Telegram Web Link
ለሲዳማ ሴቶች መልካም አጋጣሚ

ከአመታት በፊት የነበረዉ የሲዳማ ቡና የሴቶች ቡድን ከፈረሰ በኋላ በወቅቱ በክለቡ የነበሩ ሴት ተጫዋቾችን በማግኘት መረዳት እንደቻልነዉ ልጆቹ በጣም አቅም የነበራቸዉ እና ትልቅ ህልም የነበራቸዉ ሲሆን በወቅቱ በነበረዉ ሁኔታዎች ምክንያት ሳይሳካላቸዉ በመቅረቱ ብዙዎቹ ወደ ትዳር በመግባት ኳስ ማቆም ችለዋል።

አንድ አንድ በዛን ወቅት በክለቡ የነበሩ ተጫዋቾች አሁን ላይ በተለያዩ ክለቦች ዉስጥ በመጫወት ላይ ሲገኙ ይህ ቡድን ዳግም መመስረቱ እንዳስደሰታቸዉ በወቅቱ ከነበረዉ ትዝታ ጋር አጫዉተዉናል።

አሁን ላይ የሲዳማ ቡና የሴቶች እግርኳስ ክለብ መመስረቱ በክልሉ እንዲሁም በሀገራችን የእግርኳስ ተሰጦ ያላቸዉን ሴት ተጫዋቾችን የሚያካትት በመሆኑ እንደ መልካም እድል የሚቆጠር ተግባር ነዉ ፤ ክለቡ በ2015 ልጀምር ላሰበዉ የሴቶች ቡድን አሰልጣኝ በቅርብ የሚያሳዉቅ ሲሆን ከዚያ በኋላም ወደ ምልመላ እንደሚገባ ተነግሯል።

በሲዳማ እና አከባቢዋ የምትገኙ የእግርኳስ ፍላጎት ያላችሁ ሴቶች በቅርቡ ያለዉን ነገር ተከከታትለን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

#ሲዳማ_ቡና_እግርኳስ_ክለብ
@sidamacoffe
@sidamacoffe
የሲዳማ ቡና ፍሬዎች

ይገዙ ቦጋለ እና ብንያም ላንቃሞ

@sidamacoffe
@sidamacoffe
Pic of the Day

@sidamacoffe
@sidamacoffe
የጨዋታ ቀን

ሲዳማ ቡና ከ ወላይታ ዲቻ

በስምንተኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ቀን 9:00 ሲዳማ ቡና ከ ወላይታ ዲቻ ጨዋታቸዉን ያደርጋሉ ፤ ሲዳማ ቡና በዚህ አመት አንደ ጨዋታ ብቻ አሸንፎ በአምስቱ አቻ አጠናቆ አንድ አቻ ወጥቶ በሊጉ 13 ተኛ ደረጃ ላይ ሆኖ ጨዋታዉን ያደርጋል።

ክለቡ በዉጤት ቀዉስ ላይ የሚገኝ ከመሆኑም ባለፈ ባለፈዉ
ሳምንት አሰልጣኙን እንደሚያቆይ ካበሰረ በኋላ አሰልጣኙ ዛሬ በሜዳ ላይ ተአምር ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በሲዳማ ቡና በኩል አማኑኤል እንዳለ ወደ ሜዳ በመመለስ ለክለቡ ግልጋሎቱን ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ በፊት መስመሩ የተለመደዉን አሰላለፍ ይዞ ወደ ሜዳ ይገባል።

ጨዋታዉን ወደ እናንተ እንድናደርስ ስፖንሰር ያደረገልንን አዚ ሆቴል ሀዋሳን እናመሰግናለን።🙏
#ሲዳማ_ቡና_እግርኳስ_ክለብ
የሲዳማ ቡና አሰላለፍ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ የሚጠቀሙት ባስ ይህንን ይመስላል።

@sidamacoffe
ሲዳማ ቡና በዚህ አመት ካስቆጠራቸዉ ዘጠኝ ግቦች አምስቱ የተገኙት ከይገዙ ቦጋለ ናቸዉ።

@sidamacoffe
ፍሬዉ ሰለሞን ( ጣቁሩ) እና ሽመልስ በቀለ

ለረጅም አመታት በእግር ኳስ የቆዩ እና ድንቅ ክህሎት ያላቸዉ ተጫዋቾች ሲሆኑ በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ብሔራዊ ቡድናችንን በመወከል አሻራቸዉን ያሳርፋሉ ተብሎ ተስፋ ተጥሎባቸዋል።

ሁለቱም በፈጠራ ችሎታ የተካኑ ተጫዋቾች በብሔራዊ ቡድኑ በኩል በመሃል ስፍራዉ አዝናኝ እግር ኳስን የሚያስመለክቱን ይሆናል።

የአፍሪካ ዋንጫ ሊጀምር የአንድ ሳምንታት እድሜ ብቻ ቀርተዉታል ፤ መልካም እድል ለዋሊያዎቹ

#ኢትዮጵያ
#ዋሊያ
​​እንዲታይ ሰንደቁ‼️

⏯️ "በቀን በአራተኛው በእለተ ሀሙስ.."

★ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አንድ ፥ ሁለተኛ ጨዋታ፥ እምዬ ኢትዮጵያ ከ ካሜሮን

⏯️ "ያዢልኝ ቀጠሮ ቦታ ምረጪና...."

★ ዛሬ ጥር 5/2014...ከ60ሺህ ተመልካች በላይ በሚይዘው ኦሊምቢ ስታዲየም

⏯️ "ነይ ማታ ማታ....ማታ ማታ..."

★ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ

⏯️ "ይዳኝ ይዳኘኝ ያየ...ይፍረደኝ ያየ..."

★ አርቢትሩ፦ ናዳላ ንጋምቦ (ዲሞክራቲክ ኮንጎ)

⏯️ " እጅ አንሰጥም...እጅ አንሰጥም ቶሎ....."

★"ካሜሮን ጠንካራ ቡድን ነው፤ በደጋፊው ፊት ነው የሚጫወተው፤ ከቡርኪናፋሶ ጋር ያደረገውንም ጨዋታ ተመልክተናል። እኛ በኬፕቨርድ ጨዋታ የቁጥር ብልጫ ተወስዶብን ባሰብነው መንገድ አልተጫወትንም፤ ከካሜሮን ጋር ግን ጥሩ ለመጫወትና ውጤታማ ለመሆን ተዘጋጅተናል፤ እስከ መጨረሻው እንታገላለን" ⬅️ የዋሊያው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ

⏯️ " ሁሉም ቃሉን ሲሰጥ....ሰዎቹ ምን ይላሉ...."

★ "ከኢትዮጵያ ጋር ላለብን ጨዋታ እንደ መጀመሪያው ሁሉ በጥሩ ራስ መተማመንና ቆራጥነት ውስጥ ነን። ለዚህም ሁሉም ተጫዋቾች ዝግጁ ናቸው። የጨዋታ እቅዳችንም አሸንፎ መውጣት ነው "⬅️ የካሜሮን አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንሲሳኦ ዳ ሲልቫ ኦሊቬራ

⏯️ "1..2...3...4 እስኪ ቁጥር ጥሩ..."

★ ሁለቱ ሀገራት ዛሬ ለ3ኛ ጊዜ ይገናኛሉ

★ በ1970 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ካሜሮን ዋሊያውን 3ለ2 አሸንፋ ነበር፤ ለኢትዮጵያ ሁለቱን ጎሎች ያስቆጠረው ደግሞ መንግስቱ ወርቁ

★በ2016 የቻን ውድድር ደግሞ 0-0 ተለያይተዋል፤ ያሬድ ባየህ፣ አስቻለው ታመነና ጋቶች ፓኖም በ2016 የቡድኑ አባል የነበሩ አሁንም የተካተቱ ተጫዋቾች ናቸው

★ዋሊያው ከባለፉት 6 የነጥብ ጨዋታዎች አንዱን ሲያሸንፍ በሁለቱ አቻ ተለያይቷል፤ በሶስቱ ተሸንፏል፤ በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታም በኬፕቨርድ 1-0 ተሸንፏል

★የማይበገሩት አናብስት ካሜሮን ከባለፉት 6 ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ ተሸንፈው አምስቱን አሸንፈዋል፤ በአፍሪካ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታም ቡርኪናፋሶን 2-1 ረተዋል

⏯️ " ወገኔ...ዎ...ወጌ...ዎ"

★ በዋሊያው በኩል ሁሉም ተጫዋቾች የኮቪድ ምርመራ ውጤታቸው ነፃ ሆኗል

⏯️ "አይዞህ ልቤ፥ አይዞህ..."

★ በመጀመሪያው ጨዋታ በቀይ ካርድ የወጣው ያሬድ ባየህ አንድ ጨዋታ ስለተቀጣ ዛሬ አይኖርም

⏯️ "እኔስ አሞኛል...ፍፁም አልቻልኩም..."

★ በጉዳት ምክንያት የኬፕቨርድው ጨዋታ ያመለጣቸው አማካዩ ሽመልስ በቀለ በጡንቻ መሳሳብ እንዲሁም ግብጠባቂው ፋሲል ገ/ሚካኤል በትከሻ ጉዳት የዛሬውም ጨዋታ ያመልጣቸዋል

★አጥቂው ዳዋ ሁቴሳ ግን ከህመሙ አገግመሞ ለዛሬው ጨዋታ ብቁ ሆኗል

★በካሜሮን በኩል ጉዳትና ቅጣት የለም። ቡርኪናፋሶን ሲያሸንፉ ይዘውት የገቡትን አሰላለፍ ዛሬም ይደግሙታል ተብሎ ይጠበቃል

⏯️ " ዋሊያው ብርቁ እንዲታይ ሰንደቁ..."

★ኢትዮጵያ 🇪🇹
የታህሳስ ወር የፊፋ ደረጃ....137ኛ
የታህሳስ ወር የካፍ ደረጃ....40ኛ
የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ....11
የአፍሪካ ዋንጫ ባለድል....1
ተጫዋቾች...26 ከሀገር ውስጥ፥ 2 ከውጪ ክለቦች
አሰልጣኝ....ውበቱ አባተ ውበቱ
ዜግነት.....ኢትዮጵያዊ
እድሜ.....49
የቀድሞ አማካይ

⏯️ "ኢጅቤ ዛንገለዋ...ኢጂቤ ኢጂቤ...."

★ ካሜሮን🇨🇲
የታህሳስ ወር የፊፋ ደረጃ.....50ኛ
የታህሳስ ወር የካፍ ደረጃ.....7ኛ
የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ.....19
የአፍሪካ ዋንጫ ባለድል .....5
አሰልጣኝ...አንቶኒዮ ኮንሲሳኦ ዳ ሲልቫ ኦሊቬራ
ዜግነት....ፖርቹጋል
እድሜ.....60
የቀድሞ የቀኝ መስመር ተከላካይ
ተጫዋቾች...ሀያ ስምንቱም ከሀገር ውጪ ክለቦች የመጡ

⏯️ "ሀሙስ....ልቤን አለው ደስ ደስ..." (በታምሩ አለሙ)

★መልካም እድል ለብሄራዊ ቡድናችን💚💛❤️

@sidamacoffe
@sidamacoffe
የሲዳማ ቡና ታዳጊዎች

@Sidamacoffe
@sidamacoffe
የጨዋታ ቀን

ሲዳማ ቡና ከ ባህርዳር ከተማ
ምሽት 1:00

ከብሔራዊ ቡድኑ የእረፍት ጊዜያት በኋላ ዛሬ በድሬዳዋ የሚጀምር ይሆናል ፤ ምሽት 1:00 ሰአት በሚደረገዉ ጨዋታ ክለባችን ሲዳማ ቡና ባህርዳር ከተማን የሚገጥምበት ጨዋታ ተጠባቂ ጨዋታ ነዉ።

በሲዳማ ቡና በኩል ደጋፊወች ወደ ሜዳ እንዳይገቡ መከልከሉን አስመልክቶ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ የማይገቡ ይሆናል ፤ በተጨማሪ ከብሔራዊ ቡድን የተመለሱት ግብ ጠባቂዉ ተ/ማሪያም ሻንቆ እና ፍሬዉ ሰለሞን በቋምነት ጨዋታቸዉን የሚጀምሩ ይሆናል።

#መልካም_ጨዋታ
#ሲዳማ_ቡና_እግርኳስ_ክለብ
ግሩም አሰፋ💪

በሲዳማ ቡና ቤት ካሉ ድንቅ ተመላላሽ ተጫዋቾች አንዱ ሲሆን አሰልጣኝ ገ/መድህን ሀይሌ ከመጣ በኋላ ብዙዉን ጊዜ ሜዳ ዉስጥ ያልተመለከትነዉ ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም ለክለቡ ያለዉ ወኔ እና ፍቅር ተወዳጅ አድርጎትም ነበር።

ተጫዋቹን ዳግም ለማየት የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች ተናፍቀዋል

@sidamacoffe
@sidamacoffe
2024/09/27 20:20:12
Back to Top
HTML Embed Code: