Telegram Web Link
ትልቁ ጥያቄ

ማንኛውም ሰው በህይወቱ  ጭንቀት አልባና  ደስታ የተሞላበት ህይወት ፤ ጥሩ ትዳርና ጣፋጭ የፍቅር ጊዜ ፤ ፍጹም መሆንና ሃብት መታደል ፤ ክብርና የመንፈስ ከፍታ ፤ ታዋቂና ዝነኛ መሆን ብቻ መልካም የሆኑ ነገሮች ሁሉ በህይወቱ እንዲገጥመው ይመኛል፡፡ እነኚህን የህይወት ውጥኖች ለማግኘት መመኘት በራሱ ችግር ባይኖረውም ፤ ምኞት ሁሉ እውነታ እንዳልሆነ መገንዘብ ብልህነት ነው፡፡ ምኞት በራሱ ስኬት አይደለም፡፡ ወደ ስኬት ለመድረስ የምንጓዘው ጉዞ ውጤታማነት የሚለካው የሚያጋጥሙንን ችግሮች ለመጋፈጥ በምናሳየው አቅምና ተነሳሽነት ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ምንአልባትም ብዙዎቻችን የዘነጋው ትልቁ ጥያቄ  ከምኞት ባሻገር በጉዞአችን ላይ የሚያጋጥሙንን እንቅፋት ፤ መሰናክልና ፈተናዎች መጋፈጥ እንፈልጋለን የሚለው ነው፡፡ ይህንን ጥያቄ መመለስ መቻል በራሱ ህይወታችንን በየትኛው አቅጣጫ መምራት እንደምንችል ፍንጭ ይሰጠናል፡፡

እያንዳንዱ ሰው ዋስትና ያለው ዳጎስ ያለ ገቢና የገንዘብ ነጻነትን የሚያጎናጽፍ ስራ እንዲኖረው ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ችግሮችን መጋፈጥንና በላብ ወዝ የድካምን ዋጋ ማግኘት እንደሚቻል ልብ አይለውም፡፡ ከዚህ ባሻገር ያለምንም መሰናክልና መስዋዕትነት ሃብታም መሆንን ይሻል፡፡

በሌላ መልኩ በትልቅ የፍቅር ባህር ውስጥ ትንሽ የእራሱን ደሴት ሰርቶ ጤናማ ትዳር ፤ ሰላማዊ ቤተሰብና ደስተኛ ህይወትን መምራት ፤ ህልም የሚመስል የፍቅር እውነትን በገሃዱ ዓለም መኖርን የሚመኘውም ሰው ጥቂት አይደለም፡፡ ነገር ግን ሁለቱ ጥንዶች በጋራ በመስማማት ፤ በትዕግስትና በመከባበር ፤ በወርቃማ የፍቅር ሰንሰለት ተሳስረው በጋራ የሚፈልጉትን ለማግኘት ካልጣሩ እንዲህ ያለው የፍቅር ቁርኝንነት ድራማ ወይም ፊልም ላይ ብቻ የምናየው ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ደስታ ፤ ሰላምና ፍቅር ትግልን ይጠይቃሉ በመሆኑም እግር አጣምረው ወደ ሰማይ ቢያንጋጥጡ ዝም ብሎ እንደ ዝናብ የሚወርድ የፍቅር ሲሳይ የለም፡፡

ሰዎች ጤናማና የተስተካከለ የሰውነት ቅርጽ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ ፤ ነገር ግን ዘውትር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ፤ የሚመገቡትንና የሚጠጡትን መምረጥ ፤ ከሱስ የጸዳና ጤናማ የህይወት ዘይቤን መከተል ወደሚፈልጉት ግብ እንደሚያደርሳቸው አይገነዘቡም፡፡

በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ የሰው ልጆችን ጠባይና ባህሪይ ስንመለከት ፤ ምንም እንኳን የፍላጎትና የእርካታ መጠናችን ቢለያይም ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ፍላጎት አለን፡፡ አወንታዊ ተሞክሮዎችን ማስተናገድና መቆጣጠር ቀላል ሲሆን በአንጻሩ አሉታዊ ሁኔታዎችን በትዕግስት ፤በጽናትና በትግል መጋፈጥ ብዙ ጊዜ አዳጋች ይሆንብናል፡፡ ስለዚህ ብዙ ጊዜ በህይወት የምናገኛቸው ስኬቶችና መልካም ነገሮች ጥሩ በመመኘታችን ወይም ባለራዕይ ስለሆንን ብቻ ያገኘናቸው ሳይሆን አሉታዊ ተሞክሮዎችን ተሻግረን መሄድ በመቻላችን ነው፡፡

እያንዳንዱ ሰው ለራሱ በቂ ነው ብሎ የሚያስበውን ነገር ለማግኘት ይመኛል፡፡ ነገር ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች በህይወታቸው በቂ ነው ብለው የሚያስቡትን ነገር ለምን እንደሚፈልጉት እርግጠኛ ሆነው መናገር አይችሉም፡፡ ሰዎች ከወር እስከ ወር ከዓመት እስከ ዓመት አንድን ነገር በመፈለግና በመመኘት ብቻ ቢቀመጡ ወደሚፈልጉት ቦታ ላይ መድረስ አይችሉም ይህም በመሆኑ ምኞታቸው የቁም ቅዠት ፤ ሃሳባዊና የማይጨበጥ ምናብ ሆኖ ይቀርባቸዋል፡፡

ስለዚህ አንድ ሰው አንድን ነገር ከመመኘቱ በፊት ምን ዓይነት ተግዳሮትና ችግር ፤ መጋፈጥና መቋቋም እችላለው ብሎ መጠየቅ ይኖርበታል፡፡ ያለመስዋዕትነት ድል አይገኝም በህይወት መንገድ ሳይቆስሉ መዳን ውጥረትን ሳይጋፈጡ ስኬት ማየትና ድሉንም ማጣጣም አይቻልም፡፡

በአጠቃላይ በህይወት መጋፈጥ የሚፈልጉትን ነገር መጠየቅ ወደሚፈልጉት የስኬት ጎዳና ስለሚያደርስ የሁላችንም የህይወት ትልም መጋፈጥ በምንፈልገው ነገር ላይ ይወሰናል፡፡ በህይወትዎ ምን መጋፈጥ ይፈልጋሉ? ለዚህ ትልቅ ጥያቄ በቂና ተግባራዊ ምላሽ ካለዎት ወደሚቀጥለው ምዕራፍ በድል መሸጋገር ይችላሉ፡፡
መልካም ጊዜ!

©zepsychology - አንቶኒዮ ሙላቱ
@psychoet
#መልካም_የመጋቢት_ወር !
T.me/psychoet

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ፍትህ ፣ ሰላም ፣ ልማት የምንሰማበት ከኮሮና የምንጠበቅበት ወር ይሁንልን ፡፡

አንድ ቀን ነገር ሁሉ ቀላል ይሆናል ! ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ ።

#ናሁሰናይ_ፀዳሉ_አበራ

ለምትወዱት ጓደኛ #መልዕክቱን አስተላልፉ

@Psychoet
ለቻናሉ ቤተሰቦች
www.tg-me.com/psychoet
fb.com/psychologyet

ሌሎች ጓደኞቻችንን ወደዚህ ፔጅ በመጋበዝና ባለንበት ግሩፕ #Share በማረግ ሌሎችን እንጋብዝ፡፡

በቅርቡ የምፅፋቸው ውስጥ
*የአስተዳደግና የባህሪ ቁርኝት
*የአቻ ግፊትን ማሸነፍ
*የፍቅርና የጋብቻ ህይወትና መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ
ስለ ሁለንተናዊ የሕይወት ስኬት
*ስለ አዕምሮና አስተሳሰብ ጤንነት ወዘተ ...

መልካም ጊዜ !
ቴሌግራም ቻናሌ ፦ www.tg-me.com/psychoet
ዕውቀት ከአስተሳሰብ ጨለማ ነፃ ያወጣል ፡፡

ማነኛውም ጥያቄ ካላችሁ
@Psychoet_bot ላኩልኝ
ከሰዎች ጋር ያለንን ተግባቦት ለማዳበር የሚረዱ ጠባያት

1. ጥሩ አድማጭ መሆን

ተግባቦትን ለማዳበር ከሚረዱ ጠባያት ዋነኛው ጥሩ አድማጭነት ነው፡፡ ሰዎች በሚናገሩበት ሰዓት ተናግረው እስኪጨርሱ አለማቋረጥ፤ ዓይናቸውን መመልከት፤ በንግግር መሃልም መረዳታችሁን ለማመልከት ጭንቅላታችሁን ወደ ላይና ወደ ታች መነቅነቅ፤ ተናግረውም ከጨረሱ በኋላ መናገር የፈለጉትን ሃሳብ በጥቂት ቃላት ማጠቃለል የጥሩ አድማጭነት ምልክቶች ናቸው፡፡

2. የፊት ገጽታችንና የእጅ እንቅስቃሴአችን

በንግግር ወቅት ያለን የፊት እና የእጅ እንቅስቃሴ ስለምንናገረው ሃሳብ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አለ፡፡ ለምሳሌ አስደሳች ሃሳብ ለመናገር እየሞከርን የፊት ገጽታችንን ማኮሳተር፤ ማጨማደድ እና የዓይን ሽፋሽፍትን መሰብሰብ ለአድማጭችን ተቃራኒ መልዕክት ይልካል፡፡ ስለዚህም ከምንናገረው ሃሳብ ጋር ውህደት ያለው የፊት ገጽታና የእጅ እንቅስቃሴ ሊኖረን ይገባል፡፡

3. ፍሬ ሃሳቡን በተወሰኑ ቃላት መግለጽ

የሰው ልጅ ትኩረትን ሰጥቶ አንድን ድርጊት መከወን የሚችው ለጥቂት ደቂቃዎች ስለሆነ በንግግር ወቅት በጥቂት ቃላት የምንፈልገውን ሃሳብ መግለጽ ይገባል፡፡ የምናናግረውም ሰው በዚያች በሚያናግረን ሰዓት ብዙ የሚያሳስቡት እና ጊዜ ሊሰዋላቸው የሚፈልጋቸው ብዙ ጉዳዮች እንዳሉት በማመን አጭርና በተመረጡ ቃላት የተሟላ ንግግር ብናደርግ ጥሩ ተግባቦት ይኖረናል፡፡

4. ትኩረት የሚያሳጡ ነገሮችን ማራቅ

ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲህ የዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ዘልቆ በገባበት ጊዜ ውስጥ ከሰዎች ጋር በምንነጋገርበት ወቅት የምንጠቀማቸው ከሆነ ተገቢ ያልሆነ ትርጉም ይሰጣል፡፡ ለምናናግረው ሰው ውይም ስሚናገረው ሃሳብ ግድ እንደሌለን ያሳብቃል፡፡ ስለዚህም በንግግር ወቅት ተንቀሳቃሽ ስልካችንን ጨምሮ የምንከውነውን ማንኛውንም ስራ አቁመን ሙሉ ትኩረታችንን በመስጠት ልናዳምጥ እንዲሁም ምላሽ ልንሰጥ ይገባል፡፡

5. አቀማመጥን ማስተካከል

ወደ ጀርባችን ተለጥጦ መቀመጥ፤ ጀርባችንን መስጠት ወይም ፊትን ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ማዞርን የመሳሰሉ አቀማመጦች ተግባቦትን አስቸጋሪ ሊያደርጉ ስለሚችሉ ወደ ምናናግረው ሰው አቅጣጫንን ማስተካከል እንዲሁም ጠጋ በማለት አቀማመጣችንን ማስተካከል ይገባናል፡፡

6. የሚያናግሩትን ሰው ስሜት መረዳት

እጅግ የሚያሳዝን ታሪክ እየተነገረን ስሜታቸውን ከቁብ ሳንቆጥር ቅጭም ባለ አኳኋን “የምተለው ይገባኛል” ብንል ተአማኒነት ያሳጣል፡፡ የተናጋሪውን ስሜት ወደእኛም ዘልቆ እንዲገባ መፍቀድ ከቻልን መልካም ተግባቦት ይኖረናል፡፡

7. ንግግርህ ፍሰት ያለው እና ያልተዘበራረቀ እንዲሆን ማድረግ

ከአንድ ሃሳብ ወደ ሌላ ሃሳብ መዝለል ውልና ማሰሪያ የሌለው ንግግር፤ ውይይትና ክርክር ማድረግ መጨረሻቸው የማያምር ነው፡፡ ስለዚህም ትኩረትን በአንድ ሃሳብ ላይ ብቻ በማድረግ ያልተዘበራረቀ እንዲሁም ፍሰቱን የጠበቀ ንግግር ማድረግ እርሱንም አጠናቆ ወደሌላው መሻገር ተገቢ ነው፡፡

8. በየንግግሩ መሃል የሚገቡ ድምጾችንና የቃላት ድግግሞሽን ማስቀረት

ብዙውን ጊዜ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመከታተል ይልቅ ወደዚህ ጽምጸት አትኩረው እንዲያፌዙ ይጋብዛል፡፡ ስለዚህም “አ….. “ “አም….” የሚሉ ድምጸቶችን ማስወገድ ይገባል፡፡ እንዲሁም “እና” ፤ “ማለት ነው” እና “ምናምን” የሚሉ ቃላትን መደጋገም ንግግራችንን አሰልቺ ሊያደርጉት ስለሚችሉ ማስወገድ ይገባል፡፡

9. የድምጻችንን ቃና እንደየሃሳባችን ማቀያየር

በንግግር ወቅት አንድ ቃና ብቻ ያለው ወጥ ንግግር ማድረግ፤ ለሃዘኑም ለደስታውም ለቁጣውም ተመሳሳይ ድምጸት መጠቀም የአድማጭ ትኩረት እንዲበታተን የሚጋብዝ ነውና አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ አንዳንዴም ለጥቂት ሰኮንዶች ዝም እያልን በተለያየ ቃና የታጀበ ንግግር ማድረግ የአድማጭን ትኩረት ለመሳብና እስከ ንግግሩ መጨረሻ ሰብስቦ ለማቆየት ይረዳል፡፡

ተግባቦት የብዙ ሰው ችግሮ ነውና #share በማረግ ለሌሎች እነዚህን ቁልፍ ነገሮች እናሳውቅ
ፔጃችንን #Like በማረግ በየቀኑ አዕምሮዎን በመልካም ሀሳብ ይመግቡ

(በዘመነ ቴዎድሮስ)
©zepsychologist

#ለሀገራችን ቸር ሳምንት ይሁንልን

Join My Telegram Channel www.tg-me.com/Psychoet
መነሳሳት

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

 8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

 10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ) ©Zepsychology
@Psychoet
❤️❤️❤️ ||ለጥንቃቄ?
ይነበብና ሼር ይደረግ ላልሰሙት እናሰማ ይህንን ጹፍ ሼር ማድረግ የብዙ ሠዎችን ህይወት ከማዳን አይተናነስም።

ኮሮና ቫይረስን መጨነቅ እና መፍራት ሳይሆን በእውቀት መራመድ ያቆመዋል!

በውሃን ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽንለመዋጋት በስፍራው ከሚንቀሳቀስ ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዴት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ እንዴት በዕለት ተዕለት የህይወት እርምጃ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ማስቆም እንደሚቻል የተሰጠ መረጃ!< ከሮና ቫይረስ የአፍንጫ እርጥበት እና አክታ የሚያስከትል ሳል ያለው አይደለም፡፡ በተቃራኒው አፍንጫ የማያረጥብ እና ደረቅ ሳል የሚያስከትል በመሆኑ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡

< ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ ...ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣት ቫይረሱን ይገድበዋል፡፡ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡
< በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/ Snow አትመገቡ! < የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡

1. ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም። ማንኛውንም አይነት ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡
< በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው፡፡

< አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ ተጠቂ አትሆኑም፡፡

2. ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12 ሠዓታት በህይወት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደ እጀታዎች፣ በሮች፣ የቤት ዕቃዎችን፣ የአውቶቡስ የባቡር ወይም የትራም መደገፊያ እጀታዎችን ወይም ምሰሶዎችን ከነካችሁ በኋላ እጃችሁን በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡

3. ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሙሉ ዘወትር በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡ በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ጸሐይ ላይ ብታሰጡዓቸው ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ይገድለዋል፡፡ በቫይረሱ የመጠቃት ምልክቶች #ምን ምንድን ናቸው?

1. ቫይረሱ መጀመሪያ መቀመጫውን ጎሮሮ ላይ በማድረግ የጉሮሮ ብግነት እና የጎሮሮ ድርቀት ስሜት ያስከትላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት ከ3-4 ቀን በሰው ላይ ሊቆይ ይችላል::

2. ቫይረሱ በመተንፈሻ ቱቦ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመጠቀም ወደ ትራኪያ ከወረደ በኋሊ መቀመጫውን ሳምባ ውስጥ ያደርጋል፡፡

ሳምባን በማጥቃት ኒሞንያ/ የሳምባ ብግነት ያስከላል፡፡ ይህ ምልክት የሚታይባችሁ ሁሉ በፍጥነት ወደ ህክምና ሂዱ!! በቫይረሱ ላለመያዝ ምን ማድረግ ይገባል?

1. የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ቀጥታ ከንክኪ ጋር የተያያዘ ሲሆን ቫይረሱ ያረፈባቸውን ቁሳቁሶች እና ልብሶች ወዘተ... መጠቀም ዋነኛ መተላለፊያው መንገዱ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም ነገር ከነኩ በኋላበተደጋጋሚ እጅን በደምብ መታጠብ ዋነኛ መከላከያ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡

< ቫይረሱ በሰው እጅ ላይ በሕይወት መቆየት የሚችለው 10 ደቂቃ ያህል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአስር ደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ነገር ሊከናወን ይችላል፡- አይንን ማሸት፣ አፍንጫን መንካት፣ ጣቶችን ወደ አፍ መውሰድ ወይም [እንደ ጥፍር የመመጥመጥ ክፉ ልማድ] ቫይረሱን በቀላሉ ወደ ጉሮሮ እንዲሄድ ሊያደርገው ይችላል፡፡

< ስለዚህ ለራሳችሁና ለባልንጀራችሁ (ለሌላው ሰው) ደህንነት ስትሉ በጣም በተደጋጋሚ እጆቻችሁን ታጠቡ፡፡

2. አፍ እና ጉሮሮን ጸረ-ተሕዋስ መድሀኒቶችን በመጠቀም መጉመጥመጥ ቫይረሱን ሊያስወግድ ወይም ወደ ጉሮሮ የሚሄዱትን መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ አፍን መጉመጥመጥ ወደ ጉሮሮ ወደ ትራኪያ አልፎም ወደ ሳምባ ቫይረሱ የሚያደርገውን ጉዞ ሊያግደው ወይም ሊቀንሰው ይችላል፡፡

3. የኮምፒውተራችሁን ኪ-ቦርድ እና ማውዝ በጸረ- ተህዋስ በሚገባ አጽዱ።
እባካችሁ ይህን ክፉ በሽታ ወደ አገራችን እንዳይገባ ቅድሚያ መከላከል ከገባም ምን ማድረግ እንዳለብን ለሌሎች እንዲደርስ መረጃውን ሼር በማድረግ የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ

መረጃው ከዶክተር ቤዛ የቴሌግራም ቻናል
JOIN
@psychoet
@psychoet

ለወዳጅዎች #Share ያድርጉ
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ስለ ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ህብረተሰቡ ግንዛቤ አግኝቶ በሽታውን የመከላከልና ስርጭቱን የመቆጣጠር ስራ ላይ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ለማድረግ ከሰታንፎርድ ሆስፒታል የቦርድ አባል የተገኘን መረጃ እንዲህ አቅርበነዋል፡፡

ስለ ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ሊያውቁት የሚገባ መሰረታዊ መረጃ
1. በአፍንጫዎ ፈሳሽ እና ሲያስሉ አክታ የሚኖርዎት ከሆነ ህመምዎ የተለመደው ጉንፋን ነው፡፡
2. በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) የሚመጣ ተዛማች በሽታ ሳምባን የሚያጠቃ ሲሆን ምልክቱም አፍንጫ ላይ ፈሳሽ (እርጥበት) የሌለው ደረቅ ሳል ነው፡፡
3. ይህ ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) በመባል የሚታወቀው አዲስ በሽታ አምጪ ቫይረስ ሙቀትን የሚቋቋም አይደለም፡፡ በ 26/27 ድግሪ ሴንቲግሬድ በሆነ የሙቀት መጠን የሚሞት ነው፡፡ የፀሐይ ሙቀትን ይጠላል፡፡
4. በቫይረሱ የተጠቃ አንድ ሰው ቢያስነጥስ፤ ቫይረሱ መሬት ሳያርፍ በአየር ላይ መነሳፈፍና መጓዝ የሚችለው ለ10 ጫማ ያክል ነው፡፡ ቫይረሱ አየር ወለድ ቫይረስ አይደለም፡፡
5. ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) በብረት ነገሮች ላይ ቢያስ ለ12 ሰዓታት ያህል በህይወት መቆየት የሚችል ሲሆን ስርጭቱን ለመከላከል እና በቫይረሱ እንዳይጠቁ ማንኛውንም ብረት ነክ ዕቃ በነኩ ቁጥር ወዲያውኑ እጅን በንጽህና መጠበቂያ ኬሚካል (ሳሙና) በደንብ መታጠብ ያስፈልጋል፡፡ በጨርቅ ነክ (fabric) ላይ ከ6-12 ሰአታት በህይወት ሊቆይ ይችላል፡፡ ነገር ግን የተለመደው የልብስ ማጠቢያ ሳሙና ይገድለዋል፡፡
6. የሞቀ ውሃን መጠጣት ሁሉንም የቫይረስ አይነቶች ለማዳከም ውጤታማ ነው፡፡ ስለሆነም ፈሳሾችን ከበረዶ ጋር ላለመጠጣት ይሞክሩ።
7. ኮሮኖ ቫይረስ በእጅ ላይ ከ5-10 ደቂቃዎች ብቻ በህይወት ሊቆይ ይችላል፡፡ ስለሆነም እጅን ደጋግመው በሳሙና በደንብ ይታጠቡ፡፡ ከታጠቡም በኋላ ወዲያውኑ በሚመደርጉት እንቅስቃሴ እጅ ላይ ቫይረሱ ሊኖር ስለሚችል ሳያውቁት ዓይንን ሊያሹ፤ አፍንጫን ሊነካኩና ሌሎች መሰል ነገሮችን ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ከነዚህ ድርጊቶችም ይቆጠቡ፡፡
8. ሞቅ ባለ ውሃ ትንሽ ጨው በመጨመር አፍን መጉመጥመጥ እና ከኢንፌክሽን ነጻ ማድረግ ቫይረሱን ለመከላከል አንድ መንገድ አድርጎ መጠቀም ይገባል፡፡

በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) የተጠቃ ሰው ምልክቶቹ ምንድን ናቸው

1. ቫይረሱ መጀመሪያ ጉሮሮን ያጠቃል፡፡ ስለዚህ ለ3 ወይም 4 ቀናት የሚቆይ የጉሮሮ ህመም ይኖራል፡፡
2. ከፍተኛ ትኩሳት ያመጣል፡፡
3. ከዚያም ቫይረሱ ከአፍንጫ ፈሳሽ ጋር ይዋሃድና አየርን ከአፍንጫ/ ከአፍ/ ወደ ሳንባ የሚያመላልሰውን ቱቦ (trachea) ያጠቃል፡፡ በመቀጠልም ሳንባ ውስጥ ይገባና የሳንባ ምች (pneumonia) ያስከትላል፡፡ ይህ ሂደት 5 ወይም 6 ተጨማሪ ቀናት ይወስዳል።
4. የሳንባ ምቹ ከፍተኛ ትኩሳት እና የመተንፈስ ችግር ያስከትላል፡፡
5. በኮሮና ምክንያት የሚመጣው የአፍንጫ መታፈን በጉንፋን ምከንያት ከሚያጋጥመው የተለመደ ዓይነት መታፈን ጋር ተመሳሳይ አይደለም፡፡ የመዘጋት፤ አየር የማጠርና ራስን መቆጣጠር ያልቻሉ እንደሆነ ይሰማዎታል፡፡ በዚህ ጊዜ አፋጣኝ ትኩረት እና ክትትል ያስፈልግዎታል፡፡

የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ህመምን በሚያክሙ የጃፓን ሐኪሞች የተሰጠ ጥብቅ ምክር

1. ሁሉም ሰው አፉ እና ጉሮሮው እርጥብ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡ በፍፁም መድረቅ የለባቸውም፡፡ ቢያንስ በየ15 ደቂቃ ጥቂት ውሃ ይጎንጩ፡፡ ምክንያቱም ቫይረሱ ወደ አፍዎ ቢገባም እንኳን የሚጠጡት ውሃ ወይም ሌሎች ፈሳሾች ጉሮሮዎን በማጠብ ወደ ሆድ ውስጥ ያስገባቸዋል፡፡ ቫይረሱ ወደ ሆድ አንድ ጊዜ ከገባ በኋላ በጨጓራ ውስጥ ያለው አሲድ ቫይረሱን ሙሉ በሙሉ ይገድለዋል፡፡ በመደበኛነት በቂ ውሃ የማይጠጡ ከሆነ ቫይረሱ ወደ አየር ማስገቢያ ቧንቧ፤ ከዚያም ወደ ሳንባ ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ በጣም አደገኛ ነው፡፡
2. አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ለብዙ ቀናት ምንም ዓይነት የኢንፌክሽን ምልክት ለብዙ ቀናት ላያሳይ ይችላል፡፡ ታዲያ አንድ ሰው በበሽታው መያዙን እንዴት ሊያውቅ ይችላል? በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ትኩሳት እና / ወይም ሳል ኖሯቸው ወደ ሆስፒታል በወቅቱ ሲሄዱ አብዛኛውን ጊዜ ግማሽ ሳንባቸው (50%) በቫይረሱ ተጎድቶ (fibrosis) ነው የሚገኘው፡፡ ይህ ደግሞ በጣም የረፈደ ነው፡፡ የሳንባ ግማሽ (50%) በቫይረሱ ከተጎዳ በኋላ (fibrosis ከሆነ) ሊቀለበስ አይችልም። ስለሆነም ምልክቱ ከጅምሩ የታየባቸው ሰዎች በአስቸኳይ ወደ ሆስፒታል መሄድ ለባቸው፡፡

ራስን መፈተሸ ዘዴ

በዚህ ረገድ የታይዋን ባለሙያዎች ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ((COVID-19)) ላለመያዛቸው በቀላሉ ራሳቸውን የሚፈትሹበት ዘዴን እንዲህ ይመክራሉ፡፡ በየቀኑ ጠዋት ጠዋት አየር በረጅሙ ያስገቡ እና ወደ ውጪ ሳያስወጡ ከ10 ሰከንድ በላይ ለሆነ ጊዜ ይዘው ለመቆየት ይሞክሩ፡፡ ይህን ልምምድ ያለ ሳል፤ ያለ መጨናነቅ፤ ያለ መወጣጠር እና ሌላም ማድረግ ከቻሉ፤ ሳንበዎ በኢንፌክሽን ያልተጠቃ (no Fibrosis) መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ በእንዲህ ያለ አስቸጋሪ ጊዜ፣ እባክዎን በየቀኑ ጠዋት ጠዋት ንፁህ አየር ባለበት አካባቢ የዚህ አይነት ልምምዶችን በመስራት የሳንባዎን ጤንነት ያረጋግጡ ፡፡

በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ስርጭትን ለመቀነስና በበሽታው ላለመያዝ ሊደረግ የሚገባው ጥንቃቄ

1. ሰዎች በሚያስነጥሱበት እና በሚያስሉበት ወቅት አፍና አፍንጫን በሶፍት ወይም በክርን መሸፈን፤
2. እጃችንን በሳሙና እና በበቂ ውሃ መታጠብ፤
3. ከሌሎች ሰዎች ጋር ንኪኪን ማቆም (ለምሳሌም አለመጨባበጥ፤ ሰዎች በብዘት የሚሰባሰቡበትና መጨናነቅ ያለበት ቦታ አለመገኘት የመሳሰሉት)፤
4. የተጠቀምንበትን ሶፍት ወደ መፀዳጃ ቤት በመጨመር ከፍሳሹ ጋር እንዲወገድ ማድረግ፤
5. በፈሳሽ ነገሮችን (ውሃ) ቶሎ ቶሎ መጠጣት / መጎንጨት፡፡

ይህን መረጃ ለስራ ባልደረባዎ፣ ለጓደኛዎ እና ለቤተሰብዎ ያካፍሉ፡፡ ሁሉም ጥንቃቄ ያድርግ፡፡ በሃገራችን የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የሚረዱ ጥንቃቄዎችን በማድረግ የዓለም ስጋት የሆነውን ወረርሽኝ የመቆጣጠር ስራ ላይ የበኩላችንን ድርሻ እንወጣ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ምልክቱ የታየባቸው ሰዎች ቢያጋጥምዎ ወዲያውኑ በ 8335 ነጻ የስልክ መስመር ላይ በመደወል ሪፖርት ያድርጉ፡፡

የመረጃው ምንጭ፡- Stanford Hospital Board Member

@Psychoet
@Psychoet
@Psychoet
#ሶስቱ_የስብዕና/ማንነት_አካላት
www.tg-me.com/psychoet
(በአቤል ታደሰ እና ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

#ኢድ(id)፣
#ኢጎ(Ego) እና
#ሱፐር-ኢጎ(Super ego)

በታዋቂው ሲግመንድ ፍሩድ የስነ-ልቦና ጽንሰ-ሀሳብ The Psychoanalytic Theory መሠረት የሰዎች ስብዕና ውስብስብ እና ከአንድ በላይ በሆኑ ክፍሎች ነው፡፡

እነዚህ ሦስቱ የስብዕና ወይንም የማንነት አካላት ኢድ(id)፣ ኢጎ(Ego) እና ሱፐር-ኢጎ(Super ego) ተብለው ሲጠሩ ውስብስብ የሆነውን የሰዎች ባህሪ ለመፍጠር አብረው ይሰራሉ ​​፡፡ ሦስቱም የስብዕና አካላት በእያንዳንዱ ግለሰብ ላይ በተለያየ መልኩ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ፡፡

በፍሩድ ጽንሰ-ሀሳብ መሠረት የስብዕናዎ የተወሰኑ ክፍሎች በመሰረታዊ ፍላጎቶችዎ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ግፊት ሲያደርጉ ሌሎች የስብዕናዎ ክፍሎች ደግሞ እነዚህን ፍላጎቶች ወይም ምኞቶች ለመግታት እና ከእውነተኛ ፍላጎቶችዎ ጋር እንዲስማሙ ለማድረግ ይጥራሉ።

እያንዳንዳቸው እንዴት በተናጥል እንደሚሠሩ እና እንዴት እንደሚነጋገሩ እንመልከት ፡፡

#ኢድ(id)

ከተወለደንበት ጊዜ ጀምሮ የነበረ ብቸኛው የስብዕናችን አካል ሲሆን፡፡ይህ የስብዕናችን አካል ሙሉ ለሙሉ የማይታወቅ እና በደመ ነፍስ የሚመራ ባህሪያትን አካቷል ፡፡ ኢድ(id) ሁሉንም ፍላጎቶች ወዲያውኑ ለማሟላት ከሚሠራው የሰውነት የመደሰት መርህ የሚመነጭ ነው፡፡እነዚህ ፍላጎቶች ወዲያውኑ ካልተሟሉ የስብዕና ውጥረት ይፈጠራል ፡፡
ለምሳሌ ፣ የረሀብ ወይም የጥማት ፍላጎት ለመብላት ወይም ለመጠጣት አፋጣኝ ሙከራን እንድናደረግ ይገፋፋናል : ነገር ግን እነዚህን ፍላጎቶች ወዲያውኑ ማሟላት ሁልጊዜ ተጨባጭ እና የሚቻል አይደለም ፡፡ ይህ የሰውነት የመደሰት መርህ በሙሉ የሚገዛን ከሆነ ፣ ሁልጊዜ የራሳችንን ፍላጎቶች ለማርካት ስንኖር አንገኛለን፡፡
እንደ ፍሩድ ገለፃ ኢድ(id) የሚፈልገውን ፍላጎትን ለማርካት የአእምሮ ምስል በመፍጠርና የመጀመሪያ ደረጃ(ስጋዊ) ስሜትን በመጠቀም የተፈጠረውን ውጥረት ለመፍታት ይሞክራል ፡፡ ምንም እንኳን ሰዎች ውሎ አድሮ የኢድን(id) ደመ- ነፍሳዊ ፍላጎት መቆጣጠርን ቢማሩም ፣ ይህ የባህሪይ አካል በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ተመሳሳይ ሆኖ ይኖራል፡፡

#ኢጎ(Ego)

ራስን ከፍ ከፍ በማድረግ ከእውነታው ወይም ከገሀዱ አለም ጋር ለመገናኘት የሚየግዘን የስብዕና ክፍል ሲሆን እንደ ፍሩድ ገለጻ ኢጎ(Ego) ከ ኢድ(id) የሚዳብር ሲሆን የኢድ(id) ግፊቶች በእውነተኛው ዓለም ተቀባይነት ባለው መልኩ እንዲገለፁ ያደርጋል ፡፡
ኢጎ የሚሠራው በእውነተኛው መርህ ላይ በመመርኮዝ ነው ፣ ስለዚህ የኢድ(id) ፍላጎቶችን በተጨባጭና በማህበራዊ እይታ ተገቢው በሆነ መንገድ ለማርካት ይጥራል ፡፡

ለምሳሌ ፣ በሥራ ቦታ ረዥም ስብሰባ ላይ ተቀምጠው ቆዩ እንበል፡፡ ስብሰባው እየቀጠለ ሲሄድ ረሀብዎ እየጨመረ ሲሄድ ይሰማዎታል፡፡ በዚህ ጊዜ ኢድ(id) ከመቀመጫዎ ላይ እንዲወጡ እና ለምግብ እንዲወጡ ሲገፋፋዎት ኢጎ(Ego) በጸጥታ ስብሰባው እስኪያበቃ ድረስ እንዲቀመጡ በተቃራኒው ይገፋፋዎታል፡፡

#ሱፐር-ኢጎ

የመጨረሻው የሰዎች ስብዕና ክፍል ሱፐር-ኢጎ(Superego) ነው። ሱፐር-ኢጎ(Superego) ከወላጆችና ከማህበረሰብ የምናገኛቸው፡ በውስጣችን የተቀመጡ የሥነ-ምግባር መርህና አመለካከቶችን የሚይዝ የስብዕና ክፍል ሲሆን፡፡ ሱፐር-ኢጎ ውሳኔና መመሪያዎችን ይሰጣል ፡፡ ሱፐር-ኢጎ(Super ego) ባህርያችንን ፍጹም እና ስልጡን ለማሳደግ ይሠራል።

እንደ ፍሩድ ገለጻ ፣ ለጤነኛ ስብዕና ቁልፍ የሆነው ነገር በ ኢድ(id)፣ ኢጎ(Ego) እና ሱፐር-ኢጎ(Super ego) መካከል ያለው ሚዛናዊ መስተጋብር ነው ፡፡

www.tg-me.com/psychoet
www.tg-me.com/wikihabesha
❖_____________________________❖
Source:- From Personality Psychology books & verywellmind (web)

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን!
እወዳችኅለሁ
❖__________________________________❖

ስለ ሳይኮሎጂ የበለጠ ለማወቅ ፔጁን ይከታተሉ ለወዳጆችዎ ያጋሩ

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
አንዳንድ ጊዜ በፅሞና ተቀምጠህ ውስጥህን አድሞጥ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ በውስጥህ የሚመላለሰውን ሀሳብ የሚገልፅ አንደበትና ሰሚ ጆሮ አታገኝም ፡፡
@Psychoet
የካንሰር ተጋላጭነትን መቀነስ
#share ይደረግ

በካንሰር ህመም ምክንያት በዓመት ውስጥ በመላው ዓለም የበርካታ ሰዎች ህይወት ያልፋል፡፡ ድሮ ድሮ የካንሰር በሽታ የአደጉት አገሮች ችግር ብቻ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡ በአሁን ወቅት ግን አድማሱን በማስፋት በታዳጊ አገራት ላይም ትልቅ ተጽእኖን በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡ የአገራችንን ኢትዮጵያ ሁኔታ እንኳን ብንመለከት በእርግጠኝነት ያለውን ቁጥር ማስቀመጥ ባይቻልም ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በዓመት ውስጥ 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ወገኖቻችን ለጋንሰር ተጋላጭ እንደሚሆኑ ይታመናል፡፡ ካንሰርን የሚያድን መድኃኒት እስካሁን ባይገኝም አስቀድሞ ተጋላጭነትን ግን መከላከል ይቻላል፡፡ እንዴት?

*ፈጽሞ ትምባሆና የትንባሆ ውጤቶችን አለማጨስ፡፡

*ቤታችንና አካባቢያችንን ከትንባሆ ጢስ ነጻ ማድረግ፡፡

*ዘውትር አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ

*ጤናማ የአመጋገብና የኑሮ ዘይቤ በመከተል፡፡

*የአልኮል መጠጦችን አለመጠቀም ወይም መጠንን መቀነስ፡፡

*ከፍተኛ የሆነ የፀሐይ ብርሃን ተጋላጭነትን መቀነስ ወይም የፀሐይ ብርሃን መከላከያ መጠቀም፡፡

*ጡት ማጥባት የእናቶችን ለካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡

*ህጻናትን የሄፓቲቲስ ቢና ኤችፒቪ ክትባቶችን (Hepatitis B and HPV) ማስከተብ፡፡

*በየጊዜው ምርመራ ማድረግ…ወዘተ

#Share ይደረግ
©zepsychologist.com
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ደግነት ደስታን ያጎናጽፋል

ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አቀርም፡፡

እንዳሉት የክብር ዶክተር ከበደ ሚካኤል፡፡ በአንድ አጋጣሚ አንድ ቦታ ቁጭ ብዬ ለግል ጉዳይ የቀጠርኩት ሰው እስኪመጣ እጠብቃለሁ፡፡ የተቀጣጠርንበት ቦታ አስቀድሜ ብደርስም የምጠብቀው ሰው በጣም አረፈደ፡፡ ምን ይደረግ “የሐበሻ ቀጠሮ” በሚል ቢሂል መጠበቅ የግድ ስለነበረብኝ በትዕግስት እጠባበቃለሁ፡፡ ከተቀመጥኩበት ቤት ፊት ለፊት አንድ የኔ ቢጤ ቁጭ ብሎ ምጽዋት ይለምናል “ተዘከሩኝ ፤ እርዱኝ እባካችሁ“ ይላል አንጀት በሚበላና የሃዘን እንጉርጉሮ በተቀላቀለበት ዜማ፡፡ በዜማ የሚጣራውን የዕርዳታ እጃችሁን ዘርጉልኝ ድምጽ ስትሰማ አንዲት ሴትዮ ማለፍ አልቻለችም፡፡ ቆም አለችና ከቦርሳዋ አስር ሳንቲም አውጥታ ሰጠችው፡፡ የኔ ቢጤውም አስር ሳንቲሟን አገላብጦ አየት ካደረጋት በኋላ መጽዋችዋን “የእኔ እህት እዚያ ማዶ ያለው ተራራ ይታይሻል?” አላት ከፊት ለፊቱ በብዙ ርቀት የሚታየውን ጋራ በእጁ እየጠቆመ፡፡ “አዎን ይታየኛል” ብላ መለሰች፡፡ የእኔ ቢጤውም መለስ አለና “ይህችን አስር ሳንቲም ብወረውራት ተራራው ላይ የማደርሳት ይመስልሻ?” ብሎ በድጋሚ ጥያቄ አቀረበላት፡፡ መጽዋችዋም “አይመስለኝም በፍጹም ወርውረህ አታደርሰውም ስትለው ፤ በቃ ትቼዋለው” ብሎ ሳንቲሙን ወደ ኪሱ ከተተው፡፡ ሴትዩዋም መልዕክቱ ወዲያውኑ ስለገባት “አዎን ልክ ነህ አስር ሳንቲም ምንም አይገዛልህም ነገር ግን ያለኝ አስር ሳንቲም ብቻ ነው ሌላ የትራንስፖርት እንኳን የለኝም፡፡ በቃ ስትለምን ሳይህ አሳዘንከኝ እኔም ያለኝ ትንሽ ነው ሳልል ስለሰጠውህ ደስታ ተሰማኝ አለችው” ተመጽዋቹም “አብሽር ጣጣ የለውም ፈጣሪ አትረፍርፎ ይስጥሽ” ብሎ መረቃት ፤ እርሷም ምርቃቷን በጸጋ አሜን ብላ ተቀበለችና መንገድዋን ቀጠለች፡፡ የእኔ ቢጤው ቀልድ ትንሽ ቢያስፈግገኝም የሴትዬዋ ምላሽ አትኩሮቴን ሳበው በተለይ “ያለኝን ስለሰጠውህ ደስተኛ ነኝ” የምትለዋ ሀረግ፡፡ ስለመለገስና ሰዎች ለምን ይለግሳሉ የሚለው ርዕሰ ጉዳይ በብዙ የማኅበራዊ ሳይንስ መስክ ጥናትና ምርምር ተካሂዶበታል፡፡ ጥናቶቹም እንደሚያመለክቱት መለገስና ደስታ ቀጥተኛ ቁርኝነት አላቸው፡፡ እስቲ እግረ መንገዳችንን ስለደስታ ትንሽ እንመልከት፡፡

ደስታን በተመለከተ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ፈላስፋዮች ተፈላስፈዋል ፤ ሳይኮሎጂስቶች ጥናትን አካሂደዋል ፤ የህክምናም ይሁን የስነ-አእምሮ ባለ ሙያዎች መላምቶችንና ቀመሮችን አስቀምጠዋል፡፡ በተለያዩ ጸሐፍትም ደስታን ለማግኘት እነዚህን አምስቱን ፤ ሰባቱን ፤ ሃያዎቹን ነጥቦች ተከተሉ የሚሉ መጣጥፎችንና ምክሮችን ሰምተን ፤ ተመክረን አልያም አንብበን እናውቅ ይሆናል፡፡ በታሪካዊ ዳራው ፤ የምርምር ውጤትና አቅጣጫ ጠቋሚዎች ተመርተን እንሄድና የተቀመጡት መፍትሄዎች ከጊዜአዊነት ባለፈ የምንፈልገውን ደስታና ዕርካታ ሊሰጡን አይችሉም፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት ብዙዎቻችን ደስታን ከውጫዊ ነገሮች ስለምንፈልግ ነው፡፡ ምንም እንኳን ውጫዊ ነገሮች ደስታን እንድናገኝ ምክንያት ቢሆኑም ብዙ ጊዜ ልብ ልንለው የሚገባን ነገር ደስታ ከውስጥ ወደ ውጭ ነው የሚወጣው፡፡ ጥርሳቸው እየሳቀ ውስጣቸው እርር ድብን የሚልባቸው ሰዎች ሞልቷል፡፡ በተቃራኒው ጥርሳቸው ሳይስቅ ውስጣቸው ሐሴት የሚያደርጉ በርካታዎች ናቸው ፡፡ ሰዎች ቁሳዊ ሃብትና ብልጽግና ስላላቸው ብቻ ደስተኛ መሆን አይችሉም አልያም ምንም ነገር ስለሌላቸው ደስተኛ ከመሆን የሚያግዳቸው ምን ነገር አይኖርም፡፡ እንዲሁም የተትረፈረፈ ቁሳዊ ሃብትና ብልጽግና ብዙ ጊዜ ከደስታ ምንጭነት ይልቅ የጭንቀትና የውጥረት ምክንያት የመሆናቸው ዕድል ከፍተኛ ነው፡፡

በአካል በዓለማችን አሉ ከሚባሉት የባህር ዳርቻ መዝናኛ ስፍራዎች ብንጓዝና ብንዝናና ፤ አስደናቂና ታምረኛ ቦታ ብንሄድ ደስታችን ከውስጥ ወደ ውጭ የሚወጣ ካልሆነ አካላዊ ድካምን እንጂ ምንም የምናተርፈው ነገር አይኖርም፡፡ ዛሬ እንኳን ቢያስደስትን ነገ መልሶ እንደሚያስደስተን ምንም ዋስትና የለንም፡፡ እንዲሁም አንድ ነገር ሲደጋገም ከሚሰጠው ደስታ ይልቅ አሰልቺነቱ ያመዝናል፡፡ ለብዙዎቻችን ደስታ ማለት አካላዊ ወይም ስጋን ማስደሰት ነው፡፡ ዘላቂውና አብሮን ሊኖር የሚችለው ደስታ ግን ከአእምሮና ከመንፈስ ይመነጫል፡፡ ወጪ የሌለው የትም ቦታ ብንሄድም ባንሄድም አብሮን ሊኖርና ሊያስደስተን የሚችል ነው፡፡ ስለዚህ ደስታህን ከውስጥ እንጂ ከውጭ አንፈልግ፡፡ ለዚህም ነው ከላይ የተመለከትናት ሴትዮ ውስጧ ደስተኛ በመሆኑ ጥቂት ውጫዊ ነገር በማድረጓ ደስተኝነቷን የገለጸችው፡፡

በአንዲት አገር የሚኖር ታላቅ ንጉስ ነበር ፤ ሁሉ የሞላለት ሁሉን ማድረግ የሚችል፡፡ ዕለት ተዕለት ሃብትና ዝናው የሚጨምር፡፡ በራሱ እሳቤና ምልከታ የገነትን አምሳል በምድር ማየትና መዳሰስ በሚያስችል መልኩ አያሌ የዓለማችንን መሃንዲሶችን በማሰባሰብ ቤተ-መንግስቱን አሳነጸ፡፡ ጽዱና ውብ የአትክልት ስፍራንም አዘጋጀ፡፡ ሲኖር ሲኖር ደስታ ይሰጠኛል ብሎ ያሳነጸው ውብ ቤተ-መንግስትና የአትክልት ስፍራ እየዋለ እያደረ ይሰለቸውና ያስጨንቀው ጀመር፡፡ በስተመጨረሻም በሽተኛ ሆኖ አልጋ ላይ ተኛ፡፡ ባለ መድኃኒት፤ ባህላዊና ዘመናዊ ህክምናም በፍጽም ሊፈውሰው አልቻለም፡፡ ባለሟሎቹም ማድረግ የሚገባቸውን ሁሉ አደረጉ ግን ከድካም በስተቀር ምንም መፍትሄ ማግኘት አልተቻላቸውም፡፡ የአገሪቱ ሰዎችም ንጉሳችን ይህ ሁሉ ተሟልቶለት በተድላ እየኖረ እንዴት ደስተኛ አይሆንም በሽታንስ ምን አመጣው ብለው በውስጣቸው ይደነቃሉ ደስታ በሃብት ብዛት ብቻ መስሏቸው፡፡ የንጉሱ ባለሟሎች ሎሌያቸውን በመላክ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዕድላቸውን ለመሞከርና የንጉሳቸውን ጤና ለመመለስ በአገሩ ውስጥ አለ ከሚባል ጠቢብ ጋ ይሄዱና ሁሉንም ነገር ዘርዝረው አስረዱት፡፡ ጠቢበኛውም ነገሩን ካደመጠ በኋላ ንጉሳችው እንዲድንና ጤናው እንዲመለስለት እንዲሁም ደስተኛ እንዲሆን ከፈለጋችሁ የደስተኛ ሰው ልብስ ፈልጉና አልብሱት ብሏቸው አሰናበታቸው፡፡ ንጉሱም ፊት ቀርበው ነገሩን አጫወቱት፡፡ መዳንና ጤናማ መሆን እጅግ ስለጓጓ በየአቅጣጫው የደስተኛ ሰውን ልብስ ይፈልጉ ዘንድ አሰማራቸው፡፡ ሎሌዎቹም ከአንዱ ስፍራ ወደ አንዱ እየተጓዙ ሰዎችን ጠየቁ ደስተኛ መሆናቸውን እርግጠኛ ያልሆኑ ፤ ግማሹ የሚያማርር ፤ አዎ ግን ይህ ይጎድለኛል እርሱን ባገኝ ደስተኛ እሆናለሁ ከሚል በስተቀር ሙሉ ደስተኛ ሰው ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ በስተመጨረሻ አንድ እረኛ በጎቹን አሰማርቶ ፀሐይ ሲሞቅ አገኙትና ከዚህ ስፍራ ሌላ ሰው ይኖራል እንዴ ብለው ጠየቁት? በፍጹም እንደምታውቁት ስፍራው በርሃ ነው ከእኔ ሌላ እዚህ ያለ ሰው የለም! አላቸው፡፡ የእረኛው ሰውነት በጭቃ ቀለም ያጌጠ ነበር ልብስም አልለበሰም፡፡ በአገራችን ምድር ደስተኛ ሰው ፈልግን አጣን ምን ትመክረናለህ አሉት፡፡ እርሱም በመሳቅ ይኸው እኔ አለው አይደል ብሎ አስደነገጣቸው፡፡ መልዕክተኞቹም እንዴት ማለት? ምክንያት? እያሉ በጥያቄ አጣደፉት፡፡ እረኛውም አዎን! ያለኝን ከሌላቸው ጋር እካፈላለሁ ፤ ለጨነቀው ምክርን መንገድ ለጠፋበትም አቅጣጫን አሳያለሁ በዚህም ምክንያት ፍጹም ደስተኛ መሆኔን አረጋግጥላችዋለሁ አላቸው፡፡ ሰዎቹም በቃ ንጉሳችን ዳነልን ብለው ፈነደቁ፡፡ ወደ ልቡናቸው ሲመለሱ ታዲያ ንጉሳችን የአንተን ልብስ ይፈልጋል ጤናው ይመለስለት ዘንድ እባክህ ልብስህን ስጠን በእርሱ ፈንታ እጅግ ያማረና ከተለያዩ ጌጣጌጦች የተሰራ ልብስና ካባ እናመጣልሃለን አሉት፡፡ እረኛውም ከት ብሎ በመሳቅና በመገረም እንደም
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ታዩኝ ልብስ የለኝም የእኔ ልብስ ደስታዬ ነው ብሎ መለሰላቸው፡፡

ከረጅም ጉዞ በኋላ ወደ መጡበት ሄዱና ለንጉሱ ያጋጠማቸውን ሁሉ ነገሩት፡፡ ደስተኛ ሰው ማግኘት እንደተቸገሩና አንድ እራሱን ደስተኛ ነኝ ብሎ የሚጠራ እረኛ ቢያገኙም ምንም አይነት ልብስ እንደሌለው፡፡ ንጉሱም ጉዳዩን አዳመጠና በሉ ለሶስት ቀን ብቻዬን መሆን አፈልጋለው ወደ እልፍኜም ማንም እንዳይገባ ብሎ ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ አገር ሁሉ ተጨነቀ ንጉሳችን ምንሆነብን ሰውን ማግኘት አልፈለገም ብለው የሚሆነውን ነገር በሶስት ቀን ውስጥ ከመጠበቅ በቀር ምንም ማድረግ አልቻሉም፡፡ በሶስተኛውም ቀን ንጉሱ ከእልፍኙ ወጥቶ ሎሌዎቹን ጠራና ለዘመናት ያካበተውን ንብረት እየሸጡ ለድሆች እንዲያካፍሉት ትዕዛዝ ሰጣቸው፡፡ ንብረቱን ሁሉንም ሸጠው ለድዎች አካፈሉ፡፡ ንጉሱም አሁን ጤነኛ ብቻ ሳይሆን ደስተኛም ጭምር እንደሆነ ነገራቸው፡፡ ደስታ ሳይርቀውም ለረጅም ዘመን ኖረ፡፡ የደስተኛ ሰው ልብሱ ልግስና ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ ለተቸገረ ሰው ጥሩ ሃሳብ ማቀበል ቁሳቁስ ከመስጠት ይበልጣል፡፡ ስለዚህ ያለንን በጎ ምክረ ሃሳብ ለሌሎች ማካፈል እኛንም የሌሎች ደስታ ተቋዳሾች እንድንሆን ይረዳናል ፤ “ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም ፤ ከክፋት ደግነት ሳይሻል አቀርም፡፡” መልካም ጊዜ!

ማጣቀሻ

የታሪኩ ምንጭ ፕ/ር ኖስራት ፖዘሽኪያን “Oriental Stories as Tools in Positive Psychotherapy” በድጋሚ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2006 በጀርመን ውስጥ ከታተመው መጽሐፍ ገጽ 79 ላይ “The shirt of a Happy Man” ወይም በአቻ ትርኩም “የደስተኛ ሰው ልብስ”የሚለውን ለእኛ በሚስማማ መልኩ ወደ አማርኛ በመተርጎም ያቀረብኩት ነው፡፡

አንቶኒዮ ሙላቱ ©(ዘ-ሳይኮሎጂስት)
@psychoet
በምድር ላይ ትልቁ ቁም ነገር
ብዙ እድሜ መኖር ሳይሆን
ብዙ መልካም ነገር ሰርቶ ማለፍ ነው ፡፡

Nahu|ናሁ
መልካምነት የሚመነጨው ከአስተዳደጋችን ነው ወይስ በተፈጥሮ?

በተፈጥሮ የምትሉ 🌍
ከአስተዳደግ የምትሉ 👨‍👩‍👦‍👦
በሁለቱም የምትሉ 2⃣

@psychoet
የ3 ደቂቃ ስራ ናት እናንብባት ረጅም አይደለችም አጭር ፅሁፍ ናት

*አንድ የ78 ዓመት አባት እራሳቸውን ስተው ወደ ሆስፒታል ይወሰዳሉ ። ለ24 ሰዓት የሚያቆያቸው የመተንፈሻ ኦክስጅን ተሰጣቸው ። ከጥቂት ግዜ በኃላ ተሻላቸውና ዶክተሩ የተጠቀሙበትን ሂሳብ የ500 ዶላር ደረሰኝ ሰጣቸው ።
*እኝህ አባትም የተሰጣቸውን ደረሰኝ በተመለከቱ ግዜ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ ። ዶክተሩም ስለ ገንዘቡ ማልቀስ አይገባዎትም በአንድ ግዜም ባይሆን ቀስ እያሉ መክፈል እንደሚችሉ ነገራቸው ። *ሆኖም እኝህ አባት " እኔ የማለቅሰው ስለዚህ ገንዘብ አደለም ገንዘቡን በሙሉ የመክፈል አቅም አለኝ ፤ የማለቅሰው 24 ሰኣት ለተነፈስኩበት ኦክስጅን 500 ዶላር ልከፍል በመሆኑ ነው ፤
*ነገር ግን ላለፋት 78 አመታት የእግዚአብሔርን ንፁ አየር በነፃ ስተነፍስ ኖሬያለው ለእነዚ ሁሉ ግዜያት መክፈል ቢኖርብኝ ምን ያህል የእግዚአብሔር እዳ እንዳለብኝ መገመት ትችላለህ ?? " በማለት መለሱለት
*አሁን ይሄንን ወደምታነቢው እህት ወይም ወንድም ልመለስ ፤ የእግዚአብሔር ንፁህ አየር ያለ አንዳች ክልከላና ክፍያ ይሄን ያህል ስትተነፍሺ ኖረሻል ወይም ስትተነፍስ ኖረሃል ።
==========================
ከተመቸችህ አስተማሪ ናት ካልክ ሼር አድርጋት
©Selam yehune

@Psychoet
ይሉኝታ

ይሉኝታ ምንድን ነው?

የሰዎችን ደስታና ሃዘን መካፈል፤ ለሰዎች በችግራቸው ጊዜ ያአቅምን ማድረግ አብዛኞቻችን ያስደስተናል፤  እርካታም ይሰጣል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንዴ ሰዎች በይሉኝታ ሲታሰሩና ከፍላጎታቸው እና ከአቅማቸው በላይ ጊዜያቸውን፤ ገንዘባቸውን፤ ሃሳባቸውን ለሌሎች ሰዎች ደስታ ሲያውሉ ይታያል፡፡ ይሉኝታ ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል ሰበብ፤ የራስን ፍላጎት ገትቶ ሌሎችን  ለማስደሰት መጣር፤ ሌሎችን ማስቀደም ማለት ነው፡፡ ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች ከሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እና ግዴታ በላይ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ይሉኝታ የራሳቸንን ስራና አጀንዳ ወደ ጎን አድርገን ፤ ፍላጎታችንና እና ምርጫችን ተጭነን ሌሎችን ለማስደሰት የመፈለግ ውጤት፡፡

የይሉኝታ መንስኤዎች

ከመጠን በላይ የሆነ የሌሎችን ሰዎች ተቀባይነትና ትኩረት ለማግኘት መሻት

በራስ መተማመን ማነስ

ሌሎች ስለእኛ የሚያስቡት ጥሩ ብቻ እንዲሆን መጨነቅ፡-ስለራሳችን ጥሩነት የሚሰማን ሌሎች በሚሰጡን አስተያየት እና ማሞካሸት ከሆነ

የውስጥ መረጋጋት ከሌለን

አስተዳደግ፡- ያደግንበት ቤተሰብ ሰዎችን ማስደሰት እንደ ትልቅ መርህ የሚያይ ከነበረ፤ ወይም ደግሞ ቤተሰባችን ውስጥ በረባ ባልረባው የሚቆጣ ሰው ከነበረና ያንን ሰው ለማስደሰት ፍላጎታችንን እየተጫንን ያደግን ከሆነ

ያደግንበት ማኅበረሰብ ወግና ልማድ፡-በማኅበረሰባችን በማንኛውም መንገድ ቢሆን በመረዳዳት፤ ያለንን ለሰዎች በማከፈልና “እሺ ባይነትን” እንደ መልካም ባህሪያት መውሰድና ግለኝነትንና እምቢ ባይነትን ደግሞ እንደ እኩይ ባህሪይ የመውሰድ ልማድ

 ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች መገለጫ ባህሪያት

፠ ከሌሎች ሰዎች ሃሳብ ጋር ሁሌም መስማማት እንዳለብን ሲሰማን

፠ ሰዎችን ሊያስደስታቸውና ሊያስከፋቸው ይችላሉ ብለን የምናስባቸው ነገሮች ላይ በብዛት መጨነቅ

፠ ሳናምንበትም እንኳ ቢሆን ስለሌሎች ሰዎች መጥፎ ነገር ሲወራ አብሮ ማማት

፠ ሰዎች ስለኛ ምን ሊያስቡ እና ምን ሊናገሩ እንደሚችሉ ማሰብና መጨነቅ

፠ የሃሰብ ልዩነቶችንና ግጭቶችን ተጋፍጦ በሃሳብ ከመርታት ይልቅ መሸሽ፤ ሃሳቦች ሳይብላሉ ማቋረጥ

፠ ሰዎች በውይይት መሃል የተለየ ሃሳብ ሲያነሱ ከሃሳቡ ይልቅ ሰዎች ላይ ማተኮር

፠ ሃሳባችን ከማንጸባረቅና ላመንበት ነገር ከመቆም ይልቅ ለቡድን ተጽእኖ እጅ መስጠት

፠ ከደንብና መመሪያ መከበር ይልቅ በሰዎች ለመሞገስና ለመከበር ትኩረት መስጠት

፠ የፈለገውን ያህል ዋጋ ቢያስከፍለንም ሌሎችን ላለመሳከፋትና ላለማበሳጨት መጣር

፠ አይሆንም የማለት ድፍረት ማጣት፤ ለሁሉም ነገር እሺን ማስቀደም

ይሉኝታ የሚያስከትለው ጉዳት

★ በራሳችን ህይወት ደስተኞች አንሆነም፤ ስልቹዎች እንሆናለን

★ ከሰዎች የምንጠብቀውን ማበረታትና ተቀባይነት ሁሌም ላናገኝ እንችላለን

★ ራስ ወዳድና በሌሎች ሰዎች መጠቀም ለሚፈልጉ ሰዎች ተጋላጭ እንሆናለን

★ ሁሉም ቦታ ለመገኘት ስንጥር በስራችን ውጤታማ አንሆንም

ይሉኝታን ለመቀነስ የሚረዱ መንገዶች 

ለሰዎች መልካም በመሆንና በይሉኝታ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት

ለምናደርገው ነገር ከስሜት ይልቅ ምክንያታዊነትን ማስቀደም፡፡ ለምንድን ነው ይህን ጉዳይ የምፈጽመው? ሰው ምንይለኛል ብየ ስለፈራሁ? ወይስ ስለሚያስደስተኝ? ወይስ ኃላፊነት ስለሚሰማኝ?

በማድረጋችን፤ ወይም በመፈጸማችን ቆይተን የምንጸጸትበትን ጉዳይ ከማድረግ መቆጠብን መልመድ

አስፈላጊ ሲሆን “አይሆንም” ማለትን ወይም ደግሞ “ላስብበት” ማለትን መልመድ

በራስ መተማመንን ሊያዳብሩ የሚችሉ የህይወት ክህሎቶችን መለማመድ

ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ጤናማ ወሰን እንዲኖረን መጣር

ለራሳችን ክብር መስጠት፡- ሰዎች ስለኛ ምንም ቢያስቡ፤ በማንነታችን ላይ ሊያመጣው የሚችለው ተጽእኖ ብዙ እንዳልሆነ ለራሳችን መንገር

ያደግንባቸውንና ከማኅበረሰብ ያገኘናቸውን ልምዶች በህይወታችን ያመጡልን በጎና መጥፎ ጎን መከለስ፤ማስተዋል

(በሰብለወንጌል አይናለም)
@Psychoet
2024/09/30 23:32:12
Back to Top
HTML Embed Code: