Telegram Web Link
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#ክፍል_20
✿ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጊዜ የአእምሮ ጤናን ለመጠበቅ ማረግ ያለብን ነገሮች✿
www.tg-me.com/psychoet

በሰው ልጆች ታሪክ መሀከል እንደዚህ አይነት ወረርሽኞች ሲከሰቱ በሁሉም ዘንድ ፍርሀት ፣ መሸበር መከሰት ያለና የሚጠበቅ ትክክለኛ የሰው ሁሉ ምላሽ ነው ፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጁ ሁሉ የሞት ፍርሀት አልያም የሚወደውን ሰው በሞት የማጣት ተፈጥሮአዊ ፍርሀት አለበት ፡፡ ስለዚህ በእንደዚህ አይነት ወቅቶች የምናስባቸው አሉታዊ ሀሳቦች የአይሞሮአችንን ጤና ሊያውኩ ይችላሉ ፡፡ ይህም በሕይወታችን ኮሮና ቫይረስ ከሚያስከትለው ጉዳት በላይ ጠባሳ አሳርፎ ሊሄድ ይችላል ፡፡

ስለዚህ ባለንበት ጊዜ እኛ ኢትዮጵያውያን ( ይህን ወረርሽኝ በአለም አቀፍ ደረጃ መቆጣጠር እስኪቻል ድረስ) እነዚህን ነገሮች ሁሌ ልናስብና ልናደርግ ያስፈልጋል ፡፡

1. ስለ ኮሮና በሽታ ያለንን አመለካከት እናስተካክል

ምንም እንኳን የኮሮና ቫይረስ በሽታ መድኃኒትም ሆነ ክትባት ባይገኝለትም እጅግ በጣም ገዳይ / ከባድ የሚባል በሽታ አይደለም ፡፡ የበሽታው አስቸጋሪነት በቀላሉና በቶሎ ተላላፊነቱ በመሆኑ በሽታውን ከመፍራት ይልቅ ስለ በሽታው መተላለፊያ መንገዶች ፣ የበሽታው ምልክቶች እንዲሁም ማድረግ ስላለብን ነገሮች በቂ እውቀት እናዳብር፡፡ በምንሄድበት ቦታ ሁሉ ንቁ በመሆን ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን ሊገባ የሚችልበትን መንገድ እንቀንስ ፡፡

2. መልካም መልካሙን ዜና ትኩረት እንስጥ

በቫይረሱ ይሄን ያህል ሞቱ ከሚለው ይልቅ መልካም መልካሙን "ይህን ያህል ሰው ድኖ ወጣ " የሚሉትን ዜናዎች እናስብ ፣ ትኩረት እንስጥ ፡፡ እንደሚታወቀው አብዛኛው የዜና አውታሮች ሰበር ዜና ብለው ይሄን ያህል ሰው ሞተ እንጂ ይሄን ያህል ሰው ዳነ አይሉንም በዚህም ያለንን ፍርሀት ይጨምራሉ ፡፡ ስለዚህ በበሽታው ከሚሞቱ ትምህርት ለመውሰድ ቢጠቅመንሞ መልካሙንና ቀናውን ለራሳችን ፣ ለሀገራችን ብሎም ለአለማችን እናስብ ፣ እናውራ ፡፡


3. ስለ በሽታው ያሉ መረጃዎችን ከዋና ጣቢያዎች ብቻ እንከታተል ፡፡ ስለበሽታው ብዙ አሉታዊ ነገር የሚለጥፉ / የሚያወሩ ጓደኛች ካሉን ከነሱ ጋር ወሬ እንቀንስ በFacebookም ለጊዜው Unfollow በማረግ እንራቅ

ይህ የሚጠቅመን ስለ በሽታው ያለን አመለካከት በእጅጉ አሉታዊና አስፈሪ ሁኖ በሌላ ህመም የሚጠቃን ሰው ጭምር ከበሽታው ጋር እንዳናቆራኝና ለራሳችንም የበሽታው ምልክት የሆኑ ነገሮች ባየን ቁጥር በኮሮና እንሞታለን ብለን እንዳንፈራ ነው ፡፡

4. በጤና ባለሙያዎች ፣ በሀይማኖት አባቶች እና መንግስት ለሚነገሩ የትኛዎችም ማሳሰቢያዎች በደንብ ተከታትለን ታዛዥ እንሁን ፡፡ ኢትዮጵያኖች ያለን ማህበራዊ ቁርኝት የሚያስደስትና የተቀራረበ ቢሆንም ለራሳችን ሆነ ለሌሎች ስንል ለጊዜው ተጨባብጦ ፣ ተቃቅፎ ሰላም መባባሉን ብንቀንስ / ለጊዜው ብንተወው መልካም ነው፡፡ ለዚህም ራሳችንን እናሳምን፡፡

5. በሽታውን ከመከላከል ጎን ለጎን ራሳችንን በተለያዩ በሽታ ተከላካይ ምግቦች እንገንባ ፡፡ ጥሩ በሽታ የመቋቋም ጉልበት ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ ብዙ ሳይጎዱ ሊያገግሙ ይችላሉ ስለዚህ ባለን አቅም ሀይላችንን የሚጨምሩ ነገሮችና እንመገብ ፡፡ በሽታውን በመከላከል ብቻ ሳይሆን በማጥቃትም ልንወጣው እንችላለን፡፡

6.በሽታው ወደኛ ባይመጣ ራሱ የተፈጠረውን ሁኔታ ለመልካም እንጠቀምበት ፡፡ (ስራ ገበታ ከሌለ ፣ ትምህርት ከቀረ ) ከቤታችን ሳንወጣ የግል ጊዜ በመውሰድ ስለ እራሳችን ፣ ስለ ሕይወታችን እናስብ፣ እቅድ እናውጣ ፣ የረሳናቸውን ሰዎች እየደወልን እንጠይቅ / እናውራ ፡፡ እንደሚታወቀው የዚህ ዘመን ሕይወት በጥድፊያ የተሞላ ስለሆነ ሳምንታቱን ለማረፍ ፣ ቆም ብለን ለማሰብ እንጠቀምባቸው ፡፡

7. ከምንም በላይ ወደምናምነው ፈጣሪ ምህረቱን ለሰው ልጆች እንዲሰጥ እንፀልይ ። በእንደዚህ አይነት ጊዜ በተለይም የሰው ልጅ ከአቅሙ በላይ በሆነ ችግር ሲያዝ ነገሩን ለሚያምነው ፈጣሪ አስረክቦ ሲሰጥ የአዕምሮ እርጋታ ያገኛል ፡፡


(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ ) ሰላማችሁ ይብዛ………
ከጭንቀትና ፍርሃት ወጥተን ወደተግባር እንግባ
www.tg-me.com/psychoet
❖_____________________________❖

#ለተጨማሪ የሳይኮሎጂ ነክ ትንታኔና መረጃ ይህን ገጽ ይከተሉ

ባለንበት የFACEBOOK እና TELEGRAM ግሩፖች ላይ ሼር እናርገው፡፡ የምትችሉ ሰዎች በሌሎች ቋንቋ እየተረጎማችሁ ፖስት ብታረጉ ብዙ ሰው ይጠቀምበታል

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን ሀገራችንን ይጠብቅልን!
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
❖__________________________________❖
ታላቅ ብሔራዊ የፀሎት ጥሪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ !
#ረቡዕ መጋቢት 16 (በያለንበት ቦታ)

ሁሉም ሰው #ባለበት ቦታ ሆና ስለ ኢትዮጵያ ብሎም ስለ አለም ፈጣሪ ምህረቱን እንዲሰጥ ቸነፈሩን ከሰው ልጆች እንዲያነሳ እንለምን ፡፡ ሁሉም ሰው በየዕምነቱ ለአንድ ቀን ወደ ፈጣሪ እንዲለምን ጥሪ አቀርባለሁ ፡፡

በተጨማሪም የዕምነት ተቋማት መሪዎች ይህን ጥሪ ለየዕምነት ተከታዮቻችሁ በማሳወቅ እንድትቀላቀሉ እጠይቃለሁ ፡፡

#ይህንን #Share በማረግ ሁላችን ወደ ፈጣሪ አብረን በአንድ ላይ እንፀልይ ፡፡በሌሎች የሀገራችን ቋንቋዋች እየተረጓማችሁ በማህበራዊ ሚዲያ ባለንበት ግሩፖች #share በማረግ ረቡዕን ፍጥረት ሁሉ ወደ ፈጣሪው የሚፀልይበት ቀን እናርገው ፡፡

@psychoet
ሱሰኝነትን እንዴት መከላከል ይቻላል?

ሱስ ስንል ማንኛውም ነገር በሰዎች ላይ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጥገኝነት ስሜት በመፍጠር ሰዎች ለመነቃቃት ፤ ድብርትን ለማስወገድ ፤ ጀብዱ ለመስራት፤ ህመምን ለማስታገስና ከፍተኛ የደስታ (Euphoria) ስሜትን ለመጎናጸፍ ብለው የሚያጨሷቸው፤ የሚቅሟቸው በአፍንጫ የሚስቧቸውንና በደም ስር የሚወስዷቸውን ነገሮች በሙሉ ሲያካትት ያለ እነኚህ ሱሶች/ዕፆች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴአቸውን ማከናወን ሲሳናቸው ሱስ ወይም የሱሰኝነት ጠባይ እንዳለባቸው ይገለጻል፡፡

ሰዎች ምንም እንኳን ሱስ የሚያሲዙ ነገሮችን በመጀመሪያዎቹ አካባቢ በራሳቸው ተነሳሽነት የሚወስዱና የሚጠቀሙ ቢሆንም እየዋለ ሲያድር ግን በሚያስከትለው ጥገኝነት ሱስ የሚያሲዙ ንጥረ ነገሮችንና አደንዛዥ ዕጾችን መጠቀም የግድ እየሆነ ይመጣባቸዋል፡፡ ለረጅም ጊዜ በሱስ መጠመድና ተጋላጭ መሆን የአእምሮ ጉዳት ፤ የማስታወስ ክህሎት ማሽቆልቆል ፤ ተስፋ መቁረጥ ፤ እራስን መቆጣጠር አለመቻልና ሌሎች ተጓዳኝ የአካልና የስነ-ልቦና ቀውሶችንና ብሎም ሞትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ በሱስና በአደንዛዥ ዕፅ ጥገኝነት የሚመጡት የጤና እክሎች በሱስ የተጠመዱ ሰዎች ሱሰኝነትን ማቆም እንዳልቻሉ የሚያመለክቱ ሲሆን ይህንን የጤና እክል ለማስወገድ የሚደረገው ህክምና አካልና አእምሮን ከሱስ ከማጽዳት አንጻር ትልቅ ጥረትና ክትትልን ይጠይቃል፡፡ ሱስና አደንዛዥ ዕፅ በሰዎች አካል ፤ አእምሮና ስነ-ልቦና ላይ ትልቅ ተጽእኖ ስለሚኖረው የሚሰጠው ዕርዳታና ህክምና በሱስ ምክንያት የተከሰቱ አሉታዊ ተጽእኖዎችን በሙሉ ያካተተ መሆን እንዳለበት ይጠበቃል፡፡ ከዚህ በማስከተል ሱሰኝነትን ለመከላከል የሚያስችሉ ስልቶችን እንመለከታለን፡፡

የመድኃኒት ህክምና

በአደንዛዥ ዕፅና ነጥረ ነገሮች ሱስ የተያዙ ሰዎች ሱሰኝነትን እንዲያቆሙና ከሱስ የጸዳ ህይወት እንዲመሩ ለማስቻል ከሚሰጡ ዕርዳታዎች መካከል አንዱ የመድኃኒት ህክምና ሲሆን ይህም የተለያዩ መድኃኒቶቸን በመጠቀም በሱስ የተያዙ ሰዎች ሰውነት ውስጥ የተከማቹትን መርዛማ ኬሚካሎችን ማስወገድን ያካትታል፡፡ ከሱሰኝነት ጋር በተያያዘ አብዛኛውን ጊዜ የመድኃኒት ህክምናዎች ለብቻቸው ዘላቂ መፍትሄ የመስጠት ዕድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡

ስነ-ልቦናዊ ህክምና (Psychotherapy)

ሰዎች ሱስና ሱሰኝነትን ከሚያሲዙ ድርጊቶች እንዲላቀቁ የስነ-ልቦና ህክምና ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡ ከሱስ አካላዊ ጥገኝነት ይልቅ ስነ-ልቦናዊ ጥገኝነት ስለሚበልጥ ሰዎች በመጀመሪያ ከሱስ ነጻ መውጣት እንደሚችሉ እራሳቸውን ማሳመን ካልቻሉ ሌሎች የሚደረጉ ህክምናዎችና ዕርዳታዎች ውጤታማ መሆን አይችሉም፡፡ ማንኛውም ለውጥ ከአእምሮ ይጀምራል እንደሚባለው በሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች በምክር አገልግሎት ሰጪ ባለሙያ(counselor) በመታገዝ ከሱስ ለመውጣት ስነ-ልቦናዊና አእምሮአዊ ዝግጅትና ቁርጠኝነት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሰዎች የመንፈስ ጥንካሬ አእምሯቸውን ለማዘዝ የሚያስችል አቅም ሲሰጣቸው በአንጻሩ የአልችልም ባይነትን ስነ-ልቦና ከተላበሱ አእምሮአቸው ያለመቻልን ስሜት በውስጣቸው ይዘው እንዲዘልቁ ያስገድዳቸዋል፡፡ ስለዚህ ስነ-ልቦናዊ ህክምና በሱስ የተያዙ ሰዎችን ስነ-ልቦና በማጠንከር የሱስ ጥገኝነትን ለማስወገድ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡

መጠንን መቀነስ (Reducing dosage)

በሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሱሰኝነትን ቀስ በቀስ ወይም በሂደት ለመተው እንዲችሉ የሚወስዱትን ሱስ የሚያሲዙ ነገሮችን መጠን መቀነስ ይኖርባቸዋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሱስ ያለባቸው ሰዎች ሱሰኝነትን ለመተው ያስቡና ሁሉንም ነገር በአንድ ጊዜ ለማቆም ይሞክራሉ፡፡ ይህ እርምጃ ምንአልባት ለአንድና ለሁለት ቀን ያገለግል እንደሆን እንጂ ዘለቄታዊ መፍትሄን ማምጣት አይችልም፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱሰኝነት በሰውነት አካል ውስጥ በደንብ የተሰራጨ ከሆነ በአንድ ጊዜ ለመተው ማሰብ ህይወትን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል፡፡ ስለዚህ ሱሰኝነትን በአንድ ጊዜ ወይም በቅጽበት ለመተው ከማሰብ ይልቅ መጠንን እየቀነሱ ለዘለቄታው እስከመተው መድረስን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ሌሎች አማራጮችን መጠቀም

ሱሰኝነት በሰዎች አካላት ውስጥ አንዴ ከተሰራጨ መጠንን በመቀነስ ብቻ በቀላሉ ማስይወገድ ስለማይቻል መጠንን በመቀነስ ለመተው በሚደረገው ጥረት ከዚህ ቀደም ሰውነት የተላመደውን መጠን መጠቀም ስለሚፈልግ ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ግድ ይላል፡፡ ሱሰኝነትን በአወንታዊ መልኩ በትክክል የሚተካው ባይኖርም ሱሰኝነትን ለመተው በሚደረገው ጥረት የሚከሰቱትን (withdrawal symptoms) እንደ ድብት ፤ ማቅለሽለሽ ፤ ትኩረት ማጣት፤ ራስ ምታት ፤ አለመረጋጋት ፤ የእንቅልፍ ሰዓት መዛባትና እንቅልፍ ማጣትን ለማስተካከል የማነቃቃት ባህርያ ያላቸውን ትኩስ ነገሮችን መውሰድ ፤ ማስቲካ ማኘክና እንደየአስፈላጊነቱ በተደጋጋሚ ጸጉርን መታጠብ ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

ውጫዊ ተጽንኦዎችን መቋቋም

ሱሰኝነት በተለያዩ ውጫዊ ተጽእኖዎች ሊባባስ ይችላል፡፡ እነዚህን ተጽእኖዎች ለመቋቋም ሱስ ከሚያሲዙ አካባቢዎች መራቅ አንዱ መፍትሄ ሲሆን ይህ የማይቻል ከሆነ ዳግመኛ በሱስ ተጽእኖ ስር ላለመውደቅ አመለካከትን መቀየር ያስፈልጋል፡፡

በአጠቃላይ ሱሰኝነትን ለማስወገድ የሚደረጉ ዕርዳታዎች ሰዎች ከአካላዊና ስነ-ልቦናዊ የሱስ ጥገኝነት ተላቀው ጤናማ ህይወት እንዲኖሩ ማስቻል ነው፡፡ በሱስ ለተያዙ ሰዎች ከሌሎች የሚደረግላቸውን እንክብካቤና ድጋፍ ማስተናገድ ቀላል ቢሆንም ከሌሎች ዕርዳታ ተላቀው እራሳቸውን ከሱሰኝነት ለማላቀቅ በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ትልቅ ተግዳሮት ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ በመሆኑም ከሱስ የሚያገግሙ ሰዎች የሱስን አካላዊ ፤ ስነ-ልቦናዊና የውስጠ ስሜት (emotional) ቁርኝነት ከልብ በመረዳት የሱሰኝነትን ስሜት በአወንታዊ መልኩ ለመግታት መታገል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሰዎች ሱሰኝነትን ካቆሙ በኋላ የድብርት ፤ የንዴትና የብስጭት ስሜት በሚሰማቸው ወቅት ከእነዚህ ስሜቶች ለመውጣት ወደ ተዉት የሱስ ህይወት ለመመለስ ያላቸው ዕድል ከፍተኛ በመሆኑ እነዚህን አጋጣሚዎች በብልሃት ማስተናገድ ይኖርባቸዋል፡፡ መልካም ጊዜ!

#ለተጨማሪ የሳይኮሎጂ ነክ ትንታኔና መረጃ ይህን ገጽ #ሼር #ላይክ ያድርጉ 
(አንቶኒዮ ሙላቱ ©ዘ-ሳይኮሎጂስት)

@Psychoet
በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች

የኮሮናቫይረስ ወርሽኝ በዓለም ሕዝብ ላይ ፈተናን በደቀነበት በዚህ ጊዜ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ እየሞቱም ነው፤ ከተሞችና አገራትም እንቅስቃሴዎችን በሙሉ አግደው ተቆልፈዋል።

ብዙዎችም ራሳቸውን ለይተው ተቀምጠዋል፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በረራዎች በስፋት እየተሰረዙ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩም ሠራተኞች ከቤታቸው እየሰሩ ነው። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ጭንቅ ውስጥ ተስፋ የሚሰጡ ነገሮች አልታጡም።
1.የአየር ብክለት መቀነስ

አገራት እንቅስቃሴዎችን ሲገቱ የአየር ብክለ በከፍተኛ መጠን መቀነሱ እየተገለፀ ነው። በቻይናም ሆነ በሰሜናዊ ጣልያን አየርን በከፍተኛ ደረጃ የሚበክለው ናይትሮጅን ዳይኦክሳይድ በጣም ቀንሷል። ይህ የሆነው የኢንዱስትሪዎች እንቅስቃሴ በኮሮናቫይረስ ምክንያት በመገታቱ ነው።

ኒውዮርክ የሚገኙ አጥኚዎች ለቢቢሲ እንደገለፁት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በተለይም ከመኪናዎች ሚወጣው ካርቦን ሞኖክሳይድ በ50 በመቶ ቀንሰሷል።

2.የመተላለፊያዎች ከሰዎች ጭንቅንቅ ነፃ መሆን

የባህር ላይ ጉዞዎች በመቀነሳቸውም ውሃዎች ንፁህ እየሆኑ መምጣታቸው ሲነገር በጣልያኗ ቬኒስ ከተማ የሚያቋርጠው ውሃም ይህው ለውጥ እንደታየበት ነዋሪዎች ገልፀዋል። ይህ የሆነው ለወትሮው በቱሪስቶች በሚጨናነቁት የሰሜናዊ ጣልያን ጎዳናዎች ኦና በመሆናቸው ዝቃጮች በመቀነሳቸው ነው።

የወሃው አካላት ንጹህ እየሆኑ መምጣት ውሃ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አሳዎችን በግልፅ ማየት ማስቻሉም እየተገለፀ ነው።

3.የደግነት ተግባራት

ምንም እንኳ የቫይረሱ ስርጭትን እየጨመረ መሆኑን ተከትሎ የጥድፊያና የድንጋጤ ግብይቶች ብዙዎችን ላላስፈላጊ ንግግርና ብሎም ድብድብ ቢጋብዝም ኮሮናቫይረስ ዓለም ላይ ደግነትን በስፋት ቀስቅሷል ማለት ይቻላል።

ሁለት የኒውዮርክ ነዋሪዎች በ72 ሰዓታት ውስጥ ብቻ አስፈላጊ የፍጆታ እቃዎችን እንዲሁም መድሃኒቶችን ለአዛውንቶችና ለሌሎች ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች በፍቃደኝነት የሚያደርሱ 1300 በጎ ፍቃደኞችን ማሰባሰብ ችለዋል።

ፌስቡክ እንዳለው በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በእንግሊዝ ውስጥ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ በሚደረገው የበጎ አድራጎት ተግባራት ላይ በፈቃደኝነት ለማገልገል ዝግጁ ሆነዋል።
ተመሳሳይም በጎ ፍቃደኞች ካናዳ ውስጥ ሌሎችን ለመርዳት የሚኣስችላቸውን ቡድን መመስረታቸው ተገልጿል።
የአውስትራሊያ ሱፐርማርኬቶች "የአዛውነቶች ሰዓት" በማለት አዛውነቶችና አካል ጉዳተኞች ያለምንም ግፊያና ግርግር የሚፈልጉትን መሸመት የሚችሉበትን ሁኔታ አመቻችተዋል።
በሌላ መልኩ ደግሞ ብዙ ሰዎች ገንዘብ እየለገሱ ነው፤ በተጨማሪም ራሳቸውን አግልለው ለሚገኙ ሰዎች የሞራል ድጋፍ እያደረጉና ሃሳብ እየሰጡ ነው።
የተጠቀሱት አይነት የበጎ አድራጎት ሥራዎችና ድጋፎች ኢትዮጵያ ውስጥም በስፋት እየተስተዋሉ ነው።

4.በአንድነት መቆም
በሥራና በሌሎች ኃላፊነቶች ምክንያት በዙሪያችን ካሉ ሰዎች ጋር መራራቅ የዘመኑ ኑሮ ሁነኛ መገለጫ ነው። አሁን ግን የኮሮናቫይረስ ስርጭት ይህ መራራቅ አስቀርቶ ይልቁንም የዓለም ህዝብ ምንም እንኳ ርቀት ቢኖር በአንድ ላይ እንዲቆም አድርጓል።
በጣልያን በእንቅስቃሴ እገዳ ከቤት የማይወጡ የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች በየመስኮታቸው ወጥተው አንድ ላይ በመዘመርና ለጤና ባለሙያዎች የምስጋና ጭብጨባ በማድረግ በጎነትን ማወደሳቸው የዚህ አንድ ማሳያ ነው።
ብዙዎች ይህን አስቸጋሪ ጊዜ ከወዳጅ ከጓደኛ ጋር ባሉበት ሆነው በስልክና በማኅበራዊ ሚዲያ ለመገናኘት እንደ እድል እየተጠቀሙበት ነው።

5.የፈጠራ ችሎታ ማበብ

ብዙዎች በቫይረሱ ከቤት መዋላቸውን ተከትሎ አጋጣሚውን የፈጠራ ችሎታቸውን ለማውጣት እየተጠቀሙበት ነው። የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች አዳዲስ ልማዶችን እያመጡ መሆኑ እየታየ ነው። አንዳንዶች ማብሰልን ሌሎች ደግሞ ስዕል መሳልን አዲስ ልማድ አድርገዋል። ማንበብ ላይ ያተኮሩም እንዲሁ አሉ።

@Psychoet
ቫይረስ በራሱ አይንቀሳቀስም ይሁን እንጂ ሰዎች ይዘውት ይንቀሳቀሳሉ ፤ እኛ ሁላችን ባለንበት ከቆየን ቫይረሱ መንቀሳቀስ ያቆማል ከዛም ይሞታል ፡፡

ማሕበራዊ ፈቀቅታ - Social distance

#Share
Nahu|ናሁ
@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «ቫይረስ በራሱ አይንቀሳቀስም ይሁን እንጂ ሰዎች ይዘውት ይንቀሳቀሳሉ ፤ እኛ ሁላችን ባለንበት ከቆየን ቫይረሱ መንቀሳቀስ ያቆማል ከዛም ይሞታል ፡፡ ማሕበራዊ ፈቀቅታ - Social distance #Share Nahu|ናሁ @psychoet»
አፍላ ወጣቶች በአቻ ተጽእኖ ስር ለምን ይወድቃሉ?

አፍላ ወጣቶች በአቻዎቻቸው ግፊትና ተጽእኖ ስር የሚወድቁበት የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም ከዚህ የሚከተሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡

#የመገለል ፍራቻ

አፍላ ወጣቶች በህይወታቸው ውስጥ በአቻዎቻቸው የመገለልን ስሜት ያህል የሚጠሉት ነገር የለም፡፡ ይህ ዕድሜ አፍላ ወጣቶች በሰፈርና በትምህርት ቤት አካባቢ ብዙ ጓደኛ እንዲኖራቸው የሚፈልጉበት በመሆኑ ከሌሎች ላለመለየት ሲሉ ብቻ አቻዎቻቸውን ለመምሰል ይገደዳሉ፡፡ ይህን አለማድረግ በራሱ የሚያመጣው ስነ-ልቦናዊ ጫና ትልቅ በመሆኑ መገለልን አጥብቀው ይፈራሉ፡፡

#በሌሎች ላይ ጥገኛ መሆን

በሌሎች ላይ ጥገኛ መሆንና እራስን አለመቻል አፍላ ወጣቶችን በቀላሉ በአቻ ግፊት ውስጥ እንዲወድቁ ያስገድዳቸዋል፡፡ በትምህርታቸው ደካማ የሆኑና የመረጃ እጥረት አለብን ብለው የሚያስቡ ወጣቶች በሌሎች አቻዎቻቸው ላይ ጥገኛ የመሆን ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በሌሎች ፍላጎት መረብ ውስጥ በቀላሉ ይወድቃሉ፡፡

#መሳቂያና መሳለቂያ ላለመሆን

ሁላችንም እንደምናውቀው በአፍላ ወጣትነት ወቅት ጓደኞቻችን በማንኛውም ሁኔታ በእኛ ላይ እንዳያሾፉና እንዳይሳለቁ እንጠነቀቃለን፡፡ በተለይ በትምህርት ቤት አካባቢ መሳቂያና መሳለቂያ መሆን ትልቅ ሃፍረትን ያከናንባል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ መሳቂያና መሳለቂያ ላለመሆን ሲሉ ብቻ አፍላዎች ከማይፈልጉት የጓደኝነት ብድን ውስጥ ይገባሉ፡፡ ይህ በመሆኑም ፍላጎታቸውንና ጥቅማቸውን ለሌሎች አሳልፈው ለመስጠት ይገደዳሉ፡፡

#ተፈጥሮአዊ ዝንባሌ

ከሌሎች ጋር ለመሆን ተፈጥሮአዊ ዝንባሌ ያላቸው ወጣቶች ከሌሎች ወጣቶች በበለጠ ብዙ ጓደኛ ይኖራቸዋል፡፡ ቅድሚያ የሚሰጡት ለአብሮነት ስለሆነ አወንታዊና አሉታዊ የአቻ ተጽእኖዎችን መለየት ስለሚያዳግታቸው አቻዎቻቸው እንደሚፈልጉት ይመሯቸዋል፡፡ በተጨማሪም ለእራሳቸው ደስታና ለሌሎች ሲሉ አቻዎቻቸው የሚሞክሯቸውን ማንኛውንም አደገኛና የጎንዮሽ ጉዳት ያላቸውን ጠባዮች ይሞክራሉ፡፡

#አሉታዊ የአቻ ግፊትን እንዴት መከላከል ይቻላል?

*ወጣቶች በህይወታቸው ዋጋ የሚሰጡበት ነገር ከሌሎች ጋር ሊደረደሩበት የማይችሉት ስብዕናና ማንነት ከሌላቸው በቀላሉ በሌሎች ተጽእኖ ስር መውደቅ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ወጣቶች በአሉታዊ የአቻ ግፊት ውስጥ ላለመውደቅ ለእራሳውና ለፍሎጎታቸው ክብር መስጠት አለባቸው፡፡ በተጨማሪም፡-

*ያለማንም ጣልቃ ገብነት ለእራስ ህይወት ውሳኔ መስጠት

*ለማይመች የሌሎች ፍላጎት እንቢ ማለት

*ለሚተቹዋቸውና ለሚያሳንሷቸው ወጣቶች ተገቢውን ምላሽ መስጠት

*ከሌላው ልዩ መሆን አልያም ሌሎችን ለመምሰል አለመጣር

*በአቻ ተጽእኖ ስር መውደቅ የሚያስከትለውን ጉዳት አስቀድሞ መመልከት ወጣቶች ህይወታቸውን በኃላፊነት እንዲመሩ ከማስቻሉም ባሻገር ገብተው ከማይወጡበትና ዋጋ ከሚያስከፍል የህይወት ዘይቤ እንዲታቀቡ ይረዳቸዋል፡፡

*በአጠቃላይ ወጣቶች በሌሎች ተጽእኖ ስር ወድቀው ጉዳት የሚያስከትሉ ድርጎቶችን ከመተግበራቸው በፊት ሁኔታዎችን መቆጣጠር አለባቸው፡፡ ምክንያቱም አብዛኛውን ጊዜ በአካባቢያችን ያሉ ሰዎች ማንነታችንን የመቅረጽ ትልቅ ኃይል ይኖራቸዋል፡፡ ‘’ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር ፈስ ትለምዳለች” እንደሚባለው ወጣቶች አዋዋላቸው ከማን ጋር መሆን እንዳለበት ጠንቅቀው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በማይመች አኳሃን ተጉዘው በኋላ ከመጸጸት ማንነታቸውን ማነጽ ከማይችሉ ጓደኞች በመራቅ በመልካም ስብዕናና ጓዳና ላይ ሊመሯቸው ከሚችሉ አዳዲስ ወዳጆች ጋር ህብረት መፍጠር ብልህነት ነው፡፡ ይህ የማይቻል ከሆነ ሁልጊዜ ለሌሎች ፍላጎት ምርኮኛ ከመሆን እንቢተኝነትን መማር ያስፈልጋል፡፡ ሰላም!

#ለተጨማሪ የሳይኮሎጂ ነክ ትንታኔና መረጃ ይህን ገጽ #ሼር #ላይክ ያድርጉ 
©zepsychology – አንቶኒዮ ሙላቱ

@psychoet
ከመሞታችሁ በፊት ማድረግ ያለባችሁ 20 ነገሮች
Join Telegram www.tg-me.com/psychoet

1.ትላንትናን እና ነገን እያሰባችሁ አትጨነቁ፡፡ ትናንት አልፏል ነገ አልመጣም ስለዚህ ዛሬን ቀን በሙላት ፣ በደስታ ፣በሰላም ለመኖር ጥረት አድርጉ፡፡

2.የበደሏችሁን ሰዎች ይቅርታ አድርጉላቸው ፡፡

3.ሁሉንም ሰው በእኩል ዓይን እዩ፡፡

4.ወደዚህ ምድር ያመጧችሁን እናትና አባታችሁን ውደዱ ፣ አክብሩ ፣ ታዘዙ ። *

5.የምትጠሉትን ስራ አትስሩ፡፡

6.የሕይወት ግባችሁን በመለየት በቅጡ ኑሩ፡፡

7.መስታወት ውስጥ ራሳችሁን ተመልክታችሁ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ራሳችሁን ውደዱ፡፡

8.እዚህ ምድር የመጣችሁት በፈጣሪ አላማና እጅግ በጣም ጠቃሚ ሰዎች እንደሆናችሁ አስቡ ፡፡

10.ዘወትር መሄድ እፈልጋለሁ ወደምትሉት ስፍራ ሂዱ፡፡

11.በየቀኑ ለሌሎች ቢያንስ አንድ መልካም ነገር አድርጉ፡፡*

12.ለውጥን በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ ሁኑ፡፡

13.ሁሉንም ዓይነት የሕይወት ትምህርት በፀጋ ተቀበሉ፡፡

14.የሕይወት ፈተና ውስጥ ያለውን መልካም አጋጣሚ አስተውሉ እንጂ ተስፋ አትቁረጡ፡፡

15.በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ አዎንታዊ እና በጎ አሳቢ ሆናችሁ ዝለቁ፡፡

16.በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይሆን ሰውን ሁሉ ለመውደድ ጣሩ ፡፡*

17.ከቁሳ ቁስ ጋር ያላችሁን ትስስር አላሉ፡፡

18.ልባችሁን ተከተሉ፡፡

19.ሁልጊዜም ትልቅ በመሆን ሌሎችን አነቃቁ፡፡

20.ከሰዎች ሁሉ ጋር ተጫወቱ በሰላም በመግባባት ኑሩ ፤ የተቸገሩትን ደግፉ ፡፡ ደግሞም ይህን ጽሑፍ #Share አርጉ ፡፡*😍😍😍

ዘጠነኛውን አንብባችሁታል ግን? .......
የዘለልኩት እስቲ እኔ ያልጠቀስኩት መደረግ ያለበት ነገር እንድታስቡ ነው?

ሰናይ ምሽት ይሁንላችሁ !
እወዳችኀለሁ 😍

(በነጋሽ አበበና ናሁሰናይ ፀዳሉ)
©zepsychologist
Join Telegram www.tg-me.com/psychoet
እንደምን አመሻችሁ የፔጁ ቤተሰቦች !

ከነገ ጀምሮ በህይወት ጉዳይ የተለያዩ ሀሳቦችን የምፅፍ ይሆናል ፡፡ በጣም ብዙ ሰው አሁን ባለው የኮሮና ጉዳይ ተረብሾ ፣ አዝኖ ተስፋ ቆርጦ ይገኛል ፡፡ ስለዚህ የምፅፈውን በደንብ ተግባራዊ ብታደርጉ የተፈጠረውን ነገር ለመልካም እንደምትቀይሩትና በውስጥ የተፈጠረውን አሉታዊ የፍርሀት አመለካከት በአወንታዊና በተስፋ እንደምትቀይሩ አምናለሁ ፡፡

ማንኛውም ጥያቄ ካላችሁ @psychoet_bot ላኩልኝ
መልካም አዳር
#ቸሩ_ቸር_ያሰማን


@Psychoet
እንድታዳምጡት እጋብዛለሁ !

አወንታዊ አስተሳሰብን ማጎልበት አሉታዊ ነገሮችን ለማሸነፍ ቁልፍ ነገር ነው ፡፡
https://youtu.be/Qd4nzZYvUNk
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «እንድታዳምጡት እጋብዛለሁ ! አወንታዊ አስተሳሰብን ማጎልበት አሉታዊ ነገሮችን ለማሸነፍ ቁልፍ ነገር ነው ፡፡ https://youtu.be/Qd4nzZYvUNk»
ከክልሌ ውጣ ስትል የነበርከው ልጅ ግን ከቤትህ መውጣት ጀመርክ? 😎
ለጌታም ጌታ አለው !
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በሀገራችንም ሆነ በአለም የመጣው መልካም ነገሮች

👉ሁሉም እምነት በአንድነትና በአንድ ርዕስ ወደ ፈጣሪ በሀይማኖቱ መፀለይን ምህረትን መለመን ጀመረ ፣ እንዲሁም የሰው ልጅ ሕይወት አጭር መሆንን ተገነዘበ ፡፡ ወረርሽኙ ለሁሉም ሰው ልጆች የፈጣሪን መኖርና አስፈላጊነትን አስተማረ በተጨማሪም የሰው ልጅ አሁን ያለው እውቀትና ቴክኖሎጂ እንደማያዛልቀውና መተማመኛ እንደማይሆነው ተገነዘበ፡፡

👉ከሁሉም በላይ የሰው ልጅ ስራ ፣ ትምህርት ፣ ማሕበራዊ ሕይወት ... የሚኖሩት በሕይወት ሲኖር ብቻ እንደሆነ ተረዳ ፡፡ ለሰው ልጅ ከምንም በላይ ጤንነት ትልቅ መሆኑን ይህ ትውልድ በተግባር አየ ፡፡

👉በሀገራችን በዘር መከፊፈል ፣ አንዱ ለአንዱ መጠቋቆም ቀርቶ ኹሉም 'ሰውነቱን ' ማሰብ ጀመረ ፡፡

👉ትምህርት ቤቶች ፣ መስሪያ ቤቶች ፣ ስፖርት ቤቶቸች ፣ ስብሰባዎች የተለያዩ ሰዎችን በለት ተለት ሕይወታቸው የሚይዙና አትኩሮታቸውን እዚህ ቁሳዊ አለም ላይ ብቻ የሚያደርጉ ነገሮች ተዘግተው ሰዎች ተረጋግተው እንዲተነፍሱ ፣ እንዲያርፉ መልካም አጋጣሚ ተፈጠረላቸው፡፡ሁሉም የቤተሰብ ጊዜና በተለያዩ የሕይወት ሩጫዎች የተወጠረ ሰው እረፍት ፣ ቆሞ የማሰቢያ ጊዜ አገኘ ፡፡

👉ሁሉም ሰው ድሆችን ፣ መበለቶችን ፣ በጎዳና የሚኖሩ " የሕዝብ ልጆችን " እንዲያስታውስ ሆነ ፡፡ የሀገራችን መንግስትም ለጤናው ዘርፍ የተሻለ አትኩሮት መስጠት እንዳለበት ተረዳ ፡፡

👉ለሰዎች ንፅህና መጠበቅ ፣ እጆቻችንን መጠበቅ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ግንዛቤ አገኘን ፡፡ በየአመቱ የሚከበረው እጅ የመታጠብ ቀን በየቀኑ መከበር ጀመረ ፡፡

👉እኔ እንደመጀመሪያ እነዚህን አወንታዊ ነገሮች ይዤ መጥቻለሁ ፡፡ የተቀሩትን ደግሞ እናንተ ጨምሯቸው ... አወንታዊ ነገሮችን ማሰብ በሕይወታችን ለሚከሰቱ አሉታዊ ነገሮች ጥሩ መፍትሄ እንድናፈልቅ ብሎም ራሳችንን ለችግሮች እንድናዘጋጅ ይረዳናል ፡፡

በሚቀጥለው "ሕይወት ከኮሮና ወረርሽኝ በኀላ" በሚል እፅፋለሁ ፡፡

www.tg-me.com/psychoet
በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

ቸሩ ቸር ያሰማን!
አንድ ሰው ነበር ኢርዶስ የሚሉት
ክፍል 1 #አንብቡና_ለሌሎች_አጋሩት

በ20ኛው ክፍለ ዘመን የሂሳብ ሊቃውንት ዘንድ አንድ ሰው በህይወት እያለ ተረት እስከመሆን ደርሶ ነበር፡፡ ከሞተ በኋላ ደግሞ ብሶበታል – ፖል ኢርዶስ፡፡

ኢርዶስን ከአስር ዓመታት በላይ ተከታትሎ በህይወት ታሪኩ ላይ የሚያጠነጥን ‘The Man Who Only Love Numbers’ የሚል መጽሐፍ የጻፈው ፖል ሆፍማን መጽሐፉ ባለ ከፍተኛ ሽያጭ (Best-Seller) ሆኖለታል።

ለመሆኑ ፖል ኢርዶስ ማነው ?

እርግጥ ነው የ20ኛው ክፍለ ዘመን ወደር የለሽ የሂሳብ ሊቅነቱን ማንም አይጠራጠርም፡፡ እንዲያውም በርካታ የሂሳብ የምርምር ወረቀቶችን በመጻፍ እስከዛሬ ከነበሩት የሂሳብ ሊቃውንት – ታላቁ ‘ዮለር’ን ጨምሮ – ማንም አይስተካከለውም ነበር የሚባለው፡፡

በዓለም አቀፍ የሂሳብ ሊቃውንት አምባ አንድ የሂሳብ ሊቅ 50 ያህል የምርምር ወረቀቶችን ካሳተመ “ኦ!….እሱኮ ታላቅ የሂሳብ ሊቅ ነው’”ይባላል፡፡ ኢርዶሳችን ግን ስንት የምርምር ወረቀቶችን አሳተመ ? ከ1500 በላይ፡፡

በሁሉም የአለማችን ክፍል ያሉ የሂሳብ ሊቃውንት የኢርዶስ ስም ሲነሳ የሚታወሳቸው ግን ሌላ ነገር ነው። ኢርዶስ የሂሳብ ተንከራታች ነበር፣ የሂሳብ መንፈሳዊ ተጓዥ። ከሂሳብ ውጪ አንዳችም ህይወት ያልነበረው ሰው !

እርግጥ ነው ዓለማችን በሂሳብ ፍቅር የተለከፉ በርካቶችን ታዝባለች። ግን ማነው እንደ ኢርዶስ በቀን እስከ 19 ሰዓት ያህል ሂሳብ የሚሰራ? ሂሳብ ማለት ውበት ካልሆነ ውበት አላውቅም የሚለው ኢርዶስ ከሂሳብና ከሂሳብ ሊቃውንት አምባ ውጪ አንዳችም ህይወት አልነበረው፡፡ ኢርዶስ ሚስት፣ ልጆች፣ ቤትም ሆነ ቋሚ ስራ አልነበረው፡፡

ከ20ዎቹ ዓመታቱ አንስቶ የሂሳብ ኮንፈረንስ ሊከታተል በሄደበት በድንገተኛ የልብ ህመም እስከሞተበት እስከ 83 ዓመቱ ኢርዶስ ዘመኑን ያሳለፈው በሁለት ነገር ነው ማለት ይቻላል – አንድ፣ ሂሳብ ሲሰራ….ሁለት፣ ሲዞር፡፡ የሂሳብ ሴሚናር አለበት የተባለ የዓለም ክፍል ወይም ዩኒቨርሲቲ ኢርዶስ ይጠፋል ማለት ዘበት ነው፡፡

ወዳጆቹ ኢርዶስን ለማግኘት ሲፈልጉ መጀመሪያ በዓለም ዙሪያ ኢርዶስን ሊመስጥ የሚችል የሂሳብ ኮንፈረንስ ያለበት ሀገር ያጣራሉ፡፡ ከዛ ኮንፈረንሱ በሚካሄድበት ዩኒቨርሲቲ ባሉ በግምት አምስት በሚሆኑ የሂሳብ ሊቃውንት አድራሻ ደብዳቤ ይልካሉ፡፡ ያለ ጥርጥር አንዱ – ኢርዶስ ይደርሰዋል፡፡

በአንዱ የዓለማችን ዩኒቨርሲቲ የሂሳብ ኮንፈረንስ ሲካሄድ አዘጋጆቹ ኢርዶስን ለመጥራት አያሳስባቸውም፡፡ ለነገሩ እንጥራውስ ቢሉ በየትኛው አድራሻ ሊጠሩት – እሱ እንደሁ ቋሚ አድራሻ የለው፡፡ ለነገሩ እሱ ራሱ የሂሳብ ኮንፈረንስ ያለበትን አነፍንፎ ከች ይላል እንጂ፡:

📌ነገ ማታ 2:00 ይቀጥላል
www.tg-me.com/psychoet
(በግሩም ተበጀ )
GreenFire-Apr2020 (4).pdf
1023.9 KB
እንኳን ደስ አለን ! ወርሀዊዉ የMotion መጽሔት አስተማሪ ጽሑፎቹን ይዞ መቷል ።

📌የውሸት ዜናን እንዴት መለየት እንችላለን ? የዕትሙ ዋና ጽሁፍ ነው። ያንብቡት

#Share
👇👇👇👇
@psychoet
@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
አንድ ሰው ነበር ኢርዶስ የሚሉት
ክፍል 2

ለሳምንት ወይም ለሁለት ሳምንት ያህል ካረፈበት በአንዱ የዓለማችን ክፍል ካለ የሂሳብ ሊቅ ቤት ተነስቶ፣ ብዙዎቹ የዓለማችን ታላላቅ የሂሳብ ሊቃውንት የሚያውቋትን በዓለም ላይ ያሉትን ጥቂት ንብረቶቹን – ጥቂት ልብሶቹንና የሒሳብ መስሪያ ወረቀቶቹን የሚይዝባትን ያረጀች ቦርሳ ይዞ፣ ከተፍ ! ከዚያም ወደ ሂሳብ ሴሚናሩ አዳራሽ ወይም ወደ መጣበት ዩኒቨርሲቲ የሂሳብ ትምህርት ክፍል ያቀናና ያቺን ሁሉም የሚያውቋትን መፈክሩን የሃንጋሪያዊ ዘይቤ ባለው እንግሊዝኛ ያውጃል ‘My Mind is Open’ (አንጎሌ ክፍት ነው፡፡) አሁን ሂሳብ መስራት እንችላለን ነው ነገሩ፡፡

አብዛኞቹ ታላላቅ የሂሳብ ሊቃውንት ለብቻቸው መሽገው ነው ከሂሳብ እንቆቅልሾች (Problems) ጋ የተፋለሙት፡፡ ለኢርዶስ ግን ሂሳብ ከምንም በላይ ማህበራዊ ጉዳይ ነው – ሰብዓዊ መስተጋብር። ለዚህም ነው ከ1500 በላይ ከሚሆኑ የምርምር ስራዎቹ አብዛኞቹን ከ500 በላይ ከሆኑ የሂሳብ ሊቃውንትጋ በጥምረት የሰራው፡፡ ከሂሳብ ውጭ አንዳችም ዓለም ለሌለውና በተጠራበት የእራት ግብዣ ላይ ስለ ሂሳብ የሚያወራው ሰው ካጠ እዛው የእራት ጠረጴዛው ላይ ሊተኛ የሚችለው ኢርዶስ የሂሳብ ሴሚናሮችና የሂሳብ ሊቃውንት ስብስብ ብቸኛዎቹ ከሰው የመቀላቀያ ምክንያቶቹ ነበሩ፡፡

ኢርዶስ ትውልዱ ሀንጋሪ ነው – አንደኛው የዓለም ጦርነት አውሮፖን ሊያምስ አንድ ዓመት ሲቀረው በ1913 ተወለደ፡፡ ወላጆቹ የሁለተኛ ደረጃ የሂሳብ መምህራን የነበሩ አይሁዶች ናቸው፡፡ ኢርዶስ በተወለደበት ሰሞን ሁለቱም እህቶቹ በ‘ስካርሌት ፌቨር’ መቀጠፋቸው የኢርዶስን ወላጆች በብቸኛ ልጃቸው በኢርዶስ ላይ ሙጥኝ እንዲሉ አድርጓቸዋል። ጭራሽ የኢርዶስ አባት በግዞት ወደ ሳይቤሪያ መወሰዱ አኑካ የሚላት እናቱ ሙሉ ህይወቷን ለህፃኑ ኢርዶስ እንድትሰጥ አደረጋት፡፡ ተላላፊ በሽታ ፍራቻ ኢርዶስ ሁለተኛ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ የተማረው ቤት ውሰጥ ነው፡፡ በፍጹም ምሁራዊ ክባቤ ውስጥ ያደገው ኢርዶስ በሶስት ዓመቱ በሺ ቤት ያሉ ቁጥሮችን በጭንቅላቱ ማባዛት፣ ቤት የሚመጡ እንግዶችን እድሜ እየጠየቀ እስከ ዛሬ የኖሩትን በሰከንድ አስልቶ መናገረ ጀመረ፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ሲገባ ደግሞ በዝነኛው የሃንጋሪ የተማዎች የሂሳብ መጽሄት ላይ የሚወጡ የውድድር ጥያቄዎች ቀንደኛ መላሽ ሆነ፡፡ አደገኛ የሂሳብ ሰው መሆኑ በጀው እንጂ በወቅቱ በነበረው ፀረ-ሴማዊነት ሳቢያ ኢርዶስ ዩኒቨርሲቲ መግባት ባልቻለ ነበር፡፡ የሆነው ሆኖ ቡዳፔስት ያለው ትልቁ ዩኒቨርሲቲ ገባና በ21 ዓመቱ በሂሳብ Ph. Dውን ያዘ፡፡ ወቅቱ ፀረ-ሴማዊነት ዕጅጉን የተስፋፋበት ዘመን ስለነበር ለድህረ-ዶክትሬት ጥናት ማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ዕድል ሲሰጠው ሳያቅማማ ወደ እንግሊዝ አገር አቀና፡፡

@Psychoet
2024/09/30 21:27:21
Back to Top
HTML Embed Code: