Telegram Web Link
📌 👉 አደገኛው ስብእና/ Narcissism👈📌

🔥ለትዳር፣ ለጓደኝነትና አብሮ ለመስራት ፈፅሞ ልንመርጣቸው የማይገባን መርዛማ ማንነት ያላቸው ሰዎች።🔥

📌👉 ሁል ጊዜ ጥፋተኛ እንደሆናችሁ እንድታስቡ የሚያደርጉትን። ለሚሰጧችሁ መጥፎ ምላሽ ተጠያቂው/ዋ አንተ/አንቺ ነሽ የሚሉትን።

📌👉 የእነሱን ችግር እንጂ ፈፅሞ የእናንተን ማዳመጥና መረዳት የማይፈልጉትን።

📌👉 ለጥፋታቸው ሀላፊነት መውሰድ የማይፈልጉ፣ ሁል ጊዜ ትክክል ነኝ ብለው የሚያስቡና ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ምክንያቱ እናንተ እንደሆናችሁ እንዲሰማችሁ የሚያደርጉትን።

📌👉 ጉራቸው ከልክ ያለፈ። ታላቅነታቸውን፣ ችሎታቸውን፣ ተፈላጊነታቸውን እና የበላይነታቸውን ሁሌ የሚናገሩትን።
ከእናንተ የወሰዱትን ሀሳብ ጭምር የራሳቸው አድርገው የሚነግሯችሁን።

📌👉 የሰውን ትኩረት ለመሳብ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። በእያንዳንዱ ንግግራቸው እኔ....እኔ....እኔ የሚሉትን።

📌👉 ለሌላ ሰው ችሎታ እውቅና የማይሰጡና የሚቀብሩትን።

📌👉 ሌሎችን በጣም የሚያሳንሱ። የእነሱ ትልቅነት የሚጎላው የሌላውን ውድቀት፣ድክመትና አለመሳካት ሲያወሩ የሚመስላቸውን።

📌👉 ፈፅሞ አክብሮት የላቸውም። ተሳስቻለሁ....ይቅርታ የሚባል ነገር አይታሰብም። ለጥፋታቸው ሌላውን ተጠያቂ በማድረግ የሚያሸማቅቁትን።

📌👉 እነሱ የሚፈልጉትን ሀሳብ እንድትቀበሉና በነሱ ቁጥጥር ስር እንድትሆኑ የሚያደርጉትን።

📌👉ምንም አይነት ፍቅርና ርህራሄ የሌላቸውን።

📌👉 ክፋታቸውን ነቅታችሁ ስትርቋቸው ስማችሁን የሚያጠፉ። ሚስጥርና ድክመታችሁን ለሰው የሚያወሩተን። በሚችሉት ሁሉ ሊጎዷችሁ የሚሞክሩትን።

🔥ይህንን ካነበቡ በኋላ ግንኙነቶችዎን ደግመው ይመርምሩ።🔥

👉 ©በመአዛ መንክር - ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት
@Psychoet
👉👉ችግር ያሳድጋል👈👈
ችግርዎን ይጋፈጡ እንጅ ከችግርዎ አይሽሹ።

📌🔥 ኑሮ በየቀኑ የምንወጣው ተራራ ነው፡፡አንዱን ጨርሰን ስንደሰት ሌላኛው ይደቀናል፡፡ሌላኛውን ስንወጣ የባሰው ደግሞ ይጠብቅናል፡፡

📌🔥 የማያቋርት ስቃይ አለብን፡፡ስቃዩ ግን ጥሩ ነው፡፡ትክክለኛ አቅማችን የሚወጣው ከትክክለኛ ፈተና ጋር ስንታገል ነው፡፡

📌🔥 ብዙ ሰው ከፊቱ ያለውን ተራራ ግዝፈት እንጂ በውስጡ ያለውን የፈጣሪን ጉልበት አያውቅም፡፡ ተራራው ከፊትለፊቱ ሲደቀን የሚወጣበትን መንገድ ከመፈለግ ይልቅ ማማረርን ይመርጣል፡፡ምክንያቱም ማማረር ቀላል ነዋ፡፡

📌🔥 ማለቃቀሱን ማንም ያውቅበታል፡፡ወደ ተራራው ጫፍ የሚወስደውን መንገድ ማገኘት ግን ከባድ ነው፡፡ይህ የጥቂት ጀግና ሰዎች ስራ ነው፡፡ላብ፣ ደምና እንባ ማፍሰስን ይጠይቃል፡፡ብዙ ሰዎች ደግሞ ይህን ማድረግ አይፈልጉም፡፡ ፊሪ እና ሰነፎች ናቸው፡፡በራሳቸው ጉልበት ፤ በፈጣሪያቸውም ሐይል እምነት የላቸውም፡፡ ምኞታቸው ሁሉም ነገር ከአልጋ በአልጋ አንዲሆን ነው፡፡ህይወት ደግሞ ተራራ በተራራ እንጂ አልጋ በአልጋ አይደለም፡፡

📌🔥 አለም አሁን ካለችበት ከፍታ የደረሰችው በችግር ነው፡፡ችግር ባይኖር? ሰዎች ዛሬም ድረስ በዋሻ ውስጥ ነበርን፡፡መብራት፣ መኪና፣ እርሻ፣ ፕሌን፣ ኢንተርኔት፣ ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ ቤትና ሁሉም ለሰው ልጆች ጠቃሚ የሆኑ ነገሮች የተወለዱት በችግር ምክንያት ነው፡፡ሰዎች ችገራቸውን ለማሸነፍ ሲታገሉ ዛሬ ፍጹም ልዩ የሆነ አለም ፈጥረዋል፡፡ ታዲያ ምስጋና ለአቶ ችግር አይገባም ትላላችሁ?

📌🔥 ከፊትለፊታችሁ ያለው ተራራ ምንድን ነው? ችግራችሁ ምንድን ነው? ገንዘብ ማጣት? ስራ አጥነት? የተበላሸ ትዳር? ስደት? በሽታ? በራስ መተማመን ማጣት? ሱስ? ምንድን ነው?

📌🔥 ችግራችሁን የምትመለከቱትስ እንዴት ነው? ተራራችሁን የምታዩት እንዴት ነው?
ሊያሳድጋችሁ እንደመጣ ስጦታ? ወይስ ሊያስቆማችሁ እንደመጣ ፈተና?

📌🔥 ይህ የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ብዙ ሰው ችግሩን እንደ ጠላት ይመለከታል፡፡ችግራችሁን እንደ ወዳጅ አድርጋችሁ ካያችሁ ግን እናንተ ትክክለኛ ጀግና ናችሁ፡፡ እሱን ለማሸነፍት ስታነቡ፣ ሰው ስታማክሩ፣ ሞያ ስትለማመዱ፣ ስትነግዱ፣ ገንዘብ ስትቆጥቡ፣ ጸሎት ስታደርጉ ፍጹም ሌላ ሰው ትሆናላችሁ፡፡ ሌሎች ከታች ሆነው ሲያማርር እናንተ ከተራራው ጫፍ ትደርሳላችሁ፡፡ከአናቱ ሆናችሁ ንፁህ አየር ትምጋላችሁ፡፡በከፍታው ያለውን ቪውም enjoy ታደርጋላችሁ፡፡ሌላ ችግር ሲጋረጥባችሁም አትደናገሩም፡፡ሌላ መፍትሄ ፈልጋችሁ ታሸንፉታላችሁ፡፡

©ማንያዘዋል እሸቱ - Psych ጤና
የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት Watch "Dink MiKir ድንቅ ምክር" on YouTube

@Psychoet
ምስጋና እና ዘርፈ ብዙ ጥቀሞቹ
Telegram : www.tg-me.com/psychoet

በርካታ ጥናቶችም የምስጋና ባህል በተቻለ መጠን መዳበር እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ ከእነዚህ ጥናቶች መካከል የ “Positive Psychology” መስራች ሴሊግማን 411 ሰዎች ላይ ያካሄደው ጥናት ቀዳሚ ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው የተለያዩ አዎንታዊ ሀሳቦች እና ድርጊቶች ያላቸውን ውጤት በመለካት (Testing) ሲሆን ምስጋና ከሁሉም የላቀ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ታውቋል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በሕይወታችን ትልቅ ቦታ አለው የሚሉትን እና በሚገባ አመስግነው ለማያውቁት ሰው የምስጋና ደብዳቤ ፅፈው በራሳቸው እጅ እንዲያደርሱ ከተደረገ በኋላ ውጤቱን ተጠንቶ ከፍተኛ የደስታ ስሜት ተሳታፊዎቹ ላይ ታይቷል፡፡ ለውጡ ይበልጥ አስደናቂ ሊሆን የቻለው የተፈጠረው የደስታ ስሜት ለብዙ ወራት መቆየት በመቻሉ ጭምርም ነው፡፡ በዚህ መሰረት ከየትኛውም ድርጊት በበለጠ መልኩ ምስጋና አመስጋኙን ደስተኛ የማድረግ ኃይል እንዳለው ታውቋል፡፡

የምስጋና ጥቅሞች

#ደስተኛ_ያደርገናል
በቀን ለአምስት ደቂቃ ያህል ማመስገን ከአማካይ ጤንነት በላይ 10% ሁለንተናዊ ጤንነትን ያሻሽላል፡፡

#ሰዎች_እንዲወዱን_ያደርጋል
በሁለት የተለያዩ ጥናቶች ከአብዛኘው ሰው 10 % በላይ የሚያመሰግኑ ሰዎች 17.5 % ከሌሎች የበለጠ የሰው መውደድ እንዳላቸው ታውቋል፡፡ ምስጋና ሰዎች እምነት እንዲጥሉብን፣ እንዲቀርቡን እና እንዲወዱን ያደርጋል፡፡

#በሥራ_ቦታ_ስኬታችንን_ይጨምራል
ምስጋና የተሻለ መሪ፣ ተግባቢ፣ የውሳኔ ሰው እና ስኬታማ እንድትሆኑ ያግዛል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ምስጋና ጤናማ ስሜት እንዲኖረን፣ ቁሳዊ አመለካከታችን (Materialism) እንዲቀንስ፣ ራስ ወዳድነት እንዲቀንስ፣ ለራሳችን ያለን አመለካከት እንዲሻሻል፣ ጥሩ እንቅልፍ እንድንተኛ፣ ረጅም እድሜ እንድንኖር ወዘተ ያደርጋል፡፡

ምስጋና ባህል እንደመሆኑ መጠን ደግመን ደጋግመን እስከተለማመድነው ድረስ ይሻሻላልም፡፡ ይህንን ለማድረግ የምስጋና ደብዳቤ መጻፍ፣ ጊዜ ቢታጣ እንኳ በልቦናችን ማመስገን፣ የምስጋና የግል ማስታወሻ መፃፍ፣ በረከቶቻችንን መቁጠር፣ ፀሎት የመሳሰሉት የምስጋና ባህላችንን ለማሻሻል የሚረዱ ልምምዶች ናቸው፡፡

_______________
ይህን ካነበባችሁ አይቀር የማመስገን ባሕልን ዛሬውኑ መለማመድ ጀምሩ ፡፡ ሕይወታችሁ ሲለወጥ ታዩታላችሁ ፡፡

አንድ ምሳሌ ልጨምርላችሁ ፦ አንድ ዳቦ ይዛችሁ ሶስት የተቸገሩ ሰዎችን ተመለከታችሁ ፡፡ ከዛ ዳቦውን እኩል ቦታ ቆርሳችሁ አካፈላችኀቸው፤ ሰዎቹም ሲበሉም ቆይተው ሲጨርሱ
#አንዱ ይሄ ምን ያጠግባል ፣ ደግሞ የማይጣፍጥ ዳቦ ነው ብሎ ተነስቶ ሄደ
#ሌላው ደግሞ ምንም ምላሽ ሳይሰጥ ሄደ
#የቀሪው ግን እጅግ አመስግኖ እያለቀሰ ምግብ ከበላሁ 1 ቀኔ ነበር በማለት ሰጪውን ደጋግሞ አመሰገነ

እናም በዚህ ሁኔታ ሰጪው ላይ ምን አይነት አስተሳሰብ የሚጎለብት ይመስላችኀል? ተቀባዮቹስ ላይ?

ሰጪው በጣም የሚያስደስተው የሰጠው ጥቂት ዳቦ ሳይሆን ያመሰገነንውና እሱ በሰጠው ጥቂት ዳቦ ከርሀብ የወጣው ሰው ታሪክ ነው ፡፡ አማሮ ለሄደው ሰው ግን ለወደፊቱ ሞልቶ ቢተርፈውም ላይሰጠው ያስባል ስለ ሶስተኛው ሰው ግን እንዴት ምንም ሳይል ይሄዳል በሚል ብዙ ጥያቄዎችን ያወጣል ያወርዳል፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ስንባል ምንም ነገር ስናደርግ ምላሽ እንጠብቃለን ፡፡

ስለዚህ ለመልካም ግንኙነት ስንል መልካም ነገር መናገር አማራጭ የሌለው ነገር ነው ፡፡ ካልተቻለ ግን መጥፎ ነገር ከመናገር ዝም እንበል ፡፡ መልካም ነገር የሚጀምረው ደግሞ ከቀላል ምስጋና ነው፡፡

Like & Share
fb.me/psychologyet
#የብቸኝነት ስሜትን ማሸነፊያ መንገዶች
www.tg-me.com/psychoet
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ሁናችሁ ብቸኝነት ተሰምቷችሁ ያውቃል ? በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት እቤት በመክረማችሁ የብቸኝነት ስሜት እያጠቃችሁ ነው? እንግዲያውስ ይሄን ስሜተት የማሸነፊያ የሥነልቦና መፍትሔዎችንና ምክሮችን ይዤላችሁ መጥቻለሁ ፡፡
______________
አዕምሮአችን የተፈጠረው የተለያዩ አይነት ስሜቶችን እንዲረዳና እንዲያስተናግድ ነው ፡፡ እነዚህ ስሜቶች አወንታዊና አሉታዊ ሲሆኑ ለኛ ማንነትና አኗኗር ወሳኝነት አላቸው ፡፡ በውስጣችን የሚፈጠሩት አወንታዊ ስሜቶች የሚገነቡንን ያህል አሉታዊ ስሜቶች ደግሞ ከውስጥ እያፈረሱን ከውጭ ደግሞ በድካም ፣ በድብርት ፣ በጭንቀት ፣ ስለ ነገ ባለ ፍርሀት ያስሩናል ፡፡

በአዕምሮአችን ከሚፈጡሩ አሉታዊ ስሜቶች አንዱ ደግሞ የብቸኝነት ስሜት ነው ፡፡ የብቸኝነት ስሜት እድሜና ፆታ ፣ ሀብትና ስልጣን ሳይለይ ከልጅነት እስከ ሽምግልና ፣ ከደሀ እስከ ሀብታም የሚያጠቃ አሉታዊ ስሜት ነው ፡፡

አዕምሮአችን " ማንም አይወደኝም ፣ እኔ ተሸናፊ ነኝ ፣ ሁሉም ሰው ጥሩ አይደለም ፣ ይሄ ወረርሽኝ እኔና ቤተሰቤን እንዳይጎዳ" የሚሉ የተለያዩ ምክንያቶችን ሲያቀርብ በውስጣችን የብቸኝነት ስሜት እንዲያድግ ያሆናል ፡፡ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የደረሱብንን የስነልቦና ፣ የስሜት ፣ የአካል ... ጥቃቶች ፣ ትችቶች መላልሶ ሲያሰላስል እንዲሁም በሌሎች የመገለል ነገር ሲኖር ወደዚህ ብቸኝነት ስሜት ልንመጣ ይችላል ፡፡

ከዚህ በታች የብቸኝነት ስሜትን ተረድተን እንዴት በጤነኛ መንገድ ማሸነፍ እንደምንችል 3 ሀሳቦችን እናያለን

1.ብቸኝነት ስሜት እንጂ እውነታ እንዳልሆነ መረዳት

ብቸኝነት ስሜት ሲሰማን በሕይወታችን አንድ የተፈጠረ ነገር ይሄን ስሜት እንዳስነሳው መረዳት አለብን ፡፡ የብቸኝነት ስሜት የሚመጣው 'በመገለል ወይም ለብቻ በመሆን ' ብቻ አይደለም ስለዚህ ብቸኝነት ሲሰማን ቁጭ ብለን ጊዜ በመውሰድ ይህን ስሜት ያመጣብንን ምክኒያት ለማወቅ መሞከርና መንስኤውን ለማስወገድ ካልተቻለም ለመቀነስ እቅድ ማውጣት ተገቢ ነው ፡፡

2.በየቀኑ ትርጉም ያለው ስራ በመስራት ማሳለፍ

በዚህ ወረርሽኝ ወቅት ባለንበት ቦታ ( በቤትም ሆንን በውጭ ) እያንዳንዱን ቀን ትርጉም ያለው ስራ ሰርተንበት እንለፍ ፡፡ በዚህ ጊዜ ቀኑን ሙሉ ፊልም መመልከት ፣ ማሕበራዊ ሚዲያ ከአንዱ ወደአንዱ እየተሸጋገሩ ማየት ወደባሰ ድብርት ፣ ጭንቀትና ብቸኝነት ስሜት ስለሚመራ በየቀኑ አንድ አዲስ ነገር ለመስራት መሞከር ከብቸኝነት ስሜት ለመውጣት ይረዳል ፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ማታ ስንተኛ ዛሬ ከነጋ ምን ሰራሁ ብለን ራሳችንን በመጠየቅ ነገ ደግሞ ምን መስራት እንዳለብን ማቀድ መልካም ነው ፡፡


3. በጣም የምንወዳቸው ሰዎች ማግኘት ፣ የምንወዳቸውን ነገሮች መስራት

ይሄን ማድረግ በውስጣችን መልካም ሀሳብና ኢነርጂ እንዲፈጠር ያደርጋል ፡፡ ይሄም የተሻለ የስራ ተነሳሽነት ይፈጥርልናል ፡፡ ከሚወዱት ነገር ጋር ጊዜ ማሳለፍ በውስጣችን አወንታዊ ሀሳብ እንዲፈልቅ ፣ አሉታዊዉ ደግሞ እንዲቀንስ ይረዳል ፡፡ በተጨማሪም በዙሪያችን ለብቸኝነት መንስኤ ከሆኑ ሁኔታዎችና ሰዎች መሸሽ ተገቢ ነው፡፡

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ጥቂጥ መፍትሔዎች ናቸው ፡፡ የብቸኝነት ስሜት ሲሰማን ሊረዱን የሚችሉ ሌላ ብዙ መንገዶችን ከመጸሐፎች ፣ ከድህረ ገፆች፣ ከሰዎች ልናገኝ እንችላለን ፡፡ከእኔጋር በሌላ ክፍል በደንብ እንመለከተዋለን ፡፡


❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️
📖ማስታወቂያ📖
ለፔጁ ቤተሰቦች በሙሉ📌📌📌📌 ላለፉት ጥቂት ወራት በኮሮና ምክኒያት ተቋርጦ የነበረው ስልጠና ከጥቂት ሳምንታት በኀላ ብዙ ጠቃሚ ጉዳዮችን ይዞ ይቀጥላል ፡፡ ስለዚህ ከወዲሁ መሰልጠን የምትፈልጉ ተዘጋጁ ፡፡ ሙሉ የስልጠና መረጃዎች በቅርብ ይለጠፋሉ ፡፡ የስልጠና አድራሻ 4ኪሎ ቱሪስቶ ሆቴል አጠገብ ፡፡

❖_____________________________❖
ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !

የሳምንት ሰው ይበለን!
❖__________________________________❖

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
በሰው አእምሮ ውስጥ ከሚገኙ አሉታዊ አመለካከቶች አንዱ የበታችነት ስሜት ነው፡፡
ብዙ ሰው ያሰበበት ቦታ እንዳይደርስ ፣ ያቀደውን እንዳያሳካ ፣ ባለው ነገር እንዳይመካ የሚያረገው ይህ አሉታዊ ስሜት ነው፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የተዘጋጀውን ቪዲዬ "ከበታችነት ስሜት የመውጫ መንገዶች" በዩቲዩብ አድራሻችን ልታገኙ ትችላላችሁ አንድን የማንፈልገው የግል ባህሪ/አመለካከት ከመቀነሳችን በፊት ያ ባህሪ እንዳለብን ማረጋገጥ አለብን ፡፡

ይህ ቪዲዮ ስለ የበታችነት ስሜት ምልክቶች መንስኤዋችና መፍትሔዎች ማብራሪያ ይዞ መቷል ፡፡ ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት ታገኙታላችሁ
https://youtu.be/WGJYup10X2k
https://youtu.be/4ZoDlu58wMI
https://youtu.be/YXM8P4wQ2A4
የስኬታማ ሕይወት ምክሮችና እውነታዎች
www.tg-me.com/psychoet

📕ያለፍክበት የሕይወት መንገድ አስሮ ሊይዝህ አይገባም ፤ ነገህን መወሰን የራሳህ ምርጫ ነው፡፡

📕በሕይወትህ የደስታ ምንጭ መኾን ባትችል ለሌሎች የሐዘን ምክንያት አትኹን፡፡

📕ዝምታ ፣ በውስጡ ትልቅ ጩኸት የያዘ የማይጠየቅ ጠያቂ ፣ የማይመረመር መርማሪ ነውና ከዙሪያህ ካለ የሰዎች ጫጫታ በላይ በላይ የውስጥ ዝምታህን አድምጥ ፡፡

📕በምድር ላይ ምንም ፍጹም ነገር የለምና አንተም ፍጹም ለመሆን አትሞክር ሰዎችም ፍጹም እንዲሆኑ አትጠብቅ ነገር ግን ኹሉን በመልካምነትና በቅን ልቦና አከናውን ፡፡

📕ያለህን ችሎታ ፣ አቅም ፣ ዕውቀት አንተ ካላከበርከውና ካላወጣኸው ማንም መቶ ሊያከብርልህና ሊያወጣልህ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ከተቀምጥክበት ተነሳና ከምኞት ወተህ ወደ ተግባር ተሻገር ፡፡

📕በሕይወትህ ትልቅ መከራ ፣ ችግር ፣ ሀዘን ደርሶ ሊሆን ይችላል ፤ "ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል?" ብለህ አዝነህ ፣ ተክዘህ ሊሆንም ይችላል ፡፡ ግን በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር "ተስፋ" የሚባል ነገር መኖሩን ነው ፡፡

ከሜሎሪና መጽሐፍ የተወሰዱ ምክሮች
📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖

ሜሎሪና መጽሐፍን በኹሉም መጽሐፍ መደብሮች እና አከፋፋዮች እጅ ታገኛላችሁ ፡፡ ዛሬውኑ ገዝታችሁ በማንበብ ተማሩበት ደግሞም በታሪኩ ተዝናኑበት ፡፡

መልካም ቀን !
#Like #Share እናድርግ
+ሕይወታችንን የሚያበላሹ ነገሮች
www.tg-me.com/psychoet

1. ኢጎ ምንድን ነው? ኢጎ ከህጻንነትሽ ጀምሮ ማህበረሰቡ የፈጠረብሽ የውሸት ማንነት ነው፡፡ይህ እብድ የሆነ አለም እብድ አድርጎ አእምሮሽን ቀርጾታል፡፡መጥላት፣ መቅናት፣ መናቅ፣መፍረድ፣ መከፋፈል፣ ዘረኛ መሆን፣ በሀብት መመካት፣ እኔ እኔ ብቻ ማለት...ወዘተ ነገሮች በውስጥሽ ተሰግስገዋል፡፡አንዳንዴ ጊዜ ፡ "እንዴት እንደዚህ አይነት መጥፎ ሰው ሆንኩኝ?" ትያለሽ፡፡መጥፎ የሆንሽው ግን አንቺ ሳትሆኚ ኢጎሽ ነው፡፡ይህ በማህበረሰቡ ከህጻንነትሽ ጀምሮ በውስጥሽ የተከማቸ ኮተት ነው፡፡አራግፊው፡፡አንቺ ውብ፣ ድንቅ፣ ደግ፣ ተወዳጅ፣ አስገራሚ፣ ባለብዙ በረከት፣ ሰው አክባሪ፣ ርህሩህ፣ የማትነካ፣ የማትዳሰስ even የማትሞትና በፈጣሪ አምሳል የተፈጠረሽ መንፈሳዊ ፍጥረት ነሽ፡፡ይህንን እኔ ልነግርሽ አይገባኝም፡፡ይህንን ስታነቢው ራስሽ ታውቂዋለሽ፡፡ውስጥሽም ይነግርሻል፡፡
+
2. ጓደኞችሽን አሳይኝና ማንነትሽን አሳይሻለው፡፡ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር አመድ ቅማ ትመጣለች፡፡አመድ ከሚያስቅሙ ሰዎች ጋር የምትውል ሴትም እንደዛው አመዳም ናት፡፡ምርጥ ከሆኑ ሰዎች ጋር ብቻ ጊዜሽን አሳልፊ፡፡መጥፎ ሴት ብትሆኚም እንኳን በምርጥነታቸው ትሸነፊያለሽ፡፡ጓደኞችሽን በጥንቃቄ ምረጪ፡፡
+
3. ሀሳብሽን ከገንዘብሽ በላይ ተቆጣጠሪው፡፡አእምሮሽ የአሉታዊ ሀሳቦች ጭፈራ ቤት ከሆነ ሙሉ ህይወትሽ ገደል ይገባል፡፡በልብሽ ማዕከል የሚነግሰው ሀሳብ ውሎ አድሮ የህይወትሽ እውነታ ይሆናል፡፡እናም በጥንቃቄ ጠብቂው፡፡ሁልጊዜ አዎንታዊ ሀሳብን ብቻ አስቢ፡፡ለመሆኑ አሁን ምን እያሰብሽ ነው?
+
4. ሰዎችን አፍቅሪ ፣ ከልብሽ አክብሪ ፣ምን ይሉኛል ብለሽ ግን ምንም ነገር አታድርጊ፡፡ሰዎች የሚሉትን ነገር አያጡም፡፡ በውሃ ላይ ብትራመጂ ራሱ ዋና ስለማትችል ነው ማለታቸው አይቀርም፡፡ ራስሽ ላይ ብቻ አተኩሪ፡፡ አጭር ለሆነችው ህይወት ሰው ምን ይለኛል ብሎ መጨነቅ መሸወድ ነው፡፡
+
5. ቁሳቁስ ደስታ አይሰጥሽም፡፡ አሁን ደስታ የራቀሽ ብራንድ ነገር ስሌለሽ ከመሠለሽ ይቅርታ፡፡አለም ውስጥ ያለው ቁሳቁስ ሁሉ የአንቺ ቢሆንም እውነተኛ ደስታን አታገኚምም፡፡አዎ ብራንድ ነገር ስትገዢው ሊያሳብድሽ ይችላል፡፡ግን አንድ ቀን ባደረ ቁጥር የገዛሽው ነገር የሚሰጥሽ ደስታ እየተሸረሸረ ይመጣል፡፡እስቲ ከዚህ ቀደም ቋምጥሽ የገዛሻቸውን ነገሮች አስቢ፡፡እነዛ ተንሰፍስፈሽ የገዛሻቸው ነገሮች ዛሬ ያንን የቀደመ ደስታሽን ይሰጡሻል? በፍጹም፡፡ዛሬም ለመግዛት የምትንሰፈሰፊያቸው ነገሮች እንደዛው ናቸው፡፡ከገዛሻቸው በኋላ ይደብሩሻል፡፡ይህ መጥፎ ጨዋታ ነው፡፡ደስታሽ ያለው በውስጥሽ ነው፡፡ከፍያ የለውም፡፡ነጻ ነው፡፡ጥሩ ሰው መሆን ብቻ ደስታ ይሰጥሻል፡፡አንቺ ሰው እንዲያደርግልሽ የምትፈልጊውን ነገር ለሰው ስታደርጊ ደስታ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡
+
6. ሁሉም ነገር ሱስ ነው፡፡ህይወትሽን መጥፎ የሚያደርገው መጥፎ ሱስ ነው፡፡መጥፎ ሱስን ግደይው፡፡መቃም፣ ማጨስ፣ መስከር፣ መዋሸት፣ መቅናት፣ መስነፍ...ማንኛው ወደኋላ የሚጎቱትሽን ነገሮች ከህይወትሽ ነቀለሽ ጣያቸው፡፡በምትካቸው በጎ ሱስ ፈጠሪ፡፡ያ መሄድ ወደ ምትፈልጊበት አለም ይወስድሻል፡፡
+

©ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ
ጠቃሚ ስለሆነ ለሌሎችም #Share እናድርግ
"ብልህ ሰው የትም ቢሆን መፍትሔ አያጣም!"

በአንድ ከተማ የሚኖር አንድ በእድሜ የገፋ ሰው ነበር፡፡ በጓሮው በሚገኘውን ማሳ ቆፍሮ ድንች መትከል ፈልጎ እርጅና ተጫጭኖታልና አቅሙ አልፈቀደለትም፡፡ ሊረዳው የሚችለው ብቸኛ ልጁ ደሞ እስር ቤት ነው የሚገኘው፡፡ እናም አባት ለልጅ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ፃፈ፡፡

"ውዱ ልጄ ምንም ጥሩ ስሜት አየተሰማኝ አይደለም፤ ምክንያቱም የድንቹን ማሳ መቆፈር አልቻልኩም፡፡ አለመቆፈሬን አልወደድኩትም፤ ምክንያቱም እናተህ አትክልት በጣም ነበር የምትወደው፡፡ አንተ እስር ቤት ባትሆን አውቃለሁ ትቆፍርልኝ ነበር ፤ አባትህ"

በቀጣዩ ቀን አባት አጠር ያለ ፁሁፍ ደረሳቸው፡፡ "በፈጣሪ ስም ይዤካለው አባ ጓሮውን እንዳትቆፍረው፤ ሽጉጡን የቀበርኩት እዚያ ነው"

ከሰዓታት በኀላ በደርዘን የሚቆጠሩ የFBI መርማሪዎችና ፖሊሶች የሽማግሊውን ጓሮ በሙሉ በቁፋሮ ምስቅልቅሉን አወጡት፤ ነገር ግን ምንም ሽጉጥ እዛ አልነበረም፡፡

አባት በጣም ግራ በመጋባት አጠር አድርገው ለልጃቸው ምን እንደተፈጠረ እና ቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ፃፉለት፡፡

ልጅ "አሁን ድንችህን ትከል አባ፤ ከዚህ ሁኜ ላደርግልህ የምችለው ነገር ቢኖር ይህን ብቻ ነው" ብሎ ፃፈላቸው፡፡

ያለንበት ነባራዊ ሁናቴ እኛን ሊወስነን አይገባም!📡📡 📡 📡 📡
#በጽሑፉ ፈገግ ያለና የተመቸው #Share ያድርግ
©ማኅበራዊ ሚዲያ
@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
በቤተሰብ አባል ውስጥ የሥነ-ልቦና መታወክ ሲያጋጥም ምን እናድርግ?
(በአሸናፊ ካሳሁን) #SHARE

የስነ-ልቦና ወይም የስነ-ባህሪ መታወክ በሀገራችን ትኩረት ካልተሰጠባቸውና የህክምና ዘዴው (psychotherapy) ካልተስፋፋባቸው ማኅበራዊ ችግሮች ውስጥ ዋንኞቹ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በባህላዊና በሃይማኖታዊ ድጋፎች ማኅበረሰባችን ከዚህ ችግር ጋር እየተጋፈጠ ቢሆንም፣ ዋናው ጫና የዚህ ችግር ተጠቂ ከሆኑ የቤተሰብ አባላት ላይ ነው፤ምክኒያቱም እንደሰለጠነው ዓለም የህክምና ፤ ድጋፍና እንክብካቤ ሰጪ  ቦታዎች ስለሌሉን ነው፡፡ ይህን ችግር ለማቃለል እየተንቀሳቀሱ ካሉት አገር በቀል ድርጅቶች ውስጥ አንዱ መቄዶኒያ ሲሆን በዚህ አጋጣሚ ስለሚሰሩት ስራ ያለኝን አድናቆት ሳልጠቅስ አላልፍም፡፡እናንተም የተቻላችሁን ድጋፍ አድርጉላቸው፡፡

ከዚህ በመቀጠል የስነ-ልቡና መታወክ ችግር ያጋጠማቸው የቤተሰብ አባላት ይህን ተግዳሮት ለመቋቋም ምን ማድረግ አለባቸው የሚለውን በዶ/ር ቤሪ ያኮብስ መጽሐፍ መነሻነት ይጠቅማሉ ያልኳቸውን ነጥቦች አነሳለሁ፡፡ መልካም የንባብ ጊዜ!
___________________________________
#ለበሽታው_ያለንን_ግንዛቤ_ማሳደግ ፡-

ስለታመመብን ሰው የስነ-ልቡና መታወክ አይነት፣ መንስኤ፣ ምልክቶች፣ ስለሚያባብሱ ሁኔታዎችና ነገሮች እራስን ማስተማር፡፡ ስለታመመው ሰው የስነ-ልቡና ወይም የስነ-ባህሪ ችግር የተሳሳተ መረጃ ካለን ወይም ስለ ምልክቶቹና ስለሚያባብሱ ጉዳዮች ዝቅተኛ ግንዛቤ ካለን ግለሰቡንና ቤተሰቡን በአጠቃላይ ሊጎዳ የሚችል ተግባር ልንፈጽም እንችላለን፡፡

#ለምሳሌ እስኪዞፍሬኒያ (Schizophrenia) ያለባቸው ግለሰቦች ስለሚታያቸው አስፈሪ ግን በገሃዱ አለም የለለ ምስል (hallucination) ምንም ግንዛቤ ከሌለን፤ በተገቢው ተጠቂዎችን ላንረዳቸውና አግባብነት ያለው ምላሽ ላንሰጥ እንችላለን፡፡

#በለሌላ ምሳሌ በከፍተኛ ድባቴ (Depression) ውስጥ ያሉ ግለሰቦች አጥብቀው እራስን ስለማጥፋት (suicidal ideation) ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ ይህ ሃሳብ በዝርዝር እራሳቸውን እንዴት፣በምን፣የትና እራሳቸውን እነደሚያጠፉና የመሳሰሉትን በዝርዝር ማሰላሰልና ሙከራ ማድረግን ሊያካትት ይችላል፡፡ ስለዚህ እድብታ ወደ እንደዚህ አይነቱ የስነ-ልቡናና የስነ-ባህሪ ዝንባሌ ሊወስድ እንደሚችል በቂ እውቀት ከሌለን፤ በዚህ የሚሰቃይ ቤተሰባችን፣ጓደኛችን፣ፍቅረኛችንን እንዲሁም የስራ ባልደረባችንን በተገቢው መንገድ መርዳት አንችልም፡፡ አንዳንዴም ለምን ስለማይጠቅም ነገር ታስባለህ እና የመሳሰሉትን ትችቶች በመስጠት ግለሰቡን እንኮንናለን፡፡ ስለሆነም በግለሰቡ ላይ የምናያቸው እንግዳ ባህሪያትና አስተሳሰቦች ከግለሰቡ ቁጥጥር ውጭ ስለመሆናቸው መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ስለዚህ ስለ ግለሰቡ የስነ-ልቡና ችግር ያለን ግንዛቤ ለግለሰቡ ለምንሰተጠው እርደታ፣ግለሰቡን የምንረዳበትን እይታ፣እንዲሁም ለራሳችን ደህንነት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ምክኒያቱም የቤተሰብ አካል ጓደኛ ወይም ፍቀረኛ የስነ-ልቡና ችግር ሲያጋጥም የኛ ደህንነት ላይም ተጽዕኖ ስለሚያደርስ፡፡

➋ትክክለኛ የመረጃ ምንጮችን ማፈላለግ፡-

ስለ ግለሰቡ የስነ ልቡና ችግር ሳይንሳዊ ግንዛቤ ለመጨበት ትክክለኛ ምንጮችን መከተል ይገባናል፡፡ ምንም እንኳን በሀገራችን ቋንቋንዎች የተጻፉ ሳይንሳዊ መሰረት ያላቸው መጽሀፍት ባይኖሩም፣ የእንግሊዚኛ ችሎታ ካለን በእንግሊዚኛ የተጻፉ ሳይንሳዊ መጽኃፍትን ወይም ታእማኝነት ያለቸውን ድህረ-ገጾች መጠቀም፡፡ እንዲህ ስል በእንግሊዚኛ ስለተጻፈ ብቻ ጠቃሚ ነው ማለቴ ሳይሆን እነደ ዕድል ሆኖ ሳይንሱ በምዕራቡ አለም ስለተስፋፋ ብዙ ሳይነሳዊ የሆኑ መጽሀፍት በእንግሊዚኛ ቋንቋ ስለተጻፉ ነው፡፡ ስለዚህ የሀገራችን ሳይኮሎጂስቶችና ሳይካቲሪስቶች ብዙ የቤት ስራ አለብን፡፡ ምርምር ከመመረቂያ ጽሁፍ በላይ መሆን አለበት፡፡ (እዚህ ጋር ላቋርጣችሁና… የኛ አላማ ይህን ክፍት መሙላት  የሚችል በስነ-ልቡና ችግሮችን፣ ትዳርን፣ ፍቅር፣ የልጅ አስተዳደግን፣ ትምህርት ነክና ለሌች የስነ-ልቡና ጉዳዮችን የሚዳስስ ሳይንሳዊ መሰረት ያለቸውን መረጃዎች ለናንተና በውጭ ሀገር ላሉ አዳማጭ ላጡ ወገኖቻችን አማራጭ ማቅረብ ነው፡፡ ስለዚህ ለወደፊት ስለተለያዩ የስነ-ልቡና ችግሮች መንስኤ፣ምልክት፣የመጀመሪያ እርዳታ እንዲሁም ዕርዳታ እንዴት ማግኘት እነደምትችሉ የተደራጀ መረጃ በዌብሳይታችን እናቀርባልን)፡፡ወደ ወናው ሃሳብ ስመለስ ስለስነ-ልቡና ችግሮችና መፍትሄዎች የተነገሩ ወይም የተጻፉ ነገሮች ሁሉ ትክክል ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ በጋዜጦችና መጽሄቶች የሚነገሩ ነገሮችን በባለሙያተኞች የሚነገሩ ከሆኑ እንደ ግብአት መውሰድ ይቻላል፡፡ በጥቅሉ ሳይንሳዊ ዳራ ያለቸውን ታማኝ ምንጮችን ተጠቀሙ ምክሬ ነው፡፡

➌የእርዳታ ምንጮችን መፈለግ፡-

የስነ-ልቡና ችግርን በሀገራችን ካሉ ሌሎች በሽታዎች ለየት የሚያደርገው የበሽታው ተጠቂዎች ላይ የሚደርሰው አድሎና መገለል አንዱ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ምክኒያት ከማህበረሰቡ ከሚገኙ ድጋፍ ይልቅ አድሎው የሚያመዝንበት ሁኔታ አለ ምንም እንኳ የተለያዩ የሀይማኖት ተቃማት የራሳቸውን ድጋፍና እንክብካቤ ለተጠቂዎች የሚያደርጉ ቢኖሩም፡፡ በዚህም ምክኒያት የስነ-ልቡና ችግር ያለባቸው ሰዎች ስለ በሽታቸው ከሌሎች ግለሰቦች የመወያየትና ድጋፍ የማግኘት እድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ እናም የስነ-ልቡና ችግር ያለባቸው ግለሶቦች ቤተሰቦች ተመሳሳይ ችግር ያለባቸው ሌሎች ቤተሰቦች ጋር መወያየትና ሀሳብ መለዋወጥ ልምድ ከማካፈል በዘለለ ስለሚደርስባቸው ተግዳሮቶች ማውራታቸው የተወሰነም ቢሆን ስለጉዳዩ የሚሰማቸው ጭንቀት ቅልል ሊልላቸው ይችላል፡፡ ይህ እንግዲህ ፈረንጆቹ support group የሚሉት አይነት ነገር ነው፡፡ እዚህ ጋር ማንኛቸውም ሊጠቅሙ የሚችሉ ባህላዊና፣ ሀይማኖታዊ፣መንግስታዊ እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ከስነ-ልቡና ችግር ጋር በተገኘ እርዳታ የሚሰጡ ተቋማትን ማፈላለግ፡፡

........ይቀጥላል፡፡ ከዚህ ጋር በተገናኘ ማንኛውም ጥያቄ ያላችሁ #COMMENT ላይ ፃፉልኝ ? ማክሰኞ ቀጣዩን ከጥያቄያችሁ መልስ ጋር አቀርባለሁ ፡፡

__________________________________

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉

ቴሌግራም ሊንክ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet

ምንጭ ፦ Emotional survival guide for care givers ከሚለው የዶ/ር ቤሪ ያኮብስ መጽኃፍ መነሻነት የቀረቡ

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
#የሳምንት_ሰው_ይበለን !

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊
የበታችነት ስሜትን የማሸነፊያ መንገዶች
www.tg-me.com/psychoet #Share

ማንም ከበታችነት ስሜት ጋር የተወለደ ወይም የሚወለድ ሰው የለም፡፡ የበታችነት ስሜት ተፈጥሮአዊ ሳይሆን በአካባቢ ተጽእኖ የሚመጣ ውጤት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ሰዎች ስለራሳቸው የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው ከአካባቢያቸው ይማራሉ፡፡ የተማሩትን ነገር ደግሞ ትተው፣ አዲስ ነገር መማር ይችላሉ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የበታችነት ስሜት ሊለወጥ የሚችል አስተሳሰብ ነው፡፡

እያንዳንዱ ሰው በተፈጥሮ እንዲሁም ካደገበት አካባቢ አንጻር ልዩ በመሆኑ የበታችነት ስሜትን የሚያሸንፍበት አንድ ወጥ የሆነ አካሄድ ላይኖር ይችላል፡፡ ሆኖም በዚህ ዓይነት ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች ከዚህ በታች የተጠቀሱ ምክሮችን ተግባራዊ ቢያደርጉ ስለራሳቸው ጤናማ/ትክክለኛ የሆነ እይታ ሊያሳድጉ ይችላሉ፡፡

በሌሎች ሰዎች አስተያየት ላይ ጥገኛ አለመሆን

 በልጅነት ወቅት አንድ ነገር ሰርተን፣ ወላጆቻችን ወይም ትልልቆች ብለን የምናስባቸው ሰዎች ጥሩ ነው፣ ትክክል ነው፣ ጎበዝ .… እንዲሉን እንፈልጋለን፡፡ በጎልማሳነት ጊዜ እንዲህ ያለውን የልጅነት ወቅት ባህርይን መተው አስፈላጊ ነው፡፡ ከሰዎች ተገቢውን አስተያየት መጠየቅና ስራችንን መገምገም ጠቃሚ ቢሆንም፣ በእነርሱ አስተያየት ላይ ጥገኛ መሆን  ዞሮ ዞሮ ለራሳችን ያለንን አመለካከት ይጎዳል፡፡

ራሳችንን ከአሉታዊ አስተሳሰቦች መለየት

 በተቻለ መጠን ራሳችንን/ ማንነታችንን በአእምሮአችን ውስጥ ከተከማቸው አሉታዊ አስተሳሰብ መለየት አለብን፡፡ በሌላ አነጋገር በእነዚያ አሉታዊ አስተሳሰቦች ራሳችንን መመዘን ስንተው፣ እነዚያ አስተሳሰቦች ኃይል ያጣሉ፡፡ በእርግጥ ከእኛ ጋር ለረጅም ጊዜ የቆዩ ከሆኑ፣ ከእነርሱ ጋር ዝምድና ስለፈጠርን በቀላሉና ቶሎ ላይሄዱ/ላይለዩን ይችላሉ፡፡ ሆኖም ከእነርሱ ጋር ላለመኖር ከወሰንን፣ ቀስ በቀስ ስፍራውን ይለቃሉ፡፡ በእነርሱ ስፍራ ደግሞ ተገቢ የሆኑ ሃሳቦችን እናስገባለን፡፡ እነዚያ ቀስ በቀስ ገብተው ስፍራ እንደያዙ ሁሉ፣ አዲሱና መልካም የሆነው አስተሳሰብም ዕድል ከሰጠነው ቀስ በቀስ ወደ አእምሮአችን ገብቶ ሥፍራውን ይይዛል፡፡

በውድቀታችን ራሳችንን ከመኮነን ከውድቀታችን መማር

 ስህተት የማይፈጽም ሰው የለም፡፡ ልዩነት የሚያመጣው ስህተታችንን የምናስተናግድበት ሁኔታ ነው፡፡ በስህተታችን ራሳችንን እየወቀስን የምንሄድ ከሆነ፣ ራሳችንን ለመቀበል እንቸገራለን፡፡ ከስህተታችን ተምረን ወደፊት ማሻሻል የሚገባንን ነገር የምናስብ ከሆነ ደግሞ ራሳችንን ተቀብለን ወደፊት እንሄዳለን፡፡ ስለሆነም በህይወታችን በእኛም ሆነ በሌሎች ሰዎች በደረሰቡን ችግሮች፣ ውድቀቶች፣ አለመሳካቶችና መልካም ያልሆኑ ነገሮች ሁሉ ራሳችንን እንዲሁም ሌሎች ሰዎችን ከመኮነን፣ ከክፉ ነገሮች መልካምን ነገር ተምረን ወደፊት መሄድ የተሻለ አማራጭ መንገድ ነው፡፡

ራሳችንን በፉክክር ውስጥ አለማስገባት

እያንዳንዱ ሰው ልዩ ሆኖ የተፈጠረ ፍጡር ነው፡፡ በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ያለው እምቅ ችሎታ አንድ ዓይነት ላይሆን ይችላል፡፡ እያንዳንዱ ሰው ያደገበትና ያለበት ዓውድ ልዩነት አለው፡፡ ስለዚህ ከሌሎች ጋር ሁልጊዜ መፎካከርና ራሳችንን ከሌሎች አንጻር ከመገመት ይልቅ እኛ ዘንድ ያለውን መልካም ነገር በመለየት በተሻለ መንገድ መጠቀም የምንችልበትን መንገድ መቀየስ ይረዳናል፡፡ ከሌሎች ሰዎች ስኬት፣ ብርታት፣ መልካም ነገሮች፣ አሸናፊነት ለራሳችን መልካም ቁምነገሮችን መማር እንችላለን፡፡ ስለዚህ የፉክክር የህይወት ዘይቤን በመተው ከሌሎች መማርን መልመድ ጠቃሚ ነው፡፡

ስጦታችንን በመለየት ማሳደግ

 እያንዳንዱ ሰው ስጦታ እንዳለው ሁሉ እኛም ስጦታ አለን፡፡ ስለዚህ በውስጣችን ያለውን እምቅ ችሎታ፣ ፍላጎታችንንና ምቹ ሁኔታዎችን በመለየት ስጦታችንን በዕውቀትና በክህሎት ማሳደግ እንችላለን፡፡ ጎበዝ በሆንበት ወይም መስራትና መሆን በምንፈልገው ጉዳይ ላይ የበለጠ ዕውቀትና ክህሎትን በማጎልበት የበለጠ ፍሬያማ መሆን እንችላለን፡፡  በችሎታችን ራሳችንና ሌሎች ሰዎችን መጥቀም ስንችል ደግሞ እርካታና ደስታን እናገኛለን፡፡ ለሰዎችም አንድ በጎ ነገር ማድረግ መቻላችን ደግሞ ስለራሳችንም በጎ አስተሳሰብ እንዲኖረን ያግዘናል፡፡

ባለሙያን ማማከር

እንግዲህ ራሳችንን የመቀበል ችግር ሲኖረን በአብዛኛው ከበጎ ነገር ይልቅ በህይወታችን ውስጥ ባሉ ድክመቶች፣ ጉድለቶችና ስህተቶች ላይ ትኩረት እናደርጋለን፡፡ የበታችነት ስሜት መንስኤ የሆኑ ነገሮችን ለይቶ ማወቅ ተገቢውን መፍትሔ ለመፈለግ እጅግ ያግዛል፡፡ ምክንያቶቹ ከሰው ወደ ሰው የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ራሳችንን የማንቀበል ከሆነ እኛው ለራሳችን ጠላቶች ሆንን ማለት ነው፡፡ ሁልጊዜ ከራሳችን ጋር እንጣላለን፡፡ ጠላትን በውስጣችን ተሸክመን እንዞራለን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ራሳችንን በመቀበል በሰላም በመኖር የበታችነት ስሜትን ማስወገድ እንችላለን!

ገንቢ ያልሆኑ መንገዶች

በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት እንዲሁም ስለራሳችን ጥሩ ስሜት እንዲሰማን እንከን የለሽ ስራዎችን ለመስራት ጥረት ማድረግ የማይጠቅም አካሄድ ነው፡፡ ማንም ሰው በንግግሩና በስራው ፍጹም መሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ ይህን ዓይነት መንገድ መከተል የበለጠ ራስን ለውድቀት ብሎም ለበለጠ የበታችነት ስሜት እንዲሰማን ሁኔታዎችን ማመቻቸት ይሆናል፡፡

በቅናት መንፈስ ውስጥ ሆኖ ከሌሎች ሰዎች በልጦ ለመገኘት ጥረት ማድረግ የበታችነት ስሜትን አያጠፋም፡፡ ጤናማ ያልሆነ ፉክክር በማሸነፍና በመሸነፍ ሚዛን ውስጥ ያስገባናል፡፡

ብዙ ጊዜ በአሉታዊ ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ የበታችነት ስሜታችን እንዲኖር እንዲሁም እንዲያድግ ያደርጋል፡፡

ከሌሎች ሰዎች በችሎታ፣ በብቃት፣ በትምህርት ደረጃ፣ በገንዘብና በሌሎች ነገሮች እኩል ብንሆን ስለራሳችን ያለን አስተሳሰብ በጎ እንደሚሆን ማሰብ ሁልጊዜ ትክክል አይደለም፡፡ ስለዚህ ትኩረት መደረግ ያለበት ደረጃን በማሻሻል ላይ ሳይሆን በማንኛውም ደረጃ ላይ ብንሆን ራሳችንን ተቀብለን መኖር መማር ላይ ነው፡፡ ስለራሳችን ያለንን አሉታዊ ስሜት ማስወገድ ይገባናል፡፡

#Share
©Zepsychology
#ይሉኝታ
እጅግ ጠቃሚ ጽሑፍ ነዉ ። በደንብ ይነበብ ።
#ይሉኝታ_ምንድን_ነው?
የሰዎችን ደስታና ሃዘን መካፈል፤ ለሰዎች በችግራቸው ጊዜ ያአቅምን ማድረግ አብዛኞቻችን ያስደስተናል፤ እርካታም ይሰጣል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንዴ ሰዎች በይሉኝታ ሲታሰሩና ከፍላጎታቸው እና ከአቅማቸው በላይ ጊዜያቸውን፤ ገንዘባቸውን፤ ሃሳባቸውን ለሌሎች ሰዎች ደስታ ሲያውሉ ይታያል፡፡ ይሉኝታ ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል ሰበብ፤ የራስን ፍላጎት ገትቶ ሌሎችን ለማስደሰት መጣር፤ ሌሎችን ማስቀደም ማለት ነው፡፡ ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች ከሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እና ግዴታ በላይ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ይሉኝታ የራሳቸንን ስራና አጀንዳ ወደ ጎን አድርገን ፤ ፍላጎታችንና እና ምርጫችን ተጭነን ሌሎችን ለማስደሰት የመፈለግ ውጤት፡፡

#የይሉኝታ_መንስኤዎች
•ከመጠን በላይ የሆነ የሌሎችን ሰዎች ተቀባይነትና ትኩረት ለማግኘት መሻት

•በራስ መተማመን ማነስ

•ሌሎች ስለእኛ የሚያስቡት ጥሩ ብቻ እንዲሆን መጨነቅ፡-ስለራሳችን ጥሩነት የሚሰማን ሌሎች በሚሰጡን አስተያየት እና ማሞካሸት ከሆነ

•የውስጥ መረጋጋት ከሌለን

•አስተዳደግ፡- ያደግንበት ቤተሰብ ሰዎችን ማስደሰት እንደ ትልቅ መርህ የሚያይ ከነበረ፤ ወይም ደግሞ ቤተሰባችን ውስጥ በረባ ባልረባው የሚቆጣ ሰው ከነበረና ያንን ሰው ለማስደሰት ፍላጎታችንን እየተጫንን ያደግን ከሆነ

•ያደግንበት ማኅበረሰብ ወግና ልማድ፡-በማኅበረሰባችን በማንኛውም መንገድ ቢሆን በመረዳዳት፤ ያለንን ለሰዎች በማከፈልና “እሺ ባይነትን” እንደ መልካም ባህሪያት መውሰድና ግለኝነትንና እምቢ ባይነትን ደግሞ እንደ እኩይ ባህሪይ የመውሰድ ልማድ

#ይሉኝታ_የሚያጠቃቸው_ሰዎች_መገለጫ_ባህሪያት
•ከሌሎች ሰዎች ሃሳብ ጋር ሁሌም መስማማት እንዳለብን ሲሰማን

•ሰዎችን ሊያስደስታቸውና ሊያስከፋቸው ይችላሉ ብለን የምናስባቸው ነገሮች ላይ በብዛት መጨነቅ

•ሳናምንበትም እንኳ ቢሆን ስለሌሎች ሰዎች መጥፎ ነገር ሲወራ አብሮ ማማት

•ሰዎች ስለኛ ምን ሊያስቡ እና ምን ሊናገሩ እንደሚችሉ ማሰብና መጨነቅ

•የሃሰብ ልዩነቶችንና ግጭቶችን ተጋፍጦ በሃሳብ ከመርታት ይልቅ መሸሽ፤ ሃሳቦች ሳይብላሉ ማቋረጥ

•ሰዎች በውይይት መሃል የተለየ ሃሳብ ሲያነሱ ከሃሳቡ ይልቅ ሰዎች ላይ ማተኮር

•ሃሳባችን ከማንጸባረቅና ላመንበት ነገር ከመቆም ይልቅ ለቡድን ተጽእኖ እጅ መስጠት

•ከደንብና መመሪያ መከበር ይልቅ በሰዎች ለመሞገስና ለመከበር ትኩረት መስጠት

•የፈለገውን ያህል ዋጋ ቢያስከፍለንም ሌሎችን ላለመሳከፋትና ላለማበሳጨት መጣር

•አይሆንም የማለት ድፍረት ማጣት፤ ለሁሉም ነገር እሺን ማስቀደም

#ይሉኝታ_የሚያስከትለው_ጉዳት
•በራሳችን ህይወት ደስተኞች አንሆነም፤ ስልቹዎች እንሆናለን

•ከሰዎች የምንጠብቀውን ማበረታትና ተቀባይነት ሁሌም ላናገኝ እንችላለን

•ራስ ወዳድና በሌሎች ሰዎች መጠቀም ለሚፈልጉ ሰዎች ተጋላጭ እንሆናለን

•ሁሉም ቦታ ለመገኘት ስንጥር በስራችን ውጤታማ አንሆንም

#ይሉኝታን_ለመቀነስ_የሚረዱ_መንገዶች
•ለሰዎች መልካም በመሆንና በይሉኝታ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት

•ለምናደርገው ነገር ከስሜት ይልቅ ምክንያታዊነትን ማስቀደም፡፡ ለምንድን ነው ይህን ጉዳይ የምፈጽመው? ሰው ምንይለኛል ብየ ስለፈራሁ? ወይስ ስለሚያስደስተኝ? ወይስ ኃላፊነት ስለሚሰማኝ?

•በማድረጋችን፤ ወይም በመፈጸማችን ቆይተን የምንጸጸትበትን ጉዳይ ከማድረግ መቆጠብን መልመድ

•አስፈላጊ ሲሆን “አይሆንም” ማለትን ወይም ደግሞ “ላስብበት” ማለትን መልመድ

•በራስ መተማመንን ሊያዳብሩ የሚችሉ የህይወት ክህሎቶችን መለማመድ

•ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ጤናማ ወሰን እንዲኖረን መጣር

•ለራሳችን ክብር መስጠት፡- ሰዎች ስለኛ ምንም ቢያስቡ፤ በማንነታችን ላይ ሊያመጣው የሚችለው ተጽእኖ ብዙ እንዳልሆነ ለራሳችን መንገር

•ያደግንባቸውንና ከማኅበረሰብ ያገኘናቸውን ልምዶች በህይወታችን ያመጡልን በጎና መጥፎ ጎን መከለስ፤ማስተዋል

(በሰብለወንጌል አይናለም)
©zepsychology

Join My Telegram Channel www.tg-me.com/Psychoet
#መልካም_ታህሳስ_ወር !
T.me/psychoet

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ፍትህ ፣ ሰላም ፣ ልማት የምንሰማበት ይሁንልን ፡፡

አንድ ቀን ነገር ሁሉ ቀላል ይሆናል ! ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ ።
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

ለምትወዱት ጓደኛ #መልዕክቱን አስተላልፉ

@Psychoet
2024/09/29 09:26:00
Back to Top
HTML Embed Code: