Telegram Web Link
#IMF #Ethiopia

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ሠራተኞች ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የተራዘመ የብድር አቅርቦትን በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ።

አይኤምኤፍ ባወጣው መግለጫ፣ ድርጅቱ በአራት ዓመታት የሚያቀርበው የ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ የብድር አቅርቦትን (Extended Credit Facility) በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ላይ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ተደርሷል።

ስምምነቱ በይፋ በዓለም አቀፉ ገንዘብ ተቋም ዋና የአመራር ቦርድ ከታየ በኋላ ኢትዮጵያ ወደ 345 ሚሊዮን ዶላር ገደማ እንደምታገኝ ተገልጿል።

" በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመንን ጨምሮ ኢትዮጵያ አገር በቀል የምጣኔ ሃብት ፖሊሲ ማሻሻያ ማድረጓ በጥሩ ሁኔታ ውጤት እያሳየ ነው " ብሏል ተቋሙ በመግለጫው።

በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመን መተግበሩ በትይዩና በይፋዊ ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት በስፋት እያጠበበ እንደሆነ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ያለፈው ዓመት ሐምሌ ላይ በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመንን ለመተግበር ውሳኔ አሳልፎ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ የመጣው በአልቬሮ ፒሪስ የተመራው የልዑካን ቡድን ሲሆን ከተደረሰው የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በኃላ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አልቬሮ ፒሪስ ምን አሉ ?

የአይኤምኤፍ ሠራተኞችና የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣኖች ስምምነት በተቋሙ ዋና የአመራር ቦርድ በቀጣይ ሳምንታት የሚታይ ይሆናል።

ቦርዱ ከተመለከተው በኋላ ኢትዮጵያ በመጀመሪያ 345 ሚሊዮን ዶላር ታገኛለች።

የኢትዮጵያ የምጣኔ ሃብት ማሻሻያ በተለይም በገበያ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመን መተግበሩ በትይዩና በይፋዊ ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት በስፋት እያጠበበ ነው።

ለውጡ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት መጠንን በመጨመር ለአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ነው።

ወደፊት የአገር በቀል ምጣኔ ሃብት ፖለሲ ለውጡ የማክሮኢኮኖሚ መረጋጋትና የምጣኔ ሃብት እድገት ያመጣል።

የፖሊሲ ማሻሻያው በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለውን የፋይናንስ ሥርዓት በመለወጥ የዋጋ ንረትን ያረጋጋል ምጣኔ ሃብታዊ እንዲሁም ማኅበራዊ ጠቀሜታ አለው።

ገቢ መጨመርና በመንግሥት ይዞታ ሥር ያሉ ተቋማትን ለማጠናከር የሚደረጉ የፋይናንስ ዘርፍ ለውጦች መንግሥት የሚያወጣውን ወጭ ቅደም ተከተል ለማስተካከልና ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ይረዳሉ።

የዓለም የገንዘብ ተቋምን የምጣኔ ሃብት ፕሮግራም በስኬታማነት በማስተግበር ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ሊመሰገኑ ይገባል።

በአልቬሮ ፒሪስ እና ቡድናቸው ንግግር ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምሕረቱ፣ ከገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ እና ከገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ጋር ነው።

መረጃውን IMFን ዋቢ በማረግ ያጋራው ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
ንጉስ ማልት- የጣዕም ልኬት፤የደስታ ስሜት!

ደስ ደስ በንጉስ!  

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ https://www.tg-me.com/Negus_Malt

#ከአልኮልነፃ #ደስደስበንጉስ #የጣዕምልኬት_የደስታስሜት #ንጉስማልት
#MPESASafaricom

መስቀልን የት ነን ፤ቀጣዩን የሃገር ዉስጥ ጉዞ ከ M-PESA ጋር በማድረግ 5% ተመላሽ ከእጃችን አስገብተን ፤ ሽው በሰማይ !

የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቻናላችንን እዚህ እንቀላቀል 👉https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC
ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!
 
#FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት🚨 የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን " አርቲሜተር " የተባለውን በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል፡፡ መ/ቤቱ ተደርጓል ባለው የገበያ ቅኝት መድኃኒቱ መገኘቱን ፣ በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ እንዲሁም ናሙናው ተወስዶ በላብራቶሪ ሲፈተሽ አርቲሜተር (Artemether) የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ አለመገኘቱ መረጋገጡን ገልጿል፡፡ በዚህም ይህን መድኃኒት…
#እንድታውቁት🚨

የትኛው የወባ መድኃኒት ነው አትጠቀሙት የተባለው ?

አርቲሜተር የተባለ በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት /Arthemeter 80 mg/ml injection, Batch No. 231104SPF, manufacture Date; 11/2023 supplied by Shinepharm, China በተደረገ የገበያ ላይ ቅኝት የተገኘ እና በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ እንዲሁም ከገበያም ናሙና ተወስዶ በላብራቶሪ ሲፈተሸ Arthemeter የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ አለመገኘቱ መረጋገጡን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳውቋል።

ይህን መድኃኒት ነው የጤና ባለሙያዎች እንዳይጠቀሙት በተጨማሪም በየደረጃው ያሉ የክልል ተቆጣጣሪዎች በየአካባቢያቸው ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃዎች እንዲወስዱ ማሳሰቢያ የተላለፈው።

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ

“ የኢትዮ ቴሌኮም ነጻ ዳታ ሽልማት ለሁሉም አሮጌ ሲም ካርድ ተጠቃሚዎች ” በሚል ሰሞኑን ነጻ ሜጋ ባይት ለማግኘት “ ሊንክ ጠቅ ያድርጉ ” የሚል መልዕክት በማኅበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት ወደተለያዩ ግለሰቦች እየተላከና እየተዘዋወረ ነው፡፡

ይሄው ከሥሩ ሊንክ የተቀመጠበት የሚዘዋወረው መልዕክት ፡-
➡️ 6 ወር ለቆየ ሲም፣ 10GB
➡️ 1 ዓመትና ከዚያ በላይ፣ 20GB
➡️ ከ5 አመት በላይ ለቆየ ሲም፣ 50GB ነጻ ሽልማት ኢትዮ ቴሌኮም እየሰጠ መሆኑን የሚገልጽ ነው፡፡

አንዳንድ ሊንኩን የከፈቱ ሰዎችም፣ “ ስንከፍተው መረጃዎት እየተበረበረ ነው ይላል፡፡ ጉድ ተሰርተናል ” ሲሉ የተስተዋሉ ሲሆን፣ ብዙዎች ደግሞ ይህን ጉዳይ ኢትዮ ቴሌኮም ያውቀዋል ? በማለት እየጠየቁ ነው፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የሚዘዋወረውን መልዕክት ተቋሙ ያውቀዋል? ትክክለኛስ ነው? ሲል ኢትዮ ቴሌኮምን ጠይቋል፡፡

የተቋሙ ቺፍ ኮሚዩኒኬሽን ኢፊሰር አቶ መሳይ ውብሸት ምን ምላሽ ሰጡ ?

“ የኛ ቲምም ቼክ አድርጎታል፡፡ Phishing የሚሉት የማጭበርበር መልዕክቶችን የሚልኩ ናቸው፡፡

ታማኝ ከሆኑ ካምፓኒዎች የሚላኩ መልዕክቶችን በማስመስልና የሰዎችን መረጃ የሚወስዱ Phishing  ብለን የምንጠራቸው የሳይበር ጥቃት መንገዶች ናቸው፡፡

እኛ ያስቀመጥነውም እንሰጣለን ያልነው ሽልማትም የለም፡፡ የላክነውም መልዕክት የለም፡፡ የኛ የሴኩሪቲ ቲምም እየተከታተለ ነው፡፡

ሊንክ ልከው እርሱን ንኩ ነው ‘ንኩ’ የሚሉት የእድሉ ተጠቃሚ ለመሆን፡፡ ግን ፐርሰናል መረጃዎችን የመውሰድና ላልተገባ ነገር ሰዎችን ለመዳረግ የሚያደርጉት ጥረት ነው፡፡

ዌብሳይቶቹን የኛ ቲሞች ሞኒተር እያደረጉ ሰዎች ላይ ጥቃት እንዳይደርስ ቁጥጥር እያደረጉ ነው፡፡

ሳይቶቹን የመዝጋት ሥራዎች እየተሰሩ ነው በቅንጅት፡፡ ስህተት እንደሆነ፣ የኛ እንዳልሆነ ሰው እንዲያውቅ እናደርጋለን፡፡

ይኛው መልኩን ቀይሮ የሰውን መረጃ ለመውሰድ ሆነ እንጂ ብዙ ጊዜ በተለይ ቴሌግራም አካባቢ ላይ ተከታይ ለማግኘት በኢትዮ ቴሌኮም፣ በቴሌ ብር እየተከፈቱ ደንበኛ ለማብዛት የሚደረጉ ጥረቶች አሉ፡፡

ይሄም ኢንቴንሽኑ ሌላ ቢሆንም ያው ነው፡፡ ከእኛም ብቻ አይደለም ምንጩን ስናጣራው ከሌላ አገር ውስጥ የሚመጣ፣ ወደ ሌላ አገር ሪፈር የሚያደርግ ነው ሊንኩ፡፡

የትልልቅ ተቋማት መልዕክት በማስመስል ሊንኮችን አስቀምጠው አጓጊ ሽልማቶችን እየሰጡ የሰዎችን መረጃ የማጭበበርበር ነገር ነው የሚፈጠረውና Phishing በተለያዬ በኢሜይል፣ በቴክስት፣ በጥሪ መልክም ሊመጣ ይችላል፡፡

ሰዎች ሊንኩን ባለመንካት ከእንደዚህ አይነት አሳሳች መልዕክቶች ራሳቸውን ይጠብቁ፡፡ እንዲህ አይነት ጉዳይ ሲገጥማቸውም በ9090 በነጻ ደውለው በዚያ እንዲያሳውቁንም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ”
ብለዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) በበኩሉ፣  “ የኢትዮ ቴሌኮም ነጻ ዳታ ስልማት ለሁሉም አሮጌ ሲም ካርድ ተጠቃሚዎች ” በሚል መልዕክቶች ወደ ተለያዩ ግለሰቦች እየተላኩ መሆኑን እንዳረጋገጠ አስታውቋል፡፡

አስተዳደሩ፣ “ መልዕክቱ የግለሰቦችን ሚስጥራዊ መረጃዎችን የማጥመድ ጥቃት (Phishing Attack) መሆኑን ማረግገጥ ችያለሁ ” ብሎ፣ ግለሰቦች ሊንኩን ባለመክፈት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አረጋዊ ካህኑ ከነባለቤታቸው 4 ቤተሰቦቻቸው ጋር በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል " - የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሞጆ ሉሜ ወረዳ ቤተ ክህነት መ/መ/ቀ/ወልደ ኢየሱስ አያሌው የተባሉ አረጋዊ ካህን ከነባለቤታቸው 4 ቤተሰቦቻቸው ጋር በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተገልጿል። መ/መ/ቀ/ወ/ኢየሱስ…
#EOTC

በአረጋዊው መልአከ/መ/ ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌውና አራት ቤተሰባቸው ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያን በልዩ  ሁኔታ እንደሚከታተለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አሳውቋል። 

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሉሜ (ሞጆ )  ወረዳ ቤተ ክህነት  በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ  ለ41 ዓመታት ያህል ከድቁና እስከ ደብር አስተዳዳሪነት ድረስ በትኅትና ሲያገለግሉ የቆዩት መልአከ /መ/ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌ ከባለቤታቸውና ከሦስት ልጆቻቸው ጋር ባሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ይታወቃል።

ግድያው " ማንነታቸው ለጊዜው አልታወቀም " በተባሉ ኃይሎች መፈጸሙን የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከትን ዋቢ በማድረግ ያመለከተው ጠቅላይ ቤተክህነት ግድያው በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ የተፈጸመ ነው ብሏል።

ጠቅላይ ቤተክህነት በዚህ አሰቃቂ ግድያ ሕይወታቸውን ባጡ የቤተክርስቲያኗ አገልጋዮችና ቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

" ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባህርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የደረሰውን አስደንጋጭ ሀዘን ከሰሙ ጊዜ ጀምሮ ጉዳዩን በልዩ ትኩረት እየተከታተሉት ይገኛሉ " ብሏል።

ዝርዝር ሁኔታውን በሚመለከት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገርና እስከ መጨረሻው ጫፍ በመድረስ ሕጋዊ እልባት  እንዲያገኝ እንደሚደረግ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የዋጋ ጭማሪ የተደረገባቸው አገልግሎቶች ምን ምን ናቸው ?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ጭማሪ አድርጓል።

ተቋሙ በአንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ያደረገው የዋጋ ጭማሪ ከፍ ያለ ነው።

ለአብነት ፦

° የተሽከርካሪ የዋጋ ግምት ማሳወቅ አገልግሎት 500 ብር የነበረው 1,000 ብር ገብቷል።

° የተሽከርካሪ የዋጋ ግምት ለሽያጭ አገልግሎት 2,310 ብር የነበረው 4,000 ብር ገብቷል።

° የተሽከርካሪ የባለቤትነት ስም ዝውውር አገልግሎት 3,000 ብር የነበረው 5,000 ብር ገብቷል።

° ለዓመታዊ ምርመራ ተለጣፊ ምልክት (ቦሎ) ግልባጭ ለመጀመሪያ ጊዜ 1,010 ብር የነበረው 2,500 ብር ተደርጓል።

° የተሽከርካሪ ባለቤት ማረጋገጫ ሊብሬ 300 ብር የነበረው 1200 ብር ተደርጓል።

° ሊብሬ ሲበላሽ ወይም ሲጠፋ ምትክ ፣ የማደሻ ቦታው ሲያልቅ መስጠት 3,000 ብር የነበረው 3,500 ብር ሆኗል።

° መረጃ መስጠት 300 ብር የነበረው 700 ብር ተደርጓል።

° አዲስ መንጃ ፍቃድ መስጠት 680 ብር የነበረው 1500 ብር ተደርጓል።

° ለጠፋ መንጃ ፍቃድ ማፈላለጊያ ለፖሊስ ወይም ለፕሬስ የሚሰጥ መረጃ 100 ብር የነበረው 700 ብር ተደርጓል።

° ከ3 ጊዜ በላይ የፅሁፍ ፈተና ለወደቁ በየወሩ ለመፈተን የሚሰጥ አገልግሎት 100 ብር የነበረው 300 ተደርጓል።

° ከ3 ጊዜ በላይ የተግባር ፈተና ለወደቁ በየወሩ ለመፈተን የሚሰጥ አገልግሎት ከ300 ብር ወደ 600 ብር ጨምሯል።

° የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ እድሳት ከ620 ብር ወደ 1000 ብር ገብቷል።

° ለጠፋ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ምትክ መስጠት 620 ብር የነበረው 5,000 ብር ገብቷል።

(ተጨማሪ በተለያዩ አገልግሎቶች ላይ የተደረገውን የታሪፍ ጭማሪ ዝርዝር ከላይ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
2024/09/29 02:28:59
Back to Top
HTML Embed Code: