Telegram Web Link
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «እንደምን ዋላችሁ የሥነልቡና ፔጅ ቤተሰቦች! ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በጽሑፍ ከምንለጥፋቸው ትምህርቶች በተጨማሪ የተለያዩ የስነልቡና ትምህርቶችን ፣ አነቃቂ ንግግሮችን ፣ የሕይወት ክህሎት ስልጠናዎችን በYouTube ቻናላችን መለጠፍ እንጀምራለን ፡፡ ስለዚህ ካሁኑ ቻናላችንን Subscribe እንድታደርጉና ጓደኞቻችሁን እንድትጋብዙ እንጠይቃለን ፡፡ Subscribe Channel : youtube.com/t…»
#ክፍል_11
(በአሸናፊ ካሳሁን) #SHARE
#በቤተሰብ አባል ውስጥ የሥነ-ልቦና መታወክ ሲያጋጥም ምን እናድርግ?

የስነ-ልቦና ወይም የስነ-ባህሪ መታወክ በሀገራችን ትኩረት ካልተሰጠባቸውና የህክምና ዘዴው (psychotherapy) ካልተስፋፋባቸው ማኅበራዊ ችግሮች ውስጥ ዋንኞቹ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በባህላዊና በሃይማኖታዊ ድጋፎች ማኅበረሰባችን ከዚህ ችግር ጋር እየተጋፈጠ ቢሆንም፣ ዋናው ጫና የዚህ ችግር ተጠቂ ከሆኑ የቤተሰብ አባላት ላይ ነው፤ምክኒያቱም እንደሰለጠነው ዓለም የህክምና ፤ ድጋፍና እንክብካቤ ሰጪ  ቦታዎች ስለሌሉን ነው፡፡ ይህን ችግር ለማቃለል እየተንቀሳቀሱ ካሉት አገር በቀል ድርጅቶች ውስጥ አንዱ መቄዶኒያ ሲሆን በዚህ አጋጣሚ ስለሚሰሩት ስራ ያለኝን አድናቆት ሳልጠቅስ አላልፍም፡፡እናንተም የተቻላችሁን ድጋፍ አድርጉላቸው፡፡

ከዚህ በመቀጠል የስነ-ልቡና መታወክ ችግር ያጋጠማቸው የቤተሰብ አባላት ይህን ተግዳሮት ለመቋቋም ምን ማድረግ አለባቸው የሚለውን በዶ/ር ቤሪ ያኮብስ መጽሐፍ መነሻነት ይጠቅማሉ ያልኳቸውን ነጥቦች አነሳለሁ፡፡ መልካም የንባብ ጊዜ!
_______________________________________
#ለበሽታው_ያለንን_ግንዛቤ_ማሳደግ ፡-

ስለታመመብን ሰው የስነ-ልቡና መታወክ አይነት፣ መንስኤ፣ ምልክቶች፣ ስለሚያባብሱ ሁኔታዎችና ነገሮች እራስን ማስተማር፡፡ ስለታመመው ሰው የስነ-ልቡና ወይም የስነ-ባህሪ ችግር የተሳሳተ መረጃ ካለን ወይም ስለ ምልክቶቹና ስለሚያባብሱ ጉዳዮች ዝቅተኛ ግንዛቤ ካለን ግለሰቡንና ቤተሰቡን በአጠቃላይ ሊጎዳ የሚችል ተግባር ልንፈጽም እንችላለን፡፡

#ለምሳሌ እስኪዞፍሬኒያ (Schizophrenia) ያለባቸው ግለሰቦች ስለሚታያቸው አስፈሪ ግን በገሃዱ አለም የለለ ምስል (hallucination) ምንም ግንዛቤ ከሌለን፤ በተገቢው ተጠቂዎችን ላንረዳቸውና አግባብነት ያለው ምላሽ ላንሰጥ እንችላለን፡፡

#በለሌላ ምሳሌ በከፍተኛ ድባቴ (Depression) ውስጥ ያሉ ግለሰቦች አጥብቀው እራስን ስለማጥፋት (suicidal ideation) ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ ይህ ሃሳብ በዝርዝር እራሳቸውን እንዴት፣በምን፣የትና እራሳቸውን እነደሚያጠፉና የመሳሰሉትን በዝርዝር ማሰላሰልና ሙከራ ማድረግን ሊያካትት ይችላል፡፡ ስለዚህ እድብታ ወደ እንደዚህ አይነቱ የስነ-ልቡናና የስነ-ባህሪ ዝንባሌ ሊወስድ እንደሚችል በቂ እውቀት ከሌለን፤ በዚህ የሚሰቃይ ቤተሰባችን፣ጓደኛችን፣ፍቅረኛችንን እንዲሁም የስራ ባልደረባችንን በተገቢው መንገድ መርዳት አንችልም፡፡ አንዳንዴም ለምን ስለማይጠቅም ነገር ታስባለህ እና የመሳሰሉትን ትችቶች በመስጠት ግለሰቡን እንኮንናለን፡፡ ስለሆነም በግለሰቡ ላይ የምናያቸው እንግዳ ባህሪያትና አስተሳሰቦች ከግለሰቡ ቁጥጥር ውጭ ስለመሆናቸው መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ስለዚህ ስለ ግለሰቡ የስነ-ልቡና ችግር ያለን ግንዛቤ ለግለሰቡ ለምንሰተጠው እርደታ፣ግለሰቡን የምንረዳበትን እይታ፣እንዲሁም ለራሳችን ደህንነት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ምክኒያቱም የቤተሰብ አካል ጓደኛ ወይም ፍቀረኛ የስነ-ልቡና ችግር ሲያጋጥም የኛ ደህንነት ላይም ተጽዕኖ ስለሚያደርስ፡፡

➋ትክክለኛ የመረጃ ምንጮችን ማፈላለግ፡-

ስለ ግለሰቡ የስነ ልቡና ችግር ሳይንሳዊ ግንዛቤ ለመጨበት ትክክለኛ ምንጮችን መከተል ይገባናል፡፡ ምንም እንኳን በሀገራችን ቋንቋንዎች የተጻፉ ሳይንሳዊ መሰረት ያላቸው መጽሀፍት ባይኖሩም፣ የእንግሊዚኛ ችሎታ ካለን በእንግሊዚኛ የተጻፉ ሳይንሳዊ መጽኃፍትን ወይም ታእማኝነት ያለቸውን ድህረ-ገጾች መጠቀም፡፡ እንዲህ ስል በእንግሊዚኛ ስለተጻፈ ብቻ ጠቃሚ ነው ማለቴ ሳይሆን እነደ ዕድል ሆኖ ሳይንሱ በምዕራቡ አለም ስለተስፋፋ ብዙ ሳይነሳዊ የሆኑ መጽሀፍት በእንግሊዚኛ ቋንቋ ስለተጻፉ ነው፡፡ ስለዚህ የሀገራችን ሳይኮሎጂስቶችና ሳይካቲሪስቶች ብዙ የቤት ስራ አለብን፡፡ ምርምር ከመመረቂያ ጽሁፍ በላይ መሆን አለበት፡፡ (እዚህ ጋር ላቋርጣችሁና… የኛ አላማ ይህን ክፍት መሙላት  የሚችል በስነ-ልቡና ችግሮችን፣ ትዳርን፣ ፍቅር፣ የልጅ አስተዳደግን፣ ትምህርት ነክና ለሌች የስነ-ልቡና ጉዳዮችን የሚዳስስ ሳይንሳዊ መሰረት ያለቸውን መረጃዎች ለናንተና በውጭ ሀገር ላሉ አዳማጭ ላጡ ወገኖቻችን አማራጭ ማቅረብ ነው፡፡ ስለዚህ ለወደፊት ስለተለያዩ የስነ-ልቡና ችግሮች መንስኤ፣ምልክት፣የመጀመሪያ እርዳታ እንዲሁም ዕርዳታ እንዴት ማግኘት እነደምትችሉ የተደራጀ መረጃ በዌብሳይታችን እናቀርባልን)፡፡ወደ ወናው ሃሳብ ስመለስ ስለስነ-ልቡና ችግሮችና መፍትሄዎች የተነገሩ ወይም የተጻፉ ነገሮች ሁሉ ትክክል ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ በጋዜጦችና መጽሄቶች የሚነገሩ ነገሮችን በባለሙያተኞች የሚነገሩ ከሆኑ እንደ ግብአት መውሰድ ይቻላል፡፡ በጥቅሉ ሳይንሳዊ ዳራ ያለቸውን ታማኝ ምንጮችን ተጠቀሙ ምክሬ ነው፡፡

➌የእርዳታ ምንጮችን መፈለግ፡-

የስነ-ልቡና ችግርን በሀገራችን ካሉ ሌሎች በሽታዎች ለየት የሚያደርገው የበሽታው ተጠቂዎች ላይ የሚደርሰው አድሎና መገለል አንዱ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ምክኒያት ከማህበረሰቡ ከሚገኙ ድጋፍ ይልቅ አድሎው የሚያመዝንበት ሁኔታ አለ ምንም እንኳ የተለያዩ የሀይማኖት ተቃማት የራሳቸውን ድጋፍና እንክብካቤ ለተጠቂዎች የሚያደርጉ ቢኖሩም፡፡ በዚህም ምክኒያት የስነ-ልቡና ችግር ያለባቸው ሰዎች ስለ በሽታቸው ከሌሎች ግለሰቦች የመወያየትና ድጋፍ የማግኘት እድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ እናም የስነ-ልቡና ችግር ያለባቸው ግለሶቦች ቤተሰቦች ተመሳሳይ ችግር ያለባቸው ሌሎች ቤተሰቦች ጋር መወያየትና ሀሳብ መለዋወጥ ልምድ ከማካፈል በዘለለ ስለሚደርስባቸው ተግዳሮቶች ማውራታቸው የተወሰነም ቢሆን ስለጉዳዩ የሚሰማቸው ጭንቀት ቅልል ሊልላቸው ይችላል፡፡ ይህ እንግዲህ ፈረንጆቹ support group የሚሉት አይነት ነገር ነው፡፡ እዚህ ጋር ማንኛቸውም ሊጠቅሙ የሚችሉ ባህላዊና፣ ሀይማኖታዊ፣መንግስታዊ እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ከስነ-ልቡና ችግር ጋር በተገኘ እርዳታ የሚሰጡ ተቋማትን ማፈላለግ፡፡

........ ቀጣዩ ያሁኑ #ማክሰኞ በልዩ አቀራረብ ይቀጥላል፡፡ ከዚህ ጋር በተገናኘ ማንኛውም ጥያቄ ያላችሁ #COMMENT ላይ ፃፉልኝ ? ማክሰኞ ቀጣዩን ከጥያቄያችሁ መልስ ጋር አቀርባለሁ ፡፡

______________________________________

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉

ቴሌግራም ሊንክ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet

ምንጭ ፦ Emotional survival guide for care givers ከሚለው የዶ/ር ቤሪ ያኮብስ መጽኃፍ መነሻነት የቀረቡ

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
#የሳምንት_ሰው_ይበለን !

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊
አለማችን በታሪኳ በብዙ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች መካከል አልፋለች ፡፡ በእነዚህ ሁሉ ችግሮች ብዙዎች የሚወዱትን ሰው አጥተዋል ፤ ሕይወትም በብዙ ጀርባ ሰጥታቸው አልፋለች፡፡

በዘመናችን የተከሰተው የወረርሽኝ ችግርም ባለፉት ቀናት አያሌ ችግር አስከስቷል ፤ እያስከተለም ይገኛል ። ይሁን እንጂ ወረርሽኙ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ መጥፋቱ አልያም በሰው ልጅ ቁጥጥ ስር መዋሉ አይቀርም ፡፡ ግን ይህ የመጣው የወረርሽኝ እሳት ከምድራችን ብዙ የሚያቃጥላቸው ገለባዎች ደግሞም አጥርቶ የሚያወጣቸው ወርቅ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ስለዚህ በዚህ ታሪክ እየተጻፈበት ባለበት ጊዜ እንደገለባው የምንጠፋ ሳንሆን እቤታችን ተቀምጠን እንደ ወርቁ የምንጠራ እንሁን ፡፡ #STAY_HOME

ለመላ የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የሆሣዕና በዓል እመኛለሁ፡፡ " ሆሣዕና - አቤቱ አኹን አድን " ብለን ፀሎታችንንና ልመናችንን ደግሞ ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን ለአለም ሁሉ ህዝቦች እናድርገው ፡፡ ሌሎችን በሚያስፈልጋቸው ስንደግፍ ካሜራችንንና ኩራታችንን ደግሞ ከቤት እናስቀምጥ ፡፡
በተረፈ የዛሬ አመት ደግሞ ፈጣሪ ዕድሜን ጨምሮልን ይንን ቀን ወደኋላ በበጎ ለማስታወስ ያብቃን ፡፡
Share|ሼር
@psychoet
#የብራዚሉ_ባለሀብት_ከሚሊዮን_ዶላር_መኪናዬ_ጋር_ቅበሩኝ_አሉ !

በብራዚል ታዋቂዉና ባለሀብቱ ሰዉዬ ከሞትኩ በኀላ በሚሊዮን ዶላር የገዛሁትን ቅንጡ መኪና አብራችሁ ቅበሩልኝ ከሞትኩ በኀላ ልነዳዉ እችላለሁ ሲል በመገኛ ብዙሀን ገልፆ ህዝቦቹን ጉድ አሰኝቶል ፡፡ በዚህም ሳቢያ ከተለያዩ መገናኛ ብዙኀን እንዲሁም ማህበራዊ ሚዲያዋች የተለያዩ የትችት ሀሳቦችን ተቀብሏል ፡፡ አብዛኛዉ ሰዉም ስለ ባለሀብቱ ስግብግብነትና ራስ ወዳድነት በመተቸት ፅፏል ፣ አዉርቷል ፡፡ ለምን ለእርዳታ ተቋማት አይሰጥም ? ስንት በሕይወት ያሉ ሰዋች እኮ ይጠቀሙበታል ተብሏል ፡፡

ባለሀብቱም ለቀናት የሰዉን ሁሉ ሀሳብና አስተያየት ካዳመጠና ከተቀበላ በኀላ በመገናኛ ብዙኀን ቀርቦ ይህን ንግግር አቀረበ ፡፡ "ሰዋች ጥሬና ግሬ በላቤ በሚሊዮን ዶላር የገዛሁትን መኪና ለምን ትቀብረዋለህ ብለዉ ይተቹኛል ፤ ይሁን እንጂ የሰዉ ልጅ ሁሉ ከዚህ የበለጠ ዉድ ዋጋ ያለዉ ንብረት ሲሞት አብረዉ ያስቀብራል ፡፡ ለዛዉም ጥረዉ ግረዉ ያገኙትን ሳይሆን በነፃ የተሰጣቸዉን ሀብት ነዉ ፡፡ ብዙ ሰዉ ልቡን ፣ ኩላሊቱን ፣ ሳንባዉን ፣ አይኖቹን ከፈጣሪ በነፃ ተቀብሎ ሳለ እነዚህን ብዙ ሚሊዮን የሚያወጡ ንብረቶች ይዞ ይቀበራል ፡፡ ይሄ እንደዉም ትልቅ ስግብግብነት ነዉ ምክንያቱም እኛ ስንሞት ብዙ ሰዋች የተለያዩ የሰዉነት ክፍሎችን በንቅለ ተከላ ለማግኘትነ በሕይወት ለመቆየት ሲጣጣሩ ሲለምኑ እናያለን ይሁን እንጂ ብዙ ሰዉ ይህን ዉድ ዋጋ ይዞ ይቀበራል ፡፡ ስለዚህ ከዉድ እቃዋቻችን በላይ እኛ እራሳችን ዉድ መሆናችንን እንገንዘብ ፡፡ ለሰዉ ልጅ በምድር ላይ ክቡሩ ነገር ያለዉ ሀብት ፣ ዝና ሳይሆን ራሱ ማንነቱ ነዉ ፡፡

በዩቲዩብ የምንለቃቸውን የሳይኮሎጂ ትምህርቶች ለማግኘት http://youtube.com/thenahusenaipsychology
ደስታ የሚለካው ባለን ገንዘብ ሳይሆን በዙሩያችን ባሉ ደጋግ ሰዎች ነው ፡፡
@Psychoet
የኑሮ ቀውስን ማሸነፍ |Overcoming Crisis|
በዶክተር ማይልስ ሞንሮ ተጽፎ በአማረኛ ተተርጉሞ የቀረበ

በአስቸጋሪ ጊዜ የማደግ ሚስጥር
📌ሕይወት ሲከፋ እንዴት እናመልጣለን?
📌በሌላ ሰው ስህተት ስንወድቅ ምን እናረጋለን?
📌በተለያዩ የሕይወት ቀውሶች ውስጥ ስንገባ እንዴት እናመልጣለን?

አስተማሪ የሰስነልቦናዊ ምክር ስለሆነ ጊዜ ሰታችሁ አድምጡት!

https://youtu.be/B7Q1GThhups
ለለውጥ መነሳሳት

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

 8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

 10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡

#Share #Like
www.tg-me.com/psychoet

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
©Zepsychology
የኑሮ ቀውስን ማሸነፍ |Overcoming Crisis|
በዶክተር ማይልስ ሞንሮ ተጽፎ በአማረኛ ተተርጉሞ የቀረበ

በአስቸጋሪ ጊዜ የማደግ ሚስጥር
📌ሕይወት ሲከፋ እንዴት እናመልጣለን?
📌በሌላ ሰው ስህተት ስንወድቅ ምን እናረጋለን?
📌በተለያዩ የሕይወት ቀውሶች ውስጥ ስንገባ እንዴት እናመልጣለን?

አስተማሪ የሰስነልቦናዊ ምክር ስለሆነ ጊዜ ሰታችሁ አድምጡት!
ክፍል 1 | Part 1
https://youtu.be/B7Q1GThhups

ክፍል 2 | Part 2
https://youtu.be/YmVEApdaeg8

ክፍል 3 (የመጨረሻው) | Part 3 ( Last )
https://youtu.be/fo3708Pyi5o
#ክፍል_15
#ሶስቱ_የስብዕና/ማንነት_አካላት
www.tg-me.com/psychoet
(በአቤል ታደሰ እና ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

#ኢድ(id)፣
#ኢጎ(Ego) እና
#ሱፐር-ኢጎ(Super ego)

በታዋቂው ሲግመንድ ፍሩድ የስነ-ልቦና ጽንሰ-ሀሳብ The Psychoanalytic Theory መሠረት የሰዎች ስብዕና ውስብስብ እና ከአንድ በላይ በሆኑ ክፍሎች ነው፡፡

እነዚህ ሦስቱ የስብዕና ወይንም የማንነት አካላት ኢድ(id)፣ ኢጎ(Ego) እና ሱፐር-ኢጎ(Super ego) ተብለው ሲጠሩ ውስብስብ የሆነውን የሰዎች ባህሪ ለመፍጠር አብረው ይሰራሉ ​​፡፡ ሦስቱም የስብዕና አካላት በእያንዳንዱ ግለሰብ ላይ በተለያየ መልኩ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ፡፡

በፍሩድ ጽንሰ-ሀሳብ መሠረት የስብዕናዎ የተወሰኑ ክፍሎች በመሰረታዊ ፍላጎቶችዎ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ግፊት ሲያደርጉ ሌሎች የስብዕናዎ ክፍሎች ደግሞ እነዚህን ፍላጎቶች ወይም ምኞቶች ለመግታት እና ከእውነተኛ ፍላጎቶችዎ ጋር እንዲስማሙ ለማድረግ ይጥራሉ።

እያንዳንዳቸው እንዴት በተናጥል እንደሚሠሩ እና እንዴት እንደሚነጋገሩ እንመልከት ፡፡

#ኢድ(id)

ከተወለደንበት ጊዜ ጀምሮ የነበረ ብቸኛው የስብዕናችን አካል ሲሆን፡፡ይህ የስብዕናችን አካል ሙሉ ለሙሉ የማይታወቅ እና በደመ ነፍስ የሚመራ ባህሪያትን አካቷል ፡፡ ኢድ(id) ሁሉንም ፍላጎቶች ወዲያውኑ ለማሟላት ከሚሠራው የሰውነት የመደሰት መርህ የሚመነጭ ነው፡፡እነዚህ ፍላጎቶች ወዲያውኑ ካልተሟሉ የስብዕና ውጥረት ይፈጠራል ፡፡
ለምሳሌ ፣ የረሀብ ወይም የጥማት ፍላጎት ለመብላት ወይም ለመጠጣት አፋጣኝ ሙከራን እንድናደረግ ይገፋፋናል : ነገር ግን እነዚህን ፍላጎቶች ወዲያውኑ ማሟላት ሁልጊዜ ተጨባጭ እና የሚቻል አይደለም ፡፡ ይህ የሰውነት የመደሰት መርህ በሙሉ የሚገዛን ከሆነ ፣ ሁልጊዜ የራሳችንን ፍላጎቶች ለማርካት ስንኖር አንገኛለን፡፡
እንደ ፍሩድ ገለፃ ኢድ(id) የሚፈልገውን ፍላጎትን ለማርካት የአእምሮ ምስል በመፍጠርና የመጀመሪያ ደረጃ(ስጋዊ) ስሜትን በመጠቀም የተፈጠረውን ውጥረት ለመፍታት ይሞክራል ፡፡ ምንም እንኳን ሰዎች ውሎ አድሮ የኢድን(id) ደመ- ነፍሳዊ ፍላጎት መቆጣጠርን ቢማሩም ፣ ይህ የባህሪይ አካል በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ተመሳሳይ ሆኖ ይኖራል፡፡

#ኢጎ(Ego)

ራስን ከፍ ከፍ በማድረግ ከእውነታው ወይም ከገሀዱ አለም ጋር ለመገናኘት የሚየግዘን የስብዕና ክፍል ሲሆን እንደ ፍሩድ ገለጻ ኢጎ(Ego) ከ ኢድ(id) የሚዳብር ሲሆን የኢድ(id) ግፊቶች በእውነተኛው ዓለም ተቀባይነት ባለው መልኩ እንዲገለፁ ያደርጋል ፡፡
ኢጎ የሚሠራው በእውነተኛው መርህ ላይ በመመርኮዝ ነው ፣ ስለዚህ የኢድ(id) ፍላጎቶችን በተጨባጭና በማህበራዊ እይታ ተገቢው በሆነ መንገድ ለማርካት ይጥራል ፡፡

ለምሳሌ ፣ በሥራ ቦታ ረዥም ስብሰባ ላይ ተቀምጠው ቆዩ እንበል፡፡ ስብሰባው እየቀጠለ ሲሄድ ረሀብዎ እየጨመረ ሲሄድ ይሰማዎታል፡፡ በዚህ ጊዜ ኢድ(id) ከመቀመጫዎ ላይ እንዲወጡ እና ለምግብ እንዲወጡ ሲገፋፋዎት ኢጎ(Ego) በጸጥታ ስብሰባው እስኪያበቃ ድረስ እንዲቀመጡ በተቃራኒው ይገፋፋዎታል፡፡

#ሱፐር-ኢጎ

የመጨረሻው የሰዎች ስብዕና ክፍል ሱፐር-ኢጎ(Superego) ነው። ሱፐር-ኢጎ(Superego) ከወላጆችና ከማህበረሰብ የምናገኛቸው፡ በውስጣችን የተቀመጡ የሥነ-ምግባር መርህና አመለካከቶችን የሚይዝ የስብዕና ክፍል ሲሆን፡፡ ሱፐር-ኢጎ ውሳኔና መመሪያዎችን ይሰጣል ፡፡ ሱፐር-ኢጎ(Super ego) ባህርያችንን ፍጹም እና ስልጡን ለማሳደግ ይሠራል።

እንደ ፍሩድ ገለጻ ፣ ለጤነኛ ስብዕና ቁልፍ የሆነው ነገር በ ኢድ(id)፣ ኢጎ(Ego) እና ሱፐር-ኢጎ(Super ego) መካከል ያለው ሚዛናዊ መስተጋብር ነው ፡፡

በዩቲዩብ የምንለቃቸውን ትምህርቶች ለማግኘት ቻናላችንን Subscribe አድርጉ youtube.com/thenahusenaipsychology
❖_____________________________❖
Source:- From Personality Psychology books & verywellmind (web)

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን!
እወዳችኅለሁ
❖__________________________________❖

ስለ ሳይኮሎጂ የበለጠ ለማወቅ ፔጁን ይከታተሉ ለወዳጆችዎ ያጋሩ

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
ስራውን አይታችሁ የመረጣችሁት አመሰግናለሁ ፡፡
2ኛ ደረጃን አግኝቷል!
እንኳን ደስ አለህ አዲስ
አንድ ሀብታም ሰው በመስኮቱን ተመለከተና አንድ ድሃ ሰው አንድ ነገር ከቆሻሻ መጣያው ውስጥ ሲመርጥ አየ ...እርሱም እንዲህ አለ "ተመስገን አምላኬ ድሀ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
ድሃው ሰው ዘወር ብሎ ተመለከተና ራቁቱን በጎዳና የሚራመድ ሰው አየ ... እርሱም እንዲህ አለ "ተመስገን አምላኬ እንኳን እንደዚህ ሰዉዬ አልሆንኩ አለ"።
:
ራቁቱን በጎዳና የሚራመድ ሰውየ ወደ ፊት ተመለከተ እና አንድ አምቡላንስ አየ አምቡላሱን ላይ በሕመም ምክንያት የሚሰቃይና የሚያለቅስ በሽተኛ አየ... እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ በሽተኛ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
ከዚያም የታመመው ሰውየ ሆስፒታል ሲደርስ የሞተን ሰው ተመለከተ ... እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ እንኳ አልሞትኩኝ ምክንያቱም የሞተ ሰው ፈጣሪን አያመሰግንምና አለ"።
:
ዛሬ ስለ ሁሉም የፈጣሪን በረከቶች እና ምሕረት ለምን አናመሰግንም? ከሌለን ነገር እኮ ያለን በእጅጉ ይበልጣል ፡፡
:
* # ሕይወት * # ምንድን_ነው ?
ህይወት በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብህ:
* 1. መቃበር *
* 2. ሆስፒታል *
* 3. እስር ቤት *
:
በመቃብር ቦታ ሕይወት ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ትገነዘባለህ።
:
በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ ትገነዘባለህ።
:
በእስር ቤት ነፃነት በጣም ውድ ነገር እንደሆነ ትገነዘባለህ።
:
የዛሬ የምንሄደው መንገድ የነገ የሕይወታችን መሰረት ነው።

ስለዚህ ትሁት እና አመስጋኝ እንሁን። ስንት ቤተሰቦቻችን ፣ ጓደኞቻችን ዛሬ በሕይወት የሉም እኛ ግን በፈጣሪ ፈቃድ ጊዜያችንን እየጠበቅን በሕይወት መቆየት ችለናል ፡፡ ከሞትን በኀላ ደግሞ በዚህች አለም በሰወች ዘንድ የሚቀርልን ትዉስታ ስራችን ከተጨመረ ደግሞ ፎቶአችን ነዉ ፡፡ ስለዚህ ለሰዋች ደግሞ ሁል ጊዜ መልካም ነገር ሰሪ እንሁን ፡፡ በተጨማሪ ሁሌ አመስጋኝ እንሁን ሌላዉ ቢቀር ይህን ፅሁፍ በማንበባችን አምላክን እናመስግን ምክንያቱም ብዙ ሰዋች
1.ማንበብ ስለማይችሉ አያነቡትም
2.ይህን መልዕክት ስላልደረሳቸዉ አያነቡትም
ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪያችን የተመሰገነ ይሁን።
መልካም ምሽት

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
#Share if you really like it
@psychoet
እንደምን አመሻችሁ ከቤታችሁ ሳትወጡ ለምትውሉና ለምታድሩ?

እቤት በመቀመጣችሁ በሕይወታችሁ ምን ተማራችሁ ወይስ ሰልችቷችኀል?

📌ያው Telegram ላይ comment ስለማይቻል fb.com/psychologyet ላይ መታችሁ ሀሳባችሁን አካፍሉኝ
እንደምን አላችሁ የፔጁ ቤተሰቦች!

ዛሬ ለሁላችሁም በተለይ ወጣት ለሆናችሁና በትምህርት ፣ በቢዝነስና በስራ ፈጠራ ለተሰማራችሁ በሙሉ መልካም ዜና ይዤ መጥቻለሁ ፡፡

#Africa_118 ከ Google Digital skill program in Africa ጋር በመተባበር #ከ100_በለይ #ነፃ #Online #ትምህርት ለአፍሪካውያን አዘጋጅቷል


በመሆኑም መረጃ ለማግኘትና ትምህርቶቹን በቤትዋ ለመከታተል @info4digitalskill የቴሌግራም ግሩፕ #join በማረግ ወይንም 0923787201 በመደወል ሙሉ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ ፡፡


ቀጥታ ወደ ትምህርቱ ለመግባት ደግሞ ከታች ያለውን #Link በመጫን መጀመር ትችላላችሁ

https://rebrand.ly/GDSA-ET-2
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «እንደምን አላችሁ የፔጁ ቤተሰቦች! ዛሬ ለሁላችሁም በተለይ ወጣት ለሆናችሁና በትምህርት ፣ በቢዝነስና በስራ ፈጠራ ለተሰማራችሁ በሙሉ መልካም ዜና ይዤ መጥቻለሁ ፡፡ #Africa_118 ከ Google Digital skill program in Africa ጋር በመተባበር #ከ100_በለይ #ነፃ #Online #ትምህርት ለአፍሪካውያን አዘጋጅቷል በመሆኑም መረጃ ለማግኘትና ትምህርቶቹን በቤትዋ ለመከታተል @…»
2024/09/30 17:22:59
Back to Top
HTML Embed Code: