Telegram Web Link
#ሃያ አንዱ ማኅበራዊ ሕግጋት
መልዕክቱን አንብበው ሲጨርሱ #Share ያድርጉት

(Sicial Rules ተብለው የተዘረዘሩ የማኅበራዊ ሕይወት ሕግጋትን ስመለከት ለኛስ አትጠቅምም ወይ ብዬ ነው ወዲህ ማምጣቴ)
==================
1. ይሰለቹሃል
አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ!

2. 'ሼም ነው' ነው
የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!

3. አይባልም
"... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም።

4. ክፈል
አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ።

5. ነውር ነው
ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ።
============

6. አታቋርጥ
ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ። ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው።

7. አታብሽቅ
ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው። ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ።

8. አመሥግን
ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመሥግን።
9. ያለስስት አድንቅ
ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው።

10. ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ
ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ።
===================

11. ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ
ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል።

12. ስነ ስርዓት
ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው።

13. ክብር ለሁሉም
ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም።

14. ስልክህን አስቀምጥ
ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው።

15. አድብ
ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው።
==========================

16. ተቆጠብ
ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ።

17. መነጽርህን አውልቅ
ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው!

18. አትሳሳት
በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ።

19. ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት
በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው። ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው።

20. ዕቃ መልስ
የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ።

21. አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ
የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። ሌሎች እንዲወያዩበትና እንዲተቹት ክፍት አድርገው፤ አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ። ነገርህን ደገፉትም አልደገፉት ምንጊዜም ቢሆን ላነሳኸው ሐሳብ ጥሩ ግብዓት አይጠፋም። ልክ አልሆን ወይ እያልክ ወይም ሐሳቤ ያንስ ይሆን ወይ ብለህ አትሸማቀቅ፤ ተሸማቀህ ትቀራለህ!

www.tg-me.com/psychoet
©Abraham Tsehaye
ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ መጨነቅን ለማቆም ቀላል ዘዴዎች
Telegram www.tg-me.com/psychoet

‘’የማይባል ነገር ተናገርሁ እንዴ? እንዴት እንደዚህ አደርጋለሁ? ሰዎች እኮ መሃይም :ገገማ:የሚያናድድ ሰው ነው/ነች ይሉኝ ይሆናል’’ እያልን ራሳችንን የምናስጨንቅ ስንቶቻችን ነን! ሌሎች ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ በመጨነቅ አእምሯችንን በጨለማ ቦታ እንዲንከራተትና ራሳችንን በመጠራጠር የስጋት ስሜት እንዲሰፍንብንና እንዳንረጋጋ እያደረግን መሆኑን ልናውቅ ይገባል:: ለነገሩ ሁላችንም ሰዎች ስለእኛ ያላቸው ሃሳብ/አስተያየት ምን ይሆን ብለን መጨነቅ እንደሌለብን እናውቃለን ወደ ተግባር ለመቀየር ግን ስንቸገር እንታያለን:: ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዘዴዎች ብንጠቀምባቸው ይረዱናል!

1. የሰዎችን አዕምሮ ማንበብ እንደማንችል መረዳት፡- እስኪ ሰዎች ስለእኛ የሚያስቡትን በእርግጠኛነት ማወቅ እንችላለን? ብዙ ጊዜ ነገራትን ሳናጣራ ይሆናል በማለት ብቻ ማወቅ እንደምንችል ነው የምናስበው ይህ አስተሳሰባችን ደግሞ ለህይወታችን ፀር ወደሆኑ ድምዳሜዎች/ዉሳኔዎች ይመራናል::ስለዚህ እነዛ ሰዎች ሃሳባቸውን የሚገልጹበትን ዕድል አግኝተው ሃሳባቸውን እስካልገለጹልን ድረስ ስለምን እንደሚያስቡ ማወቅ በፍጹም አንችልም፡፡

2. በቋሚነት ለሚጠቅመን ነገር መስራት:- ከሌሎች ሰዎች የሚሰነዘሩ የኩነኔ አስተያየቶች በእርግጥም እኛን ይጎዱናል ነገር ግን ከእነዚህ ሰዎች የሚመጣውን አሉታዊ ምላሽ በመፍራት የምናጣቸው/የምናሳልፋቸው መልካም ዕድሎች ጥለውብን ከሚያልፉት የአእምሮ ጠባሳ አይበልጥም፡፡ እነዚህ የኩነኔ/አሉታዊ አስተያየቶች የሚያደርሱብን ጉዳት ቅጽበታዊ ሲሆን ባጣናቸው/ባመለጡን መልካም ዕድሎች ምክንያት የሚደርስብን ጸጸትና ቁጭት ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ስር እየሰደደና እያደገ ነው የሚሄደው፡፡ ስለዚህ በቋሚነት የሚጠቅመንን ነገር ለማግኘት ጊዜያዊ የሆኑ ተቀባይነት ማጣትን ለመቀበል ፈቃደኞች እንሁን::

3. ራስን ከመኮነን/በራስ ላይ ከመፍረድ መቆጠብ:- እስኪ ሰዎች ምን ይሉን ይሆን ብለን የምንጨነቅበትን ሃሳብ ለሰከንድ ቆም ብለን እናስበው! በእርግጠኝነት እኛ ለራሳችን የምናስበውን ነገር ላይ ነው ሌሎችም እንደዚ ያስባሉ ብለን የምንሰጋ፡፡ ስለዚህ በራሳችን ላይ መፍረድን አቁመን(ራስን ከመኮነን ተቆጥበን) እኛነታችንን ከተቀብለነው ወይም ለራሳችን ጥሩ ግምት ከሰጠን ሌሎቹ ስለእኛ ለሚሰጡት/ለሚያስቡት ሃሳብ ፍርሃትና ስጋት አይኖረንም ማለት ነው፡፡

4. ሌሎች ሰዎችን መኮነንን/በሌሎች ላይ መፍረድን ማቆም፡- ሰዎችን እየገመገምን፡እየኮነንና እየፈረድንባቸው የምንኖር ከሆነ እነሱም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚፈርዱብን ነው የምናስበው፤ ስለዚህ በእነሱ ላይ ከመፍረድ ይልቅ ህይወታችንን ለማሻሻልና ለማደራጀት እንደሚያግዙን ቆጥረን ብናደንቃቸውና ብናበረታታቸው የበለጠ ተጠቃሚዎች መሆን እንችላለን፡፡

5. ስለእኛ አለመሆኑን መረዳት፡- ሰዎች በራሳቸው እይታ ከደረሰባቸው ክስተት፡ ቁስል፡ ፍራቻና እንከን የተነሳ ለነገሮች የተለያዩ አሉታዊ ምላሾችን ይሰጣሉ ነገር ግን የእነሱ ምላሽ ከእኛ ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባናል፡፡ ለምሳሌ የሆነ ቢዝነስ ለመጀመር ብንወስንና አንድ ሰው ”እመነኝ ይህንን ስራ ከጀመርህ በሚቀጥሉት ወራት አሊያም ዓመታት ምንም ዓይነት የእረፍት ጊዜ አይኖርህም” ቢል ሰውዬው የተናገረው ቢዝነስ መጀመር ላይ ያለውን ሃሳብ/አመለካከት እንጂ እኛን በተመለከተ እንዳልሆነ ለይተን መረዳት ይጠበቅብናል::

6. በሚያስደስተን ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ:- ይህን ባደርግ ሰዎች ይፈርዱብኛል በማለት የሚያስደስቱንን ተግባራት ከማድረግ የምንገደብ ከሆነ(የማኅበረሰቡን እሴቶች በጠበቀ መልኩ) ጊዜያችንን ምንም ዓይነት ጥቅም በሌለው ጭንቀት እያባከንነው መሆኑን እናስተውል፡፡ ስለዚህ በህይወታችን ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የሚችለውን ብርቅ የሆነውን አቅምና ኃይላችንን በመሸርሸር ፈንታ እኛን በሚያስደስቱን ነገራት ላይ ትኩረት ልናደርግ ይገባል፡፡

7. የሚያውኩንን ነገሮች መለየት፡– ሌሎች ሰዎች አሉታዊ በሆነ መልኩ ይገመግሙናል/ይፈርዱብናል ብለን የምንጨነቀው ምናችንን በተመለከተ ነው? በስራችን ሁኔታ: ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት: ምናልባትም በክህሎታችንና ነገሮችን በመመርመር ባለን አቅም ሊሆን ይችላል:: ስለዚህ በውስጣችን መረጋጋት እንዳይኖር የሚቀሰቅሱ ነገሮችን መለየትና ማሻሻል ከቻልን ማሻሻል አሊያም እንዳሉ መቀበል ያስፈልጋል:: ምክንያቱም ከሁኔታዎች ጋር ሰላም መፍጠር ከቻልን የሰዎች አጸፋዊ ምላሽ አያስጨንቀንም ማለት ነው::

8. ራሳችንን መቀበል:– ፍጹም አለመሆናችንን፡ እንከንና ድክመቶች እንዳሉን መቀበል ነገር ግን አቻ የሌለን(ልዩ) በዓለም ላይ እኛን የሚመስል ሰብዕናና ተሰጥኦ የታደለ ሰው እንደሌለና ወደፊትም እንደማይኖር ልናስተውል ይገባል፡፡

9. አጸፋዊ ምላሾችን መጠበቅ/ተስፋ ማድረግ፡- በሰዎች ዘንድ የሚፈጠረውን አጸፋዊ መልስ በመፍራት ፈንታ ያ ምላሽ ሊፈጠር እንደሚችል አስቀድመን ተስፋ ማድረግ አለብን(የሰዎችን ስሜት ለመቀስቀስ መፍራት የለብንም) ምክንያቱም በሰዎች ዘንድ አሉታዊም ይሁን አዎንታዊ ምላሽ መፍጠር ካልቻልን ምናልባትም ራሳችንን የመሆን ድፍረቱን ልናጣ እንችላለንና፡፡

10. እየኮነኑን/እየፈረዱብን ነው ብለን ካሰብናቸው ሰዎች ጋር ማውራት፡- እንዲያው ሁኔታዎች ተመቻችተውልን ስለእኛ መጥፎነት ያስባሉ/እየፈረዱብን ነው ብለን ከምናስባቸው ሰዎቸ ጋር ተቀራርበን ብናወራ እስከምንገረም ድረስ ምንም ባለጠበቅነው ሁኔታ አዕምሯቸው በብዙ ጭንቀቶች እንደተሞላ ልናውቅ እንችላለን፡፡ ማን ያውቃል ልክ እኛ እንደምንጨነቀው እነሱም ሌሎች ሰዎች ስለእነሱ ምን ሊያስቡ/ሊሉ በሚችሉት ሃሳብ እየተጨነቁ ሊሆን ይችላል እኮ፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ግልጽ በማድረግ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ተቀራርበን ሃሳብ ማንሸራሸር ያስፈልጋል::

በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩትን ሃሳቦች ወደ ተግባረ ከቀየርናቸው እኛም መቀየር እንችላለን!

(በአለበል አዲስ)
©Zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
ራስን ማክበር

"ባለቤቱ ያቃለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይቀበለውም"
"ባለቤቱ የናቀውን ጨው አሞሌ ነው ብለው ይጥሉታል" እነዚህ ድንቅ ኢትዮጵያዊ አባባሎች ራስንና የራስ የሆነን ነገር ስለማክበር ብዙ ይናገራሉ፡፡

እንደሚታወቀው በአካባቢያችን ያሉ ትጉህ ሰራተኞች ፣ ጥበበኞችና አዋቂዎች በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ተከባሪነትና ተቀባይነት አላቸው ፤ በተቃራኒው ደግሞስ ፥ ሳይሰሩ ራሳቸውን በኢኮኖሚ ያልቻሉ፣ በሌሎች ጥገኛ የኾኑ ያን ያህል ተቀባይነትም ሆነ ክብር ከሚኖሩበት ማህበረሰብ አይቸራቸውም ፡፡

በምንኖርበት ቤት ፣ ሰፈር ፣ ማህበረሰብ ከመከበራችንም ሆነ ከመናቃችን በፊት ትልቁ ወሳኝነት ያለው እኛ #ለእራሳችን ያለን #አክብሮትና #ዋጋ ነው ፡፡ ብዙዎቻችን ለእራሳችን ክብር ስለሌለን በሌሎች አንከበርም ፣ ራሳችንን ስለማንሰማ ሌሎች አይሰሙንም ፡፡

ወደድንም ጠላንም ኹሉም ነገር የሚጀምረው ከራስ ነው ፡፡ ዋናው ቁም ነገር ግን ራስን አግዝፈን ሌላውን እንዳናኳሽሽ ፣ ራስን ከፍ አርገን ሌሎችን እንዳንረግጥ ነው ፡፡ ነገር ግን ለራሳችን የምንሰጠው ዋጋ ፣ አክብሮት ፣ ጊዜ ያለንበትን ኾነ የወደፊት ሕይወታችንን ይወስናል ፡፡

መከበር የሚፈልግ በመጀመሪያ ራሱን ያክብር ከዛም ሌሎችን ያክብር ፡፡
መልዕክቱን #share በማረግ ለሌሎችም እናድርስ
@psychoet
ከኢንተርኔት ሱሰኝነት ነጻ መውጣት

ከኢንተርኔት ሱሰኝነት ነጻ መውጣት የሚቻልባቸ መንገዶች

1.የኢንተርኔት ሱሰኝነት መድኃኒት የሌለው በሽታ አይደለም፡፡ 
ሱሰኝነትን እንደ በሽታ ከታሰበ ሰዎች የመቆጣጠር አቅም እንደሌላቸው እንዲሰማቸው ያደርጋል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ሱሰኝነትን መድኃኒት እንደሌለው በሽታ ያስባሉ፡፡ ይህ ዓይነት አስተሳሰብ ሰዎች በሱሰኝነት ቁጥጥር ሥር እንዲኖሩ የሚያደርግ የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው፡፡

2.በሱሰኝነት  የተያዙ  ሰዎች  ፈቃደኞች  ከሆኑ  ሱሰኝነትን ማሸነፍ ይችላሉ፡፡ 

ሰዎች ውሳኔ ካደረጉና ራሳቸውን መግዛት ከመፈለጉ ከማንኛውም ሱስ ነጻ መውጣት ይችላሉ፡፡ የሰዎች የማሸነፍ አቅም ከማንኛውም የሱስ ኃይል ይበልጣል፡፡ ይህ ግን እውን የሚሆነው ቆራጥነት ያለበት ውሳኔ ሲኖር ነው፡፡

እንግዲህ ሱሰኝነት በሽታ ባለመሆኑ ሰዎች ምንም ህክምና እንዲሁም የስነ-ልቦና እርዳታ ሳያገኙ በራሳቸው ከዚህ ችግር መውጣት ይችላሉ፡፡ አንዳንዶች ግን የባለሙያ ድጋፍና ምክር በሚያገኙበት ጊዜ አቅማቸውን ተጠቅመው ሱሱን ማሸነፍ ይችላሉ፡፡

በኢንተርኔት ሱሰኝነት የተያዙ ሰዎች ራሳቸውን በመርዳት ከዚህ ችግር መውጣት የሚችሉባቸው መንገዶች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡-

3. ኢንተርኔትን  በተወሰነ  ጊዜ  ለተወሰነ  ዓላማ  ብቻ  መጠቀም

በኢንተርኔት ሱሰኝነት የተያዙ ሰዎች ከዚህ ሱስ ለመላቀቅ ኢንተርኔትን ፍጹም ማቆም የለባቸውም፡፡ በዚህ ዘመን ኢንተርኔት መጠቀምን መተው ተግባራዊ ሊሆን የሚችል እርምጃ አይደለም፡፡ ምንክንያቱም በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰዎች ህይወት በአብዛኛው ከኢንተርኔት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ስለዚህ ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው እርምጃ ኢንተርኔትን ኃላፊነት ባለው ሁኔታ ለተገቢ ዓላማ ብቻ መጠቀምን መለማመድ ነው፡፡

እነዚህ ተገቢ ዓላማዎች የሚባሉ ምንድናቸው የሚል ሐሳብ ከተነሣ ኢሜይል መቀበልና መላክ፣ በኢንተርኔት አማካኝነት መነገድ፣ ተገቢ መረጃዎችን ብቻ መፈለግ፣ … ያስፈልጋል፡፡

4. ከኢንተርኔት ነጻ የሆነ የህይወት ዘይቤን መልመድ

የኢንተርኔት ሱሰኝነትን ለማሸነፍ ከኮምፕዩተርና ከሞባይል ስልክ ጋር ሁልጊዜ ያልተቆራኘ የህይወት ዘይቤን መማር አስፈላጊ ነው፡፡ ከኢንተርኔት ጋር ያልተገናኙ አዎንታዊ ሥራዎችን/ ክንውኖችን ማቀድና ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በኢንተርኔት ከመጠመድ ይልቅ ስፖርት መሥራት፣ መጻሕፍትን ማንበብ፣ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን መሥራት፣ በትርፍ ጊዜ መሥራት የሚፈልጉአቸውን ነገሮች መሥራት ይችላሉ፡፡

5. መሠረታዊ ችግሮችን መፍታት

ሰዎች በኢንተርኔ ሱሰኝነት እንዲያዙና በዚያ ውስጥ እንዲኖሩ የሚያደርገው አንዱ በህይወታቸው ያጋጠማቸውን ችግር በመሸሽ በኢንተርኔት ውስጥ መደበቅ መሞከር ነው፡፡ በኢንተርኔት ላይ ብዙ ጊዜን ማጥፋት፣ በህይወት የሚያጋጥመውን ችግር አይፈታም፡፡ ከተጨባጭ ችግሮች በዚህ ሱስ ለማምለጥ መሞከር፣ ችግሩን ይበልጥ ያባብሳል፣ ለአዳዲስ ችግሮች መምጣት ምክንያት ይሆናል፡፡

ስለዚህ የህይወትን ችግሮች ገንቢ በሆነ መንገድ ለመፍታት መሞከር እንጂ ኢንተርኔትን እንደ መሸሸጊያ ዋሻ መጠቀም ጠቃሚ አይደለም፡፡ በህይወታቸው ያለውን ጭንቀት፣ ድብርት፣ የማኅበራዊ ግንኙነት ችግር፣ ብቸኝነትና ሌሎች ችግሮችን አዎንታዊ በሆነ መንገድ መፍታት ኢንተርኔትን ለእነዚህ ችግሮች መፍትሄ እንደሆነ አድርገን እንዳንጠቀም ይረዳናል፡፡

6. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም

የኢንተርኔት ሱሰኝነት አንዱ መገለጫው ብዙ ጊዜን በኢንተርኔት ላይ ማባከን ነው፡፡ ይህን ለመቆጣጠር የኢንተርኔት አጠቃቀም የጊዜ ሰሌዳ ማውጣትና ለዚያ ራስን ማስገዛት አስፈላጊ ነው፡፡ በየዕለቱ ለምን ያህል ሰዓት፣ በምን ወቅት (ጠዋት፣ ምሳ ሰዓት፣ ምሽት፣ ሌሊት) በማለት ፕሮግራም ማውጣት ጠቃሚ ነው፡፡ በተባለው ሰዓት ለተወሰነ ጊዜ ተጠቅሞ ማቆም ያስፈልጋል፡፡ ምናልባት የታቀደው ጊዜ ማለቁን ለማስታወስ እንዲረዳቸው የሚያስታውሳቸውን ደውል መጠቀም ይችላሉ፡፡

7. ራስን ተጠያቂ ማድረግ

ከኢንተርኔት ሱሰኝነት ለመውጣት ራስን ለሚቀርቡት ሰው ተጠያቂ ማድረግ መልካም እርምጃ ነው፡፡ የኢንተርኔት ሱስ እንዳለባቸው ለወዳጃቸው በመንገር እንዲቆጣጠራቸው መፍቀድ ማለት ነው፡፡

ተጠያቂነት እንዲኖር ደግሞ በድብቅ ማድረግን ማቆም አስፈላጊ ነው፡፡ ኢንተርኔትን የሚጠቀሙት ቤት ውስጥ ከሆነ፣ ኮምፕዩተሩን ሰዎች በብዛት የሚገኙበት ወይም ሰዎች ሲያልፉ በሚያዩባቸው ሥፍራዎች በማድረግ እዚያ መጠቀም፣ ሰዎች እንዲያዩአቸው ያደርጋል፡፡ እነዚያ ሰዎች በጊዜ አጠቃቀማቸው ወይም በሚታዩ ነገሮች ላይ አስተያየት ይሰጣሉ፡፡ ሰዎች በሚያዩበት ሁኔታ ደግሞ ኢ-ስነምግባራዊ የሆኑ ነገሮችን በኢንተርኔት ላይ ለመመልከት ሃፍረት ይኖራል፡፡ ስለዚህ ለብቻ/ በገለልተኛ ሥፍራ ኢንተርኔትን መጠቀም ለብዙ ፈተናዎች ያጋልጣል፡፡

ምናልባት ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ለኢንተርኔት የሚጠቀሙ ሰዎች፣ በትምህርት ወይም በሥራ ወቅት ስልኮችን በአጠገብ አለማስቀመጥ፤ ቤት ውስጥ ከሆነ ደግሞ መኝታ ክፍል ይዞ አለመግባት ያግዛል፡፡ ኢንተርኔትን መጠቀም የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ለተወሰነ ጊዜ ከራስ ማራቅ የፈተናውን ኃይል ይቀንሳል፡፡

8. ማኅበራዊ ድጋፎችን ማግኘት

ከሱሰኝነት ለመውጣት በሚደረገው ጥረት የሰዎች ድጋፍ መኖር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች የቤተሰብ አባላት፣ ጓደኞች፣ የሥራ ባልደረቦች ወይም በማኅበረሰብ ውስጥ ያሉ ለእነዚህ ዓይነት ሰዎች ድጋፍ የሚሰጡ አካላት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ለእነዚህ ተገቢ ሰዎች የሱሰኝነት ችግሩን በመንገር አስፈላጊውን ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ፡፡

9. የባለሙያ ድጋፍ መፈለግ

ለአንዳንድ ሰዎች የኢንተርኔት ሱሰኝነትን ማሸነፍ እጅግ ከባድ ይሆናል፡፡ በዚህ ዓይነት ልምምድ ብዙ ከመቆየታቸው፣ ሌሎች የህይወት ችግሮቻቸውን ለመፍታት ዕውቀትና ክህሎት ስለሌላቸው፣ ተገቢ ማኅበራዊ ድጋፍ ማግኘት የሚችሉበት ሁኔታ ካለመኖሩ ….. የተነሳ ከሱሰኝነቱ ጋር ይጣበቃሉ፡፡

ሱሰኝነትን ለማሸነፍ የመነሻ ምክር ለማግኘት ወይም ሙከራ ተደርጎ ማሸነፍ ካልተቻለ የሰለጠነ አማካሪ ፈልጎ ማማከር ጠቃሚ ነው፡፡

(በከበደ በከሬ)
©zepsychologist

@Psychoet

መልካም ቀን ይሁንላችሁ!
እጅግ በጣም ኢንተርኔት የሚጠቀሙ ወዳጆቻችሁን ይህን ጽሑፍ አጋሯቸው፡፡
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
የአዋቂ ምክር!!!!!!!

1. ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!!

2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!!

3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!!

4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!!

5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!!

6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!!

7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!!

8. ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!!

9. ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!!

10. ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ስትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!!

11. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ግዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!!

12. እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነትተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!!

13. አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!!

14. ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!!

15. ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!!!

16. አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!!!!

@psychoet
Forwarded from Eyob
Let's save life, please share this on different channels and groups
#መልካም_የካቲት_ወር !
T.me/psychoet

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ፍትህ ፣ ሰላም ፣ ልማት የምንሰማበት ይሁንልን ፡፡

በዚህ ወር ልደታችሁን ለምታከብሩ የፔጁ ቤተሰቦች ከወዲሁ መልካም ልደትን እመኛለሁ ፡፡ 🎊🎉🎉🎉🎊
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

ለምትወዱት ጓደኛ #መልዕክቱን አስተላልፉ

@Psychoet
በሕይወታችን ብዙ ጊዜ የምንጎዳው ከዙሪያችን ካሉ ሰዎች ጋር ባለን መልካም ያልሆነ ጉርብትና ነው ፡፡ ከዚህ ለሠጸማምለጥ ደግሞ ትክክለኛው መፍትሄ ... ኹል ጊዜ ህመም ከሚሆኑብን ሰዎች በሰላም መራቅ ነው ፡፡
@psychoet
የኑሮ ቀውስን ማሸነፍ |Overcoming Crisis|
በዶክተር ማይልስ ሞንሮ ተጽፎ በአማረኛ ተተርጉሞ የቀረበ

በአስቸጋሪ ጊዜ የማደግ ሚስጥር
📌ሕይወት ሲከፋ እንዴት እናመልጣለን?
📌በሌላ ሰው ስህተት ስንወድቅ ምን እናረጋለን?
📌በተለያዩ የሕይወት ቀውሶች ውስጥ ስንገባ እንዴት እናመልጣለን?

አስተማሪ የሰስነልቦናዊ ምክር ስለሆነ ጊዜ ሰታችሁ አድምጡት!
ክፍል 1 | Part 1
https://youtu.be/B7Q1GThhups

ክፍል 2 | Part 2
https://youtu.be/YmVEApdaeg8

ክፍል 3 (የመጨረሻው) | Part 3 ( Last )
https://youtu.be/fo3708Pyi5o
📌 👉 አደገኛው ስብእና/ Narcissism👈📌

📌👉 ሁል ጊዜ ጥፋተኛ እንደሆናችሁ እንድታስቡ የሚያደርጉትን። ለሚሰጧችሁ መጥፎ ምላሽ ተጠያቂው/ዋ አንተ/አንቺ ነሽ የሚሉትን።

📌👉 የእነሱን ችግር እንጂ ፈፅሞ የእናንተን ማዳመጥና መረዳት የማይፈልጉትን።

📌👉 ለጥፋታቸው ሀላፊነት መውሰድ የማይፈልጉ፣ ሁል ጊዜ ትክክል ነኝ ብለው የሚያስቡና ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ምክንያቱ እናንተ እንደሆናችሁ እንዲሰማችሁ የሚያደርጉትን።

📌👉 ጉራቸው ከልክ ያለፈ። ታላቅነታቸውን፣ ችሎታቸውን፣ ተፈላጊነታቸውን እና የበላይነታቸውን ሁሌ የሚናገሩትን።
ከእናንተ የወሰዱትን ሀሳብ ጭምር የራሳቸው አድርገው የሚነግሯችሁን።

📌👉 የሰውን ትኩረት ለመሳብ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። በእያንዳንዱ ንግግራቸው እኔ....እኔ....እኔ የሚሉትን።

📌👉 ለሌላ ሰው ችሎታ እውቅና የማይሰጡና የሚቀብሩትን።

📌👉 ሌሎችን በጣም የሚያሳንሱ። የእነሱ ትልቅነት የሚጎላው የሌላውን ውድቀት፣ድክመትና አለመሳካት ሲያወሩ የሚመስላቸውን።

📌👉 ፈፅሞ አክብሮት የላቸውም። ተሳስቻለሁ....ይቅርታ የሚባል ነገር አይታሰብም። ለጥፋታቸው ሌላውን ተጠያቂ በማድረግ የሚያሸማቅቁትን።

📌👉 እነሱ የሚፈልጉትን ሀሳብ እንድትቀበሉና በነሱ ቁጥጥር ስር እንድትሆኑ የሚያደርጉትን።

📌👉ምንም አይነት ፍቅርና ርህራሄ የሌላቸውን።

📌👉 ክፋታቸውን ነቅታችሁ ስትርቋቸው ስማችሁን የሚያጠፉ። ሚስጥርና ድክመታችሁን ለሰው የሚያወሩተን። በሚችሉት ሁሉ ሊጎዷችሁ የሚሞክሩትን።

🔥ይህንን ካነበቡ በኋላ ግንኙነቶችዎን ደግመው ይመርምሩ።🔥

©በመአዛ መንክር - ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት
2024/09/29 09:32:05
Back to Top
HTML Embed Code: