Telegram Web Link
ለለውጥ መነሳሳት

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

 8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

 10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡

#Share #Like
www.tg-me.com/psychoet

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
©Zepsychology
#እጅግ_በጣም_ስኬታማ_የሆኑ_ሰዎች_7_ልምዶች
በጣም አስተማሪ መልዕክት ነው #SHARE
Telegram www.tg-me.com/psychoet

ከአስራ አምስት ሚሊዮን ቅጂ በላይ ተሽጧል፤ በሰላሳ ቋንቋዎች ተተርጉሞም ለንባብ በቅቷል፤ በእኛው አማሪኛ ቋንቋም ተተርጉሞ መታተሙንም አውቃለሁ፡፡ ይህ መጽሐፍ “The 7 Habits of Highly Effective people” ይባላል:: “እጅግ በጣም ስኬታማ የሆኑ ሰዎች 7 ልምዶች” ብለን ቃል በቃል እንተርጉመው፡፡ የመጽሐፉ ደራሲ ስቴቨን ኮቬይ ይባላል፡፡ ይህ መጽሐፍ በግለሰብ ደረጃ ብልፅግናን (Personal development) ለመፍጠር እንዲረዱ ታስበው እስከ ዛሬ ድረስ ከተጻፉ መጽሐፍት መካከል ወደር የማይገኝለት ነው፡፡ ካላነበባችሁት እንድታነቡት እመክራለሁ፡፡ ያነበብነውም ደግመን ልናነበው ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡

የዚህ ድንቅ መጽሐፍ ደራሲ ስቴቨን ኮቬይ “ውስጣዊ ድል ከውጫዊ ድል ይበልጣል” ይላል፡፡ እዚህ ምድር ላይ ማግኘት የምንፈልጋቸውን ነገሮች በሙሉ ለማግኘት አስቀድመን ራሳችንን ማሸነፍ፤ የህይወታችን ሾፌር መሆን፤ ውስጣዊ ማንነታችንን መቆጣጠር ወዘተ አለብን ማለት ነው፡፡ “ከተማን ከሚመራ ሰው ይልቅ ራሱን የሚመራ ሰው ይበልጣል” ይላል ጠቢቡ ሰለሞን፡፡ ራስን ማሸነፍ ሌሎች ውጫዊ ነገሮችን የማሸነፊያ ቁልፍ ነው፡፡ በመቀጠል በቅደም ተከተል የምንመለከታቸው 7 ልምዶች ማንኛውም ሰው የግል ህይወቱ መሪ እንዲሆን በእጅጉ የሚያግዙ ናቸው፡፡ አሁን ቦታውን ለእነዚህ ልምዶች ለቀቅ እናድርግ እስኪ፡፡

1. ኃላፊነት ውሰዱ

ጅብ ከሄደ በኋላ የውሻ መጮህ ምንም ውጤት አያመጣም፤ ትርፉ ድካም ነው፡፡ ውጤት የሚያመጣው ጅቡ ከመምጣቱ በፊት አስቀድሞ በማነፍነፍ ድምጽ ማሰማት ነው፡፡ ሁኔታዎችን፣ ሌሎች ሰዎችን፣ ዓለምን ወዘተ የሚወቅሱ ሰዎች በህይወታቸው የረባ ቁም ነገር አያከናውኑም፤ ሁልጊዜም ኃላፊነትን የሚያሸክሙት ከእነሱ ውጪ ላለ ሌላ አካል ነው፡፡ ኃላፊነትን መሸከም ስንችል ነው የህይወታችንን ጉዞ አቅጣጫ መወሰን የምንችለው፡፡ የተሸከርካሪውን መሪ ለሌላ አካል አሳልፈን ሰጥተን የምፈልገው ቦታ አይደለም የደረስኩት፤ በፈለኩት ፍጥነት አይደለም እየተጓዝኩ ያለሁት ወዘተ ልንል አንችልም፤ ብንልም ዋጋ የለውም፡፡ የጉዞውን አቅጣጫ፣ ፍጥነት እና አድራሻ የሚወስነው አሽከርካሪው ነው፡፡ ልምዳችን መውቀስ፣ ጣት መጠቆም፣ ራስን መከላከል ወዘተ ከሆነ እውነቱን ለመናገር የሚወቀስ ነገር ማግኘት አይከብድም፡፡ ዘወትር የእናቴ መቀነት አደናቅፎኝ ነው ማለት ህይወታችን ባለህበት እርገጥ እንዲሆን በር ወለል አድርጎ ይከፍታል፡፡ ስለዚህ ለውጥ ለማምጣት፣ የራሳችን ሰዎች ለመሆን፣ ውስጣችንን ድል ለማድረግ ወዘተ ሁልጊዜም ለገዛ ራሳችን ህይወት ሙሉ ኃላፊነት እንውሰድ፡፡ ቃላችንን የምናከብር፤ በአልንበት ቦታ የምንገኝ፤ በገዛ ራሳችን ጥረት የምንፈልገውን ማንኛውንም ዓይነት ነገር እጃችን ለማስገባት መጓዝ ያለብንን ያህል ርቀት መጓዝ የምንችል ሰዎች እንሁን፡፡ “ስራ እኮ ጠፋ! እኔ ምን ላድርግ?!” ከማለታችን በፊት ስራ ለማግኘት የምንችለውን ድንጋይ በሙሉ መፈንቀላችንን እርግጠኛ እንሁን፤ ቀጣሪዎች የሚፈልጉትን ዕውቀት እና ክህሎት ይዘን ለመገኘት ጥረት እናድርግ፤ የተለመደውንም ያልተለመደውንም አማራጭ እንፈትሽ፡፡ ሳይኮሎጂስቶች “Life is 10 % what happens to us and 90 % how we react to it” ይላሉ፡፡ የህይወታችንን አብዛኛውን (90 %) ክፍል በምንፈልገው መልኩ መስራት እንችላለን ማለት ነው፡፡ የምናጭደው የዘራነውን ነው፡፡

2. የምትፈልጉትን ነገር አስቀድማችሁ እወቁ

ስቴቨን ኮቬይ “ነገሮች ሁለት ጊዜ ይፈጠራሉ” ይላል፡፡ የመጀመሪያው ፈጠራ የሚጠናቀቀው አእምሮአችን ውስጥ ነው፡፡ ከቤት ከመውጣታችን በፊት የምንሄድበትን ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ከአንድ እና ሁለት፣ አምስት እና አስር ዓመት ወዘተ በኋላ ምንድን ነው ማግኘት፣ ማድረግ፣ መሆን ወዘተ የምንፈልገው? ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ መስጠት ነገሮቹ በተጨባጭም ወደ ህይወታችን የሚመጡበትን ዕድል ከፍ ያደርጋል፡፡ “We rise to the level of our expectations” ይባላል፡፡ የምናገኘው የምናስበውን ነው፤ የምንደርሰው እንደርሳለን ብለን የምናስበው ከፍታ ድረስ ነው፡፡ ግባችንን ማወቃችን ትኩረታችንን ለመሰብሰብ ይረዳናል፤ ከነፈሰው ጋር አንነፍስም፤ በፈተና መካከል ጸንተን እንቆማለን፡፡ ሳይኮሎጂስቶች የህይወታችንን ግብ በቅጡ ለመለየት የሚረዳን አንዱ ሁነኛ መንገድ “የቀብራችን ዕለት እንዲነበብ የምንፈልገውን የህይወት ታሪካችንን መወሰን ነው” ይላሉ፡፡ ቁጭ ብለን ልናስብበት ይገባል፡፡

3. ቅድሚያ ለሚገባቸው ነገሮች ቅድሚያ ስጡ

“ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት” ይባላል፡፡ ቅድሚያ መስጠት ላለብን ነገሮች ቅድሚያ መስጠት አለብን፡፡ ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም፡፡ ኮቬይ እንዲህ ይላል፡- “ራሳችሁን ከእነዚህ ሶስት አጉል ልምዶች በአንዱ መውቀስ ቢኖርባችሁ በየትኛው ነው የምትወቅሱት? (1) መስራት ያለብኝን ነገር በቅደም ተከተል መለየት አልችልም፤ (2) በአስቀመጥኩት ቅደም ተከተል መሰረት መስራት አልችልም፤ (3) በወሰንኩት ቅደም ተከተል መሰረት ለመስራት አስፈላጊው ቁርጠኝነት የለኝም፡፡ ብዙ ሰዎች ቁርጠኝነቱ የለኝም ነው የሚሉት፡፡ ጠለቅ ብለን ከመረመርነው ግን እውነቱ ሌላ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እውነቱ ቅደም ተከተሉ ውስጣችን በጥልቀት አለመስረጹ ነው፡፡ ልምድ 2ን ማለትም የህይወት ግባችንን አስቀድመን በሚገባ ለይተን በሚገባ ውስጣችንን መቅረጽ አለመቻላችን ነው”::

4. በጋራ እኩል ተጠቃሚነት መርህ ተመሩ

ከተቃራኒ ፆታ ጀምሮ እስከ የንግድ ስራ ግንኙነት ድረስ በጋራ እኩል ተጠቃሚነት መርህ መመራት ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ “አዎ! በሚገባ አምንበታለሁ፡፡ በእኩል ተጠቃሚነት መርህ ነው ህይወቴን የምመራው፡፡” ትሉ ይሆናል፡፡ እንደምትሉት እንደምትኖሩ ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ ለማሸነፍ ከመጣር ይልቅ እንዴት በጋራ እኩል ተጠቃሚ ለመሆን ጥረት አድርጉ፡፡ የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን፣ ከሌላው ከፍ ብሎ ለመታየት፣ ልክ ሆኖ ለመገኘት ወዘተ ከመጨነቅ ይልቅ በጋራ እኩል እንዴት ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል ማሰብ እና ይህንን መርህ በየትኛውም የግንኙነታችን መረብ ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ይበልጥ ውጤታማ ያደርገናል፡፡

5. መጀመሪያ ለመረዳት ጥረት አድርጉ

መጀመሪያ ስንረዳ የሚረዱንን እናገኛለን፡፡ ብዙ ጊዜ ግን በአንጻሩ ጊዜያችንን የምናጠፋው ሰዎች እንዲረዱን በመፍጨርጨር ነው፡፡ ቆም ብለን “ምንድነው እስኪ እያሉ ያሉት? ልክ ይሆኑ ይሆን? በየትኛው ማዕዘን ነው እነሱ ጉዳዩን ያዩት?” ወዘተ ብሎ በቀናነት ማሰብ እና ሰዎችን ለመረዳት ጥረት ማድረግ ጥሩ ነው፡፡ ሰዎችን የመረዳት ችሎታችን ጥሩ ሲሆን የሚረዱንን ሰዎች ቁጥርም ይጨምራል፡፡

6. 1 + 1 = 3

“ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” ትልቅ መልዕክት ያለው አባባል ነው፡፡ በጋራ የሚሰሩ ስራዎች በግል ከሚሰሩ ስራዎች ይልቅ የላቀ ውጤት ያመጣሉ፡፡ አንድ እጅ ብቻውን አያጨበጭብም፡፡ ሩጫን በመሰለ የግል ጥረትን በከፍተኛ ሁኔታ በሚጠይቅ የውድድር ዘርፍ እንኳን አትሌቶቻችን ሲተባበሩ የሚያስመዘግቡትን አንጸባራቂ ድል እናውቀዋለን፡፡ በየትኛውም አጋጣሚ በጋራ የመስራትን መንፈስ ማዳበር ጠንካራ ያደርጋል፤ የበዛ ፍሬም ያፈራል፡፡ አብረን መብላት ብቻ ሳይሆን አብረን መስራትንም ባህላችን እናድርግ፡፡ ስቴቨን ኮቬይ እንደሚለው “አንድ ሲ
ደመር አንድ ከሁለት በላይ ነው”፡፡

7. መጋዛችሁን ሳሉ

ስቴቨን ኮቬይ መጽሐፉ ውስጥ ግሩም አፈ ታሪክ አለ፡፡ አንድ ተጓዥ መንገደኛ በአንድ ጫካ ውስጥ አቋርጦ ሲያልፍ አንድ ምስኪን እንጨት ቆራጭ ላቡ ጠፍ እስከሚል ድረስ ያለምንም እረፍት እንጨት ሲቆርጥ ይመለከታል፡፡ ተጓዡ መንገደኛ ቆም ይልና የመጋዙን መደነዝ አስተውሎ ኑሮ “ወዳጄ! ለምን መጋዝህን ዕረፍት ወስድህ አትስለውም?” ይለዋል፡፡ ልፋ ያለው እንጨት ቆራጭ “አይ ለሱ እንኳን ጊዜ የለኝም” የሚል የዋህ ምላሽ ይሰጠዋል፡፡ ይኼ ምስኪን እንጨት ቆራጭ ዕረፍት ወስዶ መጋዙን ቢስል በተሻለ ቅልጥፍና ብዙ እንጨት መቁረጥ እንደሚችል አልተረዳም፡፡

የተራ ቁጥር ሰባት ልምድ መልዕክት ቀላል እና ግልጽ ነው፡፡ በቂ ዕረፍት ምንጊዜም አድርጉ ነው፡፡ ከስራ በኋላ ራሳችሁን ዘና የማድረግ ልምምዱ ይኑራችሁ፡፡ መዝናናት ለጊዜው ከሚሰጠው ደስታ ባሻገር ለቀጣይ ስራ ያዘጋጃል፡፡ ሁልጊዜም እንደምለው ትልልቅ ኩባንያዎች ወጪ ችለው፣ ወርሃዊ ደሞዝ መክፈላቸውን ሳያቋርጡ ሰራተኞቻቸውን የሚያዝናኑት በጣም ቸር ስለሆኑ አይደለም፡፡ ይልቁንም የተዝናና ሰራተኛ ይበልጥ ውጤታማ እንደሚሆን እና እነሱንም ይበልጥ ውጤታማ እንደሚያደርጋቸው ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው፡፡

አንድ አንድ ሰዎች “እኔ መዝናናት አይሆንልኝም” ይላሉ፡፡ “መዝናናት ራሱን የቻለ ችሎታ ነው” ይላል አንድ ሌላ ወዳጄም፡፡ በመሆኑም “እንዴት እንዝናና?” የሚል ጥያቄ ያላችሁ ሰዎች እነዚህን የመዝናኛ አማራጮች እንድትፈትlቸው እጋብዛለሁ፡- ዋና ዋኙ፤ ከወዳጅ ዘመዶቻችሁ ጋር አስደሳች ጊዜ አሳልፉ፤ ዮጋ ስሩ፤ ዳንስ ደንሱ፤ ከከተማ ከተቻለም ከሀገርም ወጣ ብላችሁ ጎብኙ፤ ደስታ ይሰጠኛል ብላችሁ የምታስቡትን የትርፍ ጊዜ የመዝናኛ አማራጭን (Hobby) ሞክሩ፡፡

ቸር እንሰንብት!

(በነጋሽ አበበ)
©zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
#በራስ_መተማመንን (Self Confidence)
👉 ለማሳደግ የሚረዱ አስር ሙያዊ ምክሮች

ለራስዎ ያለዎት ከፍ ያለ ግምት ሌሎች እርስዎን የሚያዩበት መንገድ ጥሩ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና አለው። በራስ የመተማመን ስሜት ሲኖርዎትም በተሰማሩበት ሥራ ላይ የበለጠ ስኬታማ እንዲሆኑ ከፍተኛ እርዳታ አለው።
ምንም እንኳን በራስ መተማመን ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩት ምክንያቶች ብዙዎቹ ከእርስዎ ቁጥጥር ውጭ ቢሆኑም፣ በራስ መተማመንን ለመገንባት የሚረዱ ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ። እነዚህን 10 ስትራቴጂዎች በመጠቀም ያልዎትን በራስ መተማመን ከፍ አድርገው ችሎታዎን በትክክለኛው ሁኔታ ሥራ ላይ ማዋል ይችላሉ።

1. አለባበስዎ ጥሩ ይሁን (Dress sharp)።
የእርስዎ አካላዊ ገጽታ እና አለባበስ ላይ ከማንም ሰው በላይ እርስዎ የቀረበ እይታ እና ግንዛቤ አለዎት። ስለሆነም፣ ጥሩ ሆነው እንደማይታዩ በሚሰማዎት ጊዜ፣ ከሌሎች ጋር የሚያደርጉት የሃሳብ ልውውጥ ሂደት ውስጥ ምቾት እንዳይሰማዎት ያደርጋል። ስለራስዎ ገፅታ ግን መልካም አመለካከት ሲኖርዎ ምቾትዎ ይጠበቅና ከሰዎች ጋር የሚያደርጉዋቸው ግንኙነቶች ላይ ልበ ሙል ይሆናል። የራስ ገፅታን ጥሩ ለማድረግ የሰውነትን እና የገላን ንፅህና መጠበቅ፣ ፀጉርን እና ፂምን በቅጡ መከርከም እንዲሁም በወቅቱ ተቀባይ የሆኑ ፋሺኖችን በማዎቅ እና አቅም በፈቀደ መልኩ መከተል ይረዳል። ይህ ማለት በልብስ ላይ ብዙ ገንዘብ ማውጣት አለብዎት ማለት አይደለም። ነገር ግን፣ ብዙ ርካሽ ልብሶችን ከመግዛት ይልቅ፣ ጥቂት የተመረጡ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች መግዛት አለባበስን ጥሩ ለማድረግ ከመርዳታቸውም በላይ ለረጅም ጊዜ ዘመናዊ ሆነው እንዲቆዩ ስለሚያደርጉ ረዘም ላለ ጊዜ ወጪን ይቀንሳሉ።

2. ሲራመዱ ፍጥነት በተሞላበት ሁኔታ ይራመዱ (Walk faster)።
አንድ ሰው ስለ ራሱ ያለውን ስሜት ለማወቅ ብዙዎች ከሚጠቀሙባቸው ቀላል መንገዶች ውስጥ አንዱ አረማመዱን መመርመር ነው። ዝግ ብሎ የሚራመድ ነው? ሲራመድ ድካም ይታይበታል? ወይስ ሃይል የተሞላ እና አላማ ያለው አካሄድ አለው? በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች በፍጥነት ይራመዳሉ። አፋጣኝ የሆነ ጉዳይ ባይኖርብዎትም እንኳ ፈጠን ብለው በመራመድ የራስዎን መተማመን ከፍ ማድረግ ይችላሉ።

3. ሁሌም ጥሩ የሰውነት አቋም ያሳዩ (Have a good posture)።
በተመሳሳይ መንገድ፣ አንድ ሰው ሰውነቱን የተሸከመበት መንገድ ሰውየው ስላለው የራስ መተማመን ብዙ ይናግራል። የተጣበቁ ትከሻዎች እና የተልፈሰፈሰ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ሰዎች የራስ መተማመን ማጣትን ያሳያሉ። እራሳቸውን ከፍ አድርገው አይመለከቱትም። ጥሩ አቋም በማሳየት ግን በራስ መተማመን ይሰማዎታል። ቀጥ ያለ ሰውነት ይኑርዎ፣ ጭንቅላትዎን ወደላይ ከፍ ያርጉ፣ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩ የዓይን ለአይን ግንኙነት ያድርጉ። ይህንም ሲያደርጉ ሌሎች ላይ አዎንታዊ ስሜት ያሳድራሉ፣ እናም በፍጥነት የበለጠ ንቃት እና ኃይል ያሰማዎታል።

4. ለራስዎ ስለ ራስዎ ማስታዎቂያ ይስሩ (Do personal commercial)
ጠንካራ ጎኖችዎን እና ግቦችዎን የሚያጎሉ ከ 30-60 ሰከንድ የሚዎስዱ ንግግር ይጻፉ። ከዚያም በራስ የመተማመን ስሜት በሚፈልጉበት ጊዜ በመስታወት ፊት ለፊት በመቆም (ወይም ጭንቅላትዎ ውስጥ በማነብነብ) ለራስዎ ይንገሩ።

5. በምስጋና የተሞሉ ይሁኑ (Have gratitude)
ምስጋና ሊሰማዎት የሚያነሳሳዎትን ነገሮች ሁሉ በአዕምሮዎ ውስጥ በመዘርዘር የሚያስቡበት ጊዜ በየዕለቱ ይመድቡ። ያለፉትን ስኬቶችዎን፣ ልዩ ችሎታዎችዎን፣ ወዳጆችዎን እና አዎንታዊ እንቅስቃሴዎን ያስታውሱ። ምን ያህል እርቀት እንደመጡም ለመገንዘብ ይረዳዎታል፣ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ስኬት ለመሄድም በእጅጉ ያነሳሳዎታል።

6. ለሌሎች ሰዎች ስለ ጥሩ ስራቸው አድናቆትን ይለግሱ (Complement others)።
ስለራሳችን አሉታዊ በሆነ መልኩ ስናስብ፣ ብዙውን ጊዜ ሌሎችን ማጣጣል እና በጀርባቸው ላይ መጥፎ ነገር መሸረብ ላይ ትኩረት እናደርጋለን። ይህንን የኑሮ ዘይቤ ለማቋረጥ ሌሎች ሰዎችን የማመስገን ልማድ ይኑርዎት። ከሰዎች ጀርባ መጥፎ ነገር መመኘት ወይም መጠንሰስን አስወግደው በሰሯቸው ጥሩ ስራዎች አድናቆትን ለመግለፅ ይሞክሩ። በሂደቱ ውስጥም በጣም ይወደዳሉ፣ በዚህም በራስ መተማመን ይገነባሉ ። በሌሎች ውስጥ ምርጡን በመፈለግና በመመስከር በተዘዋዋሪ ምርጡን ወደ ራስዎ ዘንድም ያመጣሉ።

7. ከፊት ረድፍ ይቀመጡ (Sit in the front row)
ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ ጽ / ቤቶች እና ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ ብዙ ሰዎች መጨረሻ ለመቀመጥ ይጥራሉ። ምክንያቱም በቀላሉ መታየቱ ያስፈራቸዋል። ይህም በራስ መተማመን ማጣትን ያሳያል። በፊተኛው ረድፍ ላይ ለመቀመጥ ሲዎስኑ ይህንን ያለፈቃድ የሚመጣ ፍርሃት አሸንፈው በራስ መተማመንዎን መገንባት ይችላሉ። በተጨማሪም ከዋናው ፊት ለፊት ለሚነጋገሩ ሰዎች በይበልጥ ግልጽ ይሆናሉ።

8. ሃሳብዎን ይግለፁ (Speak up)
በቡድን ውይይቶች ወይም ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ሁኔታ ውስጥ ብዙ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመግለፅ ይቆጠባሉ። ምክንያቱም ሰዎች ከንግግራቸው ተነስተው እንዳይገምቷቸው ስለሚፈሩ ነው። ይህ ፍርሃት ትክክል አይደለም። ብዙ ጊዜ ሰዎች ከምናስበው ይልቅ የሰውን ሃሳብ የመቀበል ፍላጎት አላቸው። በእርግጥ ብዙ ሰዎች በተመሳሳይ ፍራቻ የተጠቁ ናቸው። በእያንዳንዱ የቡድን ውይይት ቢያንስ አንድ ጊዜ ለመናገር ጥረት በማድረግ የተሻለ የህዝብ ንግግር ክህሎት እንዲያዳብሩ ፣ ይበልጥ በራስ መተማመን እንዲኖርዎት እና በእኩዮችዎ ዘንድ መሪነትን እና ተቀባይነትን እንዲያገኙ ያደርግዎታል።

9. ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ልምድዎ ይሁን (Work out)
ልክ እንደ አለባበስ አይነት፣ አካላዊ ብቃት በራስ መተማመን ዘንድ ከፍተኛ ሚና አለው። ቅርጽዎ እንደተበላሸ ከተሰማዎት በሌሎች ዘንድ ዝቅ ተደርጎ የመታየት እና ሌሎችን መማረክ አለመቻል ስሜት ይሰማዎታል። አካላዊ እንቅስቃሴን በማድረግ አካላዊ ገጽታዎን ያሻሽላሉ፣ ኃይልን ያገኛሉ፣ ለአዎንታዊ ስራም ይነሳሳሉ።

10. የሚያደርጉት አስተዋፅዎ ላይ ያተኩሩ (Focus on contribution)
ብዙውን ጊዜ እኛ ስለምንፈልጋቸው ነገሮች እንጂ የሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች እና በሌሎች ላይ ስለሚመጣው ጥሩ ለውጥ አናስብም። ስለራስዎ ማሰብ ካቆሙ እና ለተቀረው ዓለም ላይ ለውጥ እንዲመጣ በሚያደርጉት አስተዋፅኦ (መዋጮ) ላይ ካተኮሩ፣ ያሉብዎት ጉድለቶች አያስጨንቁዎትም። ይህ በራስ መተማመንን ይጨምራል እናም በከፍተኛ ተነሳሽነት እና ውጤታማነት እንዲሳተፉ ያስችልዎታል። ለዓለም ጥሩ እያደረጉ በሄዱ መጠን የግል ስኬት እና እውቅናንም እየተጎናፀፉ ይሄዳሉ።

©የፍቅር_ሳይኮሎጂ
#በቅንነት ሼር አድርጉ

@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
# የሥራ ቦታ ውጥረትን ለመቀነስ የሚረዱ 4 መንገዶች
#Share

በሠራተኛ የሥራ ቦታ ተሳትፎ ላይ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል ውጥረት (ስትረስ) በዋነኝነት የጠቀሳል ፡፡ በጥናቶች መሠረት 25 % የሚሆኑ ሰራተኞች በጭንቀት ምክንያት በሥራ ላይ ውጤታማ መሆን ይቸግራቸዋል ፡፡ ይህም በአእምሮ ደህንነት እና በአጠቃላይ የንግድ ሥራ ስኬታማነት ላይ ሊኖረው የሚችለው ተፅእኖ ከፍተኛ ቢሆንም በስራ ቦታ ውስጥ የሚከሰተውን የጭንቀት (ስትረስ) ችግር ለመቅረፍ እርምጃዎችን ሲወሰዱ አይስተዋልም ። እንደ ሥራ አስኪያጅ ወይም የንግድ ሥራ ባለቤት ሠራተኞች ውጥረት ሲሰማቸው መንከባከቡ ለድርጅትዎ ወይንም ኩባንያዎን ስኬታማነት አስፈላጊ ነው፡፡ በሠራተኞችዎ በኩል የሚከሰተውን ጭንቀት ለመቋቋም ወይም ለመከላከል የሚረዱ ጥቂት ዘዴዎችን እናያለን ፡፡

#1 አስደሳች የስራ ስፍራን መፍጠር :

አብዛኛው የሰራተኛ ጊዜ የሚያልፈው በሥራ ቦታ ነው ፣ ስለሆነም ለሁሉም ሰው የሚደሰትበት አስደሳች ስፍራ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ በሥራ ቦታ ውስጥ እያንዳንዱን ነገር ወይንም ድርጊት ዝርዝር ፣ የቀለም ምርጫ እስከ ቢሮ ዕቃዎች ትናንሽ ነገሮችን ጨምሮ በጥንቃቄ መምረጥ ይገባል፡፡ እነዚህ ጥቃቅንና እና ትልልቅ የሚመስሉ ነገሮች በሠራተኛ ተሳትፎ ላይ ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ ፡፡ የቢሮ የቀለም ዐይነት ወይንም ምርጫ ማሻሻል ፣ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እፅዋትን መትከል ፤ አንዳንድ የምሳ እረፍት ላይ መዝናኛዎችን ማከል ሠራተኞች አዕምሮአቸውን ከሥራ ወደ ኋላ ለጥቂት ጊዜ እንዲያዝናኑ ሲረዳ ፤ የውጥረት መጠናቸውን እንዲቀንሱ ይረዳቸዋል፡፡

#2 የሥራ ቦታ ደህንነትን (ጤና) ማበረታታት

የግለሰቦችን ጭንቀትን ለማስታገስ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ማሳደግ በጣም ጥሩ ከሆኑት መንገዶች ውስጥ አንዱ ነው ፡፡ በተለይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፤ ሰራተኞች አዕምሮዓቸውን ከሥራ እንዲወጡ እና ስሜታቸውን እንዲያሻሽሉ ጥሩ መንገድ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ሰውነታችን ኃይልን የማቃጠል ስራውን ስለሚሰራ የደስታን ስሜት የሚያበረታቱ ኤንዶሮፊኖችን በመልቀቅ ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው ያድርጋል።

#3 ተለዋዋጭ ሥራን ማበረታታት

ሰራተኞች በችሎታቸው፣ በሙያቸው እና በራስ መተማመናቸው አማካይነት የሚቀጠሩት በተሰጣቸው ሰዓታት ውስጥ የሚጠብቁትን ዉጤት ማምጣት እንደሚችሉ በማመን ነው፡፡ አንድ ቢሮ ሠራተኞች ሥራቸውን ለማጠናቀቅ የሚያመቻቸው ቦታ ተደርጎ መታየት አለበት ፡፡ ስለዚህ ሥራቸውን በአኗኗር ዘይቤያቸው ዙሪያ ማካሄድ እንዲችሉ ተለዋዋጭ እና ርቀት ሳየገድባቸው ባሉበት እንዲሰሩ ያበረታቱ ፡፡ ሠራተኞችዎ ሥራቸውን በከፍተኛ ደረጃ እያከናወኑ እንደሆነ እስካመኑበት ድረስ ፣ መስሪያ ቤቱ ቢሮ ሚታጎሩበት ቦታ አንደሆነ ማሰብ የለባቸውም፡፡

#4 ለሰራተኛ እውቅናን መስጠት

በከፍተኛ ሠራተኛ ሁኔታዎች ውስጥ አንድ ሠራተኛ በጥሩ ሁኔታ እየሠራ ከሆነ አለመረጋጋት ወይንም የመጠራጥ ስሜት በሚፈጠርባቸው ሁኔታዎች ውስጥ እውቅናን ለሠራተኛዎት መስጠት የበለጠ ለመሻሻል እና በሠራተኞችዎ ላይ በራስ የመተማመን ስሜትን ለማጎልበት ይረዳል፡፡ ከበላይ ሃላፊዎች አውቅናን ማግኘት ለተቀጣሪው ከፍ ያለ ግምት እንዲሰማው ሲያደርግ በተጨማሪም አሁን ባለው ተግባራቸው ላይ ጥሩ አፈፃፀም እንዲያሳዩ ስለሚረዳቸው እጅግ ጠቃሚ ተግባር ነው ፡፡
👉ጠቃሚ ምክሮች👈

1. ከአለስፈላጊ ክርክሮች ጭቅጭቆች እና እሰጣገባዎች ራቅ።

2. ራስህን ገንቢ ሃሳብ ከሌላቸው (negative) ሰዎች አርቅ። ምክንያቱም አንተን ራሱ ሳትፈልገዉ እንደነሱ እንድታስብ ትገደድ ይሆናል፡፡

3. መቀበል የምትፈልገውን ስጥ።

4. ገንቢ ያለሆኑ ጎጂ አስታያየቶችን ከመስጠት ተቆጠብ።

5. ለሰዎች ፍቅርና አክብሮት ይኑርህ።

6. ይህ መቼም በእኔ አይደርስም አትበል፣የሕይወትን አቅጣጫ ሁሌም ቢሆን ማወቅ አንችልምና።

7. የመኪና የፊት መስታወት ትልቅ ሆኖ የኋላ መመልከቻውዠ መስታወት ግን ለምን ትንሽ የሆነ ይመስልሃል....ምክንያቱም የፊቱ ካለፈው ይልቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ስለዚህም የኀላዉን ሳትዘነጋ በትልቁ የሕይወት መስታወት ወደፊት እያየህ ተጓዝ::

#መልካም_ቀን !
#Share #Like
@Psychoet
ባንተ ውስጥ ያንተን እድገት የሚቃወም ጭራቅ አለ፡፡ከድህነት እንድታመልጥ አይፈልግም፡፡ከመጥፎ ጓደኞችህ ስትሸሽ ያመዋል፡፡ከሱስ ስትርቅ ይጨንቀዋል፡፡ፍላጎቱ ለጊዛዊ ደስታ ጊዜና ሐይልህን በከንቱ እንድታባክን ነው፡፡
+
በተለይ አዲስ ነገር ስትሞክር ይንጫጫል፡፡
"ይህን ማድረግ አደጋ አለው!! ጎመን በጤና! ዋ! ትከስራለህ !ይሳቅብሃል!!" በማለት አዛኝ መስሎ እንደ ሐውልት ያስቆምሃል፡፡በጊዜ ሂደትም ወደኃላ ጎትቶ ይጥልሃል፡፡በገዛ ራስህ ህይወት አቅም ታጣለህ፡፡እሱ ንጉስ አንተ ባርያ ትሆናለህ::
+
ባርነት አልሰለቸህም? የራስህ ህይወት ንጉስ መሆን አላመማረህም? ከጭራቁ እስር ቤት ነጻ መውጣትስ? በፈለከው ሰዓት የፈለከውን ነገር ማድረግስ? የራስህን ህይወት መኪና መሪ መጨበጥስ? ህልምህን አሳክተህ ከስኬት ተራራ ጫፍ መሆንስ? አያጓጓህም? መልስህ "አዎ!" ከሆነ በመጀመርያ በውስጥህ ያንቀላፋውን ጀግና ቀስቅሰው፡፡
+
ባንተ ውስጥ ያንቀላፋ ምንም ነገር ማድረግ የሚችል ጀግና ሰው አለ፡፡ይህ ጀግና ገራሚ ሐይል ነው፡፡ይህንን ሐይል ማድመጥ ጀምር፡፡የጭራቁን አቅምና ሐይል ከውስጥህ ነቅሎ ይጥለዋል፡፡
+
ጭራቁ ማንነትህ ፈሪ ነው፡፡ጀግናው ማንነት #አማኝ ነው፡፡ጭራቁ ማንነትህ ሰነፍ ነው፡፡ጀግናው ማንነትህ #ለፊ ነው፡፡ጭራቁ ማንነትህ "ሰው ምን ይለኛል?" ይላል፡፡ስህተት ይፈራል፡፡ፍጹም መስሎ ለመታየት ይሞክራል፡፡ጀግናው ማንንትት ግን "እኔ ራሴን ምን እላለው? ፈጣሪስ ምን ይለኛል?" ይላል፡፡ፍጹም መስሎ የመታየት ምኞት የለውም፡፡እሱ የህይወት ዘመን ተማሪ ነው፡፡ ጭራቁ ማንነትህ ጊዛዊ ደስታን ብቻ ይፈልጋል፡፡ጀግናው ማንነትህ ግን ረጅሙን የውስጥ ሰላም፣ ፍቅር፣ ወሳጣዊ ደስታና ስኬት ይሻል

የላቀ አስተሳሰብና ክህሎት በማስቀደም ስኬትን መጎናጸፍ ።😍😍😍
©FB
@Psychoet
ከመሞታችሁ በፊት ማድረግ ያለባችሁ 20 ነገሮች
Join Telegram www.tg-me.com/psychoet

1.ትላንትናን እና ነገን እያሰባችሁ አትጨነቁ፡፡ ትናንት አልፏል ነገ አልመጣም ስለዚህ ዛሬን ቀን በሙላት ፣ በደስታ ፣በሰላም ለመኖር ጥረት አድርጉ፡፡

2.የበደሏችሁን ሰዎች ይቅርታ አድርጉላቸው ፡፡

3.ሁሉንም ሰው በእኩል ዓይን እዩ፡፡

4.ወደዚህ ምድር ያመጧችሁን እናትና አባታችሁን ውደዱ ፣ አክብሩ ፣ ታዘዙ ። *

5.የምትጠሉትን ስራ አትስሩ፡፡

6.የሕይወት ግባችሁን በመለየት በቅጡ ኑሩ፡፡

7.መስታወት ውስጥ ራሳችሁን ተመልክታችሁ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ራሳችሁን ውደዱ፡፡

8.እዚህ ምድር የመጣችሁት በፈጣሪ አላማና እጅግ በጣም ጠቃሚ ሰዎች እንደሆናችሁ አስቡ ፡፡

10.ዘወትር መሄድ እፈልጋለሁ ወደምትሉት ስፍራ ሂዱ፡፡

11.በየቀኑ ለሌሎች ቢያንስ አንድ መልካም ነገር አድርጉ፡፡*

12.ለውጥን በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ ሁኑ፡፡

13.ሁሉንም ዓይነት የሕይወት ትምህርት በፀጋ ተቀበሉ፡፡

14.የሕይወት ፈተና ውስጥ ያለውን መልካም አጋጣሚ አስተውሉ እንጂ ተስፋ አትቁረጡ፡፡

15.በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ አዎንታዊ እና በጎ አሳቢ ሆናችሁ ዝለቁ፡፡

16.በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይሆን ሰውን ሁሉ ለመውደድ ጣሩ ፡፡*

17.ከቁሳ ቁስ ጋር ያላችሁን ትስስር አላሉ፡፡

18.ልባችሁን ተከተሉ፡፡

19.ሁልጊዜም ትልቅ በመሆን ሌሎችን አነቃቁ፡፡

20.ከሰዎች ሁሉ ጋር ተጫወቱ በሰላም በመግባባት ኑሩ ፤ የተቸገሩትን ደግፉ ፡፡ ደግሞም ይህን ጽሑፍ #Share አርጉ ፡፡*😍😍😍

ዘጠነኛውን አንብባችሁታል ግን? .......
የዘለልኩት እስቲ እኔ ያልጠቀስኩት መደረግ ያለበት ነገር #Comment እንድታረጉልኝ ነው?
#Comment

ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ !


(በነጋሽ አበበና ናሁሰናይ ፀዳሉ)
©zepsychologist
Join Telegram www.tg-me.com/psychoet
እንደምን አላችሁ ቤተሰቦች !

ይኼን በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ መጪውን የገና በዓል በማስመልከት የተዘጋጀውን የአንድ ሳምንት የስጦታ መስጫ መርሐግብር ቪዲዬ ቪዲዮ እንድትመለከቱ እጋብዛለሁ ፡፡
http://shorturl.at/pBY67


#ስጦታችሁ_ለልባችን!
እንኳን ለ2013 ዓ.ም የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በ2012 የገና ስጦታ ዝግጅታችን በእናንተ እርዳታ ለበርካታ ሕፃናት መድረስ ችለናልና ዘንድሮም “ስጦታችሁ ለልባችን” ብለን መጥተናል፡፡
ከታህሳስ 21 እስከ 28 ድረስ በልብ ማዕከል በግልዎ ወይም ከወዳጅ ዘመድ ጋር በመገኘት የገና በዓል ስጦታዎትን ለልብ ሕሙማን ሕፃናት ይለግሱ፡፡
#ይህንን_መልዕክት_በማጋራት_ስጦታዎትን_መጀመር_ይችላሉ!
shorturl.at/pBY67
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ማኅበራዊ ፍርሃት ማስወገድ
Telegram Channel www.tg-me.com/Psychoet
ይህን ጠቃሚ ትምህርት #Share እናድርገው

ማኅበራዊ ፍርሃት #ብዙ_ሰው_በተሰበሰበበት ቦታ ለመናገር ወይም አንድን ድርጊት ለመፈጸም በተዳጋጋሚ የሚፈጠር በብዙ ግለሰቦች ላይ የሚስተዋል #ምክኒያታዊ_ያልሆነ_ፍርሃት ነው፡፡ ይህ #የጭንቀት ዓይነት ያለባቸው ግለሰቦች ብዙ ጊዜ ንግግር ያለበት ተግባር አጥብቀው #ይሸሻሉ ምክኒያቱም አይደለም ንግግር አድርገው ገና ለማድረግ ሲያስቡ የሚሰማቸው #የፍርሃት ወይም #የጭንቀት_ስሜት ከፍተኛ በመሆኑ የተነሳ፡፡ ከህጻናት በስተቀር ማኅበራዊ ፍርሃት ያለባቸው ሰዎች ፍርሃታቸው ምክኒያታዊ እንዳልሆነ ይረዳሉ ምንም እንኳን ይህ ከፈርሃታቸው ባይታደጋቸውም፡፡
★እነዚህ ከታች የተዘረዘሩት የማኅበራዊ ፍርሃት ተጠቂዎች ላይ የሚስተዋሉ ተደጋጋሚ ምልክቶች ናቸው፡-

1.ሰው የተሰበሰበበት ቦታ ንግግር ለማድረግ አጥብቆ መፍራትና በትምህርት ገበታም ሆነ በስራ ቦታ የተዘጋጁትን በአግባቡ ማቅረብ አለመቻል

2.እንደ ካፌ፣ ሬስቶራንት፣ ቤተ-መጻሕፍትና ሌሌች ብዙ ሰዎች ባሉበት ቦታ ሰዎች እኔን እየተመለከቱኝ ነው ብሎ መሳቀቅ ፣ ከልክ በላይ አንገት አቀርቅሮ መጓዝ

3.ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ንግግር ለማድረግ በሚያስቡበት ጊዜ ሌሎች ሰዎች ይተቹኛል ብሎ ማሰብ

4.ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ንግግር ሲያደርጉ በላብ በጠመቅ ወይም ልዋረድ እችላለሁ ብሎ በፍርሃት ማሰብ

5.ብዙ ሰው ባለበበት ቦታ ንግግር ለማድረግ የሆነ ያልሆነ ምክኒያት በመደርደር እራስን ማቀብ

6.አዲስ ሰው ጋር ለመገናኘት ተደጋጋሞ የሚከሰት ፍርሃት

7.ብዙ ሰው ባለበት ቦታ ምግብ በሚመገቡት ጊዜ ትንታ ወይም መታነቅ እንዲሁም ምግቡ ሊዝረከርክብኝ ይችላል ብሎ መፍራት

8.ከእነዚህ ጋር ተዛምዶ የሚከሰት እንደ የልብ ምት መጨመር፣ ላብ ላብ ማለት፣ የሰውነት መንቀጥቀጥና የመሳሰሉት ፍርሃት ወለድ አካላዊ ለውጦች ናቸው፡፡

፠፠፠ መፍትሄ ፠፠፠

1.የአስተሳሰብ ለውጥ፡-

ብዙ ጊዜ ማኅበራዊ ፍርሃት እንዲከሰት የሚያደርጉ ከበስተጀርባ ያሉ አሉታዊ አመለካከቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ለራስ የሚሰጥ ዝቅተኛ ግምት አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ለዚህ ፍርሃት መከሰት አስተዋጽኦ የሚያበረከቱ ምክኒያታዊ ያልሆኑ አሉታዊ አስተሳሰቦችን ነቅሶ በመለየትና በአዎንታዊ አመለካከት መተካት፡፡

2.መለማመድ፡-

ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ቦታ መናገር ስለሚያስፈራን ንግግር የምንሸሽ ከሆነ የፍርሃቱ መጠን እንዲጨምር መፍቀድ ነው፡፡ ከሸሻችሁት በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው መቼም ቢሆን ከዚህ ችግር እንደማትገላገሉ ነው፡፡ ስለዚህ እራስን ቀስ በቀስ ማለማመድ ዋነኛ መፍትሄ ነው፡፡

3.ስራ ላይ ማተኮር፡-

ብዙ ጊዜ የማኅበራዊ ፍርሃት ተጠቂዎች ከሚሰሩት ስራ ይልቅ ሌሎች ሰዎች ስለሚሰጧቸው አስተያየትና ምላሽ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ እዚህ ላይ መታሰብ ያለበት ከስራው ይልቅ አድማጭ ተመልካች ላይ የምናተኩር ከሆነ መጀመሪያ በተገቢው ስራን መስራት እንችልም ምክኒያቱም ቀልባችን ሌሌች ሰዎች ላይ ነውና፡፡ ሲቀጥ ልሌሎች ሰዎች ላይ ስናተኩር የበለጠ ስለፍርሃት ስሜታችን ላይ እንድናተኩርና የበለጠ አሉታዊ ሃሳቦች እንዲፈጠሩ ይገፋፋል፡፡

4.ጡንቻን ማዝናናት መለማመድ፡-

ከውስጥ ከሆድ መተንፈስ በመለማመድ ጭንቀቱ የሚፈጥረውን የረብሻ ስሜት መቀነስ፡፡ ይህ በጣም ቀላልና የትም ቦታ ሊለማመዱት የሚችሉት ዘዴ ነው፡፡ ለተወሰነ ደቂቃ (እስከ 10 ሴኮንድ) ወደ ውስጥ በመተንፈስ ትንፋሽህን መያዝ ከዚያም መልቀቅ፡፡ እንደገና ወደ ውስጥ ትንፋሽን በመያዝ አሁንም ወደ ውጪ መተንፈስ፡፡በተደጋጋሚ ይህን በማድረግ የጭንቀት ስሜቱን ማቅለል ይቻላል፡፡ ይህን ዘዴ ጭንቀቱ ቀለል እሰከሚልድረስ መከወን ይቻላል፡፡

5.የማህበራዊ ክህሎት ስልጠና መውስድ፡-

ዓይንን እየተመለከቱ ማውራት፣ ፈገግታ፣ የንግግር ፍሰትን መጠበቅና የመሰሳሰሉት ልምምዶች በንግግርና በሌሎች ማህበራዊ ተግባቦት ላይ ውጤታማነታችንን ሲለሚጨምሩ ለወደፊት የበለጠ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ መናገርና ሌሌች ተግባሮችን ለመፈጸም አወንታዊ ማበረታቻዎች ናቸው፡፡

★★★ከዚህ ጋር በተያያዘ ሥነልቡና ፔጅ የተዘጋጀውን የአንድ ወር ተግባራዊ ልምምድ ስልጠና ብትካፈሉ ብዙ የአመለካከትና የባሕሪ ለውጥ እንደምታመጡ እርግጠኛ ነኝ ፡፡ ስልጠናው ከ ኹለት ሳምንት በኀላ ይጀምራል ፡፡
# ★★★

6.ሌላው presentation ሲኖርብን ከመስታወት ፊት በመቆም በደንብ መለማመድ ፣ ስናወራ ምን እንደምንመስል ማየትና ራሳችንን እያረምን ደጋግሞ መለማመድ ፡፡ በተጨማሪ ደፋር ሰዎች ራሱ ብንሆን አንዳንድ ያልተዘጋጀናቸውን ነገሮች ስናቀርብ / ባላሰብነው ሁኔታ ውስጥ ስንገኝ ፍርሀት ሊከሰት ስለሚችል ሁልጊዜ ጠንቃቃ መሆን ይጠበቅብናል ደግሞም ከልክ ያለፈ በራስ መተማመንም ማስወገድ መልካም ነው ፡፡

የፍርሃት ስሜት ወይም ጭንቀት የዕለት ተዕለት ህይዎታችን በደስታ እንዳንመራ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ማኅበራዊ ፍርሃትም እንደዚሁ በህይወታችን ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ ተጽኖ ይኖራል፡፡ ለችግሩ መፍትሄ ማፈላለግ እንጂ ለምን ይህ ተከሰተብኝ ብሎ እራስን መኮነንና ጥፋተኛ ማድረግ አይገባም ምክኒያቱም ምንጩ እኛ ሳንሆን አስተዳደጋችን ፣ አካባቢያችን ፣ አስተማሪዎቻችን ፣ ሊሆኑ ይችላሉና ፡፡ ስለዚህ በዚህ ፍረሀት ያላችሁ ሰዎች የጠቀስኳቸውን ነገሮች በደንብ ተግባራዊ አድርጉ ፡፡ ጥያቄ ካላችሁ ጻፉልኝ፡፡

መልካም ቀን ይሁንላችሁ ።
(በአሸናፊ ካሳሁን እና ናሁሰናይ ፀዳሉ)
©zepsychologist

በቴሌግራም በዚህ አግኙኝ www.tg-me.com/Psychoet
_________________________________
በተለያዩ ማህበራዊ ፍርሀት ያለባችሁ በተለይም በትምህርት ፣ በግል ስራ እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት የምትሰሩ ወጣቶች በስልጠናው በመገኘት ክህሎታችሁን አሳድጉ ፣ ስለ እራሳችሁና ችሎታችሁ በቂ ግንዛቤ አግኙ፡፡ስልጠናው ከ ኹለት ሳምንት በኀላ ይጀምራል ፡፡ ምዝገባ ሲጀምር በዚህ ፔጅ እናሳውቃለን
_________________________________
#ይቻላል
JOIN TELEGRAM www.tg-me.com/psychoet

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
©ZePsychology

መልካም ቀን!
#Share_it
የበአል ኹለት ገጽታ

#አንዱ ለመሸመት ፣ ሌላው ለመሸጥ

#አንዱ በዓሉን ለማሳለፍ ፣ ሌላው በዓሉ ቶሎ እንዲያልፍለት

... ሌላውን እናንተ ጨምሩበት ።

@psychoet
#መልካም_ጥር_ወር !
T.me/psychoet

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ፍትህ ፣ ሰላም ፣ ልማት የምንሰማበት ይሁንልን ፡፡

ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ ።
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

ለምትወዱት ጓደኛ #መልዕክቱን አስተላልፉ

@Psychoet
#ስሜታዊ_ምክንያት
#Emotional_Reasoning

በሰነ ልቦና (ሳይኮሎጂ) የትምህርት ዘረፍ የሰው ልጅ ጥሩ ስሜት እንዳይሰማውና ያልተገባ አስተሳሰብ እንዲያስብ ከዛም በዘለለ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እንዲያከናወን ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ የተዛባ አመለካከት (አስተሳሰብ ) ነው፤ misinterpretation of reality ብንለውም ይገልፀዋል። የሳይኮሎጂ ጠበብቶች Cognitive Distortion ይሉታል ።

Cognitive Distortion በአይነቱ ብዙ ቢሆንም አንዱን እንኳን ብንጠቅስ Emotional Reasoning የሚል እናገኛለን።

ስሜታችን በሚነግረን መልእክት እውነታውን ያላገናዘበ ድምዳሜ ላይ መድረስ ማለት ነው። እየተደረገ ያለውን ነባራዊ እውነታ ትተን የስሜት መርህ መከተል የሚል አንደምታ አለው።

ይህ ማለት ማሰብ ትተን በስሜት መነዳት።
አንድ ምሳሌ እናንሳ ፦ አንድ ሰው በውስጡ የቅናት ስሜት ስለተሰማው ብቻ ሚስቱ ከሌላ ወንድ ጋር ታማግጣለች ብሎ ድምዳሜ ላይ ሊደርስ ይችላል ። እዚህ ላይ መገንዘብ ያለብን ሚስቱ ለትዳሯ ታማኝ እያለች ነው።

ስለዚህ በEmotional Reasoning እሳቤ መሠረት በነገሮች ላይ የሚኖረን አስተሳሰብ፣ እምነትና አቋም የሚወሰነው በምናስበው ምክንያታዊ አስተሳሰብ ሳይሆን እውነታውን ያላገናዘበ በሚሰማን ስሜት ነው።

Reasoning based on how we feel is something we all have done far more often than we'd like to believe. It's a trap, a trick of our brain, which sometimes has a hard time correctly interpreting and managing our emotions.

Likewise the evidence we observe won't matter either , because every objective and rational fact is deliberately ignored or rejected in favor of the "truth " assumed by our feelings.

©ከማኅበራዊ ሚዲያ
2024/09/29 07:18:17
Back to Top
HTML Embed Code: