Telegram Web Link
GreenFire-Feb2020.pdf
1 MB
" አለማችን ከዓይን ጥቅሻ በፈጠነ የለውጥ ግስጋሴ ላይ ትገኛለች ፡፡ ከአንዱ ጫፍ ወደ ሌላው ጫፍ የሚደረገው ግስጋሴ ለማመን ያስቸግራል ፡፡ ወደዚህ ምድር እስከአሁን ድረስ 108 ቢሊዮን በላይ የሰው ልጆች መተዋል ተብሎ ይታመናል ፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ ሰው ደስታን የሚሻ ነው ። ..."

😀😃😄😁😆
📌አንድ ሰው ደስተኛ ሕይወት ለመኖር ምን ምን ነገሮችን ማድረግ አለበት ?

📓 ይህ ትውልድ በተለይ በዚህ ጊዜ ወጣት የሆነ (Generation y )የሕይወትን ደስታና እርካታ እንዴት ያግኝ? በሚል የፃፍኩትን አጭር መጣጥፍ #በገፅ_8 ላይ ታገኙታላችሁ ፡፡
መልካም ንባብ !

አስተማሪ ስለሆነ ባለንበት ግሩፕ #Share እናርግ 🧳ONLY 1.0 MB

#መልካም ግንቦት 20 ይሁንላችሁ 😉
@Psychoet
ሕይወትህ ወደ መጥፎ መንገድ እየሄደ እንደሆነ የምታቅበት 10 መንገዶች

ሁላችን በዚህ ምድር ላይ ያለ አላማ አልተፈጠርንም ፡፡ የፈጠረን ፈጣሪ በምድር ላይ እንድንሰራው የሚፈልገው ትልቅ ስራ አለ፡፡ ነገር ግን ከዚህ መንገድ ስንወጣ ወይም መጥፎ ነገሮች በሕይወታችን መከሰት ሲጀምሩ ተፈጥሮ ራሷ የተለያዩ መልዕክቶችን ትልክልናለች፡፡

ይህን ተፈጥሮ በራሷ ሕይወታችን ወደ መጥፎ መንገድ እየሄደ እንደሆነ በእነዚህ 10 መንገዶች ትጠቁመናለች፡፡ የ ሁለት ደቂቃ Videoውን ይከታተሉ፡፡

የዩቲዩብ ቻናላችን ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ

https://youtu.be/6Vg_Y8Hioh0
ሰላም እንደምን አመሻችሁ!
ሁላችንም ሰዎች መጠኑ ቢለያይም በትንሽና በትልቁ እንናደዳለን ፡፡ ታዲያ ንዴታችን ሳይቆጣጠረን እንዴት እንቆጣጠረው የሚለው የሁላችን ጥያቄ ነው ፡፡ ለንዴት መቆጣጠሪያ መፍትሄ የሚሆኑ ሀሳቦችን በዚች 4 ደቂቃ ቪዲዮ ታገኛላችሁ ፡፡
https://youtu.be/ETxUH0eSi94
እንደምን አመሻችሁ !
የሳምንቱ የሳይኮሎጂ ትምህርት ከእናንተ የወሰድኩትን አስተያየት ጨምሬ በአዲስ መንገድ ከሰኔ ወር ጀምሮ ይቀጥላል ፡፡
ዛሬ ግን ሁላችሁም ይህን የምታነቡ ከመተኛታችሁ በፊት #5 ደቂቃ ወስዳችሁ ይህን እንድታስቡ እጠይቃችኀለሁ ? እመኑኝ እነዚህን ጥያቄ መልሳችሁ ከተኛችሁ ነገ ለናንተ "አንድ እሑድ" ብቻ ሳይሆን ልዩና መልካም ቀን ይሆናል ፡፡



📌 ከተወለዳችሁ አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ የሰራችሁት #ትልቁ_የደግነት_ስራ ምንድን ነው ?
📌ከተወለዳችሁ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በጣም ትልቅ የምትሉትን ውለታ የዋለላችሁ ሰው ማነው?



@Psychoet
መልካም ምሽት እና አዳር!
#ህይወትን_በአዲስ_እይታ
www.tg-me.com/psychoet

ብዙዎቻችን ህይወትን የምንደርስበት ግብ አድርገን ፣ነገ የምናገኘው፣ ከልፋት በኋላ የምንቀዳጀው፣ ከአድማስ ባሻገር ያለ የቅርብ ሩቅ አድርገን እንስለዋለን። ይህ ግን ዛሬን እንደ መራራው ኮሶ መድኃኒት እየተጋትን ነገን በሰማይ እናዳለችው ወተቷን እንደማናየው ላም እየናፈቅን የቅዠት ኑሮ፣ በተስፋ መቁረጥ የታጨቀ፣ መፍጨርጨር የተሞላበት ግቡን ቀና ብሎ የሚያይ ግን የችግሮች እንቅፋት የሚያገላድፈው እይታችን ነው። ይህንን እይታ የኑሮ መሰረታቸው አድርገው የትዳር አጋራቸውን ያለፍቃዳቸው የራቁ፣ ልጆቻቸውን የማይንከባከቡ፣ ለእራሳቸው በቂ ጊዜ የማይሰጡ፣ ነፍሳቸው የወደደችውን ነገር ማድረግ እንደ ቅንጦት የሚቆጥሩ ሞልተዋል። ይህ ደግሞ በስተመጨረሻ ቁሳዊ የሆነ ማንነት አሳቅፎ ብቻችንን ያስቀረናል።

ግን እስኪ ደግሞ በዚህ በኩል እንመልከተው! ህይወት ግብ ሳይሆን መንገድ ነው። እራሳችንን እያወቅን የምንጓዝበት፣ በመኖራችን ለውጥ የምናመጣበት፣ በስህተታችን ተምረን የምንቀየርበት፣ በገጠመኞች የተሞላ ወደ ተሻለ ማንነት የሚደረግ ጉዞ። ይህን እይታ ከያዝን ለነገ መኖርን እናቆማለን ማለት ሳይሆን ነገን እያሰብን ዛሬን እስከነ ጭራሹ ከመዘንጋት እንላቀቃለን። ግለኝነትን ያተኮረ የራሴ ጥቅም ብቻ እያልን በሰዎች ጫንቃ ላይ በመወጣጣት እኔን ብቻ ላኑር ከሚል ርካሽ አስተሳሰብ ከላያችን ላይ አራግፈን በዛሬ ውስጥ እራሳችንን ማግኘት ያስችለናል።

ዛሬ ጊዜ ያልሰጠናቸው ቤተሰቦቻችን ነገ “እንደዛ ስለፋ የነበረው አንተ የሻለ ኑሮ እንድትኖር በማሰብ ነው” “እንዲህ እንድትንደላቀቂ ብዬ ነው ቀን ከለሊት ስለፋ የነበረው” የሚል የየዋህነት አስተሳሰብ ያሳጣናቸውን ፍቅር እና አብሮነት አይተካም። ገንዘብ ለልጆቻችን ጃኬትን እንጂ ማቀፍ የሚሰጠውን የደህነትን ስሜት አይገዛም። ገንዘብ ውድ የሆነ ስጦታን እንጂ ከትዳር አጋራችን ጋር የምናሳልፈውን ጊዜ አይገዛም፣ ገንዘብ አልጋን እንጂ እንቅልፍን አይገዛም፣ ገንዘብ ምግብን እንጂ የምግብ ፍላጎትን አይገዛም። ስለዚህ በእኛነታችን የምንሰጣቸውን፣ የገንዘብ ቁልል የማይገዛቸውን፣ የመኖር ሃብቶች፣ የህይወት ስጦታዎች የሆኑትን እኚህን የዛሬ ውጤቶችን አሳጥተናቸው ነገ ገንዘብ ብንሰጣቸው ዋጋው ምንም ነው።

ህይወታችንን ግብ አድርገን ከምንስለው በዕለት ተዕለት ኑሮዋችን ውስጥ የምናደርጋቸው ማናቸውም ቁርኝቶች ድምር መሆኑን ብናምን ይህ አዲስ እይታ የብርሃን ጮራ በህይወታችን ላይ ይፈነጥቅልናል።

(ዘመነ ቴዎድሮስ) ©psychologist
www.tg-me.com/psychoet
እያንዳንዱ ትልቅ ነገር ትናንሽ መነሻዎች አሉት

ተፈጥሮ በኡደት (Process) የተመላች ናት፡፡ ዘመናትን በጊዜ ቀመር አስልታ ከአንዱ ምዕራፍ ወደ ሌላኛው ታሻግራለች፡፡ የኡደት ስሌትዋ ከትልቅ ወደ ትንሽ ሳይሆን ከትናንሽ ወደ ትላልቅ የሚያመራ ነው፡፡

የሰው ልጅ የዕድገት ለውጥ ዓላማ በተፈጥሮ የወረሰውን እምቅ ኃይል ከከፍተኛ ደረጃ ላይ ማድረስ ነው፡፡ ኤልሳቤጥ ሃርሎክ የተባለች የሳይኮሎጂ ምሁር እንደገለጸችው ሰዎች በአእምሮ ፤ በአካል ከሌሎች የተሻሉ ሆነው ለመገኘት የሚያደርጉት ጥረት ወደ ዕድገት ለውጥ ግብ ለመድረስ የሚደርጉት ጥረት ስለሆነ እነዚህን ጥረቶቻቸውን እውን ለማድረግ ይችሉ ዘንድ ዕድሉ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

እዚህ ላይ ትልቁ ጉዳይ ሰዎች እራሳቸውን ለማሻሻል እምቅ አቅምና ችሎታ ካላቸው ከወዴት ነው የሚጀሚሩት የሚለው ነው፡፡ ብዙዎቻችን በስራችንና በህይወታችን የምንፈልገውንና የምንሻውን ያህል ውጤታማ መሆን ያልቻልነው ዕቅዶቻችንንና ስኬቶቻችንን ከታች ከትንንሽ ነገሮች ስለማንጀምራቸው ነው፡፡ ቀድሞ የሚታየን ትልቁ ስዕል እንጂ ወደ ትልቁ የስኬት ጎዳና ለመድረስ ከትንሽ ነገር መጀመር እንዳለብን አንገነዘብም፡፡ ከዚህ በታች ከትንንሽ ነገር ተነስተን ወደ ትልቁ ስኬት ለመጓዝ የሚረዱንን ነጥቦች እንመለከታለን፡፡

1.ትምህርት

የተሻለ የትምህርት ደረጃ ያለቻው ሰዎች ስራዎቻቸውን የሚያከናውኑት ዕውቀትንና ዕቅድን መሰረት አድርገው ነው፡፡ በስራዎቻቸው ላይ ወሳኝ ጉዳዮችን በደንብ ስለሚያውቁ ከሌላው ሰው በተሻለ ሃሳብና መረጃ ይኖራቸዋል፡፡ ስለዚህ ዕውቀቶቻቸውን በመመንዘርና ማኅበራሰባቸውን በማገልገል የተሻለና የተሳካ ህይወት (ገቢንም ጨምሮ) መኖር ይችላሉ፡፡ ዕውቀት በጨመረ ቁጥር የሰው አስተሳሰብ አድማሱ ስለሚሰፋ ምን ሰርቶ ምን ማግኘትና የት እንደሚደርስ አቅጣጫን ይጠቁማል፡፡ ትምህርት ስንል በአንድ የትምህርት መስክ የምናገኛውን የሰርተፍኬት ብዛት ብቻ ሳይሆን በህይወት ልምድና ተሞክሮ ያገኘነውን ዕውቀት ትርጉም ባለው ስራ ላይ ማዋልና በትንሽ በትንሹ በመደበኛም ይሁን ኢ-መደበኛ ትምህርት ታግዘን ህይወትን ለማሸነፍ የምንሄድበትን የህይወት ጉዞን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡

2. ክህሎት

በአንድ ነገር ላይ የሚኖረን ክህሎት የምናስመዘግበውን ውጤት ብዛትና ጥራት ይወስናል፡፡ የምንሰራውን ስራ በደንብ ካወቅነው በስራችን ቅልጥፍና ወደ ሚቀጥለው ምዕራፍ በብቃት መሸጋገር እንችላለን፡፡ ከማናውቀው ነገር አንድ ብለን ከመጀመር የምናውቀውን ነገር አሻሽሎ በመስራትና ክህሎትን በማዳበር የተሻለ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡
3. ግንኑነትን ማስፋት
በምንሰራው ስራ ላይ ብዙ ሰዎችን ለማወቅ ከጣርን ግንኙነታችንን በማጠናከር አማራጮችን ማስፋት እንችላለን፡፡ ስለዚህ የግንኙነት አድማስን ለማስፋት ዘውትር ማኅበራዊ ገመዶቻችንን በረጅሙ መዘርጋት አለብን፡፡

4. ጥሩ የስራ ልምድ

ጥሩ የስራ ልምድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ስራዎችን እንድንሰራ ይረዳናል፡፡ ይህን ለማድረግ ስራዎቻችንን በዕቅድ መስራት አለብን፡፡ ጥሩ የስራ ልምድ አንድን ነገር ከማከናወናችን በፊት አስቀድመን እንድናስብበት ስለሚያስችለን ከስራው በኋላ የሚከሰቱትን ማንኛውንም አወንታዊና አሉታዊ ውጤቶችን አስቀድሞ መገመት ስለሚያስችል ኪሳራን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

6. አወንታዊ አመለካከት

የምንሰራው ስራ እኛነታችንን ስለሚገልጸው በስራችን ላይ አወንታዊ አመለካከት ፤ በእራስ መተማመን ፡ ከስራ ባልደረቦቻችን ጋር ጥሩ መስተጋብር ካለን ሁሌም መልካም ነገር እንድናስብ ስለሚረዳን ወደ ምንፈልግበት ደረጃ እንድንደርስ አወንታዊ አመለካከት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡

7. ስለራሳችን ጥሩ ስዕል ይኑረን

ስለራሳችን ጥሩ ስዕል ወይም ምልከታ መያዝ የምንፈልገውንና ደስተኛ ህይወት እንዲኖረን ይረዳናል፡፡ ሰዎች በውጫዊ ገጽታችን ሊገምቱንና ሊፈርጁን ይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ውጫዊ ምልከታ የእኛንም ሆነ የሌላውን ስለማይገልጽ ስለእራሳችንም ሆነ ስለሌሎች ሰዎች ጥሩና የተቃና አመለካከት ሊኖረን ይገባል፡፡

8. ፈጠራ

ፈጠራ አንድን ነገር ዘውትር በተሻለ ፍጥነት፤ ቅልጥፍና ፤ በቀላል አኳሃን እንድንተገብረው ይረዳናል፡፡ ፈጠራ አዲስ ነገር ፈጥሮ ወይም ሰርቶ ማሳየት ብቻ ሳይሆን ነገሮችን ከዚህ ቀደም ከምናያቸው ዕይታና ግንዛቤ በአዲስ መልኩና በሌላ አቅጣጫ ማየትንም የሚያካትት ነው፡፡

9. ማንነት

እራስን መግራትና ግልጽነት ብዙ የስኬት በሮችን እንድንከፍት ይረዳናል፡፡ መተማመን የግንኙነት ሁሉ መሰረት ነው፡፡ ሰዎች የሚያውቁን በድርጊታችንና በቃላችን የምንታመን ከሆነ ነገሮችን በፍጥነት በቀላልና በታማኝነት በእኛ በኩል እንደሚያገኙ ያምናሉ፡፡ ይህም ብርታትና በራስ መተማመንን ስለሚፈጥርልን ወደምንፈልገው ደረጃ ለመድረስ ትልቅ እገዛ ያደርግልናል፡፡
ዕቅድህ 15ኪሎ ክብደት መቀነስ ከሆነ በቀላሉ እንቅስቃሴ ማድረግና አመጋገብህን በማስተካከል ከትንሹ መጀመር ትችላለህ፡፡ ከዚያ ወደ ምትፈልገው ደረጃ ስትደርስ እያንዳንዱ ትልቅ ነገር ትናንሽ መነሻዎች እንዳሉት ትገነዘባለህ፡፡ ሻሎም

አንቶኒዮ ሙላቱ
©Zepsychologist
@psychoet
ሰላም እንደምን አመሻችሁ!
ሁላችንም ሰዎች መጠኑ ቢለያይም በትንሽና በትልቁ እንናደዳለን ፡፡ ታዲያ ንዴታችን ሳይቆጣጠረን እንዴት እንቆጣጠረው የሚለው የሁላችን ጥያቄ ነው ፡፡ ለንዴት መቆጣጠሪያ መፍትሄ የሚሆኑ ሀሳቦችን በዚች 4 ደቂቃ ቪዲዮ ታገኛላችሁ ፡፡
https://youtu.be/ETxUH0eSi94
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «ሰላም እንደምን አመሻችሁ! ሁላችንም ሰዎች መጠኑ ቢለያይም በትንሽና በትልቁ እንናደዳለን ፡፡ ታዲያ ንዴታችን ሳይቆጣጠረን እንዴት እንቆጣጠረው የሚለው የሁላችን ጥያቄ ነው ፡፡ ለንዴት መቆጣጠሪያ መፍትሄ የሚሆኑ ሀሳቦችን በዚች 4 ደቂቃ ቪዲዮ ታገኛላችሁ ፡፡ https://youtu.be/ETxUH0eSi94»
ከጭንቀት ነፃ የሆነ «ደስተኛ ሕይወት» ለመኖር ወሳኝ የሆኑ #አሥር_የሕይወት_መርሆች

1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው።

2. አትኩሮትህ በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ ይሁን፡- ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፡፡

4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።

5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ ሲሆን እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፣ አላማችንና ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዘን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበትም ነው፡፡

6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦ ሰዎችን አትና፤ በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡

7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ/ለፈጣሪህ ስጠው።

8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ራስህን መውደድ ተለማመድ፤ የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን ሲያጠፋ ይቅር በማለት፣ ሲደክም በማበርታት፤ ሲሳካለት በማሞካሠት ተንከባከበው፡፡

9. መልካም አስብ መልካም ተናገር፦ በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።

10. ለምን እንደምትኖር እወቅ፦ ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱን ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይቀየራል፡፡

📌❇️ ደስተኛ ህይወትን ለሁላችንም ይስጠን ! መልካም የጤና ጊዜ!!!

ምንጭ - (ቶማስ እንደፃፈዉ፣ ፅሁፉ ከዶክተር አለ የተወሰደ)

🎡@🎡መልካም ቀን
#Join #Join #Join
🔸🔹 ↘️💯💯💯↙️🔸🔹
🚗 @Psychoet👍
🚕 @Psychoet👍
🚙 @Psychoet👍
#የጥሩ_እንቅልፍ_9_ጠቀሜታዎች
ከመተኛታችን በፊት #Share እናርገው

1. እንቅልፍ ልብዎን ጤናማ ያደርገዋል

እንቅልፍ ማጣት የልብ ድካም እና የደም ግፊት አደጋ(ስትሮክ) እንደሚያባብስ ተመራማሪዎች ይናገራሉ ይህም የሚሆነው የደም ግፊት እና ኮሌስትሮል መጠንን በመጨመር መሆኑን ይናገራሉ ፡፡በእያንዳንዱ ምሽት ከ 7 እስከ 9 ሰዓታት ያህል እንቅልፍ ካገኙ የልብዎን ጤና የተጠበቀ ይሆናል ፡፡

2. እንቅልፍ ካንሰርን ለመከላከል ይረዳል

ተመራማሪዎች ለብርሃን መጋለጥ የሜላቶኒንን መጠን እንደሚቀንስ ያምናሉ ፡፡ ሜላተንቲን የእንቅልፍ ና የመንቃትን ዑደትን የሚያስተካክል ሆርሞን ሲሆን በሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠሩ ዕጢዎችን እብጠት በመቀነስ ካንሰርን ይከላከላል፡፡ ሰውነትዎ የሚፈልገውን ሜላቶኒንን ለማምረት እንዲረዳዎ መኝታዎ ጨለመ ባለ ስፍራ ያድርጉ እንዲሁም ከመኝታዎ በፊት ኤሌክትሮኒክስን ከመጠቀም ይቆጠቡ ፡፡

3. እንቅልፍ ውጥረትን ይቀንሳል

ሰውነትዎ እንቅልፍ እጥረት ሲኖርበት ወደ ውጥረት(ስተርስ) ሁናቴ ይሄዳል ፡፡ ይህም ውጥረት ወየንም ስተርስ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ የልብ ድካም እና የደም ግፊት አደጋ የመያዝ እድልን ይጨምራል፡፡

4. በቂ እንቅልፍ ማግኘት የበለጠ ንቃትን ይሰጣል

ጥሩ የሌሊት እንቅልፍ ንቃት እንዲሰማዎት እና በሚቀጥለው ቀን እንዲነቃቁ ይረዳዎታል ፣ በተጨማሪም ጥሩ ስሜት እነዲሰማዎት በማድረግ ሌላ ጥሩ የሌሊት እንቅልፍ እድልዎተን ይጨምራል።

5. እንቅልፍ የማስታወስ ችሎታዎን ያሻሽላል

ተመራማሪዎች እስካሁኑ ሰዐት ድረስ ለምን እንደምንተኛ ሙሉ በሙሉ አልተረዱም ፣ ነገር ግን እንቅልፍ የማስታወስ ዐቅምን በማጠናር ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ደርሰውበታል፡፡
በእንቅልፍ ጊዜ ሰውነትዎ አረፍ ሊል ይችላል ፣ነገር ግን አንጎልዎ ቀንዎን በማቀነባበር የተያዩ ግንኙነቶችን በማድረጉ ሥራ ላይ ነው ፡፡ እነዚሀም ግንኙነቶች በተያዩ ክስተቶች ፣ በስሜት ህዋሳት ፣ ስሜቶች እና ትውስታዎች መካከል ሲሆን በቂ እንቅልፍ ማግኘት ነገሮችን በተሻለ ለማስታወስ እና ለማስኬድ ይረዳዎታል ፡፡

6. እንቅልፍ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል

ተመራማሪዎቹ እንዳሳዩት በማታ ጥቂት ሰዓታት የሚተኙ ሰዎች ከመጠን በላይ ወፍራም ወይም ከመጠን በላይ ውፍረት ያላቸው መሆናቸውን ነው ፡፡ የእንቅልፍ እጥረት በሰውነት የምግብ ፍላጎት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሆርሞኖችን መጠን ይጎዳል፡፡ ተመራማሪዎቹ እንዳሉት የምግብ ፍላጎትን የሚያስተካክሉ ሆርሞኖች ጋሬሊን እና ሌፕቲን በእንቅልፍ እጥረት ምክንያት ተስተጓጉለው ተገኝተዋል ፡፡ ክብደትን ለማቆየት ወይም ክብደት ለመቀነስ ከፈለጉ ፣ በመደበኛነት በቂ እንቅልፍ ማግኘት ሚናው ከፍተኛ መሆኑን አይርሱ።

7. ማቅለብ ብልጥ ያደርግልዎታል

በቀኑ ውስጥ አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ወይንም ናፕ መውሰድ ለአጠቃላይ ጤናዎ ጥሩ ሲሆን በተጨማሪም የበለጠ ምርታማ እንዲሆኑ አዕምሮዎትን የሚያድስ አማራጭ ነው ፡፡ ጥናቶችእንደሚያሳዩት ከሆነ በቀኑ ውስጥ አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ወይንም ናፕ የሚወስዱ ሰዎች የአዕምሮ ወይንም ኮግኒቲቭ ተግባር እና የ ስሜት መሻሻል ማሳየታቸውን ነው፡፡

8. እንቅልፍ የጭንቀት በሽታ አደጋዎን ይቀንሳል

ሴሮቶኒንን ጨምሮ እንቅልፍ በሰውነትዎ ውስጥ ያሉትን ብዙ ኬሚካሎች ይነካል። የ serotonin ጉድለት ያላቸው ሰዎች በጭንቀት በሽታ የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው። ትክክለኛውን የእንቅልፍ መጠን እያገኙ መሆኑን በማረጋገጥ ድብርትዎን ለመከላከል በየዕለቱ ከ 7 እስከ 9 ሰዓታት ያህል የዕንቅልፍ ጊዜ ይውሰዱ፡፡

9. እንቅልፍ ሰውነቱን በራሱ እንዲጠገን ይረዳል

እንቅልፍ ዘና የማለት ጊዜ ነው ፤ ሰውነታችን በቀኑ ጊዜ፣ በአልትራቫዮሌት ጨረሮች እና በሌሎች ጎጂ ነገሮች ምክንያት የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን ጠንክሮ የሚሠራበት ጊዜ ነው ፡፡ ተኝተው እያለ ሴሎችዎ የበለጠ ፕሮቲን ያመርታሉ ፡፡ እነዚህ የፕሮቲን ሞለኪውሎች የሰውነት ክፍሎችዎን በመገንባትና በማድስ ጉዳቱን ለመጠገን ያስችላቸዋል ፡፡

©በአቤል ታደሰ

ከመተኛታችን በፊት #Share እናርገው
መልካም አዳር
@Psychoet
ትልቁ ጥያቄ

ማንኛውም ሰው በህይወቱ  ጭንቀት አልባና  ደስታ የተሞላበት ህይወት ፤ ጥሩ ትዳርና ጣፋጭ የፍቅር ጊዜ ፤ ፍጹም መሆንና ሃብት መታደል ፤ ክብርና የመንፈስ ከፍታ ፤ ታዋቂና ዝነኛ መሆን ብቻ መልካም የሆኑ ነገሮች ሁሉ በህይወቱ እንዲገጥመው ይመኛል፡፡ እነኚህን የህይወት ውጥኖች ለማግኘት መመኘት በራሱ ችግር ባይኖረውም ፤ ምኞት ሁሉ እውነታ እንዳልሆነ መገንዘብ ብልህነት ነው፡፡ ምኞት በራሱ ስኬት አይደለም፡፡ ወደ ስኬት ለመድረስ የምንጓዘው ጉዞ ውጤታማነት የሚለካው የሚያጋጥሙንን ችግሮች ለመጋፈጥ በምናሳየው አቅምና ተነሳሽነት ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ምንአልባትም ብዙዎቻችን የዘነጋው ትልቁ ጥያቄ  ከምኞት ባሻገር በጉዞአችን ላይ የሚያጋጥሙንን እንቅፋት ፤ መሰናክልና ፈተናዎች መጋፈጥ እንፈልጋለን የሚለው ነው፡፡ ይህንን ጥያቄ መመለስ መቻል በራሱ ህይወታችንን በየትኛው አቅጣጫ መምራት እንደምንችል ፍንጭ ይሰጠናል፡፡

እያንዳንዱ ሰው ዋስትና ያለው ዳጎስ ያለ ገቢና የገንዘብ ነጻነትን የሚያጎናጽፍ ስራ እንዲኖረው ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ችግሮችን መጋፈጥንና በላብ ወዝ የድካምን ዋጋ ማግኘት እንደሚቻል ልብ አይለውም፡፡ ከዚህ ባሻገር ያለምንም መሰናክልና መስዋዕትነት ሃብታም መሆንን ይሻል፡፡

በሌላ መልኩ በትልቅ የፍቅር ባህር ውስጥ ትንሽ የእራሱን ደሴት ሰርቶ ጤናማ ትዳር ፤ ሰላማዊ ቤተሰብና ደስተኛ ህይወትን መምራት ፤ ህልም የሚመስል የፍቅር እውነትን በገሃዱ ዓለም መኖርን የሚመኘውም ሰው ጥቂት አይደለም፡፡ ነገር ግን ሁለቱ ጥንዶች በጋራ በመስማማት ፤ በትዕግስትና በመከባበር ፤ በወርቃማ የፍቅር ሰንሰለት ተሳስረው በጋራ የሚፈልጉትን ለማግኘት ካልጣሩ እንዲህ ያለው የፍቅር ቁርኝንነት ድራማ ወይም ፊልም ላይ ብቻ የምናየው ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ደስታ ፤ ሰላምና ፍቅር ትግልን ይጠይቃሉ በመሆኑም እግር አጣምረው ወደ ሰማይ ቢያንጋጥጡ ዝም ብሎ እንደ ዝናብ የሚወርድ የፍቅር ሲሳይ የለም፡፡

ሰዎች ጤናማና የተስተካከለ የሰውነት ቅርጽ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ ፤ ነገር ግን ዘውትር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ፤ የሚመገቡትንና የሚጠጡትን መምረጥ ፤ ከሱስ የጸዳና ጤናማ የህይወት ዘይቤን መከተል ወደሚፈልጉት ግብ እንደሚያደርሳቸው አይገነዘቡም፡፡

በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ የሰው ልጆችን ጠባይና ባህሪይ ስንመለከት ፤ ምንም እንኳን የፍላጎትና የእርካታ መጠናችን ቢለያይም ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ፍላጎት አለን፡፡ አወንታዊ ተሞክሮዎችን ማስተናገድና መቆጣጠር ቀላል ሲሆን በአንጻሩ አሉታዊ ሁኔታዎችን በትዕግስት ፤በጽናትና በትግል መጋፈጥ ብዙ ጊዜ አዳጋች ይሆንብናል፡፡ ስለዚህ ብዙ ጊዜ በህይወት የምናገኛቸው ስኬቶችና መልካም ነገሮች ጥሩ በመመኘታችን ወይም ባለራዕይ ስለሆንን ብቻ ያገኘናቸው ሳይሆን አሉታዊ ተሞክሮዎችን ተሻግረን መሄድ በመቻላችን ነው፡፡

እያንዳንዱ ሰው ለራሱ በቂ ነው ብሎ የሚያስበውን ነገር ለማግኘት ይመኛል፡፡ ነገር ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች በህይወታቸው በቂ ነው ብለው የሚያስቡትን ነገር ለምን እንደሚፈልጉት እርግጠኛ ሆነው መናገር አይችሉም፡፡ ሰዎች ከወር እስከ ወር ከዓመት እስከ ዓመት አንድን ነገር በመፈለግና በመመኘት ብቻ ቢቀመጡ ወደሚፈልጉት ቦታ ላይ መድረስ አይችሉም ይህም በመሆኑ ምኞታቸው የቁም ቅዠት ፤ ሃሳባዊና የማይጨበጥ ምናብ ሆኖ ይቀርባቸዋል፡፡

ስለዚህ አንድ ሰው አንድን ነገር ከመመኘቱ በፊት ምን ዓይነት ተግዳሮትና ችግር ፤ መጋፈጥና መቋቋም እችላለው ብሎ መጠየቅ ይኖርበታል፡፡ ያለመስዋዕትነት ድል አይገኝም በህይወት መንገድ ሳይቆስሉ መዳን ውጥረትን ሳይጋፈጡ ስኬት ማየትና ድሉንም ማጣጣም አይቻልም፡፡

በአጠቃላይ በህይወት መጋፈጥ የሚፈልጉትን ነገር መጠየቅ ወደሚፈልጉት የስኬት ጎዳና ስለሚያደርስ የሁላችንም የህይወት ትልም መጋፈጥ በምንፈልገው ነገር ላይ ይወሰናል፡፡ በህይወትዎ ምን መጋፈጥ ይፈልጋሉ? ለዚህ ትልቅ ጥያቄ በቂና ተግባራዊ ምላሽ ካለዎት ወደሚቀጥለው ምዕራፍ በድል መሸጋገር ይችላሉ፡፡
መልካም ጊዜ!

©zepsychology - አንቶኒዮ ሙላቱ
@psychoet
ሰላም ሰላም !

የቅዳሜ ማታ የሳይኮሎጂ ትምህርት ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ በአዲስ መልክ መቅረብ ይጀምራል፡፡ እኔም ከአንድ ወር እረፍት በኀላ ከ ሰኞ ጀምሮ (በFacebook እና በTelegram ) በአዳዲስ ትምህርቶች እመጣለሁ ፡፡

በተጨማሪም ከዚህ በፊት ከእናንተ የፔጁ ቤተሰቦች በሰበሰብኩት ቃለመጠይቅ መሰረት አወንታዊ አመለካከት ላይ ያተኮሩ ሀሳቦችን አቀርባለሁ፡፡ ከሳይኮሎጂ እንዲሁም ከአስተሳሰብ አንፃር ማንኛውንም ማወቅ የምትፈልጉትን ነገር በመልዕክት መቀበያዬ @psychoet_bot ላይ ብትፅፉልኝ በዛ ርዕስ ላይ ላይ ሀሳብ እሰጥበታለሁ ፡፡

መልካም ምሽት !
@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «ሰላም ሰላም ! የቅዳሜ ማታ የሳይኮሎጂ ትምህርት ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ በአዲስ መልክ መቅረብ ይጀምራል፡፡ እኔም ከአንድ ወር እረፍት በኀላ ከ ሰኞ ጀምሮ (በFacebook እና በTelegram ) በአዳዲስ ትምህርቶች እመጣለሁ ፡፡ በተጨማሪም ከዚህ በፊት ከእናንተ የፔጁ ቤተሰቦች በሰበሰብኩት ቃለመጠይቅ መሰረት አወንታዊ አመለካከት ላይ ያተኮሩ ሀሳቦችን አቀርባለሁ፡፡ ከሳይኮሎጂ እንዲሁም ከአስተሳሰብ…»
መነሳሳት

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

 8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

 10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ) ©Zepsychology
@Psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
ሰላም ሰላም ! ከ ነገ ጀምሮ በዚህ ፔጅ ለ 15 ቀን የሚደረግ (ግንቦት 16 - ግንቦት 30) አንድ አዲስ ቻሌንጅ እንጀምራለን ፡፡ ግንቦት 30 የመጨረሻው የሚያበቃበት ይሆናል ። ቻሌንጁ እንደዚህ ነው 👉🌸የምትወዱትን መጸሐፍ ርዕስ ለሁለት ሰዋች ትልካላችሁ ፡፡ ከታች እኔ ለሁላችሁም ልኬላችኀለሁ ያንን በመላክ መጀመር ትችላላችሁ ፡፡
ሰላም ዛሬ ግንቦት 30 ነው

ከ 15 ቀን በፊት መጸሐፍ የማንበብ ቻሌንጅ ነበረን ፡፡ ምን ያህሎቻችሁ ባለፉት 15 ቀናት አዳዲስ መጻሕፍትን እንዳነበባችሁ አላውቅም ፡፡
እኔ በበኩሌ ጓደኛዬ የላከልኝን Goals የሚል መጸሐፍ አንብቤያለሁ፡፡

ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል
በሕይወታችን ጥሩ መንገድ ያሳየናል፡፡

በዚህ ቻሌንጅ የተሳተፋችሁ በሙሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡
#መልካም_የሠኔ_ወር #10

እንደምን ሰነበታችሁ ቤተሰቦቼ !
እነሆ ከ 1 ወር የFacebook እረፍት ተመልሻለሁ ፡፡ ባለፉት 30 ቀናት እጅግ ብዙ አስተማሪ የሳይኮሎጂ ትምህርቶችን ፣ ምክሮችንና እውነተኛ የህይወት ገጠመኞች ላይ የተመሰረቱ አስተማሪ ጽሑፎችን ሳዘጋጅ ነበር ፡፡ በተጨማሪም በቴሌግራም ቻናል ላይ ባስሞላሁት የእድሜ መጠይቅ መሰረት ከሳይኮሎጂ ባልራቀ መሰረት ለአብዛኞቹ የፔጃችን ወጣት ቤተሰቦች የሚሆን ማህበራዊ ሀሳቦችን ይዤ ቀርቤያለሁ፡፡ እነሱም በሚቀጥሉት ቀናት በፔጃችን በኩል የማስተላልፍ መሆኑን እገልጻለሁ ፡፡

ለማታውቁኝ ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ እባላለሁ፡፡በዚህ ሳይኮሎጂ ፔጅ ዋና ጸሐፊና አማካሪ ነኝ ፡፡ ለሁላችሁም የፔጁ ተከታዮች ትልቅ አክብሮት አለኝ፡፡ በተለይም በሳይኮሎጂ ሙያ ብዙ አመት ህዝባችንን እያገለገላችሁ ያላችሁ በአካልም ሆነ በውስጥ መስመር እየሰጣችሁኝ ስላለው ምክርና አስተያየት ከልብ አመሰግናለሁ ፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ የቴሌቪዥን ሆነ የሬዲዮ ተቋማት የምትሰሩ ሰዎች ወደ ህብረተሰባችን እንድንደርስ እያረጋችሁት ስላለው ጥረት ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ፡፡

ማንኛውም ጥያቄ ወይም አስተያየት ያላችሁ በውስጥ መስመር fb.com/psychologyet ልትፅፉልኝ ትችላላችሁ ፡፡

www.tg-me.com/psychoet
#መልካም_ሰኞ
#መልካም_ሳምንት
#መልካም_ሠኔ
የአመለካከት ለውጥ

“ሰዉዬዉ ጭልፋዉን ዉሻ ትለክፍበታለች አሉ ፡፡ ያን ጭልፋ በካህን አስባረከዉ ፡፡ በነጋታዉም ድስቱን ስትለክፍበት ድስቱንም ወስዶ አስባረከዉ ፡፡ እሷ መጠጫዉንም መብያዉንም ሁሉ ስትለክፍ እሱ እየነጠቀ ወደ ካህኑ በማመላለስ ማስባረኩን ያዘ ፡፡ በስተመጨረሻም ካህኑ የሰዉዬዉ ነገር ቢታክታቸዉ ለብቻዉ ጠርተዉት ‘ዉሻዋን ራሷን አምጣትና ልባርክልህ ‘ አሉት ይባላል። ” ይሄን ጽሑፍ የዛሬ አመት ገደማ ነበር ያነበብኩት፡፡ ጽሑፉ ስለ ሰው ልጅ የአስተሳሰብ ለውጥ አጉልቶ ያሳያል ፡፡

ሕይወት ላይ ምንም ነገር ከምንጩ ካልተቀየረ በስተቀር ውጤቱን በየጊዜው መቀያየር የሚያመጣው ትልቅ ለውጥ የለም፡፡ ለዚህ ይመስለኛል ሁልጊዜ በየሚዲያው “ስር ነቀል ለውጥ ” ሲባል የምንሰማው፡፡

የማይታጠብ ሰው አዲስ ልብስ ቢቀያይር ራሱ ንፁህ አይሆንም ምክንያቱም ዋናው ችግሩ የነበረው ከላይ ልብሱ ሳይሆን ከውስጥ ሰውነቱ ነበር ፡፡ ማንኛውም ያለንበትን ሁኔታ ለመቀየርና ለመለወጥ ስናስብ ሁልጊዜ ከላይ ከላይ ሳይሆን በደንብ ከውስጥ ለመቀየር መነሳት ይገባናል ፡፡ የሰው ልጅ ማንኛውም ለውጥ የሚጀምረው ደግሞ ከራሱ አስተሳሰብ ፣ ስሜት ተግባር ነው ፡፡

ለምሳሌ በዙሪያችን ያሉ ብዙ ችግሮችን እንመልከት ፡፡ አብዛኞቹ ችግሮች እስካሁን ያልተፈቱት ከባድ ስለሆኑ ሳይሆን እኛ እነሱን ለመፍታት የወሰድነው እርምጃ ውስጣዊ ስላልነበረ ነው፡፡ በተጨማሪም ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ብዙ ሰው ደስተኛ ሕይወት የማይኖረው ፥ “ለመኖር በሚያስበው ሕይወትና አሁን እየኖረ ባለው ሕይወት” መካከል ባለ ሰፊ ልዩነት ነው ፡፡ ይህ ልዩነት ደግሞ የሚሞላው ሀሳብ ስሜትንና ተግባርን አካቶ በያዘ “ስር ነቀል” የውስጥ ለውጥ ሂደት ነው ፡፡ አለበለዚያ ነገሩ "አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ " ይሆናል፡፡

መልካም ቀን ይሁንላችሁ!
መልዕክቱ ለሌሎችም እንዲደርስ #Share እንድታረጉት እጠይቃለሁ ፡፡ ሀሳብ አስተያየቶቻችሁን #comment ላይ አስፍሩልኝ፡፡

ናሁሰናይ ፀዳሉ
www.tg-me.com/psychoet
fb.com/psychologyet
አሻራ ጥለው የሚያልፉ ሰዎች የሚበሩ ሳይሆኑ የሚራመዱ ናቸው ፡፡

@psychoet
ውድ ሳይኮሎጂስቶች

የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሳይኮሎጂ ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመተባበር "የሳይኮሎጂስቶች ሚና በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በኢትዮጵያ: ስኬቶች እና የወደፊት አቅጣጫዎች" በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የዙም ቀጥታ ውይይት ላይ ተጋብዘዋል። በዚህ ውይይት ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ የሳይኮሎጂ ባለሙያዎችም የኢሜል አድራሻችሁን እስከ አርብ ሰኔ 5 ድረስ በመላክ በውይይቱ ላይ መሳተፍ ትችላላችሁ።
ቀን: ቅዳሜ ሰኔ 6/2012 ዓ.ም.
ሰዓት: ከቀኑ 08:00 - 10:00

+251-946-158-501

Dear Psychologist's,

MoH is inviting you to a scheduled Zoom meeting on "The role of Psychologists in COVID-19 Pandemic in Ethiopia: success and future directions" by collaborating with Ethiopian Psychologist's Association. If you want to join the meeting send your E-mail address until June 12.
Date: Jun 13, 2020
Time: 02:00 PM Africa/Addis_Ababa

+251-946-158-501


@Psychoet
2024/09/30 09:38:32
Back to Top
HTML Embed Code: