Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ የቀሰቀሰው የፋይናንስ ረቂቅ ሕግን እንደሚያስቀሩት / እንደማይፈርሙበት አስታውቀዋል። ሩቶ እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሱት ተቃውሞውን ተከትሎ ቢያንስ 20 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነው። ፕሬዜዳንቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፤ " ኬንያውያን በሕጉ ዙሪያ ያሰሙትን ተቃውሞ በደንብ ተከታትያለሁ፤ ስለዚህም ሕጉን እንደማይፈልጉት በግልጽ ተናግረዋል፤…
" በእስራት የምታቆዩበት ምንም ምክንያት የላችሁም ፤ ልቀቋቸው " - የናይሮቢ ፍርድ ቤት

ትላንት በኬንያ ናይሮቢ ከነበረው የፋይናንስ ረቂቅ ህጉ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ፖሊስ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሎ ነበር።

የታሰሩ ሰዎች 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ናይሮቢ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ፍርድ ቤቱም " ከእስር ልቀቋቸው " ብሏል።

ዛሬ ረቡዕ ፍ/ቤት የቀረቡት 56 ሰዎች ሲሆኑ ፖሊስ " ልመርምራቸው 14 ቀን ይፈቀድልኝ " ሲል ጠይቆ ነበር።

ፍርድ ቤቱ ግን የፖሊስን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

" ሰዎቹን የሚያሳስርና ዋስ የሚያስከለክል አንድም ጠንካራ ምክንያት ስለሌለ ከእስር ልቀቋቸው " ሲል አዟል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ላለፉት ስድስት ቀናት በመላ አገሪቱ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ተጠናቋል።

57 የመንግሥት እና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ማስፈተናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

ከመውጫ ፈተናው ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በተለይ ከተነገርን ይዘት እና ከተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው ቅሬታ ካቀረቡት መካከል፦
- የማኔጅመንት
-የማርኬቲንግ ማኔጅመንት
- የሀይድሮሊክና ውሃ ሃብት
- የቬተርነሪ ሳይንስ
-የኸልዝ ኢንፎርማቲክስ ተማሪዎች ይጠቀሳሉ።

ከዚህም ባለፈ ፥ " የተሰጠን ሰዓት በቂ አልነበረም ፣ፈተና ዘግይቶ የመጀመር፣ ለፈተናው በቂ ሰዓት አለመመደብ ችግር ነበር " የሚል ቅሬታ ያቀረቡም አሉ።

የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ፈተናም በድጋሜ እንዲሰጥ ተደርጓል።

አጠቃላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተላኩለትን ቅሬታዎች ይዞ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራርን አነጋግሯል።

ከፍተኛ አመራሩ ፤ " የዘንድሮው 2016 የመውጫ ፈተና ከ220 በላይ ፕሮግራሞች ያለምንም ችግር Smoothly ነው የተሰጠው " ሲሉ ገልፀዋል፡፡

" ከፈተናዎቹ ጋር የተያያዘም ምንም አይነት Issue አላጋጠመንም " ያሉት ኃላፊው፤ " አንድም ቅሬታ ለትምህርት ሚኒስቴር አልደረሰም " ብለዋል፡፡

ውጤት መቼ ይፋ ይደረጋል በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄ " በቅርብ ቀን ውስጥ ይፋ ይደረጋል " ብለዋል።

Via @tikvahuniversity
" ፍጹም ሀሰተኛ / የውሸት ይዘት ነው ተጠንቀቁ " - የጠ/ሚ ጽ/ቤት

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገውን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) እንደሰረዘው ተደረጎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

የጠ/ሚ ጽ/ቤት ያወጣው መግለጫ አስመስሎ አንድ የተቀነባበረ የጠ/ሚ ጽ/ቤት አርማ ያለበት መግለጫ በስፋት እየተዘዋወረ ይገኛል።

ይኸው መግለጫ ፦

- ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ከተለየችው ' ክልል ' ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ስምምነት (MoU) እንደሰረዘችው ፤
- ኢትዮጵያ ከዩኬ፣ ከG7 እና ከሌሎች ሀገራት ጋር ተወያይታ የሶማሌላንድን ሉዓላዊ ሀገርነት የምትደግፍበት ማስረጃ እንዳላገኘች
- የኢትዮጵያ መንግሥት ከአሁን በኃላ ህጋዊ ያልሆነ ስምምነት ከሶማሌላንድ ጋር እንደማያደርግ
- ኢትዮጵያ ፤ የሶማሌላንድ ጉዳይ የሶማሊያ ስለሆነ ፖለቲካዊ ችግራቸውን በአንድ ሀገር ጥላ ስር እንዲፈቱ እንደምትተው ... የሚገልጽ ነው።

ይህ ግን ፍጹም ሀሰተኛና መግለጫው የተቀነባበረ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ምን አለ ?

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፤ ከሶማሌላንድ ጋር ስለተፈጸመው የመግባቢያ ስምምነት በኦንላይን እየተዘዋወረ እና እየተሰራጨ ያለው መረጃ ፍጹም ሀሰተኛ / የውሸት ይዘት ስለሆነ ህዝቡ እንዲጠነቀቅ መክሯል።

በሀገር ውስጥ ፣ በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች መግለጫም ሆነ መረጃ የሚሰጠው በይፋዊ የጽ/ቤቱ ገጾች / ቻናሎች ላይ ብቻ እንደሆነ አመልክቷል።

ሁሉም ሰው የጽ/ቤቱን ይፋዊ አርማ በመጠቀም ከሚሰራጩ  እንደዚህ አይነት የውሸት መረጀዎች / ይዘቶች እራሱን እንዲጠብቅ አደራ ብሏል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#BOLIVIA

ቦሊቪያ ውስጥ ወታደሮች የሀገሪቱን ፕሬዜዳንት ቤተመንግሥት በኃይል ሰብረው በመግባት መውረራቸው ተሰማ።

እንቅስቃሴው " መፈንቅለ መንግሥት " ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሯል።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሉዊስ አርሴ የሀገሪቱን ጦር " መደበኛ ያልሆነ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው " በማለት አውግዘዋል።

ወታደሮቹ በአስቸኳይ ከቤተመንግሥት እንዲበተኑ ጠይቀዋል።

በቦሊቪያ ቴሌቪዥን ላይ የተሰራጨው ቪዲዮ አርሴ ከሠራዊቱ ዋና አዛዥ ጄነራል ጁዋን ጆሴ ዙኒጋ ጋር በቤተ መንግሥቱ ኮሪደር ላይ ሲፋጠጡና ሲነጋገሩ ታይተዋል።

አርሴ ፤ " እኔ የአንተ አለቃ ነኝ፣ ወታደሮቹንም እንድታስወጣ አዝዤሃለሁ እናም ለትዕዛዜ መገዛት አለብህ !! " ሲሉ ተደምጠዋል።

ዙኒጋ ወታደሮቹን ይዘው ወደ ቤተመንግሥት ሳይገቡ በፊት ውጭ ላይ ለሪፖርተሮች በሰጡት ቃል ፥ " ማጥፋት ይቁም፣ ሀገራችንን ወደ ድህነት መምራት ይቁም ፣ ሰራዊታችንን ማዋረድ ይቁም " ብለዋል።

የጦሩ አዛዥ ዙኒጋ ፥ " አዲስ የሚኒስትሮች ካቢኔ ይዋቀራል ፤ በእርግጠኝነት ነገሮች ይቀየራሉ፣ ሀገራችን ከዚህ በኋላ አሁን ባለው ሁኔታ መቀጠል አትችልም " ሲሉ ተደምጠዋል።

ፕሬዜዳንት አርሴ በቪድዮ ባሰራጩት መልዕክት ፥ ሀገሪቱን ከሚታየው የመፈንቅለ መንግሥት እንቅስቃሴ ለመታደግ ህዝቡ ተሰባስቦ እና ተደራጅቶ ወደ ጎዳና እንዲወጣና ዲሞክራሲውን እንዲታደግ ጥሪ አቅርበዋል።

#Bolivia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

በቦሊቪያ የተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት ከሸፈ።

ሙከራው ሰዓታትን እንኳን አልቆየም።

የፕሬዜዳንቱን ቤተመንግሥት በኃይል ሰብረው ገብተው የወረሩት ወታደሮች ከቤተመንግሥቱ አካባቢ መሄዳቸው ተሰምቷል።

ፕሬዜዳንት ሉዊስ አርሴ ፤ ወታደሮችን እየመሩ ቤተመንግሥት የገቡትን የሠራዊቱን አዛዥ ጄነራል ጁዋን ጆሴ ዙኒጋን ከስልጣን አውርደው በሌላ ተክተዋል።

አዲሱ የሠራዊት አዛዥ ጆሴ ዊልሶን ሳንቼዝ ሁሉም ቤተመንግሥት የመጡ ወታደሮች ወደ የመጡበት ወታደራዊ ሰፈር /ክፍል እንዲመለሱ አዘዋል።

ይህን ተከትሎም ወታደሮቹ ከስፋራው ለቀው ሄደዋል።

ፕሬዝዳንት አርሴ አዲስ የአየር ኃይል አዛዥ እና የባህር ኃይል አዛዥም ሾመዋል።

ፕሬዝዳንቱ ወታደሮች ቤተመንግሥቱን ሰብረው መግባታቸውን እና መውረራቸውን ተከትሎ ህዝቡ በነቂስ ተደራጅቶ ወደ ጎዳና እንዲወጣና የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እንቅስቃሴውን እንዲያከሽፍ እና ዴሞክራሲውን እንዲያስጠብቅ ጥሪ አቅርበው ነበር።

በዚህም በርካቶች የሀገሪቱን ባንዲራ ይዘው በቤተመንግሥቱ አካባቢ ተሰብሰበው ነበር።

ፕሬዝዳንቱ ሙከራው መክሸፉን ተከትሎ ህዝቡን  በእጅጉ አመስግነዋል።

ወታደሮችን እየመሩ ቤተመንግሥት የገቡት ጄነራል ጁዋን ጆሴ ዙኒጋን ምንም እንኳን የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ ነኝ ብለው በግልጽ ባይናገሩም ፥ " ጥፋት ይቁም ፤ ሀገራችንን ወደ ድህነት መምራት ይቁም፣ ሠራዊታችንን ማዋረድ ይቁም " ሲሉ ተደምጠው ነበር።

ጦሩ ዴሞክራሲን ወደነበረበት ለመመለስ እና የፖለቲካ እስረኞችን ነጻ ለማድረግ እንደሚጥርም ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ዙኒጋን አዲስ የሚኒስትሮች ካቢኔ እንደሚቋቋም ከአሁን በኃላ ሀገሪቱ አሁን ባለው መንገድ እንደማትቀጥልም ገልጻው ነበር።

ጄነራል ዙኒጋን ከሽፏል ከተባለው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በኃላ ቀጣይ ዕጣፋንታቸውን እና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለጊዜው አልታወቀም።

ቦሊቪያ 🇧🇴 ፦ በደቡብ አሜሪካ የምትገኝ ከ12 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖሩባት ሀገር ናት።

#Bolivia
#failedcoup

@tikvahethiopia
" እስራዔል ምዕራባውያንን ተማምና ጦርነቱን የምታሰፋ ከሆነ ቱርክ ሊባኖስን ለመደገፍ ትገደዳለች " - ቱርክ

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን፣ " እስራዔል የጦርነቱን አድማስ የማስፋት ፍላጎት አላት " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

" እስራዔል ትኩረቷን ሊባኖስ ላይ አድርጋለች፤ የምዕራቡ ኃይሎች ከሁነቱ ጀርባ ሆነው እስራዔልን እየገፋፉ ነው " ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡

ጠ/ሚ ኒታንያሁ ግጭቱን አስፍተው አካባቢያዊ ቀውስ ለመፍጠር ተዘጋጅተዋል ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

" እስራዔል ምዕራባውያንን ተማምና ጦርነቱን የምታሰፋ ከሆነ ቱርክ ሊባኖስን ለመደገፍ ትገደዳለች " ብለዋል።

More 👇
https://www.tg-me.com/+LM-bJ8NzZMcxMjA8

#shafaqnews
@thiqaheth
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

ወታደሮችን እየመሩ የቦሊቪያው ፕሬዚዳንት አርሴ ቤተ መንግስትን በኃይል ሰብረው በመግባትና በመውረር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ያደረጉት ጄነራል ሁዋን ሆዜ ዙኒጋ በሀገሪቱ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው እስር ቤት ገብተዋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሰኔ 17/2016 ዓ/ም አንዲት መና ከበደ የተባለች የ26 ዓመት ወጣት ሴትን በመኪና ስርቆት ወንጀል በመጠርጠር በቁጥጥር ስር አውሏል።

ፖሊስ፥ ግለሰቧ ጥዋት 12:30 ገደማ ' ቤተል ቢጫ ፎቅ ' አካባቢ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-B32912 አ.አ የሆነች ተሽከርካሪን የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤቱ ደጃፍ ላይ ሞተር ሳያጠፋ አቁሞት ጃኬት ለመደረብ በገባበት ይዛ መሰወሯንና ከግማሽ ቀን ፍለጋ በኋላ ሰሚት አካባቢ መያዟን አስረድቷል።

ፖሊስ ግለሰቧንም ከነተሽከርካሪው ፎቶ በማንሳት አሰራጭቷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ግለሰቧን እናውቃታለን ያሉ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ፤ መኪናውን መውሰድ አለመውሰዷን በግልጽ ባያሰፍሩም የሃብታም ልጅ እንደሆነች ፣ ስህተት እንደተፈጠረና ከወንጀሉ ነጻ ተብላ ወደ ቤት መግባቷን ጽፈዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይፋ ባደረገው መረጃ በተሽከርካሪ ስርቆት የተጠረጠረችው ግለሰብ መና ከበደ ክስ እንደተመሰረተባት አሳውቋል።

በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት መቅረቧንም አመልክቷል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ግለሰቧ ተሽከርካሪውን በመስረቋ ፓሊስ ምርመራ አጣርቶ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ልኮ ክስ እንዲመሰረትባት ማድረጉን አስረድቷል።

" በአንዳንድ  ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ' ግለሰቧ ተለቃለች ' እና ' ወንጀሉን ሳታውቅ ነው የፈፀመችው ' የሚሉ መረጃዎች እየተሰራጩ  ይገኛል " ያለው ፖሊስ የግል ተበዳይ መኪናቸው መሰረቁን ለፖሊስ እንዳመለከቱ ግለሰቧም ተሽከርካሪውን ለረጅም ሰዓት ይዛ መሰወሯ  ታሳቢ በማድረግና ድርጊቷም በማስረጃ በመረጋገጡ ዓቃቤ ህግ በተሽከርካሪ ስርቆት ክስ መመስረቱን አሳውቋል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#AddisAbaba⛽️

በአዲስ አበባ የሚታየው የነዳጅ እጥረት በቀጣይ ቀናት እንደሚፈታ የኢትዮጵያ የነዳጅ አቅራቢዎች ድርጅት አሳውቋል።

የነዳጅ እጥረት በከተማዋ መከሰቱን የገለጸው ድርጅቱ " እጥረቱ ያጋጠመው በዒድ አል አድሃ አረፋ በዓል ምክንያት እሑድ ሰኔ 9 በማግሥቱ ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ/ም ነዳጅ ከጂቡቲ ባለመጫኑ ነው " ብሏል።

የነዳጅ ማጓጓዝ ሒደቱ አምስት እና ስድስት ቀናትን የሚወስድ መሆኑንና አሁን የሚስተዋለው እጥረት በመጪዎቹ ቀናት እንደሚፈታ አሳውቋል።

ከሱሉልታ መጠባበቂያ ቤንዚን ከአዋሽ መጠባበቂያ ደግሞ ናፍጣ እየተጓጓዘ መሆኑንም በማመልከት የነዳጅ ችግሩ በእርጠኝነት በ2 ቀናት እንደሚፈታ ተናግሯል።

በየተለያዩ የነዳጅ ማደያዎች ላይ ከሚታየው የነዳጅ እጥረት ባለፈ ማደያዎች ነዳጅን ከተጠቃሚዎች እንደሚደብቁ አሽከርካሪዎች ለሪፖርተር በሰጡት ቃል ገልጸዋል፡፡

ሕገወጥ በሆነ መንገድ በውኃ ፕላስቲኮች ጭምር የሚሸጡ መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡

በዚህም ምክንያት ባለፉት ሳምንታት በመዲናዋ ነዳጅ ለመቅዳት የሚጠብቁ ረዣዥም የተሽከርካሪ ሠልፎች መታየታቸውንና አሁንም እጥረቱ እንዳለ አክለዋል፡፡ #ሪፖርተር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ላለፉት ስድስት ቀናት በመላ አገሪቱ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ተጠናቋል። 57 የመንግሥት እና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ማስፈተናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከመውጫ ፈተናው ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በተለይ ከተነገርን ይዘት እና ከተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው…
#MoE

የ2016 ዓ/ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የ2016 ዓ/ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና እና የዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና መቼ ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።

የትምህርት ሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራር ፥ የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በጣም ከዘገየ እስከ ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል ብለዋል፡፡

የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቅ ከመጀመራቸው በፊት ይፋ እንደሚደረግ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

#TikvahEthiopia

Via @tikvahuniversity
#eQUB_APP

መልካም ዜና ለዕቁብተኞች! የዕቁብ ክፍያዎን ካሉበት ቦታ ሆነው ለአጠቃቀም ቀላል እና ምቹ በሆነው የዕቁብ መተግበርያ ከያሉበት ቦታ ሆነው ህልሞን ያሳኩ።

የዕቁብ መተግበርያን አሁን ይጫኑ👇
📱 Android - Google Play | 📱 iPhone - App Store

Telegram Channel: @equbapp

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 0116671717 ወይም 0116670404 ይደውሉ።
#DStvEthiopia

🔥 ከከባድ የምድብ ጨዋታዎች በጓላ የአወሮፓ ጨዋታ ቅዳሜ ምሽት ጥሎ ማለፍ ጫዋታዎች ይጀምራሉ!

🤔 ፉክክሩም አይሏል! እነማን ወደ ሩብ ፍፃሜ ያልፋሉ? የእናንተን አስተያየት ከስር አጋሩን!

ለናንተ ምርጡ ቡድንስ ማነው? መልሶቻችሁን ከስር አጋሩን!

በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎች በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች በወር ከ350 ብር ከጎጆ ፓኬጅ ጀምሮ ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#Euro2024onDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ላለፉት ስድስት ቀናት በመላ አገሪቱ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ተጠናቋል። 57 የመንግሥት እና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ማስፈተናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከመውጫ ፈተናው ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። በተለይ ከተነገርን ይዘት እና ከተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው…
#MoE

ትናንት የተሰጠው የፋርማሲ ትምህርት የመውጫ ፈተና ተሰርዞ በድጋሚ ይሰጣል ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናው " የቴክኒክ ችግር " አጋጥሞት እንደነበር ገልጿል።

ተማሪዎች በበኩላቸው ቀደም ብሎ ፈተናው ወጥቶ በወረቀት እትም እና በPDF መሰራጨቱንና ተማሪዎችም ሰርተው መግባታቸውን አመልክተዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ግን ፈተናው " የቴክኒክ ችግር " ስላጋጠመው ፈተናው በድጋሜ  በድጋሜ ቅዳሜ ሰኔ 22/2016 ዓ.ም ጠዋት ከ3:00 ሰዓት ጀምሮ እና ከሰአት ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ ይሰጣል ብሏል።

ምን አይነት የቴክኒክ ችግር እንደሆነ በዝርዝር ያለው ነገር የለም።

ለፈተናው ተቀምጠው የነበሩ የፋርማሲ ተማሪዎች በየተፈተኑበት የፈተና ጣቢያ በሰዓቱ በመገኘት በድጋሜ የሚሰጠውን ፈተና እንዲወስዱ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ተማሪዎች ምን አሉ ?

የጥዋቱም ይሁን የከሰዓቱ ፈተና ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ እንዴት እንደሆነ ባይታወቅም ወጥቶ ተማሪዎች በበድን ሰርተውት እንደገቡ ገልጸዋል።

ሌላው ፈተናው ከብሉፕሪነቱ ጋር እንደማይጣጣም ፤ ትምህርቱንም የሚመዝን ፈተና እንዳልወጣ አመልክተዋል።

የባለፉት ፈተናዎችን እንዳዩና የዚህ አይነት ፈተና ግን እንዳልነበር ጠቁመው ፈተናው ማስተካከያ እንዲደረግበት አሳስበዋል።

የ2016 ዓ/ም ፈተና ትላንት መጠናቀቁ ይታወሳል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " የዘንድሮው ፈተና ከ220 በላይ ፕሮግራሞች ያለምንም ችግር Smoothly ነው የተሰጠው " ብሎ ነበር።

" ከፈተናዎቹ ጋር የተያያዘም ምንም አይነት Issue አላጋጠመንም፤ አንድም ቅሬታ ለትምህርት ሚኒስቴር አልደረሰም " ሲል ነበር ያስረዳው።

ሚኒስቴሩ ይህን ቢልም  ፤ በተለይ ከተነገርን ይዘት እና ከተዘጋጀው ብሉፕሪንት ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው ፦
- የማኔጅመንት
- የማርኬቲንግ ማኔጅመንት
- የሀይድሮሊክና ውሃ ሃብት
- የቬተርነሪ ሜድስን
- የኸልዝ ኢንፎርማቲክስ ተማሪዎች ተማሪዎች ቅሬታ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
2024/09/29 02:28:03
Back to Top
HTML Embed Code: