Telegram Web Link
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
አንድ ሰው ነበር ኢርዶስ የሚሉት
ክፍል 3

ኢርዶስ ማንችስተር ዩኒቨርሲቲ እንደገባ አንድ ቀን ያልጠበቀው ችግር ገጠመው፡፡ የሻይ ሰዓት ነው። ለተማሪዎች ዳቦና ቅቤ ቀርቧል፡፡ ተማሪዎች ዳቦው ላይ ቅቤ እየቀቡ ይበላሉ፡፡ ኢርዶስ ደነገጠ፡፡ እስከዛሬ ዳቦ ላይ ቅቤ ቀብታ የምታበላው እናቱ አኑካ ነበረች፡፡ ዳቦ ላይ ቅቤ የሚቀባበትን ጥበብ ደግሞ ፈጽሞ አያውቅም፡፡ ኢርዶስ አፈረ፡፡ ….ግን እንደምንም ሞከርኩት – ብዙም ከባድ አይደለም ይላል ኢርዶስ፡፡ በ83 ዓመት የህይወት ዘመኑ ከሂሳብ ውጪ አንዳችም ይህ ነው የሚባል ሙያ ያልነበረው ኢርዶስ ከሂሳብ ሊቃውንት ጓደኞቹ ጋ ጨዋታ ተነስቶ ስለ ምግብ ማብሰል ችሎታቸው ሲጨዋወቱ፣ ‘እኔ እንኳን…ይላል ኢርዶስ….እስከ ዛሬ ሞክሬው ባላውቅም እንቁላል መቀቀል የሚያቅተኝ አይመስለኝም፡፡’

ኢርዶስ ማንችስተር ዩኒቨርሲቲ እያለ የጀመረው የመንከራተት አባዜ ህይወቱን ሙሉ ተከትሎታል፡፡ በዚህ አመሉ ሳቢያ ለኢርዶስ ቋሚ የዩኒቨርሲቲ የማስተማር ስራ ሊሰጠው የሚፈቅድ አልነበረም፡፡ ለነገሩ እሱስ ቢሆን መች በጄ ብሎ ! በዚህ ምክንያት የኢርዶስ የገቢ ምንጭ በአብዛኛው በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት የሚሰጣቸው ሌክቸሮችና የጓደኞቹ ኪስ ነበር፡፡ 1952 ላይ ግን ለኢርዶስ የሚመች ስራ ኖትረዳም ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተገኘለት ወይም ተፈጠረለት፡፡ ይኸውም መቀመጫውን ኖትረዳም ዩኒቨርሲቲ አድርጎ ባሻው ጊዜ የፈለገው አገር እንደልቡ እየሄደ የሂሳብ ሴሚናር የሚካፈልበትን ነፃነት የሚያጎናጽፍ፡፡ ይህን ዓይነት ነፃነት ማግኘት በማስተማር ኃላፊነቶች ውጥረት ሳቢያ ለብዙ ፕሮፌሰሮች የማይታሰብ ነው፡፡ ለኢርዶስ ግን ተቻለ፡፡ ግን ምን ያደርጋል…ኢርዶስ ይህን በረከት ብዙም ሳይቋደስ አንድ ችግር ተፈጠረ፡፡ በወቅቱ በሴናተር ማካርቲ የተቀጣጠለው አሜሪካንን ከኮሚኒስት ርዝራዦች ማጥራት የተባለው ዘመቻ ኢርዶስን አንዱ ኢላማ አደረገው፡፡

ምክኒያት ?

በኮሚኒስት ሀንጋሪ ካለችው እናቱጋና በኮሚኒስት ቻይና ካለው የሂሳብ ሊቅ ሁዋን ጋ ደብዳቤ መላላኩ ! በቃ ይኸው ነው፡፡ ምንም እንኳ ኢርዶስ ለሁዋን የላካቸው አብዛኞቹ ደብዳቤዎች….

“ውድ ሁዋን….X እና yን ኢንቲጀሮች ናቸው ብለን ብንወስድ….” የሚሉ ዓይነት ቢሆኑም አጣሪ ኮምሽኑ ግን ኢርዶስን ክፉኛ ነው የጠረጠረው፡፡ እናም የአጣሪ ኮምሽኑ አባል ኢርዶስ ቢሮ ድረስ መጥቶ ኢርዶስን መረመረው፡፡
“ለመሆኑ ስለማርክስ ምን ታስባለህ ?” ጠየቀ መርማሪው፡፡

“ምንም አላስብም፡፡ እንደምታውቀው ማቲማቲሺያን ነኝ – የማርክስን ስራ ለመገምገም ብቁ ነኝ ብዬ አላስብም፡፡ ቢሆንም ግን ሰውየው ከባድ ጭንቅላት ሳይኖረው አይቀርም፡፡”አበቃ፡፡ በዚሁ ኢርዶስ አሜሪካንን ለቅቆ ከወጣ የመመለሻ ቪዛ እንማይሰጠው ተነገረው፡፡ እንደተለመደው ደግሞ አንዱ አገር አንድ የሒሳብ ሴሚናር ሊካሄድ ነው፡፡ ምንም ሳያመነታ ሄደ፡፡ለመመለስ ሲያመለክት አትገባም ተባለ፡፡ ከአስር ያህል ዓመታት በኋላ እገዳው አስኪነሳለት ድረስ ሒሳብ ባለበት ቦታ ሁሉ ዓለምን ሲያዳርስ – የሂሳብ በረከቱን ሲረጭ አሜሪካንን ግን አልረገጠም፡፡ በመሆኑም ለአስር ዓመታት ያህል ኢርዶስን አጠገባቸው ማግኘት ያልቻሉ አሜሪካውያን የሒሳብ ሊቃውንት ለረጅም ጊዜያት ያህል የአሜሪካንን ሒሳብ ድብርት ተጭኖት ነበር ይላሉ፡፡

ይቀጥላል
@Psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
ሰላም ለሁላችሁም ጓደኞቼ!

ባለፈው እለት በ Facebook ያላሰብኩት ነገር ገጥሞኝ በጣም አዘንኩ ፣ አለቀስኩ ፣ ለብዙ ሰአትም ቆም ብዬ ማሰብ ጀመርኩና ይሄን ፃፍኩ !

ታሪኩ ይኼ ነበር ፦

አንድ ፎቶ የሆነ ግሩፕ ላይ ለጥፌ ጓደኞቼን Tag እያረኩ ነበር ፡፡ በመሀል ታግ የማረጋቸው Friend List ላይ አንድ ጓደኛዬን ሳየው ሀዘኔን ፣ ድንጋጤዬን ማቆም አቃተኝ ፤ በቃ ደነገጥኩኝ ፡፡

ጓደኛዬ ከጥቂት ወራት በፊት ነበር የሞተው ፡፡ ገና በ20ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ነበር ፡፡ በቆምኩበት ሁኜ ሳስብ 3 ሌላ ልጆች አይምሮዬ ላይ መጡልኝ ፡፡ አብዛኞቹ በ 20 አመታቸው አካባቢ ነበር ( በአደጋ ፣ በሕመም ...) ይችን ምድር የተሰናበቷት ፡፡ ሁሉም ያጣኀቸው ጓደኞቼ ይቺን ምድር በዚህ የልጅነት እድሜያቸው ጥለን እንሄዳለን ብለው አስበው አያውቁም ፡፡ ሁሌ ስለነገ የሚያስቡ ፣ እንደሌላው ተምረው ስራ ይዘው አግብተው ወልደው .... መኖርን የሚያስቡ ነበሩ ፡፡ ግን ያላሰቡት አሰባቸው ፡፡ መቼም እነሱ አሁን ይቺን አለም የሚያስፈራው Corona አያሳስባቸውም ፣ የሞት ፍርሀት የለባቸውም ፣ ስለነገ መጨነቅ አያውቁም ... " ለምን? " ከተባለ አርፈዋላ!

ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ? በእነሱ ፈንታ የሞትነው እኔ / አንተ / አንቺ ብንሆንስ ? ስለዚህ ላስታውሳችሁ የምፈልገው የምንሞትበትን ቀን አናውቀውም ስለዚህ እዚህ ምድር ላይ ምንም ክፋት ፣ ጥል ፣ በደል ፣ ግፍን ዘርተን አንሙት ? ምክንያቱም ያን እኛ የዘራነውን ክፋት የሚያጭድ ቤተሰብ ፣ ማህበረሰብ ፣ ሀገር ፣ ህዝብ አለና ፡፡
መልካምነታችን የሚገለፀው በማህበራዊ ሚዲያ በምንለጥፋቸው ፅሑፎች ፣ በምንሰጠው ኮመንቶች ሳይሆን በተግባር ለቤተሰቦቻችን ፣ ለማሕበረሰባችን በምናሳየው መልካምነት ይሁን፡፡ ቁጭ ብሎ ሌላውን ማማት ፣ መሳደብ ቢቀልም ተረጋግቶ የሚከብደውን መልካም ነገርን መስራት እንምረጥ ፡፡

በታሪክ አጋጣሚ የመጣንባትን ይችን ምድር አልምተን ፣ አሳምረናት እንለፍ ፤ የበጎነት ችግኝ እንጂ ችግር ተክለን አንሙት ፡፡ ሕይወት እንረዳ ፤ ሕይወት ሲገባን ሞት አያስፈራም ያኔ ኑረን አንሞትም በእርግጥ ሙተን እንኖራለን ፡፡

#መልካም_ቀን!
📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌
ለምትወዷቸውና በሕይወታቸው ጥሩ ቦታ ደርሰው ማየት ለምትፈልጉት 10 ጓደኞቻችሁ ይህን መልዕክት ላኩላቸው !
📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌

👇👇👇👇👇
@psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «ሰላም ለሁላችሁም ጓደኞቼ! ባለፈው እለት በ Facebook ያላሰብኩት ነገር ገጥሞኝ በጣም አዘንኩ ፣ አለቀስኩ ፣ ለብዙ ሰአትም ቆም ብዬ ማሰብ ጀመርኩና ይሄን ፃፍኩ ! ታሪኩ ይኼ ነበር ፦ አንድ ፎቶ የሆነ ግሩፕ ላይ ለጥፌ ጓደኞቼን Tag እያረኩ ነበር ፡፡ በመሀል ታግ የማረጋቸው Friend List ላይ አንድ ጓደኛዬን ሳየው ሀዘኔን ፣ ድንጋጤዬን ማቆም አቃተኝ ፤ በቃ ደነገጥኩኝ ፡፡ ጓደኛዬ…»
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
አንድ ሰው ነበር ኢርዶስ የሚሉት
ክፍል 4 (የመጨረሻው )

ኢርዶስ አንዲት መሳጭ ሒሳባዊ ሃሳብ ብልጭ ካለችበት ሃሳቢቱን ለማጋራት በየትኛውም ሰዓት ይሁን የትኛውም የዓለም ክፍል ያለ የሒሳብ ሊቅ ጋ ይደውላል፡፡ አንዴ አንዲት አስደናቂ ሒሳባዊ ዘዴ ተከሰተችለትና በሌላ የዓለም ክፍል ወዳለ የሂሳብ ሊቅ ጋ ሊደውል ስልክ አነሳ፣ “ኢርዶስ፣ እንዴት በዚህ ሰዓት ሰው ቤት ስልክ ትደውላለህ። አሁንኮ’ የምትደውልለት ሰውዬጋ ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ነው” አሉት ጓደኞቹ በተቃውሞ፡፡ “አውቃለሁ…” አለ ኢርዶስ ስልኩን እየደወለ፣ “ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ከሆነ በእርግጠኝነት ከቤቱ የትም ሊሄድ አይችልም ማለት ነው፡፡”

ሒሳብ ሲሰራ ቡና መጠጣት የሚያዘወትረው ኢርዶስ የሒሳብ ሊቅ ማለት ቡናን ወደ ሒሳብ የሚለውጥ ማሽን ነው ሲል ይኮምካል፡፡ በ1971 (ያኔ ኢርዶስ 58 ዓመቱ ነው፡፡) እንደጉድ የሚወዳት እናቱ አኑካ ስትሞት ክፉኛ ነበር የተሰበረው። ሀዘኑን ለመርሳት በቀን 19 ሰዓት ያህል ሒሳብ መስራት የጀመረውም ያኔ ነው፡፡ በሃዘኑ ሳቢያ ያጋጠመውን ድብርት ለማሸነፍ አምፊታሚን የተባለ አነቃቂ መድሃኒት መጠቀም ጀመረ፡፡ የሱሰኝነት አደጋው ያሳሰበው ጓደኛው ለኢርዶስ የውድድር ሃሳብ አቀረበለት – ለአንደ ወር አምፊታሚን ካልተጠቀመ 500 ዶላር ሊሰጠው፡፡ ኢርዶስ ለአንድ ወር ያህል አምፊታሚን ሳይጠቀም ውድድሩን አሸነፈ፡፡ የ500 ዶላሩን ቼክ ከጓደኛው እየተቀበለ እንዲህ አለው ‘….ከሒሳብ ውጪ ሌላ ሱስ እንደሌለብኝ ያረጋገጥኩልህ ይመስለኛል፡፡ ችግሩ ግን አምፊታሚን ባለመውሰዴ ሳቢያ ሒሳብ በአንድ ወር ያህል ወደኋላ ቀርቷል፡፡’ኢርዶስ በቅርብ ጓደኞቹ ዘንድ በስፋት የሚታወቅ የራሱ የሆነ መዝገበ ቃላት ነበረው፡፡ በዚሁ መዝገበ ቃላቱ መሰረት አንድ የሒሳብ ሊቅ ሒሳብ መስራት ካቆመ ወይም ለሒሳባዊ ውበቱና ጥራቱ ብቻ ከሚጠናው ‘Pure Mathematics’ ወጥቶ ሒሳብ ጥቅም ላይ ወደ ሚውልባቸው ምህንድስና ወይም ወደ ሌላ ተዛማጅ ዘርፎች ከገባ ያ ሰው ሞቷል ማለት ነው፡፡ በአንድ ወቅት አንድ ሒሳብ በጣም ጎበዝ የነበረ ልጅ ነበር፡፡ ይህ ልጅ በኢርዶስ እርዳታ በ13 ዓመቱ የሒሳብ የምርምር ወረቀት ሁሉ ጽፏል፡፡ አንድ ቀን ኢርዶስ እያዘነ፣ ‘ያ ጎበዙ የሂሳብ ተማሪ…..በለጋ ዕድሜው በ17 ዓመቱ ተቀጨ’ አለ፡፡ ጓደኞቹ በድንጋጤ ክው ብለው፣ ‘ምን ሆኖ ሞተ ?’ ሲሉ ጠየቁ፡፡ ‘ሂሳብን ትቶ ኢንጅነሪንግ ገባ።’

በኢርዶስ መዝገበ ቃላት እግዚአብሔር ማለት ታላቁ ፋሽስት ነው ይላል – እንደ ቀልድ፡፡ ‘ካልሲዎቼን፣ መነጽሬንና የሃንጋሪ ፓስፖርቴን የሚደብቅብኝ እሱ እንደሆነ አውቃለሁ የሚለው ኢርዶስ ….ከሁሉ ከሁሉ ግን ታላቁ ፋሽስት እግዚአብሔር ዘንድ አንድ ትልቅ መጽሀፍ አለ’ ይላል፡፡ ይህ መጽሀፍ በሂሳብ ዓለም ያሉ ሒሳባዊ ቴረሞችና ውብ የማረጋገጫ ዘዴዎቻቸው (Proofs) ያሉበት ነው፡፡ እኛ ሒሳብ ወዳዶች አንድን የሂሳብ ጥያቄ (Problem) ለመስራት አበሳችንን ስናይ ፋሽስቱ የመጽሀፉን ገጽ ገልጦ በጨረፍታ ያሳየንና ዝግት ያደርገዋል። እኛ ደግሞ ያቺ ያየናት ብልጭ ትልብንና ከመጽሀፉ ገፆች ያላየነውን ለማግኘት አበሳችንን እናያለን – ኦ ፋሽስቱ’ ይላል ኢርዶስ፡፡

‘በእግዚአብሔር ላታምኑ ትችላለችሁ የሚለው ኢርዶስ፣ በመጽሀፉ ግን ማመን አለባችሁ’ ባይ ነው፡፡ አንድ ሒሳባዊ ቁምነገር ውብ በሆነ መልኩ ከተረጋገጠ፣ “ኦ ይሄ በቀጥታ ከመጽሀፉ የተገኘ ነው” ይላል ኢርዶስ በአድናቆት፡፡ ፖል ኢርዶስ እንዲህ እንዲህ እያለ ተዓምረኛ የሒሳብ ችሎታውንና ምንግዜም የማይረሳ አነቃቂ ማንነቱን እንደያዘ በዓለም የሒሳብ ሊቃውንት አምባ የዕውቀት በረከቱን እንደረጨ በ1996 ፖላንድ – ዋርሶ ውስጥ የሒሳብ ኮንፈረንስ ሊካፈል በሄደበት አረፈ፡፡

ለነገሩ እንኳ በኢርዶስ መዝገበ ቃላት መሰረት ‘መሞት’ ማለት ‘ለቅቆ መሄድ’ ማለት ነው፡፡ እናም በ83 ዓመቱ በለጋ የማወቅ ፍላጎት እንደጦዘ ድንገት ‘ለቅቆ ሄደ፡’ እሱንኳ መሞት የሚፈልገው እንዲህ አልነበረም፡፡ ኢርዶስ መሞት የምፈልገው ይላል ‘አንዲት ከፋሽስቱ መጽሀፍ በቀጥታ የመጣች ድንቅ የሒሳብ ሌክቸር ሰጥቼ ሳበቃ…..አንዱ እጁን አውጥቶ፣ ስለአጠቃላዩ ሁኔታስ ምን ትላለህ….’ ብሎ ሲጠይቅ፣

“መልሱን ለቀጣዩ ትውልድ ትቻለሁ…”ብዬ…እዛው መፈጠም’ ይላል፡፡ ግን አልተሳካም፡፡ ከነገ ወዲያ ሊሞት እንደዛሬ አንዱን የምርምር ወረቀቱን ጽፎ ጨርሷል፡፡ በቀጣዩ ቀን እኔ ነኝ ያለ ምርጥ ሌክቸሩን በሂሳብ ኮንፈረንሱ ላይ አቀረበ፡፡ በልብ ህመም ድንገት ሲሞት ከአንዱ የሂሳብ ጥያቄ ጋር ግብግብ ገጥሞ ነበር፡፡ ኪሱ ውስጥ በቀጣይ ዩቲኒያ ውስጥ ወደሚካሄድ የሒሳብ ኮንፈረንስ የምትወስደው የአውሮፕላን ትኬት ነበረች፡፡

ፖል ኢርዶስ…. ፡፡

@Psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#ክፍል_21
✿ ጤናማ ትዳር ✿
www.tg-me.com/psychoet

የሰዉ ልጆች ከመወለድ እስከ ሞት በተለያዩ ግንኙነቶች ታጅበን እንኖራለን ፡፡ ከእነኚህ ግንኙነቶች አንዱ ትዳር ሲሆን ዋና ከሚባሉ ግንኙነቶች ውስጥም ይመደባል፡፡

ጤናማና ጠንካራ ትዳር መሰረቱ ያመረ ቤትን ይመስላል፡፡ በወጀብ የማይናወጽ ፤ በጎርፍ የማይነቃነቅ ፤ ከችግኝነት እስከ ፍሬ ማፍራት በትዕግስትና በፈተና የሚጓዝ ነው፡፡ ትዳር ትልቁ ማኅበራዊ ተቋም ሲሆን ትዳሩ እስካልፈረሰ ድረስ የማንመረቅበት ትልቅ ትምህርት ቤት ነው፡፡

አንድ ገበሬ በብዙ ድካምና ልፍት የወዙን ምርት እንደሚያገኘው የትዳርም ውጤት በትዳራችን ላይ ምን ያህል እንደለፋን አቅጣጫን ያሳያል፡፡ ሰዎች ልምዳቸውንና ዕውቀታቸውን እንደሚመስሉ ሁሉ ዕለት ተዕለት የሚኖረን የትዳር ተሞክሮዎችና ውጥኖች ትዳራችንን እንደ አንድ ሰላማዊ ደሴት ወይም እስር ቤት እንድንቆጥረው ያደርገናል፡፡

ታዲያ የተለያዩ ሰዎች የተለያየ የትዳር ሁኔታ አላቸዉ የሰመረ/ደስተኛ እና ችግር ዉስጥ፡፡ ትዳርን የሰመረ/ደስተኛ ለማድረግ ሁለቱም ጥንዶች በጋራ መስራት አለባቸዉ ምንያቱም ትዳር በሰራነዉ ልክ ነዉ የሚወሰነዉ፡፡ መቻቻልን ሳይሆን ፍቅርንና መረዳዳትን (Understanding) መሠረት ያደረገ ትዳር ከእራስ አልፎ በሌሎች ዘንድ በተምሳሌትነቱ ይጠቀሳል፡፡ የሚያስቀና ትዳር አላቸው ተብሎ ውዳሴንና ክብርንም ያስገኛል፡፡ ይህ ታዲያ መሆን የሚችለው ትዳርን የፍቅር ትምህርት ቤት ፤ የሰላም ተቋም ፤ የባልና የሚስት የስራ ክፍፍል ተብሎ በማኅበረሰቡ ዘንድ የተቀመጠውን ድንበር አፍርሶ ቤተሰቡ ሊታነጽበትና ሊመራበት የሚችል መከባበር ፤የጋራ አመለካከትና አረዳድ ሲኖርው ብቻ ነው፡፡ ያ ሳይሆን ሲቀር ለመተጋገዝ የተመሰረተው ትዳር የጸብ ምንጭና የክርክር መድረክ ሆኖ ያበቃል፡፡ እንዲሁም ለፍቺ (divorce) አልያም ለቤት ውስጥ ጥቃት (domestic violence) በርን በመክፈት ይጓዛል፡፡ ደስተኛ/የሰመረ ትዳር መመስረት ለግለሰባዊ፣ ለቤተሰባዊ፣ ለማኅበረሰባዊ እና ለሀገራ ዕድገት ያለዉ አስተዋፅኦ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ እንደ ጋላገር እና ዌይት ትዳር ለአዕምሮ ጤንነት ጥሩ የሚባል ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በተለይም ደስተኛ ትዳር የመሰረቱ ሰዎች ደስተኝነትን፣ ተስፈኝነትን፣ ጠንካራ መሆንና እና ጥሩ የመኖር ፍላጎትን ይጨምል፡፡ በተጨማሪም ለራሳችን ያለን ግምት እንዲያድግ ይረዳል፡፡

ሌላዉ የደስተኛ ትዳር ጥቅም ማኅበረሰባዊ ቀዉሶችን ይቀንሳል፡፡ ጎዳና የሚወጡ ልጆች፣ ከትምህርት የሚቀሩ፣ ሱሰኝነት እና ሌሎችም ማህበራዊ ቀዉሶች በደስተኛ እና ጤናማ ትዳር መቀነስ ይቻላል፡፡ ያገባችሁ ትዳራችሁን ተንከባከቡት በተንከባከባችሁት ልክ መልሶ የከፍላችኋል ፤ ያላገባችሁ ደግሞ ከጤናማ ትዳር ትምህርት ቅሰሙ፡፡

መልካም ጊዜ

©zepsychology (በመአዛ መንበረ )
www.tg-me.com/psychoet
❖_____________________________❖

#ለተጨማሪ የሳይኮሎጂ ነክ ትንታኔና መረጃ ይህን ገጽ ይከተሉ

ባለንበት የFACEBOOK እና TELEGRAM ግሩፖች ላይ ሼር እናርገው፡፡ የምትችሉ ሰዎች በሌሎች ቋንቋ እየተረጎማችሁ ፖስት ብታረጉ ብዙ ሰው ይጠቀምበታል

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን ሀገራችንን ይጠብቅልን!
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
❖__________________________________❖
GreenFire-Apr2020 (4).pdf
1023.9 KB
እንኳን ደስ አለን ! ወርሀዊዉ የMotion መጽሔት አስተማሪ ጽሑፎቹን ይዞ መቷል ።

📌የውሸት ዜናን እንዴት መለየት እንችላለን ? የዕትሙ ዋና ጽሁፍ ነው። ያንብቡት

#Share
👇👇👇👇
@psychoet
@psychoet
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ኢትዮጵያውያንንና አፍሪካውያንን የሚያኮራ ንግግር አድርገዋል !
1: 54 ደቂቃ ብቻ ነው ፡፡
ተመልከቱትና#Share
👇👇👇
@psychoet
ሰላም የፔጁ ቤተሰቦች 😊
በዚህ ሰሞን ብዙ ሰዎችን እያወራሁና ጥያቄ እየተቀበልኩ ነበር ፡፡ በዚህም አሁን በተፈጠረው ወረርሺኝ ምክንያት የብዙ ሰው ሥነልቡና ተረብሿል ስለዚህ እንደ ሥነልቡና አማካሪ ምን ማድረግ ይገባናል የሚለውን ልጽፍላችሁ ወደድኩ ፡፡

ስለዚህ ከታች ያሉትን ምርጫዎች አስቀምጡልኝ
📌በዚህ ሰሞን ምን አይነት ስሜት ይሰማችኅል?

1⃣ ድብርት
2⃣ ፍርሀት ፣ ጭንቀት
3⃣ ተስፋ ቢስነት ፣ ደካማነት
4⃣ ስራ ፈትነት ፣ የኑሮ ትርጉም ማጣት
5⃣ ስለ ነገ አሉታዊ ነገሮች ማሰብና መተከዝ
6⃣ አብዛኛው ይሰማኛል

ለእነዚህ ሁሉ በሚመጡት ቀናት የሥነልቡና መፍትሔ ይዤ እቀርባለሁ !
ለሀሳብ አስተያየት @Psychoet_bot
#ሼር 👍 JOIN 👍 #ሼር
@Psychoet @Psychoet @Psychoet
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂ pinned «ሰላም የፔጁ ቤተሰቦች 😊 በዚህ ሰሞን ብዙ ሰዎችን እያወራሁና ጥያቄ እየተቀበልኩ ነበር ፡፡ በዚህም አሁን በተፈጠረው ወረርሺኝ ምክንያት የብዙ ሰው ሥነልቡና ተረብሿል ስለዚህ እንደ ሥነልቡና አማካሪ ምን ማድረግ ይገባናል የሚለውን ልጽፍላችሁ ወደድኩ ፡፡ ስለዚህ ከታች ያሉትን ምርጫዎች አስቀምጡልኝ 📌በዚህ ሰሞን ምን አይነት ስሜት ይሰማችኅል? 1⃣ ድብርት 2⃣ ፍርሀት ፣ ጭንቀት 3⃣ ተስፋ ቢስነት…»
አድናቆት

ስለእራሱ ጥሩ ነገር እየተነገረው ያደገ ልጅ ማድነቅን ይማራል
አግባብነት ያለው ማበረታቻ እያገኘ ያደግ ልጅ በእራስ መተማመንን ይማራል
መቻቻል በሰፈነበት ሁኔታ ያደገ ልጅ ትዕግስተኝነትን ይማራል
ልጅ ከአድሎ ነጻ በሆነ ሁኔታ በአግባቡ ካደገ ፍትህን ይማራል
ልጅ ዋስትናና ደህንነት በተሞላበት ኑሮ ካደገ ሰውን ማመንን ይማራል
ልጅን በማንነቱ ተቀብለን በማቅረብ ካሳደግነው ምሉዕ ፍቅር ከአለም ይማራል
ጥላቻ በተሞላበት አካባቢ ያደገ ልጅ ጠባጫሪነትን ይማራል
ልጅ በሃፍረት ካደገ የጥፋተኝነት መንፈስን ይማራል

…. እንዳለው ዶርቲ ሎው

በየትኛውም ስፍራ የሚኖር የሰው ልጅ ህጻንም ይሁን አዋቂ አድናቆትንና ሙገሳን ይወዳል እንዲሁም ይፈልጋል፡፡ መደነቅ በሰዎች ዘንድ ትኩረት ማግኘታቸንን ስለሚያመላክት ተደናቂው ክብርና የመንፈስ ከፍታ ይሰማዋል፡፡ “አንበሳ ፣ ጎበዝ ፣ ጀግና ፣ በጣም ድንቅ ስራ ነው የሰራኸው…..ወዘተ” ሰዎች አድናቆትን ለመግለጽ የሚጠቀሙባቸው ቃላት ናቸው፡፡

አድናቆት ተስፍ ለቆረጡና ምንም ማድረግ አንችልም ብለው ለተቀመጡት እንደ ጉዞ ስንቅ በማገልገል እንደገና ተስፋቸውን አለምልመው ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ይራዳቸዋል ይላሉ ፡፡

ወጣት ልጆችን እንዴት እናድንቃቸው?

ትልቁ ትኩረትና ጥያቄ ልጆችን ማድነቅ ያስፈልጋል የሚለው ሳይሆን እንዴት እናድንቃቸው የሚለው ነው፡፡ ብዙ የምርምር ስራዎች እንደሚያመለክቱት የልጆችን የስራ ሂደት ማድነቅ ልጆች ጠንክረው እንዲሰሩ ፤ እንዲማሩ ፤ እንዲመራመሩና ስለ ችሎታቸው አወንታዊ አመለካከት እንዲኖራቸው ይረዳል፡፡ በተጨማሪም በግልጽነትና በእውነተኝነት ላይ የተመሰረት አድናቆት የልጆችን በእራስ መነሳሳት ያሳድጋል፡፡ ወጣት ልጆችን ለማድነቅና ለማበረታታት ከዚህ የሚከተሉት ነጥቦች ወሳኝነት አላቸው፡-

ስለ ልጆችች ስራና ጥረት መግለጽ፡- ፍርደ ገምድልነት የሌለው ውሳኔ በመስጠት የስራዎቻቸውን ጥረት ማድነቅ

ለአወንታዊው ስራና ጥረት ትኩረት መስጠት

ተግዳሮት ለሌለውና ብዙ ጥረት ለማይጠይቅ ስራ አድናቆትን መቆጠብ

አድናቆቱና ስራው ተመጣጣኝ መሆን አለበት

አግባብነት ያለውን ድርጊት በመምረጥ አድናቆትን መስጠት

በጊዜ ሂደት አድናቆትን መቀነስ ምክንያቱም ልጆች በአድናቆት ላይ ጥገኛ በመሆን ለመደነቅ ብቻ ሲሉ አንድን ነገር እንዲከውኑ ስለሚገድባቸው፡፡

አድናቆት ተፈጥራዊ ሂደትን ተከትሎ መቅረብ አለበት ከበጎና ከመልካም ድርጊት በኋላ የሚከተል፡፡

በአጠቃላይ የአድናቆት ዋንኛው ግብ ልጆች በእራሳቸው ተነሳሽነት አንድን ድርጊት እንዲከውኑና ተግዳሮቶችን በመቋቋም ጥገኝነትን አስወግደው ወደ ሚፈልጉት የዕድገት ምዕራፍና ውጤት እንዲሸጋገሩ ማስቻል ነው፡፡ እናንተስ በአድናቆት ወይስ በትችት ነው ያደጋችሁ እስቲ ያስከተለባችሁን አወንታዊና አሉታዊ ተጽእኖዎችን አካፍሉን!? ሻሎም

በአንቶኒዩ ሙላቱ ©Zepsychology
#ለተጨማሪ የሳይኮሎጂ ነክ ትንታኔና መረጃ ይህን ገጽ #ሼር #ላይክ ያድርጉ 
@psychoet
በጎ አመለካከትን የሚገነቡ 8 ነገሮች

አሁን ባለንበት ወቅት አንዱ መጥፎ ነገር ስለ ሁኔታዎች የምናስበው አሉታዊ ነገር ነው ፡፡ እነዚህ አሉታዊ ነገሮች ደግሞ ቀናችንን ሳምንታችንን በድብርት እንድንጨርስ ብሎም ያለስራ ባክነን ሁልጊዜ ነገን ብቻ በፍርሀት እየጠበቅን እንድንኖር ያደርጉናል ፡፡

ይህን ነገር የምናሸንፈው 1ዱ በጎ አመለካከት በማዳበር ነው ፡፡ ለዚህም ከታች ያለውን የ 5 ደቂቃ ስነልቦናዊ ምክር እንድታዩት እጋብዛለሁ ፡፡ ማየት ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱን በሕይወት በመተግበር በሕይወታችሁ ለውጥ እንድታመጡ እመክራለሁ ፡፡ አይታችሁት ያላችሁን ጥያቄ በዛው ላይ ብትፅፉ እንወያይበታለን ፡፡ መልካም ቀን!

https://youtu.be/MkJTDxFN5dk
እንደምን አመሻችሁ !

የተለያዩ የሥነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን ይከታተሉ (Subscribe ያድርጉ)

በተለይ ከሀገር ውጭ ያላችሁና ስልጠናዎቻችንን በአካል ማግኘት ያልቻላችሁ ሰዎች ከአሁን ጀምሮ በቴሌግራም መሰል ስልጠናዎችንና ካለንበት ጊዜ በድል መውጫ አበረታች ሀሳቦችን አቀርባለሁ ፡፡

"የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው "
https://www.youtube.com/user/TheNahusenai
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
አወንታዊ የልጆች አስተዳደግ ለተሻለ ውስጠ ስሜትና ትምህርት

ለልጆች የመጀመሪያዎቹ መምህራን ወላጆቻቸው መሆናቸው ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ በማኅበራዊ ትምህርት መስክ የልጆች አስተዳደግ ከፍተኛ ጥናትና ምርምር ከተካሄደባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛው ነው፡፡ ጥሩና ጤናማ የልጆች አስተዳደግ ልጆችን አዛኝ፤ ግልጽ ፤ እራሳቸውን መቆጣጠር የሚችሉ ፤ ደግ ፤ የሚተባበሩና ደስተኛ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል፡፡ ፊላደልፊያ በሚገኘው የቴንፕል ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆነው ረውረንስ ስቲንበርግ ጤናማ የልጆች አስተዳደግ የልጆችን የማወቅ ጉጉት ይጨምራል፤ መነሳሳትንና ውጤታማነትን ያጎለብታል ይላል፡፡ እንዲሁም ልጆችን ከጭንቀት ፤ ከድብርት ፤ ከአመጋገብ ችግር ፤ ከዋልጌነትና ከአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት ይታደጋቸዋል፡፡

ጤናማ የልጆች አስተዳደግ የልጆችን ውስጠ ስሜት(emotion) በማነሳሳት ልጆች ደስተኛ እንዲሆኑና የትምህርት ፍላጎታቸው እንዲጨምር ይረዳል፡፡ ከመምህራኖቻቸውም ጋር የተሻለ መግባባትን በመፍጠር የመማር ማስተማር ሄደቱ ምቹ እንዲሆን ያግዛል፡፡

የወላጅ ዋና ኃላፊነት ዘውትር ልጆች ማድረግ ያለባቸውን ነገር ማደረጋቸውንና ተጠቃሚ መሆናቸውን መቆጣጠር ነው፡፡ ቸልተኛና ግዴለሽ ወላጅ የወላጅነት/የአሳዳጊነት ሚናውን በደንብ እየተወጣ እንዳልሆነ በቀላሉ ልጆቻቸው በሚኖራቸው ጠባይ ፤ ማኅበራዊ መስተጋብርና ስነ-ልቦና መረዳት ይቻላል፡፡

ወላጆች ለልጆቻቸው የሚያሳዩት አወንታዊ እንክብካቤና ፈገግታ ልጆች በትምህርታቸው ዘውትር መሻሻልንና ለውጥን እንዲያመጡ ይረዳቸዋል፡፡ በተቃራኒው ልጆች ከወላጆቻቸው በቤት ውስጥ የመሰላቸት ስሜትን የሚመለከቱ ከሆነ እነሱም የወላጆቻቸውን ስሜት ስለሚጋሩ ወደ ትምህርት ቤት በተሰላቸ መንፈስ እንዲሄዱ ይገደዳሉ፡፡ ይህ በመሆኑም ትምህርታቸውን በጥሞና ስለማይከታተሉ እየዋለ ሲያድር የትምህርት ፍላጎታቸውና ውጤታቸው እያሽቆለቆለ ይሄዳል፡፡

ስለልጆቻቸው ትምህርትና ሁለንተናቸው የሚያስቡ ወላጆች ዘውትር ልጆች ከትምህርት ቤት ሲመለሱ ቢቻል አቅፈው ጸጉራቸውን በመዳበስ ስለውሏቸውና አጠቃላይ የትምህርት ገበታቸው ላይ እያሳዩት ስላለው እንቅስቃሴ ዘውትር በቅርበት ይከታተላሉ፡፡ ማታ የሰሩትን የቤት ስራ ስንት እንዳገኙና ምን እንደተሳሳቱ በመጠየቅ ልጆች የተሳሳቱት ነገር ካለ በቶሎ በማረም ለሌላ ጊዜ እንዳይደግሙት ብርታትና ስንቅ ይሆናቸዋል፡፡ ዝቅተኛ ውጤት እንኳን ቢያመጡ ነገ እንደሚያሻሽሉት ያበረቷቷቸዋል እንጂ ጸያፍ ቃላትን በመናገር የልጆቻቸውን ቅስምና ሞራል ለመንካት አይደፍሩም፡፡ ጤናማ ፤ ውጤት ተኮርና አወንታዊ የልጆች አስተዳደግ መከተል አስቸጋሪ ቢሆንም ለልጆች ዕድገት ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው የማይካድ ነው፡፡

አወንታዊና ጤናማ የልጆች አስተዳደግ፡-

አካላዊና ስለልባናዊ ቅጣትን ያስወግዳል
ሽልማትና ቅጣት ላይ ከማተኮር ይልቅ መልካም ስነ-ምግባርን አርአያ በማድረግ ይመራል፡፡
ውጤታማ የአስተዳደግ ዘዴን በመጠቀም ስሜታዊነትን ያስወግዳል፡፡
ቀላልና በአጭሩ ውጤት ማምጣት የሚችለውን የአስተዳደግ መንገድን ይከተላል፡፡
ልጆች ተባባሪ ፤ ኃላፊነት የሚሰማቸውና ደስተኛ እንዲሆኑ ያግዛል፡፡
ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር አወንታዊና ተወዳጅ ግንኙነት እንዲኖራቸው ያስችላል፡፡
ልጆች አድገው ትልቅ ሰው ሲሆኑ ችግሮችን እንዲጋፈጡና ተለዋዋጭ ዓለምን እንዲላመዱ ዕድል ይሰጣል፡፡
ልጆች በትምህርታቸውና በአጠቃላይ ህይወታቸው የተሻሉ እንዲሆኑ በቅርበት ክትትልን ያደርጋል፡፡

ወላጆችም ከዚህ በመነሳት ለልጆቻቸው የትኛው አስተዳደግ ትክክለኛና ሚዛን የሚደፋ መሆኑን ተረድተው ለጤናማ የልጆች አስተዳደግ የሚረዳቸውን መንገድ ቢከተሉ የሚመከር ነው፡፡ ወላጆች ልጆችን መቆጣጠር በሚገባቸው መጠን መቆጣጠር ፤ ነጻነት ሊሰጧቸው በሚገባ ሁኔታ መስጠት እንዲሁም ፤ ኃላፊነት ተሰምቷቸው በሚጓዙበት መንገድ ሊያበረቷቷቸውና ሊደግፏቸው ይገባል፡፡ ገበሬ ያልዘራውን እንደማያጭድ ሁሉ ወላጆችም መልካምነት ያላቸው፤ በትምህርታቸው ጎበዞች ፤ ደስተኞችና በግብረገብነት የተሞሉ ልጆች እንዲኖራቸው ከፈለጉ የሚከተሉትን የአስተዳደግ ዘዴ መመርመር አለባቸው፡፡ ቤተሰብ ትልቅ የትምህርት ተቋም በመሆኑ ልጆች እራሳቸውን ችለው ከቤተሰብ እስኪለዩ ድረስ ተገቢውን ክትትልና ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ልጆች የሚታዩ ብቻ ሳይሆኑ በቤተሰብ ውስጥ የሚደመጡም መሆን አለባቸው፡፡ ልጆች ምንም ዕድሜያቸውና ቁመታቸው ቢያንስም የራሳቸው አስተሳሰብና አመለካከት ስላላቸው ስሜታቸው ትክክል ይሁን አይሁን ወላጆች ሊያዳምጧቸውና ሃሳባቸውን እንዲያካፍሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለባቸው፡፡

ወላጆች ምክንያታዊና በምክንያት የሚያምኑ ካልሆኑ ልጆቻቸውም የእነሱን ፈለግ ይከተላሉ፡፡ የሃሳብ ልዩነትን አይቀበሉም ስሜታቸውን መግለጽና ማስረዳት ስለሚቸገሩ ለትችትና ለመዝለፍ ብቻ ቅድሚያ ይሰጣሉ፡፡ ወላጆች በቤተሰብ ውስጥ የውይይት መድረክን ለልጆች ማስተማር ከቻሉ የሚዘልፍና የሚሳደብ ዜጋ በፍጹም አይኖርም፡፡ የቤተሰብ ውይይትና ምክክር ውጤታማ ፤ ጤናማና በምክንያት የሚያምን ትውልድ ለማፍራት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ልጆችን አይሆንም ፤ አይቻልም እያሉ መከልከል ብቻ ሳይሆን የማይሆንበትንና የማይቻልበትን ምክንያት ጭምር የማወቅ መብት እንዳላቸው መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ መልሳችን አይሆንም ብቻ ከሆነ ነገ ልጆችም አንድን ነገር ለመግለጽ ከአይሆንም ብቻ የተሻለ ምላሽ አይኖራቸውም፡፡ በዚህም መሰረት ወላጆች ለልጆቻቸው ቁሳቁስ ከመግዛት ባሻገር ሃሳብን ማካፈል ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተገንዝበው ስለልጆቻቸው አዋዋል ጠንካራና ደካማ ጎን ሊመካከሩ ይገባል፡፡ ልጆች የሚበሉት ፤ የሚጠጡት ፤ የሚለብስሱትና የትምህርት መርጃ መሳሪያ ስለተሟላላቸው ብቻ መልካም ስነ-ምግባር ይይዛሉ ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ጤናማ ግንኙነትና ተግባቦት ሲኖራቸው ልጆች እያከናወኑት ያለውን ነገር በግልጽ መረዳት ይችላሉ፡፡ካልሆነ ግን ልጆች ወዴት አቅጣጫ እየሄዱ እንደሆነ የማወቅ አጋጣሚው ውስን ይሆናል፡፡ለልጆች አስተሳሰብ ፤ አካላዊ ፤ትምህርት መዳበር፤ ስነ-ልቦናዊና ማኅበራዊ ዕድገት አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችል ጤናማ የአስተዳደግ ዘዴን መከተል ብልህነት ብቻ ሳይሆን ጥሩ ዜጋን መፍጠር መቻል ነው፡፡ መልካም አስተዳደግ ምንም ዓይነት ወጪ የማይጠይቅ በመሆኑና ለሃገርም ለቤተሰብም ጥሩ ስለሆነ ወላጆች ትኩረት ሰጥተው ሊመለከቱት የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ በአጠቃላይ አወንታዊ የልጆች አስተዳደግ የልጆችን ውስጠ ስሜትና ትምህርት በመልካም መልኩ ስለሚያሻሽል ወላጆች ለልጆቻቸው ቁሳቁስና የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ከማቅረብ ባሻገር ገንቢ ምክረ ሃሳብን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

©(በአንቶኒዮ ሙላቱ- zepsychology)
www.tg-me.com/psychoet
ጨዋታ ለልጆች ሁለንተናዊ ዕድገት

ጨዋታ በልጆች ህይወት ውስጥ ብዙ ፍላጎቶችን ያሟላል፡፡ ከብዙ በጥቂቱ ብንመለከት የመነሳሳትና የትኩረት ፤ ተፈጥሯዊ የመናገር ነፃነት ፤ ለውጥን የማወቅና የመከተል ፤ መሻትን የማርካት ፍላጎት፤ እንዲሁም ከባድና አደጋ የሌላቸውን ነገሮችን በመሞከር ፍላጎታቸውን ያሟላል፡፡

በዚህም መሠረት ጨዋታ ለልጆች ዕድገት ቁልፍ ሚና እንዳለው እንረዳለን፡፡ ጄን ፒያጄ ጨዋታን እንደ አዳዲስና  ውስብስብ ነገሮችን የመማሪያ ዘዴና አስተሳሰብን ከተግባር ጋር በማዋሃድ አመለካከትን እንደሚያሰፋ ያትታል፡፡ እንዲሁም ሃርሎክ የጨዋታን ሚና በልጆች ዕድገት ላይ ያለውን ተጽእኖ በአምስት ዋና ዋና ክፍሎች በመክፈል ያስረዳል፡፡

1. አካላዊ ሚና (The physical role)

ቀልጣፋ ጨዋታ ለጡንቻዎች ዕድገት አስፈላጊ ሲሆን የጡንቻ ዕድገት ለልጆች ደህንነትና አካባቢን ለመመለማመድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ ልጆች  ኳስ በመጫወት ፤ በመዋኘት ፤ በመሮጥ ፤ ድንጋይ በመሰብሰብና አቀበት በመውጣት ጡንቻዎቻቸውን ያዳብራሉ፡፡ ከዚህ ባሻገር ጨዋታ የተከማችን ስብ ለማስወገድ ይረዳል፡፡ የተጠራቀመና አገልግሎት ላይ የማይውል እምቅ ሃይል ለልጆች ጥሩ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ልጆችን ስሜታዊ፤ ጭንቀታምና ቁጡ ያደርጋቸዋል፡፡ እዚህ ላይ የጨዋታን ጥቅም ስንመለከት ልጆች ይህንን ሃይል በአግባቡ እንዲጠቀሙና ለጡንቻቸው እድገት እንዲያውሉት ይረዳል፡፡

2. የህክምና ሚና (The therapeutic role)

በመጀመሪያ ደረጃ የተጠራቀመና አገልግሎት ላይ የማይውል እምቅ ሃይል ለልጅ ጥሩ አለመሆኑን ከእላይ ተመልክተናል፡፡ ጨዋታ ይህንን ሃይል ጥቅም ላይ እንዲውል ይረዳል፡፡ ሁለተኛው አስተዋጽኦ ደግሞ ጨዋታ ልጆች ውስጠ ስሜታቸውን ባልተገደበ አካባቢ ወይም ሁኔታ ነፃ ሆነው እንዲገልጹ ያስችላቸዋል፡፡ ለዚህም ነው የጨዋታ ህክምና (play therapy) አንዱና ዋንኛው የልጆችን በሽታ ለማከም እንደ ፈር ቀዳጅነት ትኩረት እየተሰጠው እንደሆነ የምንመለከተው፡፡ እንደ አክሲላይን አገላለጽ የጨዋታ ህክምና (play therapy) የተመሠረተው ጨዋታ የልጆች ተፈጥሯዊና እራሳቸውን የሚገልጹበት መንገድ በመሆኑ ሲሆን ልጆችም በጨዋታ ስሜታቸውንና ችግሮቻቸውን እንዲያስረዱ ዕድል ይሰጣል፡፡ ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ጨዋታ ልጆች የልተሟላ ፍላጎታቸውን ለወላጆቻቸው ወይም አሳዳጊያቸው የሚያስረዱበት ሁነኛ መንገድ በመሆኑ ነው፡፡

3. የትምህርት ሚና (The educational role)

አንድ ልጅ ወላጆቹን እንዲህ ቢላቸው ‘’ዛሬ ትምህርት ቤት ምን እንደ ሰራው ብትጠይቁኝ፤ በቃ ተጨወትኩ ብዬ እመልሳለው፡፡ ምክንያቱም ስጫወት እማራለው፡፡ በስራዬ ደስተኛና ውጤታማ እንድሆን እየተማርኩ ነው፡፡ ዛሬ ልጅ ነኝ ስራዬም ጨዋታ ነው፡፡’’ በማያሻማ መልኩ የልጅነት ዓለሙን አስረድቷል ፤ ስለዚህ ቤተሰቦቹም ሊረዱት ይገባል፡፡

ጨዋታ እንቅስቃሴን መሰረት ካደረገ የትምህርት ሂደት ጋር ሲቀናጅ ልጆች በጨዋታ ብዙ ነገር መማር ይችላሉ፡፡ ጨዋታ የልጆችን ክህሎት ያሳድጋል፤ ነገሮችን እንዲለዩ ፤ እንዲከውኑና እንዲጠቀሙ ይረዳል፡፡ እንደ አክሲላይን ገለፃ ልጆች በጨዋታ ስለ ራሳቸውና ስለሌሎች እንዲሁም ከሌሎች ጋር ስላላቸው ግንኙነት ይማራሉ፤ ስለ ችሎታቸውና የእነርሱ ችሎታ ከሌሎች ጋር እንዴት እንደሚነጻጸር ፤ በተጨማሪም ስለራሳቸው ግልጽና እውነተኛ ማንነት እንዲመሰርቱ ያስችላቸዋል፡፡ በዋናነትም ጨዋታ ሙሉ ወይም ቀጥተኛ ኃላፊነት የማይወስዱበት ስለልጆች ለማወቅ የሚረዳ ሙከራ (experimentation) ነው፡፡ ለልጆች ዕድገትና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማሻሻል ጨዋታ አንደ አንድ ግብአት ያገለግላል፡፡ ወላጅ/ቤተሰብ የልጆቻቸው የመጀመሪያ መምህራን ሲሆኑ ፤ ትምህርቱም የሚጀመረው በጨዋታ መልክ ሲሆን ጨዋታ  ውስጥ ልጆች ስለሚከተሉት መርህና ደንብ እንዲሁም ምን እንደሚጠበቅባቸው ጥቆማ በመስጠት ሲያድጉና ትልቅ ሲሆኑ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር እንዴት መላመድና  ቅርርቦሽ መፍጠር እንዳለባቸው መልዕክት ማስተላለፊያ መንገድ ነው፡፡

4. ማኅበራዊ ሚና (The social role)

ልጆች ተቀባይነት ያላቸውንና የሌላቸውን ነገሮች በጨዋታ ውስጥ ይማራሉ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ጨዋታ በቡድን ስለሚከናወን ትክክል እና ትክክል ያልሆኑ ሁኔታዎችን እንዲያውቁ ወይንም እንዲማሩ ይረዳቸዋል፡፡ በተጨማሪም ሰጥቶ መቀበልን እንዲያውቁ ያስችላቸዋል፡፡

ጨዋታ በቤት ውስጥ ያለውን ውጥረት ይቀንሳል፡፡ ልጆች ቤተሰባቸውን በሚያስቸግሩበት ሰዓት ከአቻዎቻቸው ጋር እንዲጫወቱ ከተደረጉ ቤተሰብ ትንሽ መተንፈሻ እንዲያገኝ ያግዛል፡፡

5. ሞራላዊ ሚና (The moral role)

በጨዋታ ውስጥ ልጆች በቡድናቸው ውስጥ ትክክልና ሞራላዊ የሆኑ ነገሮችን ይማራሉ ወይም ያውቃሉ፡፡ በተጨማሪም ጥሩን ከመጥፎ እንዲለዩ ያስችላቸዋል፡፡ እንደ ባርተን አገላለጽ ልጆች በጨዋታ መሃል ቅንነትን ፤ ታማኝነትን ፤ እራስን መቆጣጠርን ይማራሉ፡፡ በአጭሩ ጨዋታ ልጆችን  ስነ-ምግባር ከምናስተምርባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡

ቤተሰብ ከልጆቹ ጋር የሚጫወትበት ጊዜ ሊኖረው ይገባል፡፡ ጨዋታውም ልጆች ጨቅላ እያሉ ሊጀመር ይገባዋል፡፡ ልጆች ፈገግታን ሲያሳዩ ቤተሰብም አጸፋውን ሲመልስ አሁን ወደ ጨዋታ እየተገባ ነው፡፡ ይህም ለአካለቸው ቅልጥፍናና አእምሮአዊ አስተሳሰብ መጎልበት ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ ልጆች ጤነኛ ሆነው እንዲያድጉ ጨዋታ ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት 75% የሚሆነው የአእምሮ ዕድገት የሚከናወነው ልጆች ከተወለዱ በኋላ ነው ለዚህም ዕድገት ጨዋታ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ምክንያቱም ጨዋታ አንጎልን በማነቃቃትና የተለያዩ መረጃዎችን ከሴሎች ጋር በመለዋወጥ የእንቅስቃሴና ነገሮችን የመጨበጥ/የመሸከም ክህሎትን በቀላሉ እንዲያዳብሩ ስለሚያስችላቸው ነው፡፡

በአጠቃላይ ጨዋታ ለልጆች ዕድገት አስፈላጊና ወሳኝ ነው፡፡ ጨዋታ ከጨቅላነት ዕድሜ እስከ ህይወት ጀምበር መጥለቅ የሚዘልቅ ነው፡፡ ጨዋታ ልጆች ምን መማርና ማወቅ እንዳለባቸው ፤ እንዲያስቡ ፤ ችግሮችን እንዲፈቱ ፤ እንዲበስሉና ደስታን እንዲያጣጥሙ ያደርጋቸዋል፡፡ ጨዋታ ልጆች ከእሳቤዎቻቸው ፤ ከአካባቢ፤ ከቤተሰቦቻቸው እና ከዓለም ጋር እንዲተዋወቁ ዕድል ይሰጣል፡፡ በልጆች ጨዋታ የቤተሰብ ተሳትፎ ለልጆች ብቻ ሳይሆን ለቤተሰብም ጠቃሚ ነው፡፡ ከልጆች ጋር መጫወት ለረጅም ጊዜ አብሮ የሚዘልቅ ጥብቅ ግንኙነትንና ታማኝነትን ይፈጥራል፡፡ ወላጅና ልጅ አብረው ሲጫወቱ የጋራ የሆነ እሴትን ለመጋራት በር ይከፍታል ፤ አግባቦትን (communication) ይጨምራል ፤ ልጅን ለማስተማር ምቹ ሁኔታን ከመፍጠሩም ባሻገር ልጆች የወላጆችን ዕርዳታ በሚሹ ሰዓት አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ ያስችላል፡፡ በተጨማሪም በጨዋታ ጊዜ ልጅና ወላጅ የሃሳብ ልዩነትን እንዲረዱና እንዲቀበሉ/እንዲፈቱ ምቹ ሁኔታን ያመቻቻል፡፡ ከዚህም ባለፈ ወላጆች ዓለምን በልጆች መነጸር እንዲመለከቱ ይረዳል፡፡

ከላይ የተመለከትናቸው ጉዳዮች ጨዋታ ለልጆች ዕድገት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት የሚያሳዩ ጠቋሚ ነጥቦችን ነው፡፡ በመሆኑም ለልጆች አካላዊ ፤ አእምሮዊና ስለ-ልቦናዊ ዕድገት ጨዋታ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ጨዋታ ይህንን ያህል ለልጆች ዕድገት አስተዋጽኦ እንዳለው ከተረዳን ልጆች በቤት ውስጥም ይሁን ትምህርት ቤት መጫወት የሚያስችላቸው በቂ ጊዜና ቦታ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ልጆች ትክክለኛውን የዕድገት መንገድ እንዲከተሉ ጨዋታ የግዴታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ እንደ
ሚሊቻምፕ ገለፃ ጨዋታ አንድን ልጅ ሙሉ ሰው ሆኖ “play helps the child to develop as a person” እንዲያድግ ይረዳዋል ይላል፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
@psychoet
እንደምን ዋላችሁ የሥነልቡና ፔጅ ቤተሰቦች!
ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በጽሑፍ ከምንለጥፋቸው ትምህርቶች በተጨማሪ የተለያዩ የስነልቡና ትምህርቶችን ፣ አነቃቂ ንግግሮችን ፣ የሕይወት ክህሎት ስልጠናዎችን በYouTube ቻናላችን መለጠፍ እንጀምራለን ፡፡ ስለዚህ ካሁኑ ቻናላችንን Subscribe እንድታደርጉና ጓደኞቻችሁን እንድትጋብዙ እንጠይቃለን ፡፡

Subscribe Channel : youtube.com/thenahusenaipsychology

Telegram : www.tg-me.com/psychoet

Facebook : fb.com/psychologyet
2024/09/30 23:43:17
Back to Top
HTML Embed Code: