Telegram Web Link
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ግዜው ሳያልፍ እንንቃ!!

በአንድ ከተማ ውስጥ የሚኖር እንጨት ፈላጭ ነበር፡፡ ሆኖም ቋሚ የሆነ ስራ ስለሌለው ገቢው እየዋዠቀበት ለመኖር እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ፈጠረበት ስለሆነም ወደ አንድ የጣውላ መሰንጠቂያ ድርጅት በመሄድ ባለቤቱን ስራ እንዲቀጥረው ጠየቀው ኃላፊውም የስራ ፈላጊውን የሰውነት ፈርጣማነት እና የስራ ተነሳሽነቱን በማድነቅ ከሚሰራበት ደን ውስጥ የተወሰነ ቦታ በመከለል ዛፎችን የመቁረጥ ስራ ሰጠው፡፡

 በመጀመሪው ቀን 18 ዛፎችን ቆረጠ፤ በዚህ የተደሰተው አለቃም እጅግ በጣም ጥሩ ስራ እንደሰራና እንደሱ ዓይነት  ዛፍ ቆራጭ አይቶ እንደማያውቅ እንዲሁም  በዚሁ እንዲቀጥልበት አበረታታው፡፡ በአለቃው የማበረታቻ ቃላት የተነሳሳው ዛፍ ቆራጭም በሁለተኛው ቀን በበለጠ ተነሳሽነት ወደ ስራው መጣ ሆኖም ግን የቆረጠው ዛፍ 15 ነበር፤ በሶስተኛው ቀን ደግሞ 10 ዛፎችን ቆረጠ፡፡ ቀናት አልፈው ቀናት በተተኩ ቁጥር የሚቆርጠው የዛፍ ቁጥር እያነሰ እያነሰ እንደውም ከሁሉም ዛፍ ቆራጮች ዝቅተኛ የሆነ የዛፍ ቁጥር የሚቆርጠው እሱ ሆኖ አረፈው፡፡ አለቃውም ይህን የማያሻሽል ከሆነ ከስራው እንደሚያባርረው ነገረው በዚህ የተደናገጠው ዛፍ ቆራጭም የዕረፍት ሰዓቱን ጭምር በመሰዋት ቢሰራም ጠብ የሚል ነገር ጠፋ፤ ጥንካሬዬን አጥቻለው ሲልም ደመደመ፡፡  በመጨረሻም አለቃው መጥቶ ከስራው እንደተባረረ ነገረው፤ በሁኔታው ግራ የተጋባው ዛፍ ቆራጭም የተቻለውን ሁሉ ቢጥርም ምን የሚፈይደው ነገር ማጣቱን ምን እየተፈጠረ እንዳለ ግራ እንደገባው ነገረው፡፡ ሁኔታው የገባው አለቃም መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ መጥረቢያህን የሳልከው ብሎ ሲጠይቀው ዛፍ ቆራጩም መጥረቢያዬን ለመሳል ጊዜ አልነበረኝም አለው፡፡ ስለዚህ የችግሩ ምንጭ የነበረው የሰውየው ጥንካሬ ማጣትና የስራ ተነሳሽነት ሳይሆን የመጥረቢያው አለመሳል ነበር፡፡

ከላይ የተጻፈው ታሪክ አብዛኞቻችን የምናውቀው ታሪክ ነው ፡፡ ውድ የ ሳይኮሎጂ ፔጅ ቤተሰቦች #አሁን ያለንበት የ#COVID-19 #ወረርሽኝ ለመልካም ከተጠቀምንበት ከስራችን እርቀን መጥረቢያችንን እንድንስል የሚረዳ መልካም ጊዜ ሰቶናል ፡፡ እኛ ግን ከወረርሽኙ በኀላ ወደአዲሷ አለም ምን ይዘን ነው የምንቀላቀለው ?

በእርግጥ ሁላችን ጤናማና ደስተኛ ሁኖ መኖር የለት ተለት ፍላጎታችን ነው፡፡ ስለዚህ የምናስበውን ኑሮ ወደፊት ለመኖር እነዚህን #ጥቂት ቀናት አዕምሮና እና አካልን የማሳረፊያ ጊዜ እናድርጋቸው ፤ ከዚህ በፊት ለመስራት አስበን ጊዜ ያጠረንን ነገሮች አሁን እንስራ ፤ ይህን እንቁ ጊዜ ሁላችን የየራሳችንን "መጥረቢያ" የምንስልበት ጊዜ ይሁን ፡፡ ይቀጥላል...

በቤታችን ስንሆን ደግሞ ልንሰራቸው የምንችላቸው ደግሞ የሚገቡ ነገሮችን ከዚህ በፊት በመጠኑም ቢሆን ፅፌያለሁና አንብባችሁ ብተገብሩት መልካም ነገር ታገኙበታላችሁ ፡፡


መልካም ሳምንት !
ላልሰሙ ሰዎች #SHARE #ሼር
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ


በተለያዩ አማራጮች ያግኙን
በፌስቡክ : FB.COM/PSYCHOLOGYET
በቴሌግራም : T.ME/PSYCHOET
በዩቲዩብ : YOUTUBE.COM/THENAHUSENAI
GreenFire-May2020.pdf
1.3 MB
እንኳን ደስ አለን ! ወርሀዊዉ የMotion መጽሔት ፭ኛ ዕትም አስተማሪ ጽሑፎቹን ይዞ መቷል ።

ማህበራዊ ፈቀቅታ
STAY HOME 👈👉STAY SAFE
📌 የዕትሙ ዋና ጽሁፍ ነው። ያንብቡት

#Share
👇👇👇👇
@psychoet
# የሥራ ቦታ ውጥረትን ለመቀነስ የሚረዱ 4 መንገዶች
#Share

በሠራተኛ የሥራ ቦታ ተሳትፎ ላይ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል ውጥረት (ስትረስ) በዋነኝነት የጠቀሳል ፡፡ በጥናቶች መሠረት 25 % የሚሆኑ ሰራተኞች በጭንቀት ምክንያት በሥራ ላይ ውጤታማ መሆን ይቸግራቸዋል ፡፡ ይህም በአእምሮ ደህንነት እና በአጠቃላይ የንግድ ሥራ ስኬታማነት ላይ ሊኖረው የሚችለው ተፅእኖ ከፍተኛ ቢሆንም በስራ ቦታ ውስጥ የሚከሰተውን የጭንቀት (ስትረስ) ችግር ለመቅረፍ እርምጃዎችን ሲወሰዱ አይስተዋልም ። እንደ ሥራ አስኪያጅ ወይም የንግድ ሥራ ባለቤት ሠራተኞች ውጥረት ሲሰማቸው መንከባከቡ ለድርጅትዎ ወይንም ኩባንያዎን ስኬታማነት አስፈላጊ ነው፡፡ በሠራተኞችዎ በኩል የሚከሰተውን ጭንቀት ለመቋቋም ወይም ለመከላከል የሚረዱ ጥቂት ዘዴዎችን እናያለን ፡፡

#1 አስደሳች የስራ ስፍራን መፍጠር :

አብዛኛው የሰራተኛ ጊዜ የሚያልፈው በሥራ ቦታ ነው ፣ ስለሆነም ለሁሉም ሰው የሚደሰትበት አስደሳች ስፍራ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ በሥራ ቦታ ውስጥ እያንዳንዱን ነገር ወይንም ድርጊት ዝርዝር ፣ የቀለም ምርጫ እስከ ቢሮ ዕቃዎች ትናንሽ ነገሮችን ጨምሮ በጥንቃቄ መምረጥ ይገባል፡፡ እነዚህ ጥቃቅንና እና ትልልቅ የሚመስሉ ነገሮች በሠራተኛ ተሳትፎ ላይ ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ ፡፡ የቢሮ የቀለም ዐይነት ወይንም ምርጫ ማሻሻል ፣ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እፅዋትን መትከል ፤ አንዳንድ የምሳ እረፍት ላይ መዝናኛዎችን ማከል ሠራተኞች አዕምሮአቸውን ከሥራ ወደ ኋላ ለጥቂት ጊዜ እንዲያዝናኑ ሲረዳ ፤ የውጥረት መጠናቸውን እንዲቀንሱ ይረዳቸዋል፡፡

#2 የሥራ ቦታ ደህንነትን (ጤና) ማበረታታት

የግለሰቦችን ጭንቀትን ለማስታገስ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ማሳደግ በጣም ጥሩ ከሆኑት መንገዶች ውስጥ አንዱ ነው ፡፡ በተለይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፤ ሰራተኞች አዕምሮዓቸውን ከሥራ እንዲወጡ እና ስሜታቸውን እንዲያሻሽሉ ጥሩ መንገድ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ሰውነታችን ኃይልን የማቃጠል ስራውን ስለሚሰራ የደስታን ስሜት የሚያበረታቱ ኤንዶሮፊኖችን በመልቀቅ ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው ያድርጋል።

#3 ተለዋዋጭ ሥራን ማበረታታት

ሰራተኞች በችሎታቸው፣ በሙያቸው እና በራስ መተማመናቸው አማካይነት የሚቀጠሩት በተሰጣቸው ሰዓታት ውስጥ የሚጠብቁትን ዉጤት ማምጣት እንደሚችሉ በማመን ነው፡፡ አንድ ቢሮ ሠራተኞች ሥራቸውን ለማጠናቀቅ የሚያመቻቸው ቦታ ተደርጎ መታየት አለበት ፡፡ ስለዚህ ሥራቸውን በአኗኗር ዘይቤያቸው ዙሪያ ማካሄድ እንዲችሉ ተለዋዋጭ እና ርቀት ሳየገድባቸው ባሉበት እንዲሰሩ ያበረታቱ ፡፡ ሠራተኞችዎ ሥራቸውን በከፍተኛ ደረጃ እያከናወኑ እንደሆነ እስካመኑበት ድረስ ፣ መስሪያ ቤቱ ቢሮ ሚታጎሩበት ቦታ አንደሆነ ማሰብ የለባቸውም፡፡

#4 ለሰራተኛ እውቅናን መስጠት

በከፍተኛ ሠራተኛ ሁኔታዎች ውስጥ አንድ ሠራተኛ በጥሩ ሁኔታ እየሠራ ከሆነ አለመረጋጋት ወይንም የመጠራጥ ስሜት በሚፈጠርባቸው ሁኔታዎች ውስጥ እውቅናን ለሠራተኛዎት መስጠት የበለጠ ለመሻሻል እና በሠራተኞችዎ ላይ በራስ የመተማመን ስሜትን ለማጎልበት ይረዳል፡፡ ከበላይ ሃላፊዎች አውቅናን ማግኘት ለተቀጣሪው ከፍ ያለ ግምት እንዲሰማው ሲያደርግ በተጨማሪም አሁን ባለው ተግባራቸው ላይ ጥሩ አፈፃፀም እንዲያሳዩ ስለሚረዳቸው እጅግ ጠቃሚ ተግባር ነው ፡፡

© www.tg-me.com/wikihabesha
በሌለን ነገር ከማማረር ባለን ነገር ማመስገን ጤናማ ያደርጋል ፡፡

ዛሬ ከሰሞኑ ያለወትሮዬ 11:30 ተነሳሁ ፡፡ በእርግጥ የቀሰቀሰኝ አላም ሳይሆን የሰዎች የለቅሶ ድምፅ ነበር ፡፡ ጓረቤታችን አርፈው ነበር ፡፡ እናም ወደ ፈጣሪ እየጸለይኩ "ጌታዬ ሆይ ይቺን ቀን ከነጉድለቴ እንድኖርባት ትልቁን ሀብት ጤንነትን ስለሰጠኝ አመሰግናለሁ ፡፡ " አልኩ ፡፡

ሁልጊዜ ስንነሳ ፈጣሪ ስለሰጠን ቀን ፣ ሳምንት ፣ ወር ፣ አመት እሱን እናመስግን ፡፡ ሌላው ቢቀር የምንወዳቸው ፣ የምንሳሳላቸው ሰዎች አሁንም በሕይወት ስላሉ ስለነሱ ፈጣሪን እናመስግን ምክኒያቱም እነሱ ዛሬን በሕይወት ባይኖሩ ኑሮ የምንነሳው በሀዘን ነበር፡፡

መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ ፡፡
ሀሳቡን ለሌሎችም አጋሩና ፈጣሪን አንድ ላይ እናመስግን ፡፡
ሥነ ልቡና - Psychology
@psychoet
ሕይወትህ ወደ መጥፎ መንገድ እየሄደ እንደሆነ የምታቅበት 10 መንገዶች

ሁላችን በዚህ ምድር ላይ ያለ አላማ አልተፈጠርንም ፡፡ የፈጠረን ፈጣሪ በምድር ላይ እንድንሰራው የሚፈልገው ትልቅ ስራ አለ፡፡ ነገር ግን ከዚህ መንገድ ስንወጣ ወይም መጥፎ ነገሮች በሕይወታችን መከሰት ሲጀምሩ ተፈጥሮ ራሷ የተለያዩ መልዕክቶችን ትልክልናለች፡፡

ይህን ተፈጥሮ በራሷ ሕይወታችን ወደ መጥፎ መንገድ እየሄደ እንደሆነ በእነዚህ 10 መንገዶች ትጠቁመናለች፡፡ የ ሁለት ደቂቃ Videoውን ይከታተሉ፡፡

የዩቲዩብ ቻናላችን ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ

https://youtu.be/6Vg_Y8Hioh0
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «ሕይወትህ ወደ መጥፎ መንገድ እየሄደ እንደሆነ የምታቅበት 10 መንገዶች ሁላችን በዚህ ምድር ላይ ያለ አላማ አልተፈጠርንም ፡፡ የፈጠረን ፈጣሪ በምድር ላይ እንድንሰራው የሚፈልገው ትልቅ ስራ አለ፡፡ ነገር ግን ከዚህ መንገድ ስንወጣ ወይም መጥፎ ነገሮች በሕይወታችን መከሰት ሲጀምሩ ተፈጥሮ ራሷ የተለያዩ መልዕክቶችን ትልክልናለች፡፡ ይህን ተፈጥሮ በራሷ ሕይወታችን ወደ መጥፎ መንገድ እየሄደ እንደሆነ…»
#መልካም_የግንቦት_ወር ! #9
T.me/psychoet

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ የኮሮና ተያዢ ሰዎችን ዜና ሳይሆን አገግመው የሚወጡትን በብዛት የምንሰማበት ፣ ከፖለቲካ ሽኩቻ ወተን ወደ ልማትና ትብብር የምንገባበት ይሁንልን ፡፡

ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ በቴሌግራምና በዩቲዩብ ቻናል የምለቃቸው ትምህርቶች ሰኞ ፣ሮብ ፣ አርብ ማታ በቋሚነት ይቀጥላሉ ፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ በሺዎች የምትቆጠሩ የፔጁ ቤተሰቦች ዩቲዩባችንን ስለተቀላቀላችሁ አመሰግናለሁ ፡፡ እስካሁን ያልተቀላቀላችሁም ቶሎ ቤተሰብ ሁኑ youtube.com/thenahusenai

እስካሁን በዚህ ፔጅ የለጠፍኳቸውን ትምህርቶች በPDF አርጌ ማታ 2:00 ላይ POST አረጋለሁ ፡፡
T.ME/PSYCHOET

ፈጣሪ ደግሞ ለሰው ልጆች ሁሉ መልካም ዜናን ያሰማ! ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ ።
#እወዳችኀለሁ!
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
Psychology .pdf
465.9 KB
ሰላም እንደምን አላችሁ!

ላለፋት 20 ሳምንታት ያቀረብኩትን የሥነልቡና ትምህርት አቀናጅቼ አንድ ላይ አድርጌ አቅርቤያለሁ ፡፡

ብታነቡት ብዙ እውቀት የምታገኙበት ደግሞም በሕይወታችሁ እየተገበራችሁ የምትጠቀሙበት ነው፡፡ ሌሎችም እንዲያነቡት ባላችሁበት ግሩፕ #Share እንድታረጉና ለጓደኞቻችሁ እንድትልኩላቸው እጠይቃለሁ

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
@Psychoet
@Psychoet
ሕይወትህ ወደ መጥፎ መንገድ እየሄደ እንደሆነ የምታቅበት 10 መንገዶች

ሁላችን በዚህ ምድር ላይ ያለ አላማ አልተፈጠርንም ፡፡ የፈጠረን ፈጣሪ በምድር ላይ እንድንሰራው የሚፈልገው ትልቅ ስራ አለ፡፡ ነገር ግን ከዚህ መንገድ ስንወጣ ወይም መጥፎ ነገሮች በሕይወታችን መከሰት ሲጀምሩ ተፈጥሮ ራሷ የተለያዩ መልዕክቶችን ትልክልናለች፡፡

ይህን ተፈጥሮ በራሷ ሕይወታችን ወደ መጥፎ መንገድ እየሄደ እንደሆነ በእነዚህ 10 መንገዶች ትጠቁመናለች፡፡ የ ሁለት ደቂቃ Videoውን ይከታተሉ፡፡

የዩቲዩብ ቻናላችን ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ

https://youtu.be/6Vg_Y8Hioh0
አንድን የማንፈልገው የግል ባህሪ/አመለካከት ከመቀነሳችን በፊት ያ ባህሪ እንዳለብን ማረጋገጥ አለብን ፡፡
በዚህ ሳምንት ስለ የበታችነት ስሜት እናያለን ፡፡ በመጀመሪያ የበታችነት ስሜት ምልክቶች ከዛም መንስኤውንና መፍትሔውን እናያለን ፡፡

ይህ ቪዲዮ ስለ የበታችነት ስሜት ምልክቶች ማብራሪያ ይዞ መቷል https://youtu.be/4ZoDlu58wMI
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «አንድን የማንፈልገው የግል ባህሪ/አመለካከት ከመቀነሳችን በፊት ያ ባህሪ እንዳለብን ማረጋገጥ አለብን ፡፡ በዚህ ሳምንት ስለ የበታችነት ስሜት እናያለን ፡፡ በመጀመሪያ የበታችነት ስሜት ምልክቶች ከዛም መንስኤውንና መፍትሔውን እናያለን ፡፡ ይህ ቪዲዮ ስለ የበታችነት ስሜት ምልክቶች ማብራሪያ ይዞ መቷል https://youtu.be/4ZoDlu58wMI»
የበታችነት ስሜት 6 ምልክቶች: 6 Signs of Inferiority Complex
Psychology ሳይኮሎጂ
06:39, 6.23 MB
የበታችነት ስሜት 6 ምልክቶች

በዩቲዩብ መከታተል ያልቻላችሁ በ Audio እንድታዳምጡት እጋብዛለሁ፡፡
መልካም ምሽት!
@psychoet
#ይቻላል
JOIN TELEGRAM www.tg-me.com/psychoet

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
©ZePsychology

መልካም ቀን!
#Share_it
ሰላም ፥
ዛሬ ጠዋት ግድ ለሆነ ለአንድ ስራ ከቤት ወጥቼ ባየሁት ነገር በጣም ነው የተደሰትኩት ፡፡ በመንገድ ላይ ከ 90% በላይ የሚሆነው ሰው Facemask አርጎ ነበር የሚጓዘው ፡፡ እርግጠኛ ነኝ ቀሪው 10% ደግሞ ባያረግም በቦርሳው ፣ በኀላ ኪሱ ከቶት የሚጓዝ ነው ፡፡

እና ግን አሁን ለማውራት የምፈልገው ስላላረጉት 10% ሳይሆን ስላረጉት 90% ሰዎች ነው ፡፡ ምክንያቱም 90% ጥሩ እያለ ስለ 10% ስህተት ብቻ ማሰብና ማውራት አንዱ የአሉታዊ አመለካከት መገለጫ ነው but not always (ይህ ማለት ሁሌ ስለ ስህተት አታሳቡ ማለት አይደለም) ፡፡ እናም ይህ 90% ሰው እያረገ ያለው ጥንቃቄ በጣም የሚያስደስት ነው ፡፡ ይህን ቻናል የምትከታተሉ የሀገሬ ልጆች ፥በተለያየ የሀገሪቱ ጥግ የምትኖሩ እንዲሁም በአፍሪካ ፣ በአውሮፓ ፣ በአሜሪካና በኤዢያ የምትገኙ ይህ ወረርሽኝ እስኪያልፍ ድረሰ ከ 90% ሰው መካከል ሁናችሁ እንድትቆዩ እጠይቃለሁ ፡፡

ግን አንድ ወሳኝ ሀሳብ ነግሬያችሁ ላጠናቅቅ ፡፡ በአሜሪካ በተለይም በኒውዮርክ በተጠናው ጥናት እንደተገለፀው ፦ ወረርሽኙ ውጭ ከሚወጡና ስራ ከሚሰሩ ሰዎች ይልቅ በቤት ባሉ ሰዎች ላይ የበለጠ ተስፋፊነት እንዳለው መረጃዎች ጠቁመዋል ፡፡ ስለዚህ ጥንቃቄያችን ከቤት ውጭ ብቻ ሳይሆን እቤት ውስጥም ስንሆን የበለጠ እንጠንቀቅ ፡፡ ምክንያቱም ቫይረሱ እግር ኑሮት እቤታችን ባይመጣም እግር ያላቸው ሰዎች ግን ያለንበት ቦታ ይዘው ድረስ ሊያመጡ ይችላሉ ፡፡

ፈጣሪ ሁላችንን ይጠብቀን እኛም እንጠንቀቅ ፡፡
መልካም ቀን ይሁንላችሁ
እወዳችኀለው፡፡
2024/09/30 17:24:15
Back to Top
HTML Embed Code: