Telegram Web Link
እናንተ ከየትኛው ወገን ናችሁ?
ለምን?
Social Psychology በዚህ ላይና በያንዳንዱ ግብረ መልስ ላይ ትንታኔ አለው ፡፡ ወደፊት በዚህ ላይ የተጻፉ ትንታኔዎችን ይዤ እቀርባለሁ ፡፡ መልካም አዳር !
@psychoet
አንተን ሁለት ነገሮች ይገልፁሀል ፡፡ የመጀመሪያው ምንም የሌለህ ጊዜ የምታሳየው ትዕግስት ሲሆን ሁለተኛው ሁሉም ሲሟላልህ የምታሳየው ጠባይ ነው ፡፡
-ኢማም አሊ
በሰው አእምሮ ውስጥ ከሚገኙ አሉታዊ አመለካከቶች አንዱ የበታችነት ስሜት ነው፡፡
ብዙ ሰው ያሰበበት ቦታ እንዳይደርስ ፣ ያቀደውን እንዳያሳካ ፣ ባለው ነገር እንዳይመካ የሚያረገው ይህ አሉታዊ ስሜት ነው፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የተዘጋጀውን ቪዲዬ "ከበታችነት ስሜት የመውጫ መንገዶች" በዩቲዩብ አድራሻችን ልታገኙ ትችላላችሁ

https://youtu.be/YXM8P4wQ2A4
25 ሕይወት ቀያሪ አባባሎች

1. አንተ ጠንክረህ በዝምታ ስትሰራ ፣ ስኬትህ ጮኾ ይናገራል፡፡
-ፍራንክ ኦሽን

2. በሕይወትህ ከዚህ በፊት ያልነበረህ አዲስ ነገር ለማግኘት ከፈለክ፣ አዲስ ሰርተኸው የማታውቀው ስራ ለመስራት መፍቀድ ይኖርብሀል ፡፡
-ቶማስ ጄፈርሰን

3. ትክክለኛ ሕይወት የሚጀምረው የምቾት ቀጠና ሲያልቅ ነው ፡፡
-ዶናልድ

4. አንተን ሁለት ነገሮች ይገልፁሀል ፡፡ የመጀመሪያው ምንም የሌለህ ጊዜ የምታሳየው ትዕግስት ሲሆን ሁለተኛው ሁሉም ሲሟላልህ የምታሳየው ጠባይ ነው ፡፡
-ኢማም አሊ

5. በምድር ላይ ትልቁ አስደሳች ነገር ሰዎች አትችልም ያሉህን ሰርተህ ማሳየትህ ነው ፡፡
-ዋልተር ባግሆት

6. ወንዝ ድንጋይ ቦርቡሮ የሚገባው ሀይለኛ ስለሆነ ሳይሆን ያለማቋረጥ ስለሚፈስ ነው ፡፡
-ጂም ዋትኪንስ

7. ህልምህን ለመፈፀም ብዙ ጊዜ በመውሰዱ ተስፋ አትቁረጥ ምክንያቱም ጊዜ ስለሚበር አርቀህ ያየኸው ህልም በፍጥነት መፈፀሙ አይቀርም ፡፡
-አርል ኒተንጋል

8. ሰዎች በምታቅደው እቅድ ካልሳቁ ወይም ካልተገረሙ እቅድህ ትንሽ ነው ማለት ነው ፡፡
-አዚም ፕሪሚጂ

9. ለመጀመር ትልቅ መሆን አይጠበቅብህም ነገር ግን ትልቅ ለመሆን መጀመር አለብህ ፡፡
-ዚግ ዚግላር

10. ደስተኛ የሆነ ሕይወት ለመኖር ከፈለክ ከሁኔታና ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከአላማና እቅድህ ጋር ተጣበቅ ፡፡
-አልበርት አንስታይን

11. አንተ የምርጫህ ውጤት እንጂ በአንተ ላይ የሚደርሱት ነገሮች ውጤት አይደለህም ፡፡
-ካርል ጉስታቭ

12. ባለትላልቅ አእምሮ ሰዎች በሃሳብ ላይ ይወያያሉ ፣ መካከለኞች በ ድርጊት / ሁኔታዎች ላይ ይወያያሉ ባለትናንሾች ቁጭ ብለው ሰው ያማሉ ፡፡
-ሪያኖር ሮዝቪልት

13. እስካልቆምክ ድረስ በምንም ዝግታ ብትጓዝ መድረስህ አይቀርም ፡፡
-ኮንፊሺየስ

14. ችሎታ ያለው ሰው ምንም ስራ እስካልሰራ ድረስ ችሎታ በሌለው ጠንካራ ሰራተኛ ይበለጣል ፡፡
-ቲም ኖትኪ

15. ከውድቀት ይልቅ ጥርጣሬ የነገ ህልምን ይገላል ፡፡
-ሱዚ ካስም

16. እውቀት ብቻ አይበቃም ተግባራዊ ካልተደረገ በስተቀር ፣ ፍቃደኛነት ብቻ አይበቃም ካልተሰራ በስተቀር ፡፡
-ብሩስ ሊ

17. የዛሬ አመት በዚህ ሰአት ምናለ ምናለ ከአመት በፊት በጀመርኩ የምትላቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፡፡
-ካረን ላንብ

18. ጀማሪዎቹ ለመስራት ከሞከሩት ጊዜ በላይ አለቃቸው ብዙ ጊዜ ወድቋል ፡፡
-ስቴፈን ማክክሬን

19.ብዙ ጊዜ ላለመስራት የምትተዋቸው ስራዎች በውስጣቸው ብዙ እድልን የያዙ ናቸው ፡፡
-ሮቢን ሻርማ

20. አለም የምትቀየረው በአንተ አስተያየት ሳይሆን በአንተ ተግባራዊ ስራ ነው ፡፡
-ፖል ኮኢልሆ

21. መተንፈስ እንደምትፈልግ ያህል ለስኬታማ ሕይወት ጥልቅ ፍላጎት ካለህ ይሳካልሀል ፡፡
-ኤሪክ ቶማስ

22. ፊትህን ወደ ፀሀይ ስታዞር ጥላህ ከኀላህ ይወድቃል ፡፡
-የማዎሪ አባባል

23. 99% የሚሆኑ ሰዎች ሀሳብህን ከተጠራጠሩህ ፣ እጅጉን ስተሀል አልያም ታሪክ ልትሰራ ነው ፡፡
-ስኮት ቤልስካይ

24. ፈፅሞ አትድከም ምክንያቱም አሁን እጅግ ከባድ የሆነብህ ስራ ከጥቂት ጊዜያት በኀላ ለሌላ ስራ መሟሟቂያ ይሆናል ፡፡
-ያልታወቀ ሰው

25. ሕይወት ልክ እንደ ካሜራ ነች ፡፡ የምትፈልገውና ጠቃሚ ነገር ላይ ስታተኩር ሌሎቹ የማያስፈልጉት እየደበዘዙ ይሄዳሉ ፡፡


@Psychoet
ለሌሎች ወዳጆቻችንም ሼር እናርጋቸው
@Psychoet
እንደምን ከረማችሁ የቻናሉ ቤተሰቦች ። ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ይዣቸው ለምመጣው የሳይኮሎጂ ትምህርት የቻናሉ አባላትን እድሜ ማወቅ ስለፈለኩ ከታች ባለው ምርጫ እንድታሳውቁኝ እጠይቃለሁ ፡፡

1⃣ 15-20
2⃣ 21-25
3⃣ 26-30
4⃣ 31-35
5⃣ 36-40
6⃣ 41 በላይ
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «እንደምን ከረማችሁ የቻናሉ ቤተሰቦች ። ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ይዣቸው ለምመጣው የሳይኮሎጂ ትምህርት የቻናሉ አባላትን እድሜ ማወቅ ስለፈለኩ ከታች ባለው ምርጫ እንድታሳውቁኝ እጠይቃለሁ ፡፡ 1⃣ 15-20 2⃣ 21-25 3⃣ 26-30 4⃣ 31-35 5⃣ 36-40 6⃣ 41 በላይ»
ሰላም ሰላም !
ከ ነገ ጀምሮ በዚህ ፔጅ ለ 15 ቀን የሚደረግ (ግንቦት 16 - ግንቦት 30) አንድ አዲስ ቻሌንጅ እንጀምራለን ፡፡ ግንቦት 30 የመጨረሻው የሚያበቃበት ይሆናል ።

ቻሌንጁ እንደዚህ ነው
👉🌸የምትወዱትን መጸሐፍ ርዕስ ለሁለት ሰዋች ትልካላችሁ ፡፡ ከታች እኔ ለሁላችሁም ልኬላችኀለሁ ያንን በመላክ መጀመር ትችላላችሁ ፡፡
#ሰላም ጓደኛዬ
እስካሁን ካነበብኳቸው መጸሐፍቶች በጣም የወደድኳቸው እነዚህ ናቸው
1. ቆንጆዎቹ
2. ጥበቡ የምድረበዳው እረኛ

አንተም / አንቺም ይህን መልዕክት #Copy በማረግ የመጸሐፍቶቹን ርዕስ ብቻ በመቀየር ለእኔና ለሌሎች ሁለት ሰዎች 2 መጸሐፎችን ላክልን / ላኪልን ፡፡

ቻሌንጁ የ #15 ቀን ስለሆነ ከላኩልህ / ከላኩልሽ መጸሐፍ አንዱን በ 15 ቀን ( ሰኔ 1 ድረስ) አንብብ/አንብቢ ፡፡ ይህን ታሪካዊ ወቅት ጠቃሚ ነገሮችን በማድረግ በጥንቃቄ እናሳልፍ ፡፡

© @psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «#ሰላም ጓደኛዬ እስካሁን ካነበብኳቸው መጸሐፍቶች በጣም የወደድኳቸው እነዚህ ናቸው 1. ቆንጆዎቹ 2. ጥበቡ የምድረበዳው እረኛ አንተም / አንቺም ይህን መልዕክት #Copy በማረግ የመጸሐፍቶቹን ርዕስ ብቻ በመቀየር ለእኔና ለሌሎች ሁለት ሰዎች 2 መጸሐፎችን ላክልን / ላኪልን ፡፡ ቻሌንጁ የ #15 ቀን ስለሆነ ከላኩልህ / ከላኩልሽ መጸሐፍ አንዱን በ 15 ቀን ( ሰኔ 1 ድረስ) አንብብ/አንብቢ ፡፡…»
.مع كل الحب، البركات، والسلام في هذا اليوم المجيد. عيد فطر سعيد
ለእስልምና እምነት የፔጁ ቤተሰቦች እንኳን ለ1,441ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እመኛለሁ!

ዒድ ሙባረክ!
@psychoet
እንደምን አመሻችሁ ቤተሰቦቼ!
🌙💫የኢድ አልፈጥር በዓልን በማስመልከት ከዚህ ቀደም ያነበብኩትን አንድ ጥሩ አስተማሪ ትምህርት ላጋራችሁ ፡፡ ትምህርቱ ለሁሉም ዕምነት የሚሆን ስለሆነ አንብባችሁ ትጠቀሙበት ዘንድ እጋብዛለሁ ፡፡ 🌙💫
_____________________________
ተዝኪያህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

91፥9 *"ነፍሱን ያጠራት በእርግጥ ዳነ"*፡፡ قَدْ أَفْلَحَ مَن زَكَّاهَا

"ነፍሥ" نَفْس ማለት "እራስነት"own self" ማለት ነው፥ የነፍሥ ብዙ ቁጥር "ኑፉሥ" نُفُوس‎ ወይም "አንፉሥ" أَنْفُس‎ ነው። "ነፍሢ" نَفْسِي ስል "እራሴ"my self" ማለቴ ነው፣ "ነፍሢከ" نَفْسِكَ ስል "እራስክ"your self" ማለቴ ነው፣ "ነፍሢሂ" نَفْسِهِ "እራሱ"him self" ማለቴ ነው። ነፍሥ በሰዋስው ደሙ0ሩ አን-ነፍሢያህ" ህህ ማለትም "ድርብ ተውላጠ-ስም”reflexive pronoun” ነው። በነፍሥ ውስጥ ያለው ዝንባሌ ደግሞ "ነፍሢያህ" نَفْسِيَّة‎ ይባላል፦
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር *”በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ

“አህዋእ” أَهْوَآء ማለት “ዝንባሌ”inclination” ማለት ነው፥ ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት፣ ቡድንተኝነት ምንጫቸው ዝንባሌ ነው። ዝንባሌ ደግሞ ቦታ ከተሰጠው ሊመለክ የሚችል ክፉ አዛዥ ነው፦
25፥43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

ሸይጧን ለአላህ አልታዘዝም ብሎ ያመጸው ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ ስለያዘ ነው፥ የሸይጧንን እርምጃ የሚከተል ሰው ኀጢአትን ተሸከመ፦
24፥21 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *"የሰይጣንን እርምጃዎች አትከተሉ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች የሚከተል ሰው ኀጢአትን ተሸከመ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ وَمَن يَتَّبِعْ خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ

በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት። ነፍሱን ያጠራት በእርግጥ ዳነ፥ በኀጢኣት የሸፈናትም በእውነት አፈረ፦
79፥40 *በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ* وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى
79፥41 *ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ
91፥9 *"ነፍሱን ያጠራት በእርግጥ ዳነ"*፡፡ قَدْ أَفْلَحَ مَن زَكَّاهَا
91፥10 *"በኀጢኣት የሸፈናትም በእውነት አፈረ"*፡፡ وَقَدْ خَابَ مَن دَسَّىٰهَا

"አፍለሐ" أَفْلَحَ የሚለው አላፊ ግስ ሲሆን "ትድኑ ዘንድ" ለሚለው "ቱፍሊሑነ" تُفْلِحُونَ በሚል መጥቷል፦
24፥31 *”ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ በመመለስ ተጸጸቱ”* وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
5፥35 *”ትድኑ ዘንድም በእርሱ መንገድ ታገሉ”*። وَجَاهِدُوا فِي سَبِيلِهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

ነፍስን ከዝንባሌዋ ማጥራት "ተዝኪያህ” ይባላል፥ “ተዝኪያህ” تَزكِية የሚለው ቃል “ዘካ” زَكَىٰ ማለትም “ጠራ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መጥራራት" ማለት ነው፦
2፥151 በውስጣችሁ ከእናንተው የኾነን *በእናንተ ላይ አንቀጾቻችንን የሚያነብላችሁ እና “የሚያጠራችሁ”፣ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ፣ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁ የኾነን መልክተኛ እንደላክን ጸጋን ሞላንላችሁ*፡፡ كَمَا أَرْسَلْنَا فِيكُمْ رَسُولًا مِّنكُمْ يَتْلُو عَلَيْكُمْ آيَاتِنَا وَيُزَكِّيكُمْ وَيُعَلِّمُكُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُعَلِّمُكُم مَّا لَمْ تَكُونُوا تَعْلَمُونَ

“የሚያጠራችሁ” ለሚለው ቃል የገባው “ዩዘኪኩም” يُزَكِّيكُمْ መሆኑ ይህንን ታሳቢና ዋቢ ያረገ ነው። ተዝኪያህ ሦስት ደረጃዎች አሉት፥ እነርሱም፦
1ኛ. “ተዕሊም” تَعْلِيم‎ ማለትም “ትምህርት”
2ኛ. “ተርቢያህ” تربية ማለትም “እድገት”
3ኛ. “ተዕዲል” تَعْدِيل‎ ማለትም “ግብረገብ” ነው።
አል-አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 273
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“እኔ የተላኩትን መልካም ሥነ-ምግባርን ላሟላ ነው”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ إِنَّمَا بُعِثْتُ لِأُتَمِّمَ صَالِحَ الأَخْلاق

ተዝኪያህ ከራሳችን ዝንባሌ ጋር የሚደረግ ጂሃድ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 22, ሐዲስ 3
ፈዷላህ ኢብኑ ዑበይድ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *"ከራሱ ነፍስ ጋር የታገለ ሙጃሂድ ነው"*። فَضَالَةَ بْنَ عُبَيْدٍ، وَسَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏"‏ الْمُجَاهِدُ مَنْ جَاهَدَ نَفْسَهُ

እዚህ ሐዲስ ላይ "የታገለ" ለሚለው የገባው ቃል "ጃሀደ" جَاهَدَ መሆኑን ልብ አድርግ። “ጂሃድ” جِهَاد የሚለው ቃል “ጃሀደ” جَاهَدَ‎ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ትግል” ማለት ነው፥ እውነትን ለማንገስ ሐሰትን ለማርከስ፥ ከሙገሳ እና ከወቀሳ ነጻ ሆኖ በአላህ መንገድ በልቡ፣ በምላሱ እና በእጁ የሚታገል ሙጃሂድ” ْمُجَاهِد ይባላል። ነፍስን ለማጥራት ተሰዉፍ ማድረግም “ጁሁድ” جُهْد ነው፥ ሸይኩል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁሏሁ ስለ ጂሃዱ አን-ነፍሥ ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል፦
ረውደቱል ሙሒቢን 1/478
*"ከነፍስ እና ከስሜት ጋር የሚደረግ ጂሃድ ከኩፋርን እና ከሙናፊቂን ጋር ለሚደረግ ጂሃድ መሠረት ነው። እርሱ(ሙሥሊም) እነርሱን ከመታገሉ በፊት ቅድሚያ ነፍሱና ስሜቱን መታገል ይቀድማልና"*። جِهَادُ النَّفْسِ وَالْهَوَى أَصْلُ جِهَادِ الْكُفَّارِ وَالْمُنَافِقِينَ فَإِنَّهُ لَا يَقْدِرُ عَلَى جِهَادِهِمْ حَتَّى يُجَاهِدَ نَفْسَهُ وَهَوَاهُ أَوَّلًا حَتَّى يَخْرُجَ إلَيْهِمْ

እንግዲህ ከነፍስ ጋር ጂሃድ ማድረግ ውስጣዊ ትግል ሲሆን ከዲኑ ጠላቶች ጋር ጂሃድ ማድረግ ውጫዊ ትግል ነው። አላህ በእርሱ መንገድ ከራሳችን ጋር የምንታገል ሙጃሂድ ያርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር

ወሠላሙ ዐለይኩም
______________________
#Share
@Psychoet
ሰላም እንደምን አመሻችሁ!
ሁላችንም ሰዎች መጠኑ ቢለያይም በትንሽና በትልቁ እንናደዳለን ፡፡ ታዲያ ንዴታችን ሳይቆጣጠረን እንዴት እንቆጣጠረው የሚለው የሁላችን ጥያቄ ነው ፡፡ ለንዴት መቆጣጠሪያ መፍትሄ የሚሆኑ ሀሳቦችን በዚች 4 ደቂቃ ቪዲዮ ታገኛላችሁ ፡፡
https://youtu.be/ETxUH0eSi94
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «ሰላም እንደምን አመሻችሁ! ሁላችንም ሰዎች መጠኑ ቢለያይም በትንሽና በትልቁ እንናደዳለን ፡፡ ታዲያ ንዴታችን ሳይቆጣጠረን እንዴት እንቆጣጠረው የሚለው የሁላችን ጥያቄ ነው ፡፡ ለንዴት መቆጣጠሪያ መፍትሄ የሚሆኑ ሀሳቦችን በዚች 4 ደቂቃ ቪዲዮ ታገኛላችሁ ፡፡ https://youtu.be/ETxUH0eSi94»
#በራስ_መተማመንን (Self Confidence)
👉 ለማሳደግ የሚረዱ አስር ሙያዊ ምክሮች

ለራስዎ ያለዎት ከፍ ያለ ግምት ሌሎች እርስዎን የሚያዩበት መንገድ ጥሩ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና አለው። በራስ የመተማመን ስሜት ሲኖርዎትም በተሰማሩበት ሥራ ላይ የበለጠ ስኬታማ እንዲሆኑ ከፍተኛ እርዳታ አለው።
ምንም እንኳን በራስ መተማመን ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩት ምክንያቶች ብዙዎቹ ከእርስዎ ቁጥጥር ውጭ ቢሆኑም፣ በራስ መተማመንን ለመገንባት የሚረዱ ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ። እነዚህን 10 ስትራቴጂዎች በመጠቀም ያልዎትን በራስ መተማመን ከፍ አድርገው ችሎታዎን በትክክለኛው ሁኔታ ሥራ ላይ ማዋል ይችላሉ።

1. አለባበስዎ ጥሩ ይሁን (Dress sharp)።
የእርስዎ አካላዊ ገጽታ እና አለባበስ ላይ ከማንም ሰው በላይ እርስዎ የቀረበ እይታ እና ግንዛቤ አለዎት። ስለሆነም፣ ጥሩ ሆነው እንደማይታዩ በሚሰማዎት ጊዜ፣ ከሌሎች ጋር የሚያደርጉት የሃሳብ ልውውጥ ሂደት ውስጥ ምቾት እንዳይሰማዎት ያደርጋል። ስለራስዎ ገፅታ ግን መልካም አመለካከት ሲኖርዎ ምቾትዎ ይጠበቅና ከሰዎች ጋር የሚያደርጉዋቸው ግንኙነቶች ላይ ልበ ሙል ይሆናል። የራስ ገፅታን ጥሩ ለማድረግ የሰውነትን እና የገላን ንፅህና መጠበቅ፣ ፀጉርን እና ፂምን በቅጡ መከርከም እንዲሁም በወቅቱ ተቀባይ የሆኑ ፋሺኖችን በማዎቅ እና አቅም በፈቀደ መልኩ መከተል ይረዳል። ይህ ማለት በልብስ ላይ ብዙ ገንዘብ ማውጣት አለብዎት ማለት አይደለም። ነገር ግን፣ ብዙ ርካሽ ልብሶችን ከመግዛት ይልቅ፣ ጥቂት የተመረጡ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች መግዛት አለባበስን ጥሩ ለማድረግ ከመርዳታቸውም በላይ ለረጅም ጊዜ ዘመናዊ ሆነው እንዲቆዩ ስለሚያደርጉ ረዘም ላለ ጊዜ ወጪን ይቀንሳሉ።

2. ሲራመዱ ፍጥነት በተሞላበት ሁኔታ ይራመዱ (Walk faster)።
አንድ ሰው ስለ ራሱ ያለውን ስሜት ለማወቅ ብዙዎች ከሚጠቀሙባቸው ቀላል መንገዶች ውስጥ አንዱ አረማመዱን መመርመር ነው። ዝግ ብሎ የሚራመድ ነው? ሲራመድ ድካም ይታይበታል? ወይስ ሃይል የተሞላ እና አላማ ያለው አካሄድ አለው? በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች በፍጥነት ይራመዳሉ። አፋጣኝ የሆነ ጉዳይ ባይኖርብዎትም እንኳ ፈጠን ብለው በመራመድ የራስዎን መተማመን ከፍ ማድረግ ይችላሉ።

3. ሁሌም ጥሩ የሰውነት አቋም ያሳዩ (Have a good posture)።
በተመሳሳይ መንገድ፣ አንድ ሰው ሰውነቱን የተሸከመበት መንገድ ሰውየው ስላለው የራስ መተማመን ብዙ ይናግራል። የተጣበቁ ትከሻዎች እና የተልፈሰፈሰ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ሰዎች የራስ መተማመን ማጣትን ያሳያሉ። እራሳቸውን ከፍ አድርገው አይመለከቱትም። ጥሩ አቋም በማሳየት ግን በራስ መተማመን ይሰማዎታል። ቀጥ ያለ ሰውነት ይኑርዎ፣ ጭንቅላትዎን ወደላይ ከፍ ያርጉ፣ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩ የዓይን ለአይን ግንኙነት ያድርጉ። ይህንም ሲያደርጉ ሌሎች ላይ አዎንታዊ ስሜት ያሳድራሉ፣ እናም በፍጥነት የበለጠ ንቃት እና ኃይል ያሰማዎታል።

4. ለራስዎ ስለ ራስዎ ማስታዎቂያ ይስሩ (Do personal commercial)
ጠንካራ ጎኖችዎን እና ግቦችዎን የሚያጎሉ ከ 30-60 ሰከንድ የሚዎስዱ ንግግር ይጻፉ። ከዚያም በራስ የመተማመን ስሜት በሚፈልጉበት ጊዜ በመስታወት ፊት ለፊት በመቆም (ወይም ጭንቅላትዎ ውስጥ በማነብነብ) ለራስዎ ይንገሩ።

5. በምስጋና የተሞሉ ይሁኑ (Have gratitude)
ምስጋና ሊሰማዎት የሚያነሳሳዎትን ነገሮች ሁሉ በአዕምሮዎ ውስጥ በመዘርዘር የሚያስቡበት ጊዜ በየዕለቱ ይመድቡ። ያለፉትን ስኬቶችዎን፣ ልዩ ችሎታዎችዎን፣ ወዳጆችዎን እና አዎንታዊ እንቅስቃሴዎን ያስታውሱ። ምን ያህል እርቀት እንደመጡም ለመገንዘብ ይረዳዎታል፣ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ስኬት ለመሄድም በእጅጉ ያነሳሳዎታል።

6. ለሌሎች ሰዎች ስለ ጥሩ ስራቸው አድናቆትን ይለግሱ (Complement others)።
ስለራሳችን አሉታዊ በሆነ መልኩ ስናስብ፣ ብዙውን ጊዜ ሌሎችን ማጣጣል እና በጀርባቸው ላይ መጥፎ ነገር መሸረብ ላይ ትኩረት እናደርጋለን። ይህንን የኑሮ ዘይቤ ለማቋረጥ ሌሎች ሰዎችን የማመስገን ልማድ ይኑርዎት። ከሰዎች ጀርባ መጥፎ ነገር መመኘት ወይም መጠንሰስን አስወግደው በሰሯቸው ጥሩ ስራዎች አድናቆትን ለመግለፅ ይሞክሩ። በሂደቱ ውስጥም በጣም ይወደዳሉ፣ በዚህም በራስ መተማመን ይገነባሉ ። በሌሎች ውስጥ ምርጡን በመፈለግና በመመስከር በተዘዋዋሪ ምርጡን ወደ ራስዎ ዘንድም ያመጣሉ።

7. ከፊት ረድፍ ይቀመጡ (Sit in the front row)
ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ ጽ / ቤቶች እና ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ ብዙ ሰዎች መጨረሻ ለመቀመጥ ይጥራሉ። ምክንያቱም በቀላሉ መታየቱ ያስፈራቸዋል። ይህም በራስ መተማመን ማጣትን ያሳያል። በፊተኛው ረድፍ ላይ ለመቀመጥ ሲዎስኑ ይህንን ያለፈቃድ የሚመጣ ፍርሃት አሸንፈው በራስ መተማመንዎን መገንባት ይችላሉ። በተጨማሪም ከዋናው ፊት ለፊት ለሚነጋገሩ ሰዎች በይበልጥ ግልጽ ይሆናሉ።

8. ሃሳብዎን ይግለፁ (Speak up)
በቡድን ውይይቶች ወይም ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ሁኔታ ውስጥ ብዙ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመግለፅ ይቆጠባሉ። ምክንያቱም ሰዎች ከንግግራቸው ተነስተው እንዳይገምቷቸው ስለሚፈሩ ነው። ይህ ፍርሃት ትክክል አይደለም። ብዙ ጊዜ ሰዎች ከምናስበው ይልቅ የሰውን ሃሳብ የመቀበል ፍላጎት አላቸው። በእርግጥ ብዙ ሰዎች በተመሳሳይ ፍራቻ የተጠቁ ናቸው። በእያንዳንዱ የቡድን ውይይት ቢያንስ አንድ ጊዜ ለመናገር ጥረት በማድረግ የተሻለ የህዝብ ንግግር ክህሎት እንዲያዳብሩ ፣ ይበልጥ በራስ መተማመን እንዲኖርዎት እና በእኩዮችዎ ዘንድ መሪነትን እና ተቀባይነትን እንዲያገኙ ያደርግዎታል።

9. ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ልምድዎ ይሁን (Work out)
ልክ እንደ አለባበስ አይነት፣ አካላዊ ብቃት በራስ መተማመን ዘንድ ከፍተኛ ሚና አለው። ቅርጽዎ እንደተበላሸ ከተሰማዎት በሌሎች ዘንድ ዝቅ ተደርጎ የመታየት እና ሌሎችን መማረክ አለመቻል ስሜት ይሰማዎታል። አካላዊ እንቅስቃሴን በማድረግ አካላዊ ገጽታዎን ያሻሽላሉ፣ ኃይልን ያገኛሉ፣ ለአዎንታዊ ስራም ይነሳሳሉ።

10. የሚያደርጉት አስተዋፅዎ ላይ ያተኩሩ (Focus on contribution)
ብዙውን ጊዜ እኛ ስለምንፈልጋቸው ነገሮች እንጂ የሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች እና በሌሎች ላይ ስለሚመጣው ጥሩ ለውጥ አናስብም። ስለራስዎ ማሰብ ካቆሙ እና ለተቀረው ዓለም ላይ ለውጥ እንዲመጣ በሚያደርጉት አስተዋፅኦ (መዋጮ) ላይ ካተኮሩ፣ ያሉብዎት ጉድለቶች አያስጨንቁዎትም። ይህ በራስ መተማመንን ይጨምራል እናም በከፍተኛ ተነሳሽነት እና ውጤታማነት እንዲሳተፉ ያስችልዎታል። ለዓለም ጥሩ እያደረጉ በሄዱ መጠን የግል ስኬት እና እውቅናንም እየተጎናፀፉ ይሄዳሉ።

©የፍቅር_ሳይኮሎጂ
#በቅንነት ሼር አድርጉ

@psychoet
ሰላም ቤተሰቦቼ !

ዛሬ በሥነልቡና ጤንነት ላይ የሚሰራ አንድ ተቋም ላስተዋውቃችሁ ፡፡ አሃ የስነ-ልቦና አገልግሎት ማዕከል ይባላል ፡፡ የብዙ አመት ልምድ ባላቸው የሳይኮሎጂ ሙያተኞች የተከፈተ ሲሆን በአካል ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ በቴሌግራምና የፌስቡክ ገፆቻቸውን ጥሩ ትምህርት እየሰጡ ይገኛሉ ፡፡

ስለዚህም ፔጃቸውን Like በማድረግ እግጅ በጣም ጥሩ የሥነልቦናዊ ምክሮችና ትምህርቶች እንድታገኙ እመክራለሁ ፡፡
📌TELEGRAM
@Ahapsychology
📌FACEBOOK
https://www.facebook.com/Ahapsychology/

በአካል ለሚደረግ ማንኛውም የሥነልቦና ምክር ከፈለጋችሁ ደውላችሁ ቀጠሮ ማስያዝና መረጃ መጠየቅ ትችላላችሁ ፡፡
አሃ የስነ-ልቦና አገልግሎት
22 አንበሳ ኢንሹራንስ ህንጻ 5ኛ ፎቅ
ስልክ፡ 0940200454፣ 0116622437
ኢሜይል [email protected]
#የዛሬው_ውድቀት_ለነገው_ድል_ምስክር_ነው

እኛ ሁላችን በምድር ላይ አንዳች አምሳያ ላይኖረን ልዩ ተደርገን ተፈጥረናል ፡፡ ሁላችን ወደዚህ ምድር ለትልቅ አላማ መተናል ፡፡ ስለዚህ ዛሬ ያለፈውን ትናንትናችንን በፀፀት የምናማርርበት ሳይሆን ለነገ ድላችን የምንዘጋጅበት እናርገው ፣ ከተረፋቸው ሰዎች ለመለመን የምንጥርበት ሳይሆን ነገ ለሌላቸው ለመስጠት የምንሰራበት ቀን ይሁንልን ፡፡ምክንያቱም ተስፋና እምነት ላለው ሰው ማታ ለቅሶ ቢሆንም ጠዋት ደስታ ይሆናል ፡፡

ውድ በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም ያላችሁ የፔጃችን ቤተሰቦች ባላችሁበት መልካምና ደስ የሚል ቀን ይሁንላችሁ ፡፡
Nahu|ናሁ

🔸🔹 ↘️💯💯💯↙️🔸🔹
👍 @Psychoet 👍
2024/09/30 11:37:08
Back to Top
HTML Embed Code: