጠቅላይ አቃቤ ህግ የአስገድዶ መድፈር ክስ ወደ ፍርድ ቤት መቅረቡን እንዲያረጋግጡ አሳስበዋል።
የአስገድዶ መድፈር ጉዳዮችን በባህላዊ በሆነ መንገድ የመፍታት ዘዴ በአስገድዶ መድፈር ሰለባዎች ላይ " ኢ-ፍትሃዊነትን የሚያሰፍን ነው " ብለዋል።
የፕሬዚዳንቱ ትዕዛዝ የጎሳ መሪዎች የአስገድዶ መድፈር ጉዳዮች ላይ ጣልቃ መግባትን የሚከለክል እንደሆነ ተጠቁሟል።
ይህን ትዕዛዝ ለማስተላለፍ የተገደዱት በሶማሌላንድ ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች መበራከታቸውን ተከትሎ ነው።
@tikvahethiopia

#Amhara
" እስኪበቃን ተገዳድለናል ፤ እስኪበቃን ተዋጋን አሁን ይብቃን !! መፍትሔው ንግግር ነው፣ መነጋገር ነው፣ መከባበር ነው " - አቶ አገኘሁ ተሻገር
በአማራ ክልል ያለው የትጥቅ ግጭት በውይይት እና በድርድር እንዲቋጭ መንግስት በድጋሚ ጥሪ አቀረበ።
ጥሪውን ያቀረበው በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው የሰላም ኮንፈረንስ ነው።
የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ምን አሉ ?
" ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ መሄድ ቅንጦት ሆኗል፣ ከአዲስ አበባ ባሕር ዳር መምጣት ቅንጦት ሆኗል ያላቸው በአውሮፕላን ነው የሚሄዱ፣ የእኔና የእናንተ ቤተሰቦች በአውሮፕላን መሄድ አይችሉም።
ተማሪዎች ትምህርታቸውን መማር አልቻሉም ፣ በርካታ ተማሪዎች ለክልላዊ እና ለአገራዊ ፈተናዎች መቀመጥ አልቻሉም ፣ እየተማሩ ያሉ ተማሪዎች ተገቢ የሆነ ውጤት ለማምጣት እየተቸገሩ ነው፣ በርካታ ተማሪዎችም ትምህርታቸውን እያቋረጡ ነው።
መንግስት የልማት ስራዎችን መስራት አልቻልም።
በኢኮኖሚውም ዘርፍ የአማራ ክልል 35 ከመቶ እና ከዚያ በላይ የሚሆነውን የአገሪቱን የሰብል ምርት የሚሸፍን ሆኖ ሳለ ፣ ዛሬ ማምረት እንኳ አልቻለም ፣ ማዳበሪያ ማሰራጨት አልቻለም ፣ ምርጥ ዘር ማሰራጨት አልቻልም ፣ የአበዳሪ ተቋማት ብድር መሰብሰብ አልቻሉም ፣ ባንኮች አገልግሎት መስጠት አልቻሉም ፣ ነጋዴው ሰርቶ ፣ ነግዶ ራሱን ማሻሻል አልቻለም፡፡
ህዝባችን የከፋ ችግር ውስጥ ነው ያለው አይናገርም ቢናገር ችግር ይደርስበታል።
መገዳደሉና ፣ በጠላትነት መፈላለጉ ከበቂ በላይ ነው። ይሄን መገዳደል ካላስቆምን በስተቀር ክልላችን ወደፊት መራመድ / ፈቀቅ እንኳን ማለት አይችልም።
በቃ !! እስኪበቃን ተገዳድለናል፣ እስኪበቃን ተዋጋን ስለዚህ አሁን ይብቃን፣ መፍትሔው ንግግር ነው፣ መነጋገር ነው፣ መከባበር ነው።
ሌለው አካል ብቻ ችግር ያለበት አድርጌ እኔ እራሴን ከችግር እያወጣው አይደለም፣ እኔ ችግር የለብኝም እያልሁም አይደለም፣ እኔም ሁላችንም የችግሩ አካል ነን፣ ስለዚህ ይብቃን፣ ህዝባችን ከችግር እናውጣው።
አሁንም መንግስታችን እና ፓርቲያችን የሰላም ጥሪ ያቀርባል፣ ለመነጋገር ፣ ለመወያየት ለመደራደር ፣ ለመመካከር የክልሉም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ዝግጁ ነው። "
#Ethiopia
#AmharaRegion

TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የሀገሪቱን ፓርላማ በኃይል ጥሰው የገቡት መንግሥት ያረቀቀውን የፋይናንስ ሕግ የሚቃወሙ የኬንያ ወጣቶች በፓርላማው ካፍቴሪያ ምግብ ሲበሉ ታይተዋል። ወጣቶቹ ዛሬ ጨምሮ ላለፉት ተከታታይ ቀናት " ታክስ ለመጨምር ያሰበው ረቂቅ ሕግ ኖሮ ያከብድብናል ፤ ተውት ይቅር ! አንደግፈውም " በማለት እየተቃወሙ ይገኛሉ። በዛሬው ተቃውሞ የጸጥታ ኃይሎች በተኮሱት ጥይት የሰው ህይወት የጠፋ ሲሆን ወጣቶቹ ግን…
#Kenya
የኬንያ መከላከያ ሰራዊት ሰላምና የህግ ስርዓትን እንዲያስከብር ትዕዛዝ ተሰጠው።
የሀገሪቱ መንግሥት ለቀናት ከዘለቀው የፋይናንስ ህግ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የኬንያ መከላከያ ሰራዊት የህዝቡን ደህንነት፣ ሰላምና የህግ ስርዓት እንዲያስከብር አሰማርቷል።
በሌላ በኩል ፤ የኬንያው ፕሬዜዳንት መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በመግለጫቸው የዛሬውን ታቃውሞ ፤" እንደ ሀገር ክህደት / ከሃዲነት " የሚቆጠር እንደሆነ ገልጸው ፤ የጸጥታ ኃይሎች የኬንያውያንን ደህንነት እንዲያስጠብቁ መመሪያ እንደሰጡ ተናግረዋል።
ተቃዋሚዎች የኬንያ ፓርላማን ሰብረው ስለገቡበት ክስተት ጉዳይም ምርመራ እንደሚደረግ አመልክተዋል።
የወንጀል ድርጊትና ወንጀለኞችን ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው የተቃውሞ ሰልፍ ከሚያደርጉት መለየት ይገባል ብለዋል።
ፕ/ት ሩቶ " አደገኛ ወንጀለኞች " ሲሉ የጠሯቸው አካላት ሊፈጸሙት የሚችልን ማንኛውም ሙከራ ከንቱ ሆኖ እንዲቀር የደህንነት አካላት እርምጃ እንዲወስዱ እንዳዘዙ ገልጸዋል።
ህዝቡንም " ዛሬ ማታ ተኙ ! የናተ፣ የቤተሰቦቻችሁ እና የንብረቶቻችሁ ደህንነት ከምንም በላይ ቅድሚያ ሰጥተን እንጠብቃለን " ብለዋል።
" የተቃውሞው የፋይናስ ምንጮች ላይም ምርመራ ይደረጋል " ሲሉ አክለዋል።
በኬንያ ዛሬ ማክሰኞ በነበረው ተቃውሞ እስካሁን በታወቀው ብቻ 10 ሰዎች ከጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል።
#Kenya
#FinanceBill2024

#eQUB_APP
በ20ሺህ ብር ብቻ ዕቁብ ገብታችሁ የቤት ዕቃዎችን የምታሟሉበት መተግበሪያ - eQUB APP! የሄ እድል እንዳያመልጥዎ!
Download the App Here👇
📱 Android - Google Play | 📱 iPhone - App Store
Telegram Channel: @equbapp
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 0116671717 ወይም 0116670404 ይደውሉ።

#ዳሽን_ከፍታ: በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው "ዳሽን ከፍታ" የሥራ ፈጠራ ውድድር ሶስተኛ ምዕራፍ ሊጀመር ነው፡፡
በዳሸን ከፍታ የመጀመሪያውና ሁለተኛው ዙር የስራ ፈጠራ ውድድሮች ተሳትፈው አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ሸልማትና የፋይናስ ድጋፍ አግኝተው በተለያዩ የስራ ዘርፎች ስኬታማ እየሆኑ ነው፡፡ ለሌሎችም የስራ ዕድል መፍጠር ችለዋል፡፡
በዚህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ ነዎት?
ዳሽን ከፍታ የሥራ ፈጠራ ውድድር በምዕራፍ ሶስት የቅድመ ውድድር ጅማሬ ስልጠና ለመስጠት በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ይንቀሳቀሳል!
የስልጠና ቦታዎች ፡ አዲስ አበባ ፣ ባህርዳር ፣ አዳማ ፣ መቀሌ ፣ ድሬዳዋ ፣ ሀዋሳ ፣ ወላይታ ፣ ጅማ እና ደሴ
ምዝገባ እስከ #ሰኔ_22/2016 ዓ.ም. ድረስ በሁሉም የዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች የሚካሄድ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ ወደ 6333 ይደውሉ ወይም የባንኩን የማህበራዊ ትስስር ገጾች ይጎብኙ፡፡
ዳሸን ባንክ ሁልጊዜም አንድ እርምጃ ቀዳሚ!

" በየሶሻል ሚዲያ የሚፈጸም ስም ማጥፋት በህግ እንጅ በሶሻል ሚዲያ መልስ መስጠት አያስፈልግም " - የሰላምና ጸጥታ ቢሮ
የሀዋሳ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ፥ ያለ ማስረጃ በየተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የከተማዋን ስም እያጠፉ ያሉ አካላትን ጉዳይ በህግ እየተከታተልኩ ነው አለ።
ይህን ያለው ከሰሞኑን ' ቲክቶክ ' እና ' ዩትዩብ ' ላይ የከተማዋን ሁኔታ የሚገልጽ የወጣቶች ንግግር ከተሰራጨ በኃላ ነው።
ወጣቶቹ ከተማይቱ ለደህንነት የምታሰጋ ፣ እግታም የሚፈጸምባት እንደሆነ በመግለጽ ዜጎች ወደ ሀዋሳ እንዳይሄዱ ጥሪ ሲያቀርቡ ይደመጣል።
ይህንን ተከትሎ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃሉን የሰጠው የሀዋሳ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ፤ " ጉዳዩን በህግ አግባብ እየተከታተልነዉ ነዉ " ብሏል።
" በየሶሻል ሚዲያ የሚፈጸም ስም ማጥፋት በህግ እንጅ በሶሻል ሚዲያ መልስ መስጠት አያስፈልግም " ሲል አመልክቷል።
" በእኛ በኩል እንዲህ ያለን የስም ማጥፋት አይተን ባናልፈውም ነዋሪው እና ሀዋሳን የጎበኙ እንግዶች ራሳቸዉ ምን አይነት አስተማማኝ ደህንነት እንዳለ ምላሽ ቢሰጡበት የተሻለ ነዉ " ሲል አክሏል።
ቢሮው ፥ " አሁን ላይ በኢትዮጵያ ካሉ ከተሞች ሀያ አራት ሰአት ሰዉ በነጻነት መንቀሳቀስ የሚችልባት ከተማ ሀዋሳ መሆኗን ላረጋግጥላችሁ እዉዳለሁ " ብሏል።
በጉዳዩ ላይ አስተያየታችንን መስጠት እንፈልጋለን ያሉ ወጣቶች ደግሞ ተጎዳው የሚል ማንኛውም ዜጋ በማስረጃ ለፍትህ አካል ማመልከት ይቻላል ብለዋል።
" እኛ እስከምናውቀው ድረስ ከተማይቱ የምታስፈራ ከተማ አይደለችንም ፤ ሀገሪቱ ውስጥ ካሉ ከተሞች ደህንነት ያለባት ናት ፤ በዚህ ደረጃ ስም ማጥፋት እና መግለጽ ፍጹም ያልተገባ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
#TikvahEthiopiaHawassa

#Update “ ከታገቱ ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም ሰባት ወራት ይሆናቸዋል። እንደቀላል ነገር በወጡበት ቀሩ ” - የታጋች ባለቤት ከ6 ወራት በፊት ወደ ባቱ (ዝዋይ) ለስራ ጉዳይ እየተጓዙ በታጣቂዎች ታገቱ ከተባሉ 6 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች መካከል 3ቱ ቢለቀቁም 3ቱ ግን እንዳልተለቀቁ ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም የሚችለውን ሁሉ…
#Update
“ በታጣቂዎች ከታገቱ 9 ወራት አለፉ፤ ያሉበትን እንኳ አናውቅም። ወደ ማን እንጩህ ? ”- የታጋች ባለቤት
መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም በታጣቂዎች ታግተው የተወሰዱ 3 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች ደብዛቸው እንደጠፋ መሆኑን የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
ወደባቱ ለስራ እየተጓዙ በነበረበት ወቅት በታጣቂዎቸ ታገቱ የተባሉት ሠራተኞቹ ያልተለቀቁት አጋቾቹ ገንዘብ ጠይቀው ከ2.8 ሚሊዮን ብር ከተላከ በኋላ እንደሆነ የታጋች ቤተሰቦች ከዚህ ቀደምም ገልጸው ነበር።
አሁንስ ምን አዲስ ነገር አለ ?
- አቶ ልዑል አስፋወሰን
- አቶ ሰይፉ እንዳለ
- አቶ አብዩ ደገፋው የተባሉ ሠራተኞች በህይወት ይኑሩ አይኑሩ አይታወቅም።
ትላንት ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ 2 የታጋች ቤተሰቦች ስለ 3ቱም ታጋቾች ምንም የሰሙት ፍንጭ እንኳ እንደሌለ ገልጸዋል።
አንዷ የታጋች ባለቤት “ በታጣቂዎች ከታገቱ 9 ወራት አለፉ ፤ ያሉበትን እንኳ አናውቅም። ወደ ማን እንጩህ ? ” ሲሉ ሀዘን ያጀበው ጥያቄ አንስተዋል።
የሰው ልጅ ለ9 ወራት ያህል ያለበት እንኳን አለማወቅ ከባድ ሀዘን መሆኑን ፤ ኤሌክትሪክ ኃይልን በቅርቡ ቢጠይቁም ካቅሙ በላይ እንደሆነበት መግለጹን ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን እየተሰራ እንደሆነ ጥያቄ ያቀረበለት የኤሌክትሪክ ኃይል ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት መግለጹ ይታወቃል።
#TikvahEthiopaFamilyAA

#Reminder 🔔
የአከራይ ተከራይ ውል ስምምነት ምዝገባ ሊጠናቀቅ 11 ቀናት ቀርቶታል።
አከራይ እና ተከራዮች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም አስፈላጊ ሰነዶችን በመያዝ ምዝገባውን እንዲያከናውኑ ጥሪ ቀርቧል።
ከሰኔ 30 በኃላ የሚደረግ ማንኛውም ምዝገባ ቅጣት እንደሚኖረው ተገልጿል።

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" ' ሞባይል ስልክ ጠፍቶብኛል ' የሚል ግለሰብ ማስረጃ በማቅረብ ስልኩን መውሰድ ይችላል " - ፖሊስ
በአዲስ አበባ በሞተር ሳይክል እየተንቀሳቀሱ ከግለሰቦች ሞባይል በመንጠቅ ሱቅ ውስጥ ሲያከመቹ የነበሩ 4 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።
አቶ ሱራፌል ቢያብል የተባሉ የግል ተበዳይ በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ዋና ስራ አስፈፀሚ ሲሆኑ ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በክፍለ ከተማው ልዩ ቦታው ኢምፔሪያል አካባቢ እየተሰራ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራዎችን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ እያደረጉ ነበር።
በወቅት 2 ተጠርጣሪዎች በጥቁር ሞተር ሳይክል ኮድ 2 A19216 ደ.ሕ (ደቡብ ህዝብ) በሆነ 1ኛ ተጠርጣሪ እያሽከረከረ ፣ 2ኛ ተጠርጣሪ ሞተር ሳይክል ላይ ከኋላ በመሆን ከግለሰቡ ሞባይል ስልክ ነጥቀው በፍጥነት እያሽከረከሩ ከአካባቢው ይሰወራሉ።
የግል ተበዳይ ወንጀሉ እንደተፈፀመባቸው በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለገርጂ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ያመለክታሉ።
ፖሊስም የግል ተበዳዩን አቤቱታ በመቀበል ባደረገው ክትትል ከሁለቱ ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ከሌቦቹ የሚረከቡ 2 ተጠርጣሪዎች በድምሩ 4 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።
ህግን ተከትሎ ባደረገው ብርበራ ተጠርጣሪዎቹ ተከራይተው የሞባይል ጥገና የሚሰሩበት ሱቅ ውስጥ በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ ግለሰቦች ተቀምተው የተከማቹ 32 ስማርት ሞባይል ስልኮችን በኤግዚቢት ተይዘዋል።
" ሞባይል ስልክ ጠፍቶብኛል " የሚል ማንኛውም ግለሰብ በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያያ በአካል በመቅረብና ትክክለኛ ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መውሰድ እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
#AddisAbabaPolice

Photo
#Kenya
የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ የቀሰቀሰው የፋይናንስ ረቂቅ ሕግን እንደሚያስቀሩት / እንደማይፈርሙበት አስታውቀዋል።
ሩቶ እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሱት ተቃውሞውን ተከትሎ ቢያንስ 20 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነው።
ፕሬዜዳንቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፤ " ኬንያውያን በሕጉ ዙሪያ ያሰሙትን ተቃውሞ በደንብ ተከታትያለሁ፤ ስለዚህም ሕጉን እንደማይፈልጉት በግልጽ ተናግረዋል፤ ይህንንም ተቀብዬ በሕጉ ላይ አልፈርምም፣ ስለዚህም ቀሪ ይሆናል። ሕዝቡ ፍላጎቱን አሳውቋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ሕዝቡ ረቂቅ ሕጉን እንደማይፈልገው ገልጿል ያሉት ሩቶ " እኔም በዚህ ተስማምቻለሁ " በማለት ነው በሕጉ ላይ ፊርማቸውን እንደማያኖሩ በይፋ ያሳወቁት።
ከሰሞኑን በኬንያ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲካሄድ ነበር። ትላንትም ተቃዋሚዎች የሀገሪቱን ፓርላማ ጥሰው በመግባት ቁጣቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። #BBC

#ያንብቡ
የገንዘብ ሚኒስቴር በቁርጥ በተጣለ የኤክሳይዝ ታክስ ማስከፈያ ምጣኔ ላይ ማስተካከያ የተደረገበት መመሪያ አውጥቷል።
መመሪያው " በቁርጥ በተጣለ የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ላይ ማስተካከያ ለማድረግ የወጣ መመሪያ ቁጥር 1007/2016 " ይሰኛል።
አዲሱ የተስተካከለ መመሪያ ከከዚህ ቀደሙ ጭምሪ የተደረገበት ነው።
የአልኮል መጠጦች እና የፕላስቲክ ከረጢት(ፌስታል) ኤክሳይዝ ታክስ መጣኔ፦
➡️ ከብቅል የተዘጋጀ ቢራ - የተስተካከለው የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ 40% ወይም 28 ብር በሊትር ከሁለቱ አንዱ የበለጠውን
➡️ ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ተመርቶ በበቀለ ገብስ የተመረተ ቢራ - የተስተካከለው 35% ወይም 23 ብር በሊት ከሁለቱ አንዱ የበለጠውን
➡️ ውሃን ሳይጨምር ቢያንስ ከክብደቱ 75% የሚያህለው በአገር ውስጥ ግብዓት የተመረተ ቢራ - የተስተካከለው የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ 30% ወይም 21 ብር በሊትር ከሁለቱ አንዱ የበለጠውን
➡️ የሚፈሉ መጠጦች (ሲዳር፣ ፔሪ፣ ኦፓክ ቢራ፤ የሩዝ አልኮል መጠጥ)፣ የሚፈሉ መጠጦችና የአልኮል አልባ መጠጦች ድብልቅ፣ ስታውት፤ ሌሎች ከቢራ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ መጠጦች፣ ዱቄት ቢራ፣ የአልኮል ይዘታቸው ከ7% ያልበለጠ - የተስተካከለው 40% ወይም 28 ብር በሊትር ከሁለቱ አንዱ የበለጠውን
➡️ በድብልቅ የተዘጋጁ፣ የአልኮል ይዞታቸው ከ7% ያልበለጠ ጥንካሬ ያላቸው መጠጦች - የተስተካከለው 40% ወይም 28 ብር በሊትር ከሁለቱ አንዱ የበለጠውን
➡️ የፕላስቲክ ከረጢት(ፌስታል) - የተስተካከለው 103 ብር በኪሎግራም
ትምባሆና የትምባሆ ውጤቶች የኤክሳይዝ ታክስ መጣኔ ፦
🔵 ትምባሆ የያዙ ሲጋሮች፤ ቼሩትስና ሲጋሪሎስ - የተስተካከለው 30% + 644 ብር በኪሎግራም
🔵 ትምባሆ የያዙ ሲጋራዎች - የተስተካከለው 30% + 20 ብር በፓኬት (20 ፍሬ)
🔵 እንደ ትምባሆ ከሚያገለግሉ የተዘጋጁ ሲጋሮች፣ ቼሩትስና ሲጋሪሎስ እና ሲጋራዎች - የተስተካከለ 30%+20ብር በፓኬት ( 20 ፍሬ)
🔵 የሚጨስ ትምባሆ፣ በማናቸውም ምጣኔ እንደ ትምባሆ የሚያገለግሉ ነገሮችን የያዘ ቢሆንም (የፍራፍሬ ጣዕም እንዲኖራቸው የተደረጉም ያልተደረጉም የትምባሆና ግላይሰሮል ቅልቅል የያዘ ትምባሆ ለማጨስ የሚያገለግል በውሃ ማስተላለፊያ ቱቦ የሚጨስ መዓዛ ሰጭ ዘይት እና ምዝሞዙች ፣ ሞላሰስ ወይም ስኳር ከተጨመረባቸውም ካልተጨመረባቸው በስተቀር) - የተስተካከለው 30% + 644ብር ኪሎግራም
🔵 " የተዋሐደ " ወይም " እንደገና የተዘጋጀ " ትምባሆ - የተስተካከለ 30%+644 ብር በኪሎግራም
🔵 ሱረት፤ የትምባሆ ምዝምዞችና ኤስንሶች - የተስተካከለ 30%+644ብር በኪሎግራም
መረጃው የተላከው ከገንዘብ ሚኒስቴር ነው።
#TikvahEthiopia