Telegram Web Link
#EDR

ኢጂነር ታከለ ኡማ ሹመት ተሰጣቸው።

ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ኢንጂነር ታከለ ኡማን ከዛሬ ጀምሮ የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርገው እንደሾሟቸው የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አ.ማ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አሳውቋል።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ላለፉት ዓመታት በትምህርት ላይ ነበሩ።

ለትምህርታቸው ወደ ውጭ ሀገር ከመጓዛቸው በፊት የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ከዛ ቀድሞ አዲስ አበባ አስተዳደርን በከንቲባነት ሲያገለግሉ እንደቆዩ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ፈቃድ መስጠት የሚያስችል መመሪያ በካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ወደ ትግበራ እንዲገባ መደረጉ ታውቋል።

ይህ መመሪያ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን እና ያልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያን ፈቃድ ለመስጠት የሚያስችል ነው።

የመንግስትና የግል ድርጅቶች ገበያውን በመጠቀም የድርጅቶችን የድርሻ እና የብድር ስነዶችን በመሸጥ እና ገንዘብ በመስብሰብ ፕሮጀክቶችን ለመስራት አቅም ለመፍጠር ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርላቸው ተመላክቷል።

በሌላ በኩል መመሪያው መውጣቱ የድርሻ ወይም የብድር ሰነድ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ኢንቨስተር ፈቃድ ካለው ገበያ አስፈላጊው ቁጥጥርና ግልጸኝነት በተሟላበት የግብይት አሰራር፣ ፈቃድ ባለው ተገበያይ አማካኝነት የተፈቀዱ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ለመግዛት እና ለመሸጥ ምቹ ሁኔታ ይፈጥርለታል ተብሏል።

#EthiopianCapitalMarketAuthority

@tikvahethiopia
#Ethiopia #UAE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ማዕከላዊ ባንክ የተፈራረሙት ስምምነት ምንድነው ?

1ኛ. በኢትዮጵያ ብር እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ (UAE) ድርሀም መካከል የምንዛሬ ልውውጥ ለማድረግ ተስማምተዋል።

ይህ ስምምነት 46 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር እና 3 ቢሊዮን UAE ድርሃም በማዕከላዊ ባንክ በኩል ለመቀያየር / ለመለዋወጥ ያመቻችላቸዋል።

ዓላማው ፦
° በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የፋይናንስ እና የንግድ ትብብርን ለመደገፍ ነው።
° ድንበር ተሻጋሪ ግብይቶችን የበለጠ ውጤታማ እና ቀልጣፋ ለማድረግ ነው።

2ኛ. ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ/UAE በራሳቸው ገንዘብ (በብር እና ድርሃም) ለመገበያየት የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ተፈራርመዋል።

ዓላማው ፦
° የንግድ ልውውጦችን በራሳቸው (በሁለቱ ሀገራት ገንዘብ) ለማድረግ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል።
° የፋይናንስ እና የባንክ ትብብርን ያጠናክራል።
° የፋይናንስ ገበያዎችን ያዳብራል።
° የሁለትዮሽ ንግድን ያመቻቻል።
° የቀጥታ ኢንቨስትመንት ያበረታታል።
° የሙያ እና መረጃ ልውውጥ እንዲኖር ያመቻቻል።

3ኛ. የክፍያ እና የመልዕክት መለዋወጫ ስርዓቶችን ለማገናኘት የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ተፈራርመዋል።

ዓላማው ፦
° ድንበር ተሻጋሪ የገንዘብ ልውውጦችን ውጤታማነት ያሳድጋል።
° በፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ እና በማዕከላዊ ባንኮች ዲጂታል ምንዛሬዎች ላይ ትብብር እንዲደረግ ይረዳል።
° በክፍያ መድረክ አገልግሎቶችና በኤሌክትሮኒክ ስዊች በኩል ትብብር ያደርጋሉ። በክፍያ ስርዓቶቻቸው በኩል ኢቲስዊች እና ዩኤኢስዊች እንዲሁም በመልእክት መላላኪያ ስርዓቶች በሀገራቱ የቁጥጥር መስፈርቶች በማገናኘት ትብብር ያደርጋሉ።

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) በአሁን ሰዓት ጠንካራ ከሚባሉ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር አንዷ ናት።

ሁለቱም የ #BRICS+ አባል ሀገራት እንደሆኑም ይታወቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያሰባሰበው ከብሔራዊ ባንክ እና ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ማዕከላዊ ባንክ ነው።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#ይነበብ ወጣቶችን ወስደው ምንድነው የሚያሰሯቸው ? በኦንላይን ወይም በደላሎች አልያም በኤጀንሲዎች " እዚህ ሀገር ጥሩ ስራ አለ ፤ ክፍያውም ከፍ ያለነው " ተብለው ብዙ ወጣቶች ከተለያዩ ሀገራት ይዘዋወራሉ። ለአብነት ያህል ወጣቶች ከሚዘዋወሩባቸው ሀገራት መካከል የሳይበር ማጭበበር ( Cyber Scam) ማዕከላት ተብለው ወደ ሚታወቁት ፦ • ማይናማር ፣ • ካምቦዲያ፣ • ላኦስ • ማይናማር ታይላንድ…
#OnlineScam

ባለፈው ወር ላይ የላኦ እና የቻይና ፖሊስ በሰሜን ላኦስ ጎልደን ትሪያንግል ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በህገወጥ የጥሪ ማእከል የኦንላይን ማጭበርበር (Online Scam) ተግባር ላይ ተሰማርተዋል ያሏቸውን 280 ቻይናውያንን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

ግለሰቦቹም ወደ ቻይና ዲፖርት ተደርገዋል።

ፖሊስ ግለሰቦቹን በያዘበት ወቅት 460 ኮምፒዩተሮች እና 1,345 ስልኮችን ይዟል።

እንዚህ አካላት በኦንላይን የተለያዩ ሀገራት ያሉ ሰዎችን በውሸት ማንነት እያነጋገሩ ገንዘብ የሚያጭበረብሩ ናቸው።

Photo Credit - Lao Security

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update “ ሃያ (20) ሄክታሩን አጥረውታል። መጋዘኖችንም እያፈረሷቸው ነው። ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንገደዳለን ” - ቤተክርስቲያኗ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን፣ 40 በመቶ የሚሆን የኩሪፍቱ ማዕከል ይዞታዋን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ‘ በጉልበት ሊወስደው ነው ’ ስትል ከሰሞኑን በተደጋጋሚ መግለጫ መስጠቷ ይታወቃል። ጉዳዩ ከምን ደረሰ ? ቤተ ክርስቲያኗ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠችው…
#Update

“ መሬቱ ከዚህ በፊት በNGO እጅ የነበረ ነው ” - የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር 

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን “ 20 ሄክታር ” የሚሆነውን የኮሪፍቱ ማዕከል ይዞታዋን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር “ በጉልበት አጥሮታል ” ስትል ትላንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃሏን ሰጥታ ነበር።

ለጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፣ ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ደብዳቤ እንዳስገባችም ገልጻ፣ ምላሽ ካልተሰጣት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንደምትገደድ ነው የገለጸችው።

ቤተ ክርስቲያኗ፣ ይህን ቃል ከመስጠቷ በቀደሙት ቀናት ውስጥም ከተማ አስተዳደሩ 40 በመቶ የሚሆነውን ይዞታዋን “ በጉልበት ሊወስደው ነው ” ስትል ተደጋጋሚ መግለጫ መስጠቷ ይታወቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለቤተ ክርስቲያኗ ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጥ የጠየቀው የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ምላሹን ሰጥቷል።

አስተዳደሩ ፤ “ መሬቱ ከዚህ በፊት በNGO እጅ የነበረ ነው። በበጎ አድራጎት እጅ ነው የነበረው ” ብሏል።

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር አካል፣ “ በኢትዮጵያ ሲቪክ ማኀበራት በኩል NGO ስራውን ጨርሶ መሬቱን ለመንግስት አስረክቦ ሂዷል ” ብለዋል።

“ በቤተ ክርስትያኗ ጥያቄ ለአምልኮ ወይም ለቀብር ቦታ ተብሎ የተሰጠ መሬት አይደለም ” ያሉት እኝሁ አካል፣ “ NGO ለበጎ አድራጎት ስራ ወስዶ ሲሰራበት የነበረ፣ በኋላ ፍቃዱን መልሶ የወጣበት የNGO መሬት መሆኑን ነው የማውቀው ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ ያለው ሂደት ደግሞ በህግ በኩል ነው ተይዞ ያለው። ስለዚህ ‘ በአስተዳደሩ ተወሰደብን፣ ወከባ ተፈጠረብን ’ ለሚለው ነገር አስተዳደሩ የፈጠረው ወከባ የለም ” ብለዋል።

“ ለቤተ ክርስትያን መሬቱ ሲሰጥና ሲቀበሉ ውል አልነበረም፤ እነዚህ ሦስተኛ አካል ናቸው ማለት ነው ”  ሲሉ አክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፥
- ቤተ ክርስቲያኗ እኮ መሬቱ ይዞታዋ ስለመሆኑ ማረጋገጫ እንዳላት፣
- ከግቢው ውስጥ የነበራት መጋዘን ትላንት እንደፈረሰ፣
- ሃያ (20) ሄክታሩ ይዞታዋ እንደታጠረ ነው የገለጸችው ለዚህ ምላሽዎ ምንድን ነው ? ሲል በድጋሚ ጥያቄ አቅርቧል።

የአስተዳደሩ አካል ፥ “ መሬቱ በእጃቸው ላይ የነበረ አይደለም። በNGO እጅ የነበረ ነው። ስለዚህ ይህን በተመለከተ ይህንን ነው ማድረግ የሚቻለው ” ብለዋል።

“ 12 ሚሊዮን የቃለ ህይወት እምነት ተከታዮች ወይም 35 ሚሊዮን ወንጌላዊያን ተከታዮችን ጠቅሰው እያስኬዱት ያሉትም ስህተት ነው ” ሲሉ አክለዋል።

“ ምክንያቱም ቢመለከትም የቢሾፍቱ ቃለ ሕይወትን ነው እንጂ በአጠቃላይ የወንጌላዊያን ጥያቄና የመብት ጥሰት አድርገው በማቅረባቸው እኛም ትንሽ ከፍቶናል ” ነው ያሉት።

“ የሚመጣውን ስሞታ እንደ መንግስት ተቀብለን እናስተናግዳለን ” ያለው አስተዳደሩ፣ “ ባለመብት ከሆኑ ሚዲያ መጥራትና ሰላም እንዲጠፋ መቀስቀሱ ተገቢ አይደለም ” ሲል ወቅሷል።

ስለዚህ ይዞታው የቤተክርስቲያን አይደለም ብላችሁ ነው የምታምኑት ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ፣ “ በNGO እጅ ነው የነበረው። NGO ደግሞ የወሰደው ለበጎ አድራጎት ስራ ነው። ለአምልኮት፣ ለመቃብር አይደለም ” የሚል ምላሽ ነው የሰጡት።

መጨረሻም፣ “ የህግን መንገድ መከተሉ የተሻለ ነው የሚሆነው። አዲስ ጥያቄ ከሆነ ከእነርሱ ተቀብለን እናስተናግዳለን ” ሲሉ ተናግረዋል።

#TilvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ያለሙትን አሳክተው እፎይ የሚሉበትን የተሻለ አማራጭ ይዘን እየመጣን ነው‼️
በቅርብ ቀን ይጠብቁን …
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

“ ከሆስፒታሉ ውጪ በ3 እጥፍ ዋጋ መድኃኒት እየገዛን ነው ” - ታካሚዎች

“ የአቅርቦት እጥረት አለ ” - የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል 

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በመድኃኒት እጥረት ሳቢያ ታካሚዎች ከ3 እጥፍ በላይ በሆነ ዋጋ ከግል መድኃኒት ቤቶች መድኃኒት ለመግዛት እየተገደዱ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረሩ።

በርካታ ታካሚዎች ዋጋው ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ህክምናቸውን እያቋረጡ መሆኑን፣ ችግሩ መቀረፍ ሲገባው ተባብሶ እንደቀጠለ አስረድተዋል።

በተለይ እንደ ሴፍትሪያክዞን፣ ዲ40% የመሳሰሉ መድኃኒቶች ከሆስፒታሉ ከጠፉ ወራት እንደተቆጠሩ ተናግረዋል።

“ ከሆስፒታል ውጪ በ3 እጥፍ ዋጋ መድኃኒት እየገዛን ነው” ያሉት ታካሚዎቹ፣ የላብራቶሪ ምርመራዎች ‘በተደጋጋሚ ተበላሽተዋል’ እየተባለ የምርመራ ከሆስፒታል ውጪ ለማሰራት እየተገደዱ መሆኑን ተናግረዋል።

ችግሩ ለምን ተፈጠረ ? ሲል ቲክቫህ የጠየቃቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲው ሆስፒታል ቺፍ ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶ/ር መኳንንት መለሰ፣ “ አሁን ባለው የበጀት Ristriction፣ የፋይናንስ እጥረት ምክንያት አንዳንድ መድኃኒቶች አይኖሩም ” የሚል ምላሽ ተሰጥተዋል።

“ በወቅታዊ ችግር አሁን በወቅታዊ ችግር መንገድ ዝግ ነው። መድኃኒት ቀጥታ ከአዲስ አበባ በደጀን በኩል ነበር የሚመጣው አሁን በአፋር ክልል ነው የሚመጣው። የአቅርቦት እጥረት አለ ” ብለዋል።

➡️ ዲ 40% የተሰኘው መድኃኒት ያልነበረው “ትራውማ ካዡዋሊቲ” በዝቶ ስለነበር እንደሆነ፣
➡️ ይሁን እንጂ አሁን የመድኃኒት አቅርቦቱ እንዳለ፣ 
➡️ የላብራቶሪ ማሽኑ በመብራት መቆራረጥ ሳቢያ በመቆሙ ለሳምንት የተመላላሽ ታካሚዎች ህክምና ተቋርጦ እንደነበርና ማሽኑም እየተጠገነ መሆኑን አስረድተዋል። 

ሆስፒታሉ በቀን ከ3,000 በላይ፣ በአጠቃላይ ደግሞ 13 ሚሊዮን ለሚሆኑ ሰዎች የተለያዩ የህክምና አገልሎቶች እንደሚሰጥ ተገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል፤ ከ2 እስከ 3 ወር ባለው ጊዜ ወደ ተግባር ይገባል " - የአ/ አ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

በአዲስ አበባ ከተማ ጥዋትና ማታ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ሊደረግ ነው።

ጎዶሎ ቁጥር እና ሙሉ ቁጥር የኮድ 2 ተሽከርካሪዎችን በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የሕግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ ተነግሯል።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ፥ በሁለት እና በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች ወደ ፈረቃ እንዲገቡ ይደረጋል ብሏል።

" ጥዋት ስራ መግቢያ እና ስራ መውጫ ሰዓት አካባቢ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ይታያል " ያለው መ/ቤቱ " ይህንን ለመቀልበስ ባለስልጣን መ/ቤቱ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ጥናት አስጠንቶ በአዲሱ ዓመት ተግባራዊ የሚደረጉ የፍሰት ማሻሻያዎች አሉ " ብሏል።

ከነዛ ውስጥ አንዱ የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ የሚንቀሳቀሱበት እንደሆነ ገልጿል።

የኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ቅድመ ዝግጅት መደረጉንና የሕግ ማዕቀፍም መዘጋጀቱን በጣም ከዘገየ ከ2 እስከ 3 ወር ወደ ተግባር እንደሚገባ አስረድቷል።

" ይሄ ፍሰቱን ያሻሽላል " ያለው መ/ቤቱ " ፒክ ሀወር / ስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ጎዶሎና ሙሉ ቁጥር ተብሎ ፕሮግራም ወጥቶለት ለምሳሌ ዛሬ ሙሉ ቁጥር የሚንቀሳቀስ ከሆነ ነገ ጎዶሎ ቁጥር በፈረቃ እንዲንቀሳቀስ የሕግ ማዕቀፍ ረቂቅ ተዘጋጅቷል ሌሎችም ቅድመ ሁኔታዎች እየተመቻቹ ነው " ሲል አሳውቋል።

የኦሮሚያ እና ፌዴራል ታርጋ ሳይጨምር የአዲስ አበባ ታርጋ ብቻ ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከ755 ሺህ በላይ እንደሆኑ የተገለጸው የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ከነዚህ ውስጥ የሚበዙት ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በመሆናቸው ነው ጥዋት እና ማታ በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ የሚደረገው ብሏል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

#AddisAbaba #ኮድ2

@tikvahethiopia
#SafricomEthiopia

🎉 የምስራች ለሁላችን!
🎁 ተወዳጆቹ ሜጋ ጥቅሎች ተመልሰው መጥተዋል! ለ90 እና ለ180 ቀን የሚቆዩትን ልዩ የኢንተርኔት ጥቅሎች በM-PESA በመግዛት እስከ 500 ብር የሚደርስ ቅናሽ አግኝተን ፏ እንበል! 🌐🤳
  
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
⚠️ እባካችሁ ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ ⚠️

ዛሬም በትራፊክ አደጋ የበርከታ ሰዎች ህይወት አልፏል።

የዛሬው አደጋ በጌዴኦ ዞን ጮርሶ ወረዳ ዲባንድቤ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው የደረሰው።

በዚህም የ9 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ አልፏል።

ከሟቾች ባሻገር በ4 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሰ ሲሆን ተጎጂዎቹም ወደ ዲላ ሪፈሪያል ሆስፒታል ሪፈር ተብለው ገብተዋል።

የጮርሶ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፤  የአደጋው መንስኤ ታርጋ ቁጥሩ ኢት ኮድ (03)19178 የሆነ ሲኖትራክ፣ ከዲላ ወደ ሞያሌ ሲጓዝ ከነበረው ዶልፈን ሚኒንባስ ኮድ 0322503፣ በተመሳሳይ ከዲላ ወደ ከቡለሆራ ሲጓዝ ከነበረ FSR መኪና ታርጋ ቁጥር AA ከድ 03 74596 ጋር በመጋጨቱ መሆኑን አሳውቋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የአሽከርካሪዎችድምጽ

" ከገቢያችን በላይ ለኮቴ እየተጠየቅን ነው፤ ይህን ለምን ሆነ ብለን በመጠየቃችንም ለእስር ተዳርገናል " - የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች

" 5100 ብር ማስከፈል የጀመርነዉ አስጠንተንና በምክር ቤት አስወስነን ነው " - የአካባቢው አስተዳደር


ከሰሞኑ አሽዋና ሌሎች እቃዎችን የጫኑ መኪናዎችን የሚያሽከረክሩ የከባድ መኪና ሾፌሮች በሀላባ ዞን ዊራ ዲጆ ወረዳ ያሉ የጸጥታ አስከባሪዎች የተጋነነ የኮቴ ክፍያ እየጠየቋቸው መሆኑንና ለምን ? ብለው የጠየቁ አሽከርካሪዎችም ለእስር መዳረጋቸዉን በመግለጽ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።

በአካባቢዉ የኮቴ ማስከፈል የተለመደ መሆኑን የሚገልጹት አሽከርካሪዎች ክፍያው እስከቅርብ ጊዜ ድረስ 3 ሺህ/600 ብር እንደነበር ይገልፃሉ።

" ይሁንና ከሰሞኑ የዘነበውን ዝናብ ተከትሎ ከፍተኛ ችግር ውስጥ በሆንበትና በየመንገዱ ቁመን በምንውልበት በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ክፍያውን 5 ሺህ አስገቡት በማለት ይህ ደግሞ ከገቢያችንም በላይ በመሆኑ የሚመለከተዉ አካል መፍትሄ ይስጠን ጠይቀዋል።

የአሽከርካሪዎችን ጥያቄ ይዘን ያነጋገርናቸው በሀላባ ዞን ዊራ ዲጆ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አብዲ አደም " 5100 ብር ማስከፈል የጀመርነው አስጠንተንና በምክር ቤት ውሳኔ ነው " ብለዋል።

የዋጋ ጭማሪው በሁለት መንገድ መፈጸሙንም ገልጸዋል።

" አንደኛው ፥ አሸዋውን ከሰባ አንስቶ ከመቶ ሀያ ሽህ ብር የሚሸጡት መሆኑን መረጃ አለን ፤ ሁለተኛ በህዝብ ተሳትፎ የተገነባውን የአካባቢዉ መንገድ እነዚህ አሽዋ ጫኝ ሲኖዎችና ተሳቢ የያዙ መኪኖች እያበላሹት በመሆኑ ለጥገና ገቢ በማስፈለጉ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

በሌላ በኩልም ፤ መንገዱ በከፍተኛ ሁኔታ ጥገና እንደሚያስፈልገው አክለዋል።

ከክፍያ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ አለመግባባት የታሰሩ አሽከርካሪዎችን በተመለከተ ላነሳንላቸዉ ጥያቄም መንገዱን ለመጠገን ስምምነት ላይ መደረሱን እና በዚህ ሳምንት እንደሚጀምር ተናግረዋል።

የታሰሩ የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች በተደረገ ውይይት መለቀቃቸው የጠቆሙት ኃላፊው አሁንም የተያዙ ካሉ ከእስር እንደሚለቀቁ ቃል ገብተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update “ መሬቱ ከዚህ በፊት በNGO እጅ የነበረ ነው ” - የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር  የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን “ 20 ሄክታር ” የሚሆነውን የኮሪፍቱ ማዕከል ይዞታዋን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር “ በጉልበት አጥሮታል ” ስትል ትላንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃሏን ሰጥታ ነበር። ለጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፣ ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ደብዳቤ እንዳስገባችም…
#Update!

" መሬቱ ጭራሽ በNGO እጅ ገብቶ አያውቅም ከመጀመሪያው ጀምሮ የቤተ ክርስቲያኗ እጅ የነበረ ነው " - ቤተ ክርስቲያኗ

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን 40 በመቶ የሚሆነው የኩሪፍቱ ማዕከል ይዞታዋን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር " በጉልበት ሊወስደው ነው " ስትል በተደጋጋሚ መግለጿ ይታወቃል።

ለቤተ ክርስቲያኗ ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጥ ቲክቫህ ትላንት የጠየቅነው የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ደግሞ፣ "መሬቱ በNGO እጅ የነበረ ነው" የሚል ምላሽ ሰጥቶ ነበር።

ቤተ ክርስቲያኗ ምን አለች ?

የከተማ አስተዳደሩ የሰጠውን ምላሽ በተመለከተ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃሏን የሰጠችው ቤተ ክርስቲያኗ፣ " ቦታው በNGO እጅ ጭራሹኑ ያልነበረ ከመጀመሪያው ጀምሮ የቤተ ክርስቲያኗ እጅ የነበረ ነው " ብላለች።

" ' መሬቱ ከዚህ በፊት በNGO እጅ የነበረ ነው። በቤተ ክርስቲያን ጥያቄ ለአምልኮ ወይም ለመቃብር ቦታ የተሰጠ አይደለም' " የሚለው የከተማ አስተዳደሩ ምላሽ " የተሳሳተ መረጃ ነው " ነው ያለችው።

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ዋና ፀሐፊ ስምኦን ሙላቱ (ዶ/ር)፣ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " ይሄ መሬት የተሰጠው ከመጀመሪያ ከ1981 ዓ/ም ጀምሮ ለኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" መሬቱ በNGO እጅ ገብቶ አያውቅም።  እሳቸው (የከተማ አስተዳደሩ አካል ማለታቸው ነው) የሚያወሩት ስለምን መሬት እንደሆነ አውቃለሁ። ሌላ ጉዳይ ነው ፤ የሌላ ቤተ እምነት ነው " ብለዋል።

" በደርግ መንግሥት ጊዜ በህፃናት ኮሚሽን በተፃፈ ደብዳቤ መቼ እንደተረከብነው፤ Every detail በመጀመሪያው መግለጫ ተሰጥቷል " ነው ያሉት።

" ስለዚህ እሳቸው (ከከተማ አስተዳደሩ ምላሽ የሰጡትን አካል ማለታቸው ነው) የሰጡት መልስ ስለሌላ ቦታ እንጂ ስለኩሪፍቱ የቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አይደለም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ፣ ከተማ አስተዳደሩ ምላሽ የሰጠው ቤተክርስቲያኗ ' ሊወሰድብኝ ነው ' ስላለችው ኩሪፍቱ ማዕከል ነው፤ እርስዎ ምላሽ ተሰጠበት ያሉት የትኛው ቦታ ነው ታዲያ ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።

ዋና ፀሐፊው፣ " የሌላ ቤተ እምነት ነውና አሁን ስለሌላ ቤተ እምነት ማውራት ለእኔ ጥሩ ስላልሆነ ነው። የዚህ ነው የዛ ነው ባልልም እነርሱ ያውቁታል በትክክል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

" ምክንያቱም በሁለቱም ጉዳዮች ከንቲባ ጽሕፈት ቤትም ስንመላለስ ነበር፤ ያኛው ሌላ ጉዳይ ነው " ሲሉ አክለዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ጉዳዩ የሚመለከታት የቢሾፍቱ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን እያለች የ35 ሚሊዮን ወንጌላዊያን የመብት ጥሰት አድርጎ ማቅረብ ልክ እንዳልሆነ ስለሰጠው ምላሽ ቤተክርስቲያኗ፣ ጉዳዩ የሁሉም የቃለ ሕይወት አማኞች እንደሆነ አጸፋ ሰጥታለች።

" 20 ሄክታሩን ወስደዋል፤ የቀረውን 20 ሄክታሩንም 'በላዩ ላይ አፍርሱ፣ የቀረውን ደግሞ ወደ መሬት ሊዝ ይግባ' እየተባለ ብዙ ነገር እየገፋ ነው ያለው " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update! " መሬቱ ጭራሽ በNGO እጅ ገብቶ አያውቅም ከመጀመሪያው ጀምሮ የቤተ ክርስቲያኗ እጅ የነበረ ነው " - ቤተ ክርስቲያኗ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን 40 በመቶ የሚሆነው የኩሪፍቱ ማዕከል ይዞታዋን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር " በጉልበት ሊወስደው ነው " ስትል በተደጋጋሚ መግለጿ ይታወቃል። ለቤተ ክርስቲያኗ ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጥ ቲክቫህ ትላንት የጠየቅነው የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር…
" የሚዲያ ዘመቻችሁን እንድታቆሙ እንጠይቃለን " - የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር

የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ፥ " በሕገ-ወጥ መንገድ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይለማ የቆየ 280,000 ካሬ ሜትር ለልማት እንዲውል ማድረግ ሕገ- መንግስትን ማስከበር እና ማክበር እንጂ የሚያስወቅስ ጉዳይ አይደለም " አለ።

ይህን ያለው ዛሬ ባወጣው ማሳሰቢያ ነው።

አስተዳደሩ ፥ " ሕግ እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ማስከበር የአንድ የመንግስት አካል ሃላፊነት ሆኖ እያለ ለ40 ዓመታት ያለ ልማት ( ያለ ህዝብ ጥቅም) የቆየ 280,000 ካሬ ሜትር ስኩዌር (የህዝብ እና የቀጣይ ትውልድ ውስን ሐብትን በሕገ -ወጥ መንገድ በየትኛውም መንገድ በሚዲያ ጫናም ሆነ በጉልበት ይዞ መገኘት ወንጀል ነው " ብሎታል።

" በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ኩሪፍቱ ሃይቅ ዙርያ የሆነው እንደሱ ነው " ሲል አክሏል።

ከተማ አስተዳደሩ ፥ " የመንግስት እና የሀዝብ ውስን ሃብትን የመጠበቅ ፥የማስተዳደር እና ለልማት እንዲዉል የማድረግ ህዝባዊ ፣ መንግስታዊ ግዴታ እና ተጠያቂነት አለበት " ያለ ሲሆን " ተደጋግሞ የሚደረግብን የሚዲያ ጥላቻ እና ዘመቻ የህዝብን ጥቅም ከማረጋጋጥ ጉዞዋችን ቅንጣት የማይገታን መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን " ብሏል።

" የከ/መስተዳድሩ ይህን መሬት ለልማት እንዳያውል በሃይማኖት ሽፋን ሕገ- ወጥ ሁከት እና ዘመቻ እያደረጋችሁ ያላችሁ አካላት በሙሉ ከድርጊታቸሁ እንድትታቀቡ " ሲልም አሳስቧል።

" ከዚህ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ላይ የሕግ-የበላይነት ለማስከበር እንገደዳለን " ሲልም አስጠንቅቋል።

" የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ይህንን ተረድተዉ የተጀመረውን ሃገራዊ እና የሕዝቦችን ተጠቃሚነት ጉዞ የሚያደናቅፍ የሚዲያ ዘመቻውን እንድያቆምልን እንጠይቃለን " ብሏል።

#Bishoftu

@tikvahethiopia
#CHAPA

⚠️በዚህ ዲጂታል ዘመን በረቀቁ ስልቶች በመጠቀም የክፍያ መጭበርበር በተደጋጋሚ እየተከሰተ ነው!

ቻፓ ንግድዎን ከአጭበርባሪዎች በመከላከል ለደንበኛዎችዎ በጣም ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የክፍያ ስርአት ያቀርባል።

➡️ ዘመናዊ የደህንነት ስርዓታችን አጭበርባሪዎችን አስቀድሞ በመያዝ የለፉበት ገንዘብ እንዳይሰረቅ ይከላከላል።
➡️ ፈጣን እና ቀላል የክፍያ ስርዐታችን ያለምንም ተጨማሪ መዘግየቶች ፈጣን እና ውጣውረድ የሌለው ክፍያ ለማድረግ ያስችላል።

እርስዎ ንግድዎ ላይ ያተኩሩ ፣ ቻፓ ክፍያዎችዎን ይቆጣጠራል። ንግድዎን ዛሬውኑ ቻፓ ላይ በማስመዝገብ ክፍያዎትን ያዘምኑ!
🌐ለበለጠ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ፡ https://chapa.co/ ወይንም ዛሬውኑ በ 8911 ይደውሉልን።

Website | Instagram | Facebook |LinkedIn |X
#Tigray #TPLF

" ' አቶ ጌታቸው ሰብሰባው ረግጠው ወጡ ' ተብሎ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች የሚሰራጨው ወሬ ልክ አይደለም " - የስብሰባው ተሳታፊ

ከሰሞኑን ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ስብሰባ ላይ ነበር የከረመው።

ስብሰባው 11 ቀናትን የፈጀ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 5 የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አበላት ከድርጅቱ የከፍተኛ አመራሮች እና ካድሬዎች ሰብሰባ መቅረታቸውን ከአንድ የስብሰበው ተሳታፊ መስማት ችሏል።

የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እና ካድሬዎች ስብሰባ ተሳታፊ የነበረው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጭ በስብሰባው የመጨረሻ ሁለት ቀናት ያልተገኙት ፦
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንትና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ
- የማእከላይ ኮሚቴ አባልና የትእምት ዋና ስራ አስፈፃሚ በየነ ምክሩ
- የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራርና የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት
- የክልሉ የህብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲ ሃላፊና የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል ነጋ ኣሰፋ 
- የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል ብርሃነ ገብረየሱስ እንደሆኑ ጠቁመዋል።

" ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 5 የህወሓት የማእከላዊ ኮሚቴ አመራሮች ' ሰብሰባው ረግጠው ወጡ ' ተብሎ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች የሚሰራጨው ወሬ ልክ አይደለም " ያሉት እኚህ የመረጃ ምንጭ ፥ " ፕሬዜዳንቱ በፍቃድ ምክንያት ሀምሌ 7 ቀን 2016 ዓ/ም ከሰአት በኋላ ያልተገኙ ሲሆን ሀምሌ 8 እና 9/2016 ዓ/ም ያልፍቃድ መቅረታቸው በስብሰባው ታውጇል " ብለዋል።

" የተቀሩት 4 የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በተለያዩ ጊዚያት በየግላቸው ከስብሰባው እንደወጡ አለመመለሳቸው ለተሰብሳቢው ተነግሮታል "  ሲሉ አክለዋል።

ከሰኔ 26 አስከ ሀምሌ 9 ቀን 2016 ለ11 ቀናት ከፍተኛ አመራሮች እና ካድሬዎች ስብሰባ ያካሄደው ህወሓት ባወጣው መግለጫ የድርጅቱ 14ኛው ጉባኤ በተያዘው የሀምሌ ወር 2016 እንደሚካሄድ አመልክቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
 
2024/09/30 12:19:29
Back to Top
HTML Embed Code: