Telegram Web Link
Audio
ግጥም ለምትወዱ በሙሉ
በጣም የምወደውና የማከብረውን የወንድዬ አሊ ግጥም ጋበዝኳችሁ፡፡

ግጥም
ርዕስ:- ብዕር አታስለቅስ
ከውበት እና ሕይወት የግጥም መድብል
ገጣሚ:- ወንድዬ አሊ
አንባቢ:- ተስፋዬ ማሞ

#14MB
@PSYCHOET
ታላቁ የቻይና ፈላስፋና መምህር ኮንፊሽየስ በተራራ ላይ ተቀምጦ ድንኳን ዘርግቶ እያስተማረ በነበረበት አንድ ቀን ደቀ-መዝሙሩ ትዙሉን ውሃ እንዲያመጣለት አዘዘው ። ትዙሉም ውሃ ሊያመጣ ወደ ወንዝ ሲወርድ ነብር ያጋጥመውና ነብሩን ጭራውን ይዞ ይገድለዋል ። በሰራው ጀብድም ኩራት ስለተሰማው የነብሩን ጅራት ቆርጦ ኪሱ ከቶ አምጣ የተባለውን ውሃ ቀድቶ ወደ ኮንፊሽየስ ድንኳን ይመለሳል ። ኮንፊሽየስንም እንዲ ሲል ይጠይቀዋል ፦
ትዙሉ አንድ ታላቅ ሰው ነብርን እንዴት አድርጎ ይገድለዋል አለው?

ኮንፊሽየስም፦ አንድ ታላቅ ሰው ነብር የሚገድለው ጭንቅላቱን ይዞ ነው አለው ።

ትዙሉ፦ተራ ሰውስ?

ኮንፊሽየስ፦አንድ ተራ ሰው ነብር የሚገድለው ጆሮውን ይዞ ነው ።

ትዙሉ፦የማይረባ ከንቱ ሰውስ?

ኮንፊሽየስ፦የማይረባ ከንቱ ሰው ነብር የሚገድለው ጭራውን ይዞ ነው ።

ትዙሉ የኮንፊሽየስን ምላሽ በሰማ ጊዜ ከድንኳኑ ርቆ በመሄድ የነብሩን ጭራ ከኪሱ በማውጣት ወረወረው ፤ በንዴት ውስጥም ሆኖ መምህሬ ከወንዝ አጠገብ ነብር እንዳለ እያወቀ የላከኝ በነብር ተበልቼ እንድሞትና እንድገደል ስለሚፈልግ ነው አለና ኮንፊሽየስን ለመግደል በኪሱ ድንጋይ ይዞ ሄደ ።
ኮንፊሽየስ ጋር በደረሰም ጊዜ በድጋሚም እንዲ ሲል ጠየቀ፦
አንድ ታላቅ ሰው ሰው ሊገድል የሚችለው እንዴት ነው አለ ትዙሉ ?

ኮንፊሽየስም፦ታላቅ ሰው ሰው ሊገድል የሚችለው የሚፅፍበትን ብዕር ተጠቅሞ ነው አለ ።
ትዙሉም፦ተራ ሰውስ ሰው ሊገድል የሚችለው እንዴት ነው?
ኮንፊሽየስም፦ተራ ሰው ሰው ሊገድል የሚችለው ምላሱን ተጠቅሞ ነው አለው ።

ትዙሉ ፦የማይረባ ከንቱ ሰውስ እንዴት ነው ሰው ሊገድል የሚችለው አለ?

ኮንፊሽየስም ፦ የማይረባ ሰው ከሆነ ሰው ሊገድል የሚችለው ድንጋይን በመጠቀም ነው አለ ።
ትዙሉ የኮንፊሽየስን መልስ በሰማ ጊዜ አሁንም እንደ ቀድሞው ከድንኳኑ ርቆ በመሄድ መምህሩን ሊገድልበት የነበረውን ድንጋይ ወረወረው ። ትዙሉም ከዚያ ግዜ ጀምሮ የኮንፊሽየስን የእውነት ታላቅ ሰው መሆን አምኖ ተቀበለ ፤ መምህሩን የሚያከብር ተማሪም ሆነ ።
አንድ ታላቅ ሰው በነብር የተመሰለውን የሱን ሀሳብ ተቃራኒ የሆነ ጠላት በጭንቅላቱ ይዞ ወይም በሀሳቡ በልጦት ያሸንፈዋል ። ተራ ሰው ግን በነብር የተመሰለውን የሱን ተቃራኒ የሆነ ጠላት በጆሮ ይዞ በጣፋጭ ቃላት ደልሎ ያሸንፈዋል ። በማይረባ ከንቱ ሰው ደግሞ በነብር የተመሰለውን የሱ ተቃራኒ የሆነ ጠላት በጭራው በመያዝ ከጀርባው ሆኖ በሀሜትና ስሙን በማጥፋት ያሸንፈዋል ።
©ታዛ መፅሔት

፨ በሀሳብ ለማሸነፍ እንሞክር

ይህንን ካነቡ አይቀር
👉ለሌሎች ይህን #Share ይርጉ፡፡
✴️
እኔ ሀላፊነቴን ተወጥቻለሁ!
🙌🙌🙌
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
🎡@🎡መልካም ቀን
#Join #Join #Join
🔸🔹 ↘️💯💯💯↙️🔸🔹
🚗 www.tg-me.com/Psychoet 👍
🚕 www.tg-me.com/Psychoet 👍
የአእምሮ ጤንነትን የሚጠብቁና የሚያሳድጉ 5 ተግባራት
(በናሁሰናይ ፀዳሉ)

የአእምሮ ጤንነት ለሰው ልጅ ወሳኝ የሆነ የሕይወት ማገር ነው፡፡ ሰው እንደ ሰው ፣ ህዝብ እንደህዝብ ፣ ሀገርም እንደሀገር እንዲቀጥልና እንዲያድግ ዋናውን ሚና የሚጫወተው የአዕምሮ ጤንነት ነው ፡፡ በተለይም አሁን ባለንበት የኮሮና ወረርሽኝ ጊዜ ደግሞ ይህ የአእምሮ ጤንነት በመንግስትም ሆነ በዘርፉ ባለሙያዎች ከፍተኛ ትኩረት ተሰቶበት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው። በዚህ ጊዜም ከወረርሽኙ የተነሳ በአለማችን ሆነ በአገራችን ብዙ ሰዎች ለአዕምሮ (ሥነልቦናዊ) ቀውስ እየተጋለጡ ይገኛሉ በዚህም ብዙዎች ቀናቸውን በድብርት ፣ በፍርሀት ፣ ተስፊ በመቁረጥ ፣ ስለ ነገ አሉታዊ ነገሮችን በማሰብ ያሳልፉሉ ብሎም ብዙ ሰዎች ራሳቸውን አጥፍተዋል ፣ ከስራተቸው ለቀዋል ፣ ማህበራዊ ህይወታቸውን አቁመዋል ... ብዙ ብዙ ፡፡ ይህ ሁሉ ወረርሽኙ ያስከተለው የሥነልቦና ቀውስ ነው፡፡

ይህ ወረርሽኝ ከሚያመጣው የሥነልቦና ቀውሶች ለመውጣት ወይንም የአእምሮ ጤንነታችንን ጠብቀን ለመቆየት የሚያስችሉን 5 ተግባራትን እንመለከታለን፡፡

1. አካላዊ ጤንነትንና ንቃትን ማዳበር

አካላዊ ጤንነትና ንቃት ማለት ሁለንተናችን የተመጣጠነ እድገት ሲኖረውና ሰውነታችንን ከተለያዩ በሽታዎች ሲጠበቅ ማለት ነው፡፡ አካላዊ ጤንነት ሁልጊዜ ከአዕምሮ ጤንነት ጋር ይያያዛል ፡፡ በዚህ ንቃት ውስጥ የሚዳብር በራስ መተማመን ፣ ማቀድና መፈፀም እንዲሁም ችግሮችን በስልት መፍታት በሰውነታችን ውስጥ የኬሚካሎች ለውጥ እንዲኖር ያደርጋል ይህም ለኬሚካል ለውጥ በባህሪያችንና በስሜታችን ላይ አወንታዊ ለውጥን ያመጣል፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች

ባለንበት ቦታ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የተለያዩ የሚያስደስቱንን ስራዎች በቤታችን ሁነን መስራት ፣ ጥሩ መጸሐፍትን ማንበብ ፊልሞችን መመልከት ፣በትንሹ እቅድ ማቀድና መተግበርን መለማመድ፡፡

2. አዳዲስ ክህሎቶችን መማር

ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዳዲስ ክህሎቶችን መማር ለአዕምሮ ጤንነትና እድገት ወሳኝ እንደሆነ ነው ፡፡ አዳዲስ ክህሎቶችን መማር በራስ መተማመናችንን ያሳድጋል ፣ የሕይወትን አላማ የቀለጠ እንድንረዳ ያግዛል በተጨማሪም ከሌሎች ሰዎች ጋር የትውውቅና የስራ እድል ይፈጥራል፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች
አዳዲስ ክህሎቶችን ለመማር ዩኒቨርስቲ / ኮሌጅ መግባት ፣ ብዙ ገንዘብ ማፍሰስ አይጠይቅም ባሉበት ሆኖ በቅርብ በሚቀኙ ቁሳቁሶች በመጠቀም መማር ይቻላል ፡፡

በዚህ ጊዜ እቤቱ ያለ ሰው የተለያዩ ምግብ አሰራሮችን በየቀኑ መማር ፣ ዩቲዩብ ላይ የተለያዩ ቲቶሪያሎች በማውረድ በነፃ ክህሎቶችን መግኘት ፤ በነፃ ትምህርት የሚሰጡ Online ትምህርቶችን መከታተል በተጨማሪም አዳዲስ ልማዶችን መሞከር ለምሳሌ መጻፍ ፣ መሳል ፣ጥልፍ መስራት አዳዲስ የእስፖርት አይነቶችን መለማመድና እቤት ውስጥ የተበላሸ ነገሮችን መጠገንና ማስተካከል ይቻላል፡፡

በመስሪያ ቤት ያለ ሰው አዳዲስ ሀላፊነቶች
ስራችን ላይ ጨምሮ ቢወጣ ( እዚህ ላይ ግን አብዛኞቻችን ስለምንሰንፍ አሁን ያለኝን ሃላፊነት ራሱ በስነስርአቱ አልተወጣንም ብለን እናስባለን ) ግን አዲስ ሀላፊነት መቀበል የበለጣ የሚከብድ ነገር አይደለም እንዲያውም ቋሚ ሃላፊነቱን የበለጠ እንድንወጣ ይረዳናል፡፡

3. ለሌሎች ማካፈል

ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ደስተኛ ነው ፡፡ ሁሉም ሰው ወይ ለሀይማኖቱ አልያም ለሕሊናው ሲል መለገስ / ማካፈል ይወዳል ፡፡ ይህም የሆነው ሰዎች ከሰጠን / ለሌሎች ካካፈልን በኀላ በውስጣቸን የሚፈጠረው የኬሚካል ለውጥ ምክንያት በጣም ደስተኛ ስለምንሆን ነው ፡፡ መስጠት አወንታዊ አመለካከትን ይፈጥርልናል ፣ ከፈጣሪ ጥሩ መልስ እንድንጠብቅ ያደርጋል ፣ ለራሳችን ያለንን አመለካከት ያሳድግልናል አላማችንን የበለጠ ለመፈፀም ያተጋናል ፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች

*ሰዎች ላደረጉልን ነገሮች ምስጋናን መለገስ
*በቅርብ ያሉ ሰዎችን ስለውሎአቸው መጠየቅ
*ጊዜያችንን ለሚፈልጉ ሰዎች መገኘት
*ካለን ገንዘብ ፣ ችሎታ ለሌሎች ለተቸገሩ ወገኖች መስጠት
*በመጨረሻም ዋናው መስጠት የምንችለው በጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ላይ መሰማራት


4. ከሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት አጥብቆ መያዝ

ጥሩ ወዳጅነት / ዝምድና አይምሮን ከሚያድሱ ነገሮች ቀዳሚው ነው ፡፡ ከሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠር ለራሳችን ያለንን አመለካከት ከማሳደጉ በተጨማሪ አስደሳች ጊዜያቶችን እንድናሳልፍ ዕድል ይሰጠናል ፡፡ ከሰዎችም የድጋ ስሜት እንድንቀበልና እንድንሰጥ ይረዳናል ፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች

*ከቤተሰቦቻችን ጋር ጊዜ ሰተን የጫዎታ ፣ የመወያያ የመመገቢያ ጊዜ ማሳለፍ ፡፡
*ድጋፍ የሚፈልጉ ጓረቤት ዘመዶችን ጊዜ ሰተን መጠየቅ ፣ ሰዎችን በሆስፒታልና በእስር ቤት መጎብኘት፡፡
*ካገኘናቸው ጊዜያት ያስቆጠሩ ወዳጆቻችንን ጋር መደወል።
*በዝንባሌያችን መሰረት በአካባቢያችንም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የተለያዩ ሕብረቶች ውስጥ መሳተፍ፡፡

5. ከነገና ከትናንት ይልቅ በአሁን ባለው ነገር ላይ ትኩረት መስጠት

ከምንም በላይ አሁን ላሉበት ነገር ትኩረት መስጠት የአዕምሮ ጤንነታችን እንዲጠበቅ ያደርጋል ፡፡ ብዙ ሰው አሁን ባገኘው ነገር እንደመደሰትና ፈጣሪን እንደማመስገን ትናንት ስለደረሰበት በደል እያሰበ ያዝናል ፣ ትናንት ስለሰራው ስህተት እየተፀፀተ ይኖራል ። ከዚህም ሲቀጥል ስላልኖረበት ነገ መኖሩን ሳያውቅ ከልክ በላይ "ምን እሆን ?"ብሎ እየተጨነቀ ዛሬውን ያበላሻል ፡፡

ሁልጊዜ አሁን ላይ ትኩረት መስጠት ሕይወትን የበለጠ እንድንረዳና እንድንወድ ያረገናል፡፡

#ማድረግ ያለብን ነገሮች

ትናንት በሕይወታችን የሆኑ መጥፎ ነገሮች መርሳት ባንችልም እነዛ ነገሮች ግን ዛሬ ላይ መተው ሕይወታችንን እንዲረብሹ አለመፍቀድ፡፡

በዚህ ርዕስ (5ኛው ላይ) መጸሐፌ ውስጥ ወሳኝ የሆነ ስለጊዜና አስተሳሰብ ያለንን አመለካከት የሚቀይር አጭር ሀሳብ አካትቻለሁ ፡፡ ሲወጣ ታገኙታላችሁ ፡፡

ምንጭ : Mental wellbeing & my personal reflection
መልካም ቀን ይሁንላችሁ!

ጽሑፉ ለናንተ ከጠቀማችሁ ሎችም እንዲጠቀሙበት #Share በማድረግ አካፍሉ! ማካፈል ከዚህ ይጀምራል፡፡
www.tg-me.com/psychoet
ሰላም ቤተሰቦቼ !

ዛሬ በሥነልቡና ጤንነት ላይ የሚሰራ አንድ ተቋም ላስተዋውቃችሁ ፡፡ አሃ የስነ-ልቦና አገልግሎት ማዕከል ይባላል ፡፡ የብዙ አመት ልምድ ባላቸው የሳይኮሎጂ ሙያተኞች የተከፈተ ሲሆን በአካል ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ በቴሌግራምና የፌስቡክ ገፆቻቸውን ጥሩ ትምህርት እየሰጡ ይገኛሉ ፡፡

ስለዚህም ፔጃቸውን Like በማድረግ እግጅ በጣም ጥሩ የሥነልቦናዊ ምክሮችና ትምህርቶች እንድታገኙ እመክራለሁ ፡፡

📌TELEGRAM
www.tg-me.com/Ahapsychology
www.tg-me.com/Ahapsychology
www.tg-me.com/Ahapsychology

📌FACEBOOK
https://www.facebook.com/Ahapsychology/
https://www.facebook.com/Ahapsychology/
https://www.facebook.com/Ahapsychology/

በአካል ለሚደረግ ማንኛውም የሥነልቦና ምክር ከፈለጋችሁ ደውላችሁ ቀጠሮ ማስያዝና መረጃ መጠየቅ ትችላላችሁ ፡፡
አሃ የስነ-ልቦና አገልግሎት
22 አንበሳ ኢንሹራንስ ህንጻ 5ኛ ፎቅ
ስልክ፡ 0940200454፣ 0116622437
ኢሜይል [email protected]
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «ውድ ሳይኮሎጂስቶች የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሳይኮሎጂ ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመተባበር "የሳይኮሎጂስቶች ሚና በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በኢትዮጵያ: ስኬቶች እና የወደፊት አቅጣጫዎች" በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የዙም ቀጥታ ውይይት ላይ ተጋብዘዋል። በዚህ ውይይት ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ የሳይኮሎጂ ባለሙያዎችም የኢሜል አድራሻችሁን እስከ አርብ ሰኔ 5 ድረስ በመላክ በውይይቱ ላይ መሳተፍ ትችላላችሁ።…»
ሳይኮቢዝ #1

ሰላም ሰላም የፔጃችን ቤተሰቦች !
በእለተ አርብ ከዚህ በኀላ ለወጣቶች የስራ ፈጠራ የሚያግዙ ሀሳቦችን የማቀርብ ይሆናል ፡፡ በዚህ አምድ ስር በየሳምንቱ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እንዴት ብለው እራሳቸውንና አስተሳሰባቸውን ለቢዝነስ ያዘጋጃሉ የሚሉ ጥቆማዎች ይቀርባሉ ፡፡ ከመላው አለም ያሉ የወጣት የስራ ፈጣሪዎች መነሻ ታሪክ ፣ የቢዝነስ ሳይኮሎጂያቸው ተተንትኖ ለወጣቶች በሚሆን መንገድ ይቀርባል ፡፡

"ሳይኮቢዝ " ማለት " ሳይኮሎጂ + ቢዝነስ" ማለት ሲሆን የተለያዩ የሳይኮሎጂ እውቀቶችን እንዴት በቢዝነስ ላይ በመጠቀም ውጤታማና ስኬታማ ሰዎች እንሆናለን የሚለውን የሚያስተምር ነው ፡፡ በመሆኑም በማኔጅመንት ትምህርት ያገኘሁት የቢዝነስ እውቀት ላይ የሳይኮሎጂን ትምህርት ጨምሪ ጠቃሚ ሀሳቦችን አነሳለሁ፡፡

ብዙ ወጣቶች በወጣትነታቸው የራሳቸው የሆነ ጥሪት ማለትም ቤት ፣ መኪና ፣ ጥሩና የተደላደለ ትዳር እንዲኖራቸው ይመኛሉ ፡፡ ምኞታቸውን ግን የሚያሳኩት ጥቂት ሲሆኑ እነሱም አልያም ከቤተሰብ ጥሪት ወርሰው ካልሆነም እጣ ፈንታ ገጥሟቸው ነው ፡፡ በምድር ላይ ከምንም ተነስተው ትልቅ ደረጃ የደረሱ ሰዎች እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው ፡፡ እስቲ በዙሪያችሁ ያሉትን ተሳካላቸው የምትሏቸው 3 ጓደኞቻችሁን አስቡ ? ቆይ እንዴት ሊሳካላቸው ቻለ?

እኔ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ?
እናንተስ ለምን አሁን ያላችሁበት ቦታ ላይ ልትኖሩ ቻላችሁ ? ለምን ያሰባችሁትን መኪና ለመግዛት ከበዳችሁ ? ለምን ቤት ተከራይቶ መውጣት አቃታችሁ ? ለምን ገንዘባችሁን ወር እስከ ወር ቆጥባችሁ መጠቀም አቃታችሁ ?

በእነዚህ ርዕሶች ላይ በየሳምንቱ አርብ ጥሩ ትምህርት እጀምራለሁ ፡፡ ከቢዝነስ አንፃር ማወቅ የምትፈልጉት ወይም በዚህ ጉዳይ ብትፅፍበትና ገለፃ ብታደርግበት የምትሉትን #comment / Inbox ላይ ልትፅፉልኝ ትችላላችሁ ፡፡

ይህን የሳይኮቢዝ ትምህርት ለሌሎች እንዲደርስ #ሼር በማድረግ እንድታደርሱ እጠይቃለሁ በተጨመሪም ትምህርቱን ማግኘት አለባቸው የምትሉትን ጓደኞቻችሁን ወደፔጁ ጋብዙ ፡፡ ሶሻል ሚዲያችንን ከፊዝና ከስድድብ አውጥተን ለመሻሻል ፣ ሕይወታችንን ለመቀየር እንጠቀም፡፡

በዚህ ርዕስ ላይ የሚነሱት በሙሉ የያንዳንዳችንን የቢዝነስ ሳይኮሎጂ የሚቀይሩና ወደ ተገቢው የአስተሳሰብ ስርአት የሚወስዱ ናቸው ፡፡
📌አንድ ቀን ተስፋ አለኝ አርብ ጠዋት ይህን ጽሑፍ አንብቦ የመስሪያ ቤቱን ሰዎች ለመጨረሻ ቀን ተሰናብቶ ሰኞ የራሱን ስራ የሚጀምር ሰው እንደማገኝ፡፡
📌አንድ ቀን ተስፋ አለኝ ይህን ጽሑፍ አንብቦ ካለበት የልምድ ምቹ ቀጠና ወጥቶ የብዙዎችን ሕይወት የሚቀይር የፈጠራ ስራ የሚሰራ ሰው እንደማገኝ ፡፡
📌አንድ ቀን ተስፋ አለኝ ይህን ጽሑፍ አንብቦ በስራው ታታሪና ትጉ ሁኖ በአለቆቹ የሚመሰገንና የሚሸለም ጎበዝ ሰራተኛ እንደማገኝ ፡፡


ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
🎡@🎡መልካም ቀን
#Join #Join #Join
🔸🔹 ↘️💯💯💯↙️🔸🔹
🚗 www.tg-me.com/Psychoet 👍
🚕 www.tg-me.com/Psychoet 👍
በሰው አእምሮ ውስጥ ከሚገኙ አሉታዊ አመለካከቶች አንዱ የበታችነት ስሜት ነው፡፡
ብዙ ሰው ያሰበበት ቦታ እንዳይደርስ ፣ ያቀደውን እንዳያሳካ ፣ ባለው ነገር እንዳይመካ የሚያረገው ይህ አሉታዊ ስሜት ነው፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የተዘጋጀውን ቪዲዬ "ከበታችነት ስሜት የመውጫ መንገዶች" በዩቲዩብ አድራሻችን ልታገኙ ትችላላችሁ አንድን የማንፈልገው የግል ባህሪ/አመለካከት ከመቀነሳችን በፊት ያ ባህሪ እንዳለብን ማረጋገጥ አለብን ፡፡

ይህ ቪዲዮ ስለ የበታችነት ስሜት ምልክቶች መንስኤዋችና መፍትሔዎች ማብራሪያ ይዞ መቷል https://youtu.be/WGJYup10X2k
https://youtu.be/4ZoDlu58wMI
https://youtu.be/YXM8P4wQ2A4
25 ሕይወት ቀያሪ አባባሎች

1. አንተ ጠንክረህ በዝምታ ስትሰራ ፣ ስኬትህ ጮኾ ይናገራል፡፡
-ፍራንክ ኦሽን

2. በሕይወትህ ከዚህ በፊት ያልነበረህ አዲስ ነገር ለማግኘት ከፈለክ፣ አዲስ ሰርተኸው የማታውቀው ስራ ለመስራት መፍቀድ ይኖርብሀል ፡፡
-ቶማስ ጄፈርሰን

3. ትክክለኛ ሕይወት የሚጀምረው የምቾት ቀጠና ሲያልቅ ነው ፡፡
-ዶናልድ

4. አንተን ሁለት ነገሮች ይገልፁሀል ፡፡ የመጀመሪያው ምንም የሌለህ ጊዜ የምታሳየው ትዕግስት ሲሆን ሁለተኛው ሁሉም ሲሟላልህ የምታሳየው ጠባይ ነው ፡፡
-ኢማም አሊ

5. በምድር ላይ ትልቁ አስደሳች ነገር ሰዎች አትችልም ያሉህን ሰርተህ ማሳየትህ ነው ፡፡
-ዋልተር ባግሆት

6. ወንዝ ድንጋይ ቦርቡሮ የሚገባው ሀይለኛ ስለሆነ ሳይሆን ያለማቋረጥ ስለሚፈስ ነው ፡፡
-ጂም ዋትኪንስ

7. ህልምህን ለመፈፀም ብዙ ጊዜ በመውሰዱ ተስፋ አትቁረጥ ምክንያቱም ጊዜ ስለሚበር አርቀህ ያየኸው ህልም በፍጥነት መፈፀሙ አይቀርም ፡፡
-አርል ኒተንጋል

8. ሰዎች በምታቅደው እቅድ ካልሳቁ ወይም ካልተገረሙ እቅድህ ትንሽ ነው ማለት ነው ፡፡
-አዚም ፕሪሚጂ

9. ለመጀመር ትልቅ መሆን አይጠበቅብህም ነገር ግን ትልቅ ለመሆን መጀመር አለብህ ፡፡
-ዚግ ዚግላር

10. ደስተኛ የሆነ ሕይወት ለመኖር ከፈለክ ከሁኔታና ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከአላማና እቅድህ ጋር ተጣበቅ ፡፡
-አልበርት አንስታይን

11. አንተ የምርጫህ ውጤት እንጂ በአንተ ላይ የሚደርሱት ነገሮች ውጤት አይደለህም ፡፡
-ካርል ጉስታቭ

12. ባለትላልቅ አእምሮ ሰዎች በሃሳብ ላይ ይወያያሉ ፣ መካከለኞች በ ድርጊት / ሁኔታዎች ላይ ይወያያሉ ባለትናንሾች ቁጭ ብለው ሰው ያማሉ ፡፡
-ሪያኖር ሮዝቪልት

13. እስካልቆምክ ድረስ በምንም ዝግታ ብትጓዝ መድረስህ አይቀርም ፡፡
-ኮንፊሺየስ

14. ችሎታ ያለው ሰው ምንም ስራ እስካልሰራ ድረስ ችሎታ በሌለው ጠንካራ ሰራተኛ ይበለጣል ፡፡
-ቲም ኖትኪ

15. ከውድቀት ይልቅ ጥርጣሬ የነገ ህልምን ይገላል ፡፡
-ሱዚ ካስም

16. እውቀት ብቻ አይበቃም ተግባራዊ ካልተደረገ በስተቀር ፣ ፍቃደኛነት ብቻ አይበቃም ካልተሰራ በስተቀር ፡፡
-ብሩስ ሊ

17. የዛሬ አመት በዚህ ሰአት ምናለ ምናለ ከአመት በፊት በጀመርኩ የምትላቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፡፡
-ካረን ላንብ

18. ጀማሪዎቹ ለመስራት ከሞከሩት ጊዜ በላይ አለቃቸው ብዙ ጊዜ ወድቋል ፡፡
-ስቴፈን ማክክሬን

19.ብዙ ጊዜ ላለመስራት የምትተዋቸው ስራዎች በውስጣቸው ብዙ እድልን የያዙ ናቸው ፡፡
-ሮቢን ሻርማ

20. አለም የምትቀየረው በአንተ አስተያየት ሳይሆን በአንተ ተግባራዊ ስራ ነው ፡፡
-ፖል ኮኢልሆ

21. መተንፈስ እንደምትፈልግ ያህል ለስኬታማ ሕይወት ጥልቅ ፍላጎት ካለህ ይሳካልሀል ፡፡
-ኤሪክ ቶማስ

22. ፊትህን ወደ ፀሀይ ስታዞር ጥላህ ከኀላህ ይወድቃል ፡፡
-የማዎሪ አባባል

23. 99% የሚሆኑ ሰዎች ሀሳብህን ከተጠራጠሩህ ፣ እጅጉን ስተሀል አልያም ታሪክ ልትሰራ ነው ፡፡
-ስኮት ቤልስካይ

24. ፈፅሞ አትድከም ምክንያቱም አሁን እጅግ ከባድ የሆነብህ ስራ ከጥቂት ጊዜያት በኀላ ለሌላ ስራ መሟሟቂያ ይሆናል ፡፡
-ያልታወቀ ሰው

25. ሕይወት ልክ እንደ ካሜራ ነች ፡፡ የምትፈልገውና ጠቃሚ ነገር ላይ ስታተኩር ሌሎቹ የማያስፈልጉት እየደበዘዙ ይሄዳሉ ፡፡


@Psychoet
ለሌሎች ወዳጆቻችንም ሼር እናርጋቸው
@Psychoet
ከመሞታችሁ በፊት ማድረግ ያለባችሁ 10 ነገሮች

1. *ትናንትናንም ሆነ ነገን እያሰባችሁ አትጨነቁ ፡፡ ትናንት አልፏል ነገ አልመጣም ፡፡ ስለዚህ ዛሬን በደስታ ኑሩ


2. *የበደሏችሁን ሰዎች ይቅርታ አድርጉላቸው ፡፡
ይህን የምታረጉት እነሱ ጥሩ ስለሰሩ አልያም አውቀው ሆነ ሳያውቁ ስላጠፉ ሳይሆን ለራሳችሁ የአስተሳሰብ ጤንነት ስትሉ ነው ፡፡

3. *መስራት አለብኝ የምትሉትን ስራ ጊዜው ቢያልፍም ሳትሰሩ አትለፉ

4. *በተቻላችሁ መጠን ሰጪ እንጂ ተቀባይ አትሁኑ

5. *ከማይመቻችሁ ከናንተ ሀሳብ ጋር ከማይሄድ ሰው ጋር ጓደኛነት አትፍጠሩ ፡፡

6. *ማንንም ለመሆን ሳይሆን ራሳችሁን ለመሆን ጣሩ ፣ ያልሆናችሁትን በውሸት አታስመስሉ

7.*ትልቁ እውቀት ዲግሪ መደርደር ሳይሆን ራስን ማወቅ ነውና ሁልጊዜ እራሳችሁን ለማወቅ ጣሩ

8. *በየቀኑ ቢያንስ አንድ መልካም ነገር አድርጉ

9 *በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይሆን ሰውን ለመውደድ ጣሩ

10. የምትወዱትን / ማረግ የሚያስደስታችሁን #5 ነገሮች ፃፋና በሳምንት ውስጥ ቢያንስ አንዱን አድርጉ


በናሁሰናይ ፀዳሉ
www.tg-me.com/psychoet
fb.com/psychologyet
youtube.com/thenahusenai
#ክፍል_22
#አራቱ የሰው ባህሪ አይነቶች
www.tg-me.com/psychoet
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

እንደምን ሰነበታችሁ የፔጃችን ቤተሰቦች !
ተቋርጦ የነበረው ሳምንታዊ የሳይኮሎጂ ትምህርታችን ዛሬ ጀምሯል፡፡

በዛሬው ርዕስ ለሰው ልጆች ተግባቦትና የቀን ተቀን መስተጋብር ወሳኝ ስለሆነው አመል ( Temperament) እንመለከታለን፡፡ እንደሚታወቀው ማንኛውም ባህሪ መነሻ ምክኒያት አለው ፡፡ ምክንያቶቹ ደግሞ #ተፈጥሮአዊ ወይም #አካባቢያዊ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡

1. ተፈጥሮአዊ ተፅዕኖ :- ተፈጥሮአዊ ተፅዕኖ ስንል በዘር ከወላጆቻችን የምንወርሰው ሲሆን

ለምሳሌ ፦ አንድ ልጅ እናቱ ወይም አባቱ ያላቸውን ባህሪ ሲወርስ

2. አካባቢያዊ :- ከቤተሰብ ጋር ባለ ግንኙነት ፣ በጓደኛ ተፅዕኖ ፣ በትምህርት ቤት ቆይታና በምንኖርበት ባህል የምንወርሳቸውን ባህሪያቶች ያጠቃልላል

ለምሳሌ ፦ አንድ ሰው በጣም ተሳዳቢ ቢሆን ( ያን ስድብ የወረሰው በአካባቢው ከሚኖሩ ሰዎች አልያም ከሰዎች በተለያዩ መንገድ ከተመለከታውና ከሰማው ሊሆን ይችላል )


የስነልቦና ተመራማሪዎች የሰውን ተፈጥሮአዊ አመል (Temperament ባህሪ) በአራት በመክፈል ያስቀምጡታል

1 .📌ሳንጊዊን (Sanguine)
ሳቂታና ተጫዎች ...
#ተግባቢና ምክኒያታዊ ናቸው

2.📌ኮለሪክ (Choleric)
ተነጫናጭ/ አዛኝና አኩሪፊ ...
#ተግባቢና ስሜታዊ ናቸው

3 .📌ሜላንኮሊክ (Melancholic)
አይናፋር ...
#ጭምቶችና ስሜታዊ ናቸው

4. 📌ፊላግማቲክ (Phlegmatic)
ግትር...
#ጭምተኛና ምክኒያታዊ ናቸው

እነዚህ አራት የሰው አመሎች የየራሳቸው መገቸጫ አላቸው

📌ሳንጊዊን
❇️አየር ⭕️ማሕበራዊ ሰዎች

ሳንጊዊን አመል ያላቸው ዋናው መገለጫቸው አብዝቶ ተጫዎችና ወሬኛነት ፣ ነገሮችን ለመስራት ፈጣንነት ፣ ማሕበራዊነት ይገኙበታል ፡፡ ሳንጊዊኖች በጣም ተግባቢና የሕብረት ነገር የሚወዱ ናቸው፡፡ ይህ አመል ያላቸው ሰዎች ሁልጊዜም ለራሳቸው ሳይሆኑና ምንም ሳይሰሩ ኑሮአቸውን የግል ሳይሆኖ የጋራ ያረጋሉ፡፡

📌ኮለሪክ
❇️ እሳት ⭕️አስተዳዳሪዎች
ኮለሪኮች በጣም ተግባቢ ሲሆኑ የሚገለፁበት ባህሪ በውሳኔ ሰጭነታቸው ፣ በግብ ተኮርነታቸው ፣ በምኞታቸው ፣ በኢጥገኛነታቸው ነው፡፡ በተጨማሪም ኮለሪኮች ቁጡዎች ቂም የሚይዙ ለስሜት ቅርቦች ናቸው፡፡

📌ሜላንኮሊክ
❇️መሬት ⭕️ሰዎችን ከሕይወታቸው አግላይ

ሜላንኮሊክ ሰዎች አስተዋያዮችና ዝርዝር ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጪዎች ደግሞም ጥልቅ አሳቢዎችና ጭምቶች ናቸው ፡፡ ከዛ በተጨማሪ ራሳቸውን ብዙ ሰዉ ካለበት ቦታ ማግለል / ማሸሽ የሚመርጡ ናቸው ፡፡ እነዚህ አይነት ሰዎች ሁሌም ፍፁም ለመሆን የሚሞክሩና የሚፈልጉ ናቸው፡፡ይህ ባህሪ ሰዎችን ራሳቸውን ችለው እንዲቆሙ የሚገፋፋ ፣ ቁጥብ እንዲሆኑ የሚያረግ ነው ፡፡

📌ፊላግማቲክ
❇️ውሀ ⭕️ሰዎችን ከወደሕይወታቸው አቅራቢ

ፊላግማቲክ ሰዎች ረጋ፣ ፈታ ያሉና ከሁሉ ጋር እንደውሀ የሚራመዱ ናቸው ፡፡ ለሌሎች በጣም የሚያዝኑ ግን የራሳቸውን ስሜት በማፈን የማይገልፁ ናቸው ፡፡ እነዚህ ሰዎች  የተለያዩ ሀሳቦችን እና ችግሮችን ወደአንድ በማምጣት ለመፍታት የሚሞክሩ ናቸው ፡፡


አንዳንድ ሰዎች ከነዚህ ባህሪያት ሁለቱን ወይንም ከዛ በላይ ሊያሳዩ ይችላሉ ፡፡ በቅርብም የተጠኑ ጥናቶች ከ4ቱ አመሎች ላይ አንድ ጨምረው 5 አድርሰውታል ፡፡ አምስተኛው ደግሞ የሁሉም ቅልቅል ያለበት ከሁሉም መሀል የሆነ ሲሆን (SUPINE )ብለው ጠርተውታል፡፡

የናንተ ባህሪ ከየትኛው ይመደባል ? በ #Comment አሳውቁኝ ?

በዩቲዩብ የምንለቃቸውን ትምህርቶች ለማግኘት ቻናላችንን Subscribe አድርጉ
youtube.com/thenahusenaipsychology
❖_____________________________❖
ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !

የሳምንት ሰው ይበለን!
❖__________________________________❖

ስለ ሳይኮሎጂ የበለጠ ለማወቅ ፔጁን ይከታተሉ ለወዳጆችዎ ያጋሩ

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «#ክፍል_22 #አራቱ የሰው ባህሪ አይነቶች www.tg-me.com/psychoet (በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ) እንደምን ሰነበታችሁ የፔጃችን ቤተሰቦች ! ተቋርጦ የነበረው ሳምንታዊ የሳይኮሎጂ ትምህርታችን ዛሬ ጀምሯል፡፡ በዛሬው ርዕስ ለሰው ልጆች ተግባቦትና የቀን ተቀን መስተጋብር ወሳኝ ስለሆነው አመል ( Temperament) እንመለከታለን፡፡ እንደሚታወቀው ማንኛውም ባህሪ መነሻ ምክኒያት አለው ፡፡ ምክንያቶቹ ደግሞ…»
በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት መደረግ ያለባችው 10 ነገሮች

1. ስለወረርሽኙ የምናነበውንና የምንሰማውን የዜና መጠን መወሰን ፣ ያገኙትን ሁሉ አለማንበብ / አለመስማት

2. የሚሰማን የፍርሃት ስሜት ተፈጥሮአዊ እንደሆነ መረዳትና ፣ አብዝቶ አለመጨነቅ / አለመሸበር

3. ሁልጊዜ ስለወረርሽኙ አሉታዊ ነገር የሚያወሩ ሰዎችን ከአጠገባችን ማራቅ ወይም ከእነሱ መራቅ ፦

አንዳንድ ሰዎች ዛሬ ይሄን ያህል ጨመረ ፣ ይሄን ያህል ሞተ ነገ ምን ሊውጠን ነው እያሉ በማሸበር ከኮሮና በላይ በፍርሀትና በጭንቀት ሊገሉን ይችላሉ ፡፡

4. ትክክለኛ መረጃ ከማን ማግኘት እንዳለብን መምረጥ

5. እጅግ አብዝተን ማህበራዊ ሚዲያ አለመጠቀም ፣ መድሀኒት / ክትባት ተገኘ የሚሉ ያልተረጋገጡ መረጃዎችን አለማጋራት

6.ትኩረትን መላምት ላይ ሳይሆን የተረጋገጡ መረጃዎች ላይ ማድረግ

7. ይህ የኮሮና ወቅት ይዞ የመጣው አሉታዊ ነገር ቢኖርም አወንታዊ ነገሩ ላይ ማተኮር

ለምሳሌ ( ከቤተሰቦቻችን ጋር ጥሩ ጊዜ እንድናሳልፍ ዕድል ሰቶናል ፣ ቁጭ ብለን እንድናስብ አስችሎናል ፣ ሕይወት አጭር እንደሆነች ጥቁምታ ሰቶናል በዚህም ስለ አላማ እንድናስብ እረድቶናል .... )

8. በዙሪያችን ያሉ የተቸገሩ ሰዎችን በቻሉት መጠን መርዳት፡፡ ይህ ወረርሺኝ እንዲጠፋ ቀን ከለሊት ወደ ፈጣሪ መፀለይና ወረርሽኙን ላለማስተላለፍም ሆን ከሌሎች እንዳይተላለፍ መጠንቀቅ

9. በየቀኑ አሉታዊ ነገሮችን ሳይሆን እንደዚህ አይነት አበረታች መልዕክቶችን #Share ያደርጋሉ 😉 ጥሩ መልዕክት ለወዳጆቻቸው ያስተላልፉሉ ፡፡

10. ....10 ኛውን ለእናንተ ክፍት አድርጌያለሁ ፡፡ መደረግ አለባቸው የምትሉትን የቀሩ ነገሮች ኮመንት ላይ ጻፉልኝ ፡፡ ሰው እኔ ከፃፍኩት በላይ የናንተን ኮመንት አይቶ ሊማር ይችላል ፡፡

መልካም ቀን !
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

ቴሌግራም www.tg-me.com/psychoet
ዩቲዪብ youtube.com/thenahusenai
#ጭንቀትን_መቀነሻ_ቴክኒኮች

ይህም በሥልጠናና በባለሙያ የካውንሰሊንግ አገልግሎት ሊገኝ ይችላል፡፡ ሁለት ቴክኒኮችን ብቻ እንመልከት (በርካታ ቴክኒኮች እንዳሉ መገንዘብ ያስፈልጋል)፡-

1⃣ #ABCDE_ቴክኒክ :

ይህ ቴክኒክ አልበርት ኤሊስ (Albert Ellis) በተባሉ የስነልቦና ባለሙያ የተገኘ ዘዴ ነው፡፡

አልበርት ኤሊስ ሰዎች ወደ ጭንቀት የሚገቡት አግባብ ያልሆነ አስተሳሰቦችና እምነቶች (Irrational beliefs and thoughts) ሲጠናወቷቸው ነው ብለው ያምናል።

ለምሳሌ:-

👉ሰው ሁሉ ይጠላኛል፣
👉ሰው ሁሉ ይወደኛል፣
👉ከሰው ሁሉ ተቀባይነትን ማግኘት አለብኝ፤
👉በምሰራው ስራ ሁሉ መሳሳት የለብኝም...ወዘተ የሚሉ እምነቶችና አስተሳሰቦች ለጭንቀት እንደሚዳርጉ ያሰምሩበታል።

እኚህ ሰው እንደሚሉት፥

✔️አሉታዊ ነገሮችን አጋኖ ማየት (Awfulising)

✔️ጥቁርና ነጭ እሳቤ (Black and White thinking 👉ይህ እንግዲህ አንድን ነገር ጥሩ ወይም መጥፎ ብሎ መመደብና በውስጡ ሊኖር የሚችለውን የተወሰነውን ጥሩ ነገር አለማየት ነው።

✔️ጠቅላይ እሳቤ(Over generalizing) 👉ሁልጊዜ፣ ሁሉም ሰው፣ በፍፁም.....ወዘተ የሚሉ ቃላትንና ሃሳቦችን መጠቀም፤
(ሁሉም የሚል አባዜ አለባቸው)

✔️Personalizing የማይመለከተንን ነገር ከራሳችን ጋር አቆራኝቶ ማየት፤

✔️Filtering በሁኔታዎች ውስጥ አሉታዊን ነገር ብቻ መርጦ ማየት፤

✔️Mind reading ይህንን አስቦ ነው ብሎ ያለምንም ማስረጃ ድምዳሜ ላይ መድረስ፤

✔️Blaming 👉ሰዎችን መተቸትና መውቀስ

✔️Labeling 👉ለራስ ስያሜ መስጠት

ለምሳሌ: ደካማ ነኝ፤ዋጋ ቢስ ነኝ...ወዘተ ማለት አግባብ ላልሆኑ አስተሳሰቦች ምክኒያት ናቸው ይሉናል፡፡

ቴክኒኩን ተንትነን ለማየት እንሞክር

#Antecedent (Activating event, Stimulus)፡

ይህ ማለት ጭንቀትን የሚቀሰቅሰው ሁኔታ ወይም ነገር ነው (ተንኳሽ እንበለው)፡፡
" ይህ ተንኳሽ የኛን ምላሽ (Response) ይጠይቃል።

ለምሳሌ:- ከስንት አንድ ቀን ቀጠሮ ብናረፍድ ጭንቀት ሊፈጠርብን ይችላል፡፡ በዚህ ምሳሌ መሰረት ጭንቀትን የሚፈጥርብን ጉዳይ ማርፈዳችን ነው ማለት ነው፡፡

#Belief_our_cognition_about_the_situation ፡-

ይህ እንግዲህ ስለ ተንኳሹ ያለን ሃሳብና እምነት ነው፡፡

ለምሳሌ ማርፈዴ ያለኝን ተቀባይነት ያሳጣዋል፣ በምንም አይነት ምክኒያት ቢሆን ማርፈድ አሳማኝ አይደለም...ወዘተ የሚል እምነት ማለት ነው፡፡

#Consequences- the way that we feel and behave፡

ይህ ውጤት ነው - ጭንቀታችን፡፡ ይህ ምን ባህሪ ይፈጥራል? ቶሎ ለመድረስ አላግባብ ጣልቃ እየገባን መኪናችንን መንዳትን፣ በእጃችንም በአንደበታችንም የተንቀረፈፈ የመሰለንን ሾፌር መስደብ፣ መቆጣት፤ ከአስፋልት ወጥቶ በእግረኛ መንገድ መንዳት... ወዘተ ማለት ነው፡፡

እዚህ ላይ አልበረት ኤሊስ ይሞግታሉ “ያስጨነቀን ማርፈዳችን ነው ወይስ ስለ ማርፈድ ያለን አስተሳሰብና እምነት ነው?”

አሳቸው እንደሚሉት፤ ውጤቱን የፈጠረው ማርፈዳችን (stimulus) ሳይሆን ስለ ማርፈድ ያለን አስተሳሰብና እምነት ነው ባይ ናቸው፡፡

#Dispute:- is the process of challenging the way we think about situations:

ይኸኛው አስተሳሰባችንን የምንሞግትበት ዘዴ ነው። እሳቸው አግባብነት የሌለውን አስተሳሰብና እምነት መሞገት ያስፈልጋል ይላሉ፡፡

ለምሳሌ ከላይ የጠቀስነውን ማርፈድ ብንወስድ እምነታችንን ስንሞግተው እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
“ብዙ ጊዜ በሰዓቱ የምገኝና ቀጠሮ አክባሪ የሆንኩ ሰው ነኝ፡፡ አንድ ዛሬን ባረፍድ ተቀባይነቴን አያሳጣም”፣ “ለማርፈዴ ምክኒያት የሆነኝ የትራፊክ መጨናነቅና ያልጠበቅሁት የመንገዶች መዘጋጋት ነው፡፡ ስለዚህ በቂ ምክኒያት ሊሆን ይችላል፡፡” እነዚህን ምክኒያቶች በማሰብ ነባሩን ሃሳብ መሞገት እንደሚገባ ይጠቁማሉ፤ አልበርት ኤሊስ፡፡

#Effect : ይሄ አዲሱ ውጤት ነው።
አስተሳሰባችንን ከሞገትነውና በአዲስ አስተሳሰብ ከተካነው በኋላ የሚፈጠር ባህሪ ነው፡፡ የላይኛውን ምሳሌ ብንከተል ተረጋግቶ መንዳት፤ ተራ መጠበቅ፤ በተፈቀደው አስፋልት መንዳት... ወዘተ ማለት ነው፡፡

👉ማስተዋል ያለብን ሃሳብ ስሜታችን እና ባህሪያችን ላይ ተፅእኖ ይፈጥራል፡፡ ማወቅና አስተሳሰብን መለወጥ ደሞ አስፈላጊ ነው፡፡

#share

©የፍቅር_ሳይኮሎጂ
Telegram : www.tg-me.com/psychoet
youtube : youtube.com/thenahusenai
መልካም ቀን!
2024/09/30 11:41:08
Back to Top
HTML Embed Code: