Telegram Web Link
#ጭንቀትን_መቀነሻ_ቴክኒኮች

ይህም በሥልጠናና በባለሙያ የካውንሰሊንግ አገልግሎት ሊገኝ ይችላል፡፡ ሁለት ቴክኒኮችን ብቻ እንመልከት (በርካታ ቴክኒኮች እንዳሉ መገንዘብ ያስፈልጋል)፡-

1⃣ #ABCDE_ቴክኒክ :

ይህ ቴክኒክ አልበርት ኤሊስ (Albert Ellis) በተባሉ የስነልቦና ባለሙያ የተገኘ ዘዴ ነው፡፡

አልበርት ኤሊስ ሰዎች ወደ ጭንቀት የሚገቡት አግባብ ያልሆነ አስተሳሰቦችና እምነቶች (Irrational beliefs and thoughts) ሲጠናወቷቸው ነው ብለው ያምናል።

ለምሳሌ:-

👉ሰው ሁሉ ይጠላኛል፣
👉ሰው ሁሉ ይወደኛል፣
👉ከሰው ሁሉ ተቀባይነትን ማግኘት አለብኝ፤
👉በምሰራው ስራ ሁሉ መሳሳት የለብኝም...ወዘተ የሚሉ እምነቶችና አስተሳሰቦች ለጭንቀት እንደሚዳርጉ ያሰምሩበታል።

እኚህ ሰው እንደሚሉት፥

✔️አሉታዊ ነገሮችን አጋኖ ማየት (Awfulising)

✔️ጥቁርና ነጭ እሳቤ (Black and White thinking 👉ይህ እንግዲህ አንድን ነገር ጥሩ ወይም መጥፎ ብሎ መመደብና በውስጡ ሊኖር የሚችለውን የተወሰነውን ጥሩ ነገር አለማየት ነው።

✔️ጠቅላይ እሳቤ(Over generalizing) 👉ሁልጊዜ፣ ሁሉም ሰው፣ በፍፁም.....ወዘተ የሚሉ ቃላትንና ሃሳቦችን መጠቀም፤
(ሁሉም የሚል አባዜ አለባቸው)

✔️Personalizing የማይመለከተንን ነገር ከራሳችን ጋር አቆራኝቶ ማየት፤

✔️Filtering በሁኔታዎች ውስጥ አሉታዊን ነገር ብቻ መርጦ ማየት፤

✔️Mind reading ይህንን አስቦ ነው ብሎ ያለምንም ማስረጃ ድምዳሜ ላይ መድረስ፤

✔️Blaming 👉ሰዎችን መተቸትና መውቀስ

✔️Labeling 👉ለራስ ስያሜ መስጠት

ለምሳሌ: ደካማ ነኝ፤ዋጋ ቢስ ነኝ...ወዘተ ማለት አግባብ ላልሆኑ አስተሳሰቦች ምክኒያት ናቸው ይሉናል፡፡

ቴክኒኩን ተንትነን ለማየት እንሞክር

#Antecedent (Activating event, Stimulus)፡

ይህ ማለት ጭንቀትን የሚቀሰቅሰው ሁኔታ ወይም ነገር ነው (ተንኳሽ እንበለው)፡፡
" ይህ ተንኳሽ የኛን ምላሽ (Response) ይጠይቃል።

ለምሳሌ:- ከስንት አንድ ቀን ቀጠሮ ብናረፍድ ጭንቀት ሊፈጠርብን ይችላል፡፡ በዚህ ምሳሌ መሰረት ጭንቀትን የሚፈጥርብን ጉዳይ ማርፈዳችን ነው ማለት ነው፡፡

#Belief_our_cognition_about_the_situation ፡-

ይህ እንግዲህ ስለ ተንኳሹ ያለን ሃሳብና እምነት ነው፡፡

ለምሳሌ ማርፈዴ ያለኝን ተቀባይነት ያሳጣዋል፣ በምንም አይነት ምክኒያት ቢሆን ማርፈድ አሳማኝ አይደለም...ወዘተ የሚል እምነት ማለት ነው፡፡

#Consequences- the way that we feel and behave፡

ይህ ውጤት ነው - ጭንቀታችን፡፡ ይህ ምን ባህሪ ይፈጥራል? ቶሎ ለመድረስ አላግባብ ጣልቃ እየገባን መኪናችንን መንዳትን፣ በእጃችንም በአንደበታችንም የተንቀረፈፈ የመሰለንን ሾፌር መስደብ፣ መቆጣት፤ ከአስፋልት ወጥቶ በእግረኛ መንገድ መንዳት... ወዘተ ማለት ነው፡፡

እዚህ ላይ አልበረት ኤሊስ ይሞግታሉ “ያስጨነቀን ማርፈዳችን ነው ወይስ ስለ ማርፈድ ያለን አስተሳሰብና እምነት ነው?”

አሳቸው እንደሚሉት፤ ውጤቱን የፈጠረው ማርፈዳችን (stimulus) ሳይሆን ስለ ማርፈድ ያለን አስተሳሰብና እምነት ነው ባይ ናቸው፡፡

#Dispute:- is the process of challenging the way we think about situations:

ይኸኛው አስተሳሰባችንን የምንሞግትበት ዘዴ ነው። እሳቸው አግባብነት የሌለውን አስተሳሰብና እምነት መሞገት ያስፈልጋል ይላሉ፡፡

ለምሳሌ ከላይ የጠቀስነውን ማርፈድ ብንወስድ እምነታችንን ስንሞግተው እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
“ብዙ ጊዜ በሰዓቱ የምገኝና ቀጠሮ አክባሪ የሆንኩ ሰው ነኝ፡፡ አንድ ዛሬን ባረፍድ ተቀባይነቴን አያሳጣም”፣ “ለማርፈዴ ምክኒያት የሆነኝ የትራፊክ መጨናነቅና ያልጠበቅሁት የመንገዶች መዘጋጋት ነው፡፡ ስለዚህ በቂ ምክኒያት ሊሆን ይችላል፡፡” እነዚህን ምክኒያቶች በማሰብ ነባሩን ሃሳብ መሞገት እንደሚገባ ይጠቁማሉ፤ አልበርት ኤሊስ፡፡

#Effect : ይሄ አዲሱ ውጤት ነው።
አስተሳሰባችንን ከሞገትነውና በአዲስ አስተሳሰብ ከተካነው በኋላ የሚፈጠር ባህሪ ነው፡፡ የላይኛውን ምሳሌ ብንከተል ተረጋግቶ መንዳት፤ ተራ መጠበቅ፤ በተፈቀደው አስፋልት መንዳት... ወዘተ ማለት ነው፡፡

👉ማስተዋል ያለብን ሃሳብ ስሜታችን እና ባህሪያችን ላይ ተፅእኖ ይፈጥራል፡፡ ማወቅና አስተሳሰብን መለወጥ ደሞ አስፈላጊ ነው፡፡

#share

©የፍቅር_ሳይኮሎጂ
Telegram : www.tg-me.com/psychoet
youtube : youtube.com/thenahusenai
መልካም ቀን!
#በራስ_መተማመንን (Self Confidence)
👉 ለማሳደግ የሚረዱ አስር ሙያዊ ምክሮች

ለራስዎ ያለዎት ከፍ ያለ ግምት ሌሎች እርስዎን የሚያዩበት መንገድ ጥሩ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና አለው። በራስ የመተማመን ስሜት ሲኖርዎትም በተሰማሩበት ሥራ ላይ የበለጠ ስኬታማ እንዲሆኑ ከፍተኛ እርዳታ አለው።
ምንም እንኳን በራስ መተማመን ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩት ምክንያቶች ብዙዎቹ ከእርስዎ ቁጥጥር ውጭ ቢሆኑም፣ በራስ መተማመንን ለመገንባት የሚረዱ ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ። እነዚህን 10 ስትራቴጂዎች በመጠቀም ያልዎትን በራስ መተማመን ከፍ አድርገው ችሎታዎን በትክክለኛው ሁኔታ ሥራ ላይ ማዋል ይችላሉ።

1. አለባበስዎ ጥሩ ይሁን (Dress sharp)።
የእርስዎ አካላዊ ገጽታ እና አለባበስ ላይ ከማንም ሰው በላይ እርስዎ የቀረበ እይታ እና ግንዛቤ አለዎት። ስለሆነም፣ ጥሩ ሆነው እንደማይታዩ በሚሰማዎት ጊዜ፣ ከሌሎች ጋር የሚያደርጉት የሃሳብ ልውውጥ ሂደት ውስጥ ምቾት እንዳይሰማዎት ያደርጋል። ስለራስዎ ገፅታ ግን መልካም አመለካከት ሲኖርዎ ምቾትዎ ይጠበቅና ከሰዎች ጋር የሚያደርጉዋቸው ግንኙነቶች ላይ ልበ ሙል ይሆናል። የራስ ገፅታን ጥሩ ለማድረግ የሰውነትን እና የገላን ንፅህና መጠበቅ፣ ፀጉርን እና ፂምን በቅጡ መከርከም እንዲሁም በወቅቱ ተቀባይ የሆኑ ፋሺኖችን በማዎቅ እና አቅም በፈቀደ መልኩ መከተል ይረዳል። ይህ ማለት በልብስ ላይ ብዙ ገንዘብ ማውጣት አለብዎት ማለት አይደለም። ነገር ግን፣ ብዙ ርካሽ ልብሶችን ከመግዛት ይልቅ፣ ጥቂት የተመረጡ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች መግዛት አለባበስን ጥሩ ለማድረግ ከመርዳታቸውም በላይ ለረጅም ጊዜ ዘመናዊ ሆነው እንዲቆዩ ስለሚያደርጉ ረዘም ላለ ጊዜ ወጪን ይቀንሳሉ።

2. ሲራመዱ ፍጥነት በተሞላበት ሁኔታ ይራመዱ (Walk faster)።
አንድ ሰው ስለ ራሱ ያለውን ስሜት ለማወቅ ብዙዎች ከሚጠቀሙባቸው ቀላል መንገዶች ውስጥ አንዱ አረማመዱን መመርመር ነው። ዝግ ብሎ የሚራመድ ነው? ሲራመድ ድካም ይታይበታል? ወይስ ሃይል የተሞላ እና አላማ ያለው አካሄድ አለው? በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች በፍጥነት ይራመዳሉ። አፋጣኝ የሆነ ጉዳይ ባይኖርብዎትም እንኳ ፈጠን ብለው በመራመድ የራስዎን መተማመን ከፍ ማድረግ ይችላሉ።

3. ሁሌም ጥሩ የሰውነት አቋም ያሳዩ (Have a good posture)።
በተመሳሳይ መንገድ፣ አንድ ሰው ሰውነቱን የተሸከመበት መንገድ ሰውየው ስላለው የራስ መተማመን ብዙ ይናግራል። የተጣበቁ ትከሻዎች እና የተልፈሰፈሰ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ሰዎች የራስ መተማመን ማጣትን ያሳያሉ። እራሳቸውን ከፍ አድርገው አይመለከቱትም። ጥሩ አቋም በማሳየት ግን በራስ መተማመን ይሰማዎታል። ቀጥ ያለ ሰውነት ይኑርዎ፣ ጭንቅላትዎን ወደላይ ከፍ ያርጉ፣ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩ የዓይን ለአይን ግንኙነት ያድርጉ። ይህንም ሲያደርጉ ሌሎች ላይ አዎንታዊ ስሜት ያሳድራሉ፣ እናም በፍጥነት የበለጠ ንቃት እና ኃይል ያሰማዎታል።

4. ለራስዎ ስለ ራስዎ ማስታዎቂያ ይስሩ (Do personal commercial)
ጠንካራ ጎኖችዎን እና ግቦችዎን የሚያጎሉ ከ 30-60 ሰከንድ የሚዎስዱ ንግግር ይጻፉ። ከዚያም በራስ የመተማመን ስሜት በሚፈልጉበት ጊዜ በመስታወት ፊት ለፊት በመቆም (ወይም ጭንቅላትዎ ውስጥ በማነብነብ) ለራስዎ ይንገሩ።

5. በምስጋና የተሞሉ ይሁኑ (Have gratitude)
ምስጋና ሊሰማዎት የሚያነሳሳዎትን ነገሮች ሁሉ በአዕምሮዎ ውስጥ በመዘርዘር የሚያስቡበት ጊዜ በየዕለቱ ይመድቡ። ያለፉትን ስኬቶችዎን፣ ልዩ ችሎታዎችዎን፣ ወዳጆችዎን እና አዎንታዊ እንቅስቃሴዎን ያስታውሱ። ምን ያህል እርቀት እንደመጡም ለመገንዘብ ይረዳዎታል፣ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ወደ ስኬት ለመሄድም በእጅጉ ያነሳሳዎታል።

6. ለሌሎች ሰዎች ስለ ጥሩ ስራቸው አድናቆትን ይለግሱ (Complement others)።
ስለራሳችን አሉታዊ በሆነ መልኩ ስናስብ፣ ብዙውን ጊዜ ሌሎችን ማጣጣል እና በጀርባቸው ላይ መጥፎ ነገር መሸረብ ላይ ትኩረት እናደርጋለን። ይህንን የኑሮ ዘይቤ ለማቋረጥ ሌሎች ሰዎችን የማመስገን ልማድ ይኑርዎት። ከሰዎች ጀርባ መጥፎ ነገር መመኘት ወይም መጠንሰስን አስወግደው በሰሯቸው ጥሩ ስራዎች አድናቆትን ለመግለፅ ይሞክሩ። በሂደቱ ውስጥም በጣም ይወደዳሉ፣ በዚህም በራስ መተማመን ይገነባሉ ። በሌሎች ውስጥ ምርጡን በመፈለግና በመመስከር በተዘዋዋሪ ምርጡን ወደ ራስዎ ዘንድም ያመጣሉ።

7. ከፊት ረድፍ ይቀመጡ (Sit in the front row)
ትምህርት ቤቶች ውስጥ፣ ጽ / ቤቶች እና ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ ብዙ ሰዎች መጨረሻ ለመቀመጥ ይጥራሉ። ምክንያቱም በቀላሉ መታየቱ ያስፈራቸዋል። ይህም በራስ መተማመን ማጣትን ያሳያል። በፊተኛው ረድፍ ላይ ለመቀመጥ ሲዎስኑ ይህንን ያለፈቃድ የሚመጣ ፍርሃት አሸንፈው በራስ መተማመንዎን መገንባት ይችላሉ። በተጨማሪም ከዋናው ፊት ለፊት ለሚነጋገሩ ሰዎች በይበልጥ ግልጽ ይሆናሉ።

8. ሃሳብዎን ይግለፁ (Speak up)
በቡድን ውይይቶች ወይም ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ሁኔታ ውስጥ ብዙ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመግለፅ ይቆጠባሉ። ምክንያቱም ሰዎች ከንግግራቸው ተነስተው እንዳይገምቷቸው ስለሚፈሩ ነው። ይህ ፍርሃት ትክክል አይደለም። ብዙ ጊዜ ሰዎች ከምናስበው ይልቅ የሰውን ሃሳብ የመቀበል ፍላጎት አላቸው። በእርግጥ ብዙ ሰዎች በተመሳሳይ ፍራቻ የተጠቁ ናቸው። በእያንዳንዱ የቡድን ውይይት ቢያንስ አንድ ጊዜ ለመናገር ጥረት በማድረግ የተሻለ የህዝብ ንግግር ክህሎት እንዲያዳብሩ ፣ ይበልጥ በራስ መተማመን እንዲኖርዎት እና በእኩዮችዎ ዘንድ መሪነትን እና ተቀባይነትን እንዲያገኙ ያደርግዎታል።

9. ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ልምድዎ ይሁን (Work out)
ልክ እንደ አለባበስ አይነት፣ አካላዊ ብቃት በራስ መተማመን ዘንድ ከፍተኛ ሚና አለው። ቅርጽዎ እንደተበላሸ ከተሰማዎት በሌሎች ዘንድ ዝቅ ተደርጎ የመታየት እና ሌሎችን መማረክ አለመቻል ስሜት ይሰማዎታል። አካላዊ እንቅስቃሴን በማድረግ አካላዊ ገጽታዎን ያሻሽላሉ፣ ኃይልን ያገኛሉ፣ ለአዎንታዊ ስራም ይነሳሳሉ።

10. የሚያደርጉት አስተዋፅዎ ላይ ያተኩሩ (Focus on contribution)
ብዙውን ጊዜ እኛ ስለምንፈልጋቸው ነገሮች እንጂ የሌሎች ሰዎች ፍላጎቶች እና በሌሎች ላይ ስለሚመጣው ጥሩ ለውጥ አናስብም። ስለራስዎ ማሰብ ካቆሙ እና ለተቀረው ዓለም ላይ ለውጥ እንዲመጣ በሚያደርጉት አስተዋፅኦ (መዋጮ) ላይ ካተኮሩ፣ ያሉብዎት ጉድለቶች አያስጨንቁዎትም። ይህ በራስ መተማመንን ይጨምራል እናም በከፍተኛ ተነሳሽነት እና ውጤታማነት እንዲሳተፉ ያስችልዎታል። ለዓለም ጥሩ እያደረጉ በሄዱ መጠን የግል ስኬት እና እውቅናንም እየተጎናፀፉ ይሄዳሉ።

©የፍቅር_ሳይኮሎጂ
#በቅንነት ሼር አድርጉ

@psychoet
የቀለም ምርጫዎ ማንነትዎን ሊገልጽ እንደሚችል ያውቃሉ?
(Color Psychology)

የቀለም ምርጫችን የስብዕናችን አካል በመሆን በባህሪያችንና በቀን ውሏችን ላይ ተጽእኖ ማሳደር ይችላል፡፡በተለያየ ወቅት ለተለያዩ የቀለማት ዓይነቶች ያለን ትኩረት፤ በተለያዩ የቀለም ዓይነቶች የመሳብ ዝንባሌ፤ ወይም አንድን ከለር የመጥላትና ሌላውን የመውደድ ፍላጎት ከስነ-ልቦና ለውጥ ጋር ተያያዥነት ሊኖረው ይችላል፡፡ እስኪ የቀለም ምርጫዎ ምን አይነት እንደሆነ እና የቀለሙ ትርጉም ምን ማለት እንደሆነ ይመልከቱ፡-

ጥቁር፤ ቀይ፤ቡኒ ወይም ግራጫ /BLACK, RED, BROWEN, OR GRAY COLORS

እነዚህ ቀለማት ራስን ከአደጋ ከመጠበቅ ስሜት ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳላቸው ይታመናል፡፡ በልብስ፤ በቤት ቀለም፤ ወይም በምግብ ምርጫዎ ወደእነዚህ ቀለማት የመሳብ ዝንባሌ ካለዎት እርስዎ በጣም ጠንካራ፤ ትጉና ለስራ ተነሳሽ የሆነ ሰብዕና ያልዎት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም እነዚህ ቀለሞች ምርጫቸው የሆኑ ሰዎች ውስጣቸው ወይም ልባቸው ስስ፤ ከላይ ሲታዩ ግን ኮስታሮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ብርቱካናማ ቀለም/ORANGE COLOR/

ወደ ብርቱካናማ ቀለም የሚሳቡ ሰዎች በአብዛኛው አዳዲስ ነገሮችን የመፍጠር ችሎታ እንዳላቸው ይታመናል፡፡ አለምን መጎብኘትና አደጋ ያለባቸውን አካባቢዎች ሳይቀር የመመርመር ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ብርቱካናማ ቀለም ይስባቸዋል

ቢጫ ቀለም/YELLOW COLOR/

ቢጫ ቀለም የበዛባቸውን ነገሮች የሚያዘውትሩ ሰዎች በጣም ሀይለኞችና የውሰኔ ሰዎች የመሆን ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ የሚያሰቡትን ነገር ወደ ድርጊት ለመቀየር የሚተጉ ሰዎችን ትኩረት  ቢጫ ቀለም ይስባቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ጥሩ ነጋዴዎችና መሪዎችም ሊሆኑ ይችላሉ

አረንጓዴ ቀለም/GREEN COLOR/

አረንጓዴ ቀለም ቀዳሚ ምርጫዎ ሆነ ማለት ልብዎ ወይም ቀልብዎ  የሚነግርዎትን ለማዳመጥና ለመተግበርና፤ ስሜትዎን ለማዳመጥ በጣም ቅርብ ነዎት ማለት ነው፡፡ የአረንጓዴ ቀለም ምርኮኛ ከሆኑ የሌሎችን ሰዎች ስሜት ለመረዳትና የሰዎችን ችግርም ለመረዳትና ለመርዳት ፍላጎት ሊኖርዎት ይችላል

ሰማያዊ ቀለም/BLUE COLOR/

ሰማያዊ ቀለም ሲያዩ የሚማረኩ ከሆነ እርስዎ በቀላሉ ተግባቢና ራስዎን ለሌሎች ሰዎች መግለጽ አያስቸግርዎትም ማለት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሰማያዊ ቀለም ምርጫቸው የሆኑ ሰዎች በቀላሉ ስሜታዊ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ወይንጠጅ/PURPLE COLOR/

ወይንጠጅ ቀለም የሚወዱ ከሆነ እርስዎ ለስድስተኛው የስሜት ህዋስዎ ቅርብ ነዎት፡፡ ከቁስ አካል  ይልቅ የማይታየው ዓለም ይመስጥዎታል ማለት ነው፡፡ የወይን ጠጅ ቀለም ወዳጆች የስነ-ልቦና ባለሙያ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለሰዎች መንፈሳዊና ስነ-ልቦናዊ ህይወት የማወቅ ጉጉት ሊኖርዎት ይችላል

ሮዝ ቀለም/PINK COLOR/

ሮዝ ቀለም የሚወዱ ከሆነ እርስዎ ደስተኛ ለመሆን እና ሌሎች ሰዎች ደስተኛ እንዲሆኑ ሲጥሩ ይታይሉ፡፡ የህይወትን ጎደሉ ጎን ሳይሆን መልካም ገጽታዋን አጉልተው ያያሉ፡፡ ህይወትን ሳያከብዱ ቀለል አድርገው የሚኖሩ ሰዎች ከሮዝ ቀለም ጋር ትስስር አላቸው፡፡

(በሰብለወንጌል አይናለም)
©Zepsychology
@psychoet
መነሳሳት

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

 8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

 10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ) ©Zepsychology
@Psychoet
እንደምን አመሻችሁ ቤተሰቦች!

ዛሬ ካነበብኩት ውስጥ ...

#ሰው_ኦፕሬሽን_የሚደረገው_ጠባሳ_ፈልጎ_አይደለም

በእርግጥ በሕይወታችን ያሉ ጠባሳዎች የሚያመለክቱት ያለፍንባቸውን መንገዶችንና የወሰናቸውን ውሳኔዎች እንዲሁም የደረሱብን ሽንፈትና ድሎችን ነው ፡፡

ሁልጊዜ በሰው ላይ ከምናየው ጠባሳ ባሻገር ብዙ ምስጢር አለና ሰውን ከፊት በምናየው ብቻ አንለካ ፡፡ ምን ፣ ለምን ፣ እንዴት .... ብለን እንጠይቅ ፡፡

መልካም አዳር
Nahu|ናሁ
@psychoet
የ3 ደቂቃ ስራ ናት እናንብባት ረጅም አይደለችም አጭር ፅሁፍ ናት

*አንድ የ78 ዓመት አባት እራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል ይወሰዳሉ ። ለ24 ሰዓት የሚያቆያቸው የመተንፈሻ ኦክስጅን ተሰጣቸው ። ከጥቂት ግዜ በኃላ ተሻላቸውና ዶክተሩ የተጠቀሙበትን ሂሳብ የ500 ዶላር ደረሰኝ ሰጣቸው ።
*እኝህ አባትም የተሰጣቸውን ደረሰኝ በተመለከቱ ግዜ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ ። ዶክተሩም ስለ ገንዘቡ ማልቀስ አይገባዎትም በአንድ ግዜም ባይሆን ቀስ እያሉ መክፈል እንደሚችሉ ነገራቸው ። *ሆኖም እኝህ አባት " እኔ የማለቅሰው ስለዚህ ገንዘብ አደለም ገንዘቡን በሙሉ የመክፈል አቅም አለኝ ፤ የማለቅሰው 24 ሰኣት ለተነፈስኩበት ኦክስጅን 500 ዶላር ልከፍል በመሆኑ ነው ፤
*ነገር ግን ላለፋት 78 አመታት የእግዚአብሔርን ንፁ አየር በነፃ ስተነፍስ ኖሬያለው ለእነዚ ሁሉ ግዜያት መክፈል ቢኖርብኝ ምን ያህል የእግዚአብሔር እዳ እንዳለብኝ መገመት ትችላለህ ?? " በማለት መለሱለት
*አሁን ይሄንን ወደምታነቢው እህት ወይም ወንድም ልመለስ ፤ የእግዚአብሔር ንፁህ አየር ያለ አንዳች ክልከላና ክፍያ ይሄን ያህል ስትተነፍሺ ኖረሻል ወይም ስትተነፍስ ኖረሃል ።
==========================
ከተመቸችህ አስተማሪ ናት ካልክ ሼር አድርጋት
©Selam yehune

@Psychoet
እንደምን አመሻችሁ !

በተገቢው ዕድሜ የማግባት ጥቅሞች በሚል የተዘጋጀው የ 7 ደቂቃ video ክፍል 1 ቀርቧል ። ጉዳዩ ብዙ ያላገቡ / ለማግባት ያሰቡ ወጣቶችን ስለሚመለከት በሌላም ጊዜ በተለየ መልክ በውይይት እንቀጥለዋለን፡፡

መነሻ ፅሑፉ (በከበደ በከሬ©zepsychology) ሲሆን አንባቢው ደግሞ ምስጋና ዮሴፍ ነው፡፡

ዩቲዩብ ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ ።
https://youtu.be/p4mDYOGD8o4
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «እንደምን አመሻችሁ ! በተገቢው ዕድሜ የማግባት ጥቅሞች በሚል የተዘጋጀው የ 7 ደቂቃ video ክፍል 1 ቀርቧል ። ጉዳዩ ብዙ ያላገቡ / ለማግባት ያሰቡ ወጣቶችን ስለሚመለከት በሌላም ጊዜ በተለየ መልክ በውይይት እንቀጥለዋለን፡፡ መነሻ ፅሑፉ (በከበደ በከሬ©zepsychology) ሲሆን አንባቢው ደግሞ ምስጋና ዮሴፍ ነው፡፡ ዩቲዩብ ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ ። https://youtu.be/p4mDYOGD8o4»
ራስን በመቆጣጠር ድብርትን መከላከልና መጋፈጥ
#Share
የራስ ቁጥጥርና (self-regulation) የድብርት ስሜት ተዛማጅና ግንኙነት ያላቸው የስነ-ልቡና ክስተቶች ናቸው፡፡ ራስን መቆጣጠር ማለት አንድን ነገር ከግብ ለማድረስ ውስጠ ስሜትን፣አስተሳሰብንና ጠባይን መግራት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ራስን መቆጣጠር ከግብ ወይም አላማችን ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ለምሳሌ ግባችን መማር፤ጥሩ ስራ መያዝ፤ የፍቅር ጓደኛ መያዝ፤ትዳር መመስረትና ልጆች ማፍራትና የመሳሰሉት ሊሆን ይችላል፡፡ እናም አላማችን ከትናንሽ የዕለተለት ግቦች እስከ ላቅ ያሉ ለህይወታችን ከፍተኛ ትርጉም ያላቸው ግቦች ድረስ ሊሆን ይችላል፡፡

ራስን መቆጣጠርና የድብርት ስሜትን ምን አገናኛቸው?

ራስን መቆጣጠር ውስጠ ስሜትን፣አስተሳሰብና፣ጠባይንና ከአላማነችን አንጻር መግራት ነው በሚለው ከተስማማን፤ የግባችን የስኬት መጠን ከድርጊታችን በኋላ ለሚሰማን ሰሜት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ ያሰብነውና ያቀድነው ነገር በተሰካ ጊዜ ደስታ፣እርካታ፣ተሰፋና ለነገ የተነሳሽነት ስሜት ይፈጥርልናል፡፡ ያሰብነውና ያለምነው ነገር ሳይሳካ ሲቀር በተቃራኒው የድብርተና ተዛማጅ አሉታዊ ስሜቶች ሊፈራረቁ ይችላሉ፡፡ በዚህም ምክኒያት ራስን መቆታጠርና ድብርት የጠለቀ ግንኙነት አላቸው፡፡

የድብርት ስሜት ለራስ ቁጥጥር ያለው እንድምታ

ምንም እንኳን የድበርት ስሜት ምችት የማይሰጥ ቢሆንም ሳይንሳዊ መላምቶችና ምርምሮች እንደሚያመላክቱት ከሆነ እራሳችን ለመቆጣጠር የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ለምሳሌ ለፍቅረኛችን ታማኝ መሆን ሲገባን በስህተት ተማኝነታችንን ብናጎድል ከፈጸምነው በኋላ የድብርት ስሜት ሊፈጠርብን ይችላል፡፡ ይህ የድብርት ስሜት ነገ ተደጋጋሚ ስህተት ላለመፈጸም ለእራሳችን ግበረ-መልስ (feedback loop) ነው:: ስለዚህ አላማችን ያማረ የፍቅር ህይወት መመስረት ከሆነ ለዚህ አላማችን መሳካት የእራሳችንን ጠባይ እንድንቆጣጠር የድብርት ስሜቱ አስተዋጽኦ ያበረክታል ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ሁሌም ታማኝነታችንን እያጎደልን ከፈጸምነው በኋላ ፌሽታና ደስታ የሚሰማን ከሆነ በዛው እምነት አጉዳይነታችን የመቀጠላችን እድል የሰፋ ነው፡፡ በተመሳሳይም በትምህርታችን ጥሩ ውጤት የማስመዝገብ አላማ ቢኖረንና ጊዜያችንን በአግባቡ ሳንጠቀም የፈለግነው ውጤት ባይመጣ አሁንም የድበርት ስሜት ሊከስት ይችላል፡፡ ይህ የድብርት ስሜት ለእራሳችን ጠባይ ከሰነቅነው አላማ አንጻር ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ አእምሯችን እራሱን የሚገመግምበት ግብረ-መልስ ሲሆን፤ ለወደፊት ይህ እንዳይከሰት የማስጠንቀቂያ ደወል ነው፡፡ በአጭሩ በዚህ የአረዳድ ድባብ መሰረት የድብርት ስሜት መፈጸም በምንፈለግገውና በፈጸምነው መካከል ልዩነት ሲፈጠር የሚከሰት ነው ማለት ነው፡፡

ተደጋጋሚ ውድቀትና ድብርት

በተደጋጋሚ ያሰብነውና ያቀድነው ነግር በማይሳካ ጊዜ የድብርት ስሜቱም እየጠነከረ በተደጋጋሚ ስለሚሰማን የድብርት ስሜት፣መንስኤና ውጤት አትኩሮት ሰጥተን እንድናሰላስል በር ይከፍታል፡፡ ይህም ክስተት rumination በመባል ይታወቀል፡፡ ይህ አጥብቆ ስለሚሰማን የድብርት ስሜት ማንሰላሰል ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን ይችላል፡፡ አብዛኞቹ በዚህ ዙሪያ የሚያጠኑ የስነ ልቡና ጠበብቶች አጥብቆ ከልክ በላይ ማሰቡ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን አጽኖት ሰጥተው ይናገራሉ፡፡

ስለዚህ ከድብርት እራሳችን ለመካከልና ለመቋቋም ምን እናደርግ?

❖ተግባራዊ ግብ

በተደጋጋሚ ነገሮች ሳይሳኩ ሲቀሩ የድበርት ስሜት የሚከሰት ከሆነ፣ በተደጋጋሚ ላለመውደቅ ሊተገበር የሚችል ግብ ማውጣት፡፡ የነገሮች አለመሳክት ሁልጊዜ የችሎታ ማነስ፣እድለቢስነትና የሌሎች ተዛማጅ ነገሮች እጥረት ሳይሆን፤ በህይወታችን የምንሰነቃቸው ግቦች ሊተገበሩ የማይችሉና የራስ ቁጥጥራችን ደካማ ስለሆነ ሊሆን ይችላል፡፡

❖ግባችን ለመምታት አስፈላጊ ግብዓቶቸን ማፈላለግ

ተግባራዊ እቅዶችን ከነደፍን በኋላ ወደዚያ ጎዳና ለመድረስ የሚያስችሉ ግብዓቶችን ከእራሳችንንና ከአካባቢያችን ማፈላለግ፡፡ ተሰጥኦቻችንን ማበልጸግ፤ ድክመታችንን ማሻሻልና የሚጎድለንን መሙላት፡፡

❖ጽናት

ተግባራዊ ግቦችን ካስቀምጥንና ወደ አላማችን የሚያደርሱንን ግብዓቶችንን ካመቻቸንን፤ ቀጣዩ የአላማ ጽናት (persistence) ነው፡፡ ሁሌም አዲስ ነገር ሲጀመር በወረትና በመነሳሳት መንፈስ ማደርግ የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን ወደ ድርግጊቱ መሃል ሲገባና ጫና ሲበዛ መፍረክረክ ግባችንን እንዳናሳካ ያደርገናል፡፡ ፈተና ሊበዛ ይችናል፡፡ ነገር ግን ካለ ተግዳሮትና ፈተና የሚገኝ የቤተሰብ ውርስ ብቻ ነው፡፡ የራሳችን ነገር፣ በእራሳችን ብርታት የምንፈልግ ከሆነ ፈተናና ተግዳሮት አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም ከፈተናና ተግዳሮት ልምድ መቅሰምና እራሳችንን እንዲጠቅመን መቀየር ነው፡፡ ለዚህም ራስን ማዘጋጀት፡፡ ሁሉም ነገር አልጋባልጋ ይሆናል ብለን ከተነሳን፤ በኋላ ተግዳሮቶች ሲከሰቱ የመንፈስ ስበራቱ ያለምነው ግባችን ላይ እንዳንደርስ መሰናክል ይሆናል፡፡ ስለዚህ ለተግዳሮቶችና ፈታናዎች ራስን በማዘጋጀት የአይበገሬነት መንፈስ መቀናጀት፡፡

❖አንዴ አልተሳካም ማለት ህይወት አከተመላት ማለት አይደለም

ህይወት መስመሯ አባ ጎርባጣ እነደመሆኑ መጠን ዛሬ ያቀድነው ነገር አልተሳካም ማለት አጠቃላይ ህይዎታችን አለቀላት ማለት አይደለም፡፡ እንደዚህ አይነቱ አስተሳሰብ ለድበርት ስሜትና ለሌች የስነ ልቡና ችገሮች መከሰት ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ምክኒያታዊ ያልሆነ አስተሳሰብ (irrational belief) ነው፡፡ ዛሬ ያፈቀርካትን ልጅ ስላላገኘሀት አጠቃላይ የፍቀር ህይዎትህ ዜሮ ሆነ ማለት አይደለም፡፡ ዛሬ የፈለግኸውን ስራ ስላላገኘህ የነገ መንገድህ ተቆረጠ ማለት አይደለም፡፡ ያለተሳካው ከብዙ የህይወት ግብ ውስጥ እንዱ ወይም የተወሰኑት ናቸው፡፡ ህይወት ደግሞ በአንድና ሁለት እቅድ አትመዘነም፡፡ ይህም የህይወትንና የተፈጥሮን ታላቅንት ማሳነስ ነው፡፡

❖ራስን መቆጣጠር ልምምድ ይፈልጋል

እንግዲህ ተግባራዊ ግብ ማስቀመጥና አስተሳሰባችንን፤ውስጠ ስሜታችንንና ጠባይያችንን ከዚህ ግብ አንጻር መግራት የራስ ቁጥጥር አንኳር መገለጫዎች ናቸው፡፡ የማይተገበር ግብ ማስቀመጥም ለውድቀት ይዳርጋል፤ ተግባራዊ ግብ ቢኖረንም በጽናት ጠባይያችንንና nአስተሳሰባችንን ካልገዛነውም ለውድቀት እንዳረገልን፡፡ ስለዘህ እራሳችንን የመቆጣጠር ክህሎት ለመካን ከትናንሽ ነገሮች ጀምረን እንለማመደው፡፡ ያኔ የስብእናችን ዋነኛ ምሰሶ ይሆናል፡፡
(በአሸናፊ ካሳሁን)©Zepsychology

@psychoet
#የጥሩ_እንቅልፍ_9_ጠቀሜታዎች
ከመተኛታችን በፊት #Share እናርገው

1. እንቅልፍ ልብዎን ጤናማ ያደርገዋል

እንቅልፍ ማጣት የልብ ድካም እና የደም ግፊት አደጋ(ስትሮክ) እንደሚያባብስ ተመራማሪዎች ይናገራሉ ይህም የሚሆነው የደም ግፊት እና ኮሌስትሮል መጠንን በመጨመር መሆኑን ይናገራሉ ፡፡በእያንዳንዱ ምሽት ከ 7 እስከ 9 ሰዓታት ያህል እንቅልፍ ካገኙ የልብዎን ጤና የተጠበቀ ይሆናል ፡፡

2. እንቅልፍ ካንሰርን ለመከላከል ይረዳል

ተመራማሪዎች ለብርሃን መጋለጥ የሜላቶኒንን መጠን እንደሚቀንስ ያምናሉ ፡፡ ሜላተንቲን የእንቅልፍ ና የመንቃትን ዑደትን የሚያስተካክል ሆርሞን ሲሆን በሰውነታችን ውስጥ የሚፈጠሩ ዕጢዎችን እብጠት በመቀነስ ካንሰርን ይከላከላል፡፡ ሰውነትዎ የሚፈልገውን ሜላቶኒንን ለማምረት እንዲረዳዎ መኝታዎ ጨለመ ባለ ስፍራ ያድርጉ እንዲሁም ከመኝታዎ በፊት ኤሌክትሮኒክስን ከመጠቀም ይቆጠቡ ፡፡

3. እንቅልፍ ውጥረትን ይቀንሳል

ሰውነትዎ እንቅልፍ እጥረት ሲኖርበት ወደ ውጥረት(ስተርስ) ሁናቴ ይሄዳል ፡፡ ይህም ውጥረት ወየንም ስተርስ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ የልብ ድካም እና የደም ግፊት አደጋ የመያዝ እድልን ይጨምራል፡፡

4. በቂ እንቅልፍ ማግኘት የበለጠ ንቃትን ይሰጣል

ጥሩ የሌሊት እንቅልፍ ንቃት እንዲሰማዎት እና በሚቀጥለው ቀን እንዲነቃቁ ይረዳዎታል ፣ በተጨማሪም ጥሩ ስሜት እነዲሰማዎት በማድረግ ሌላ ጥሩ የሌሊት እንቅልፍ እድልዎተን ይጨምራል።

5. እንቅልፍ የማስታወስ ችሎታዎን ያሻሽላል

ተመራማሪዎች እስካሁኑ ሰዐት ድረስ ለምን እንደምንተኛ ሙሉ በሙሉ አልተረዱም ፣ ነገር ግን እንቅልፍ የማስታወስ ዐቅምን በማጠናር ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ደርሰውበታል፡፡
በእንቅልፍ ጊዜ ሰውነትዎ አረፍ ሊል ይችላል ፣ነገር ግን አንጎልዎ ቀንዎን በማቀነባበር የተያዩ ግንኙነቶችን በማድረጉ ሥራ ላይ ነው ፡፡ እነዚሀም ግንኙነቶች በተያዩ ክስተቶች ፣ በስሜት ህዋሳት ፣ ስሜቶች እና ትውስታዎች መካከል ሲሆን በቂ እንቅልፍ ማግኘት ነገሮችን በተሻለ ለማስታወስ እና ለማስኬድ ይረዳዎታል ፡፡

6. እንቅልፍ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል

ተመራማሪዎቹ እንዳሳዩት በማታ ጥቂት ሰዓታት የሚተኙ ሰዎች ከመጠን በላይ ወፍራም ወይም ከመጠን በላይ ውፍረት ያላቸው መሆናቸውን ነው ፡፡ የእንቅልፍ እጥረት በሰውነት የምግብ ፍላጎት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሆርሞኖችን መጠን ይጎዳል፡፡ ተመራማሪዎቹ እንዳሉት የምግብ ፍላጎትን የሚያስተካክሉ ሆርሞኖች ጋሬሊን እና ሌፕቲን በእንቅልፍ እጥረት ምክንያት ተስተጓጉለው ተገኝተዋል ፡፡ ክብደትን ለማቆየት ወይም ክብደት ለመቀነስ ከፈለጉ ፣ በመደበኛነት በቂ እንቅልፍ ማግኘት ሚናው ከፍተኛ መሆኑን አይርሱ።

7. ማቅለብ ብልጥ ያደርግልዎታል

በቀኑ ውስጥ አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ወይንም ናፕ መውሰድ ለአጠቃላይ ጤናዎ ጥሩ ሲሆን በተጨማሪም የበለጠ ምርታማ እንዲሆኑ አዕምሮዎትን የሚያድስ አማራጭ ነው ፡፡ ጥናቶችእንደሚያሳዩት ከሆነ በቀኑ ውስጥ አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ወይንም ናፕ የሚወስዱ ሰዎች የአዕምሮ ወይንም ኮግኒቲቭ ተግባር እና የ ስሜት መሻሻል ማሳየታቸውን ነው፡፡

8. እንቅልፍ የጭንቀት በሽታ አደጋዎን ይቀንሳል

ሴሮቶኒንን ጨምሮ እንቅልፍ በሰውነትዎ ውስጥ ያሉትን ብዙ ኬሚካሎች ይነካል። የ serotonin ጉድለት ያላቸው ሰዎች በጭንቀት በሽታ የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው። ትክክለኛውን የእንቅልፍ መጠን እያገኙ መሆኑን በማረጋገጥ ድብርትዎን ለመከላከል በየዕለቱ ከ 7 እስከ 9 ሰዓታት ያህል የዕንቅልፍ ጊዜ ይውሰዱ፡፡

9. እንቅልፍ ሰውነቱን በራሱ እንዲጠገን ይረዳል

እንቅልፍ ዘና የማለት ጊዜ ነው ፤ ሰውነታችን በቀኑ ጊዜ፣ በአልትራቫዮሌት ጨረሮች እና በሌሎች ጎጂ ነገሮች ምክንያት የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን ጠንክሮ የሚሠራበት ጊዜ ነው ፡፡ ተኝተው እያለ ሴሎችዎ የበለጠ ፕሮቲን ያመርታሉ ፡፡ እነዚህ የፕሮቲን ሞለኪውሎች የሰውነት ክፍሎችዎን በመገንባትና በማድስ ጉዳቱን ለመጠገን ያስችላቸዋል ፡፡

©በአቤል ታደሰ

ከመተኛታችን በፊት #Share እናርገው
መልካም አዳር
@Psychoet
እንደምን አመሻችሁ !

በተገቢው ዕድሜ የማግባት ጥቅሞች በሚል የተዘጋጀው የ 7 ደቂቃ video ክፍል 1 ቀርቧል ። ጉዳዩ ብዙ ያላገቡ / ለማግባት ያሰቡ ወጣቶችን ስለሚመለከት በሌላም ጊዜ በተለየ መልክ በውይይት እንቀጥለዋለን፡፡

መነሻ ፅሑፉ (በከበደ በከሬ©zepsychology) ሲሆን አንባቢው ደግሞ ምስጋና ዮሴፍ ነው፡፡

ዩቲዩብ ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ ።
https://youtu.be/p4mDYOGD8o4
2024/09/30 15:38:48
Back to Top
HTML Embed Code: