Telegram Web Link
ከሰዎች ጋር ያለንን ተግባቦት ለማዳበር የሚረዱ ጠባያት
1. ጥሩ አድማጭ መሆን

ተግባቦትን ለማዳበር ከሚረዱ ጠባያት ዋነኛው ጥሩ አድማጭነት ነው፡፡ ሰዎች በሚናገሩበት ሰዓት ተናግረው እስኪጨርሱ አለማቋረጥ፤ ዓይናቸውን መመልከት፤ በንግግር መሃልም መረዳታችሁን ለማመልከት ጭንቅላታችሁን ወደ ላይና ወደ ታች መነቅነቅ፤ ተናግረውም ከጨረሱ በኋላ መናገር የፈለጉትን ሃሳብ በጥቂት ቃላት ማጠቃለል የጥሩ አድማጭነት ምልክቶች ናቸው፡፡

2. የፊት ገጽታችንና የእጅ እንቅስቃሴአችን

በንግግር ወቅት ያለን የፊት እና የእጅ እንቅስቃሴ ስለምንናገረው ሃሳብ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ አለ፡፡ ለምሳሌ አስደሳች ሃሳብ ለመናገር እየሞከርን የፊት ገጽታችንን ማኮሳተር፤ ማጨማደድ እና የዓይን ሽፋሽፍትን መሰብሰብ ለአድማጭችን ተቃራኒ መልዕክት ይልካል፡፡ ስለዚህም ከምንናገረው ሃሳብ ጋር ውህደት ያለው የፊት ገጽታና የእጅ እንቅስቃሴ ሊኖረን ይገባል፡፡

3. ፍሬ ሃሳቡን በተወሰኑ ቃላት መግለጽ

የሰው ልጅ ትኩረትን ሰጥቶ አንድን ድርጊት መከወን የሚችው ለጥቂት ደቂቃዎች ስለሆነ በንግግር ወቅት በጥቂት ቃላት የምንፈልገውን ሃሳብ መግለጽ ይገባል፡፡ የምናናግረውም ሰው በዚያች በሚያናግረን ሰዓት ብዙ የሚያሳስቡት እና ጊዜ ሊሰዋላቸው የሚፈልጋቸው ብዙ ጉዳዮች እንዳሉት በማመን አጭርና በተመረጡ ቃላት የተሟላ ንግግር ብናደርግ ጥሩ ተግባቦት ይኖረናል፡፡

4. ትኩረት የሚያሳጡ ነገሮችን ማራቅ

ተንቀሳቃሽ ስልክ እንዲህ የዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ዘልቆ በገባበት ጊዜ ውስጥ ከሰዎች ጋር በምንነጋገርበት ወቅት የምንጠቀማቸው ከሆነ ተገቢ ያልሆነ ትርጉም ይሰጣል፡፡ ለምናናግረው ሰው ውይም ስሚናገረው ሃሳብ ግድ እንደሌለን ያሳብቃል፡፡ ስለዚህም በንግግር ወቅት ተንቀሳቃሽ ስልካችንን ጨምሮ የምንከውነውን ማንኛውንም ስራ አቁመን ሙሉ ትኩረታችንን በመስጠት ልናዳምጥ እንዲሁም ምላሽ ልንሰጥ ይገባል፡፡

5. አቀማመጥን ማስተካከል

ወደ ጀርባችን ተለጥጦ መቀመጥ፤ ጀርባችንን መስጠት ወይም ፊትን ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ ማዞርን የመሳሰሉ አቀማመጦች ተግባቦትን አስቸጋሪ ሊያደርጉ ስለሚችሉ ወደ ምናናግረው ሰው አቅጣጫንን ማስተካከል እንዲሁም ጠጋ በማለት አቀማመጣችንን ማስተካከል ይገባናል፡፡

6. የሚያናግሩትን ሰው ስሜት መረዳት

እጅግ የሚያሳዝን ታሪክ እየተነገረን ስሜታቸውን ከቁብ ሳንቆጥር ቅጭም ባለ አኳኋን “የምተለው ይገባኛል” ብንል ተአማኒነት ያሳጣል፡፡ የተናጋሪውን ስሜት ወደእኛም ዘልቆ እንዲገባ መፍቀድ ከቻልን መልካም ተግባቦት ይኖረናል፡፡

7. ንግግርህ ፍሰት ያለው እና ያልተዘበራረቀ እንዲሆን ማድረግ

ከአንድ ሃሳብ ወደ ሌላ ሃሳብ መዝለል ውልና ማሰሪያ የሌለው ንግግር፤ ውይይትና ክርክር ማድረግ መጨረሻቸው የማያምር ነው፡፡ ስለዚህም ትኩረትን በአንድ ሃሳብ ላይ ብቻ በማድረግ ያልተዘበራረቀ እንዲሁም ፍሰቱን የጠበቀ ንግግር ማድረግ እርሱንም አጠናቆ ወደሌላው መሻገር ተገቢ ነው፡፡

8. በየንግግሩ መሃል የሚገቡ ድምጾችንና የቃላት ድግግሞሽን ማስቀረት

ብዙውን ጊዜ ሰዎች ሃሳባቸውን ከመከታተል ይልቅ ወደዚህ ጽምጸት አትኩረው እንዲያፌዙ ይጋብዛል፡፡ ስለዚህም “አ….. “ “አም….” የሚሉ ድምጸቶችን ማስወገድ ይገባል፡፡ እንዲሁም “እና” ፤ “ማለት ነው” እና “ምናምን” የሚሉ ቃላትን መደጋገም ንግግራችንን አሰልቺ ሊያደርጉት ስለሚችሉ ማስወገድ ይገባል፡፡

9. የድምጻችንን ቃና እንደየሃሳባችን ማቀያየር

በንግግር ወቅት አንድ ቃና ብቻ ያለው ወጥ ንግግር ማድረግ፤ ለሃዘኑም ለደስታውም ለቁጣውም ተመሳሳይ ድምጸት መጠቀም የአድማጭ ትኩረት እንዲበታተን የሚጋብዝ ነውና አንዴ ከፍ አንዴ ዝቅ አንዳንዴም ለጥቂት ሰኮንዶች ዝም እያልን በተለያየ ቃና የታጀበ ንግግር ማድረግ የአድማጭን ትኩረት ለመሳብና እስከ ንግግሩ መጨረሻ ሰብስቦ ለማቆየት ይረዳል፡፡

ቴሌግራም ቻናሌ ፡ www.tg-me.com/psychoet
ለሌሎች #Share በማረግ ተግባቦታችንን እናሳድግ

©Zepsychology.com (በዘመነ ቴዎድሮስ)
GreenFire-June-2020_160620152301.pdf
985.4 KB
👆👆👆👆Green Fire 6ተኛ እትም አንብቡኝ ትላችኋለች።
@psychoet
ሰላም ቤተሰቦቼ !

ዛሬ በጣም ደስ የሚል ቀን ነው። ካለፈው ህይወታችን የተሻለ ነጋችን የምንሰራበት ውብ ቀን ነው።

ዛሬ አንድ ወዳጄን ላስተዋውቃችሁ!
"ዛሬም ነገም #ሰው_ሆኖ_አለመቻል_አይቻልም! " በሚለው ንግግሩ ይታወቃል
ተመስገን አብይ

ዛሬ ልደቱ ነው እና በዛውም እንኳን ተወለድክ ማለት እፈልጋለሁ 🎊🎉🎊🎊🎊🎉 ፡፡ በቴሌግራም ፔጁ የተለያዩ የስነልቦናዊ ጉዳዮችን እያነሳ ንግግር ያደርጋል ፣ ጥሩ ትምህርትም ያቀርባል ፡፡በሬዲዮና በቴሌቪዥንም እየቀረበ ንግግር ያደርጋል ፡፡ በተለይ ወደፊት አሰልጣኝ ፣ አነቃቂ ንግግር ተናጋሪ ፣ ሰዎችን አማካሪ መሆን የምትፈልጉ ወጣቶች በቴሌግራም ቻናሉ ቤተሰብ ሁኑት ፡፡
👇👇👇👇
@temuabiy @temuabiy @temuabiy
ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ መጨነቅን ለማቆም ቀላል ዘዴዎች
Telegram www.tg-me.com/psychoet

‘’የማይባል ነገር ተናገርሁ እንዴ? እንዴት እንደዚህ አደርጋለሁ? ሰዎች እኮ መሃይም :ገገማ:የሚያናድድ ሰው ነው/ነች ይሉኝ ይሆናል’’ እያልን ራሳችንን የምናስጨንቅ ስንቶቻችን ነን! ሌሎች ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ በመጨነቅ አእምሯችንን በጨለማ ቦታ እንዲንከራተትና ራሳችንን በመጠራጠር የስጋት ስሜት እንዲሰፍንብንና እንዳንረጋጋ እያደረግን መሆኑን ልናውቅ ይገባል:: ለነገሩ ሁላችንም ሰዎች ስለእኛ ያላቸው ሃሳብ/አስተያየት ምን ይሆን ብለን መጨነቅ እንደሌለብን እናውቃለን ወደ ተግባር ለመቀየር ግን ስንቸገር እንታያለን:: ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዘዴዎች ብንጠቀምባቸው ይረዱናል!

1. የሰዎችን አዕምሮ ማንበብ እንደማንችል መረዳት፡- እስኪ ሰዎች ስለእኛ የሚያስቡትን በእርግጠኛነት ማወቅ እንችላለን? ብዙ ጊዜ ነገራትን ሳናጣራ ይሆናል በማለት ብቻ ማወቅ እንደምንችል ነው የምናስበው ይህ አስተሳሰባችን ደግሞ ለህይወታችን ፀር ወደሆኑ ድምዳሜዎች/ዉሳኔዎች ይመራናል::ስለዚህ እነዛ ሰዎች ሃሳባቸውን የሚገልጹበትን ዕድል አግኝተው ሃሳባቸውን እስካልገለጹልን ድረስ ስለምን እንደሚያስቡ ማወቅ በፍጹም አንችልም፡፡

2. በቋሚነት ለሚጠቅመን ነገር መስራት:- ከሌሎች ሰዎች የሚሰነዘሩ የኩነኔ አስተያየቶች በእርግጥም እኛን ይጎዱናል ነገር ግን ከእነዚህ ሰዎች የሚመጣውን አሉታዊ ምላሽ በመፍራት የምናጣቸው/የምናሳልፋቸው መልካም ዕድሎች ጥለውብን ከሚያልፉት የአእምሮ ጠባሳ አይበልጥም፡፡ እነዚህ የኩነኔ/አሉታዊ አስተያየቶች የሚያደርሱብን ጉዳት ቅጽበታዊ ሲሆን ባጣናቸው/ባመለጡን መልካም ዕድሎች ምክንያት የሚደርስብን ጸጸትና ቁጭት ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ስር እየሰደደና እያደገ ነው የሚሄደው፡፡ ስለዚህ በቋሚነት የሚጠቅመንን ነገር ለማግኘት ጊዜያዊ የሆኑ ተቀባይነት ማጣትን ለመቀበል ፈቃደኞች እንሁን::

3. ራስን ከመኮነን/በራስ ላይ ከመፍረድ መቆጠብ:- እስኪ ሰዎች ምን ይሉን ይሆን ብለን የምንጨነቅበትን ሃሳብ ለሰከንድ ቆም ብለን እናስበው! በእርግጠኝነት እኛ ለራሳችን የምናስበውን ነገር ላይ ነው ሌሎችም እንደዚ ያስባሉ ብለን የምንሰጋ፡፡ ስለዚህ በራሳችን ላይ መፍረድን አቁመን(ራስን ከመኮነን ተቆጥበን) እኛነታችንን ከተቀብለነው ወይም ለራሳችን ጥሩ ግምት ከሰጠን ሌሎቹ ስለእኛ ለሚሰጡት/ለሚያስቡት ሃሳብ ፍርሃትና ስጋት አይኖረንም ማለት ነው፡፡

4. ሌሎች ሰዎችን መኮነንን/በሌሎች ላይ መፍረድን ማቆም፡- ሰዎችን እየገመገምን፡እየኮነንና እየፈረድንባቸው የምንኖር ከሆነ እነሱም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚፈርዱብን ነው የምናስበው፤ ስለዚህ በእነሱ ላይ ከመፍረድ ይልቅ ህይወታችንን ለማሻሻልና ለማደራጀት እንደሚያግዙን ቆጥረን ብናደንቃቸውና ብናበረታታቸው የበለጠ ተጠቃሚዎች መሆን እንችላለን፡፡

5. ስለእኛ አለመሆኑን መረዳት፡- ሰዎች በራሳቸው እይታ ከደረሰባቸው ክስተት፡ ቁስል፡ ፍራቻና እንከን የተነሳ ለነገሮች የተለያዩ አሉታዊ ምላሾችን ይሰጣሉ ነገር ግን የእነሱ ምላሽ ከእኛ ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባናል፡፡ ለምሳሌ የሆነ ቢዝነስ ለመጀመር ብንወስንና አንድ ሰው ”እመነኝ ይህንን ስራ ከጀመርህ በሚቀጥሉት ወራት አሊያም ዓመታት ምንም ዓይነት የእረፍት ጊዜ አይኖርህም” ቢል ሰውዬው የተናገረው ቢዝነስ መጀመር ላይ ያለውን ሃሳብ/አመለካከት እንጂ እኛን በተመለከተ እንዳልሆነ ለይተን መረዳት ይጠበቅብናል::

6. በሚያስደስተን ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ:- ይህን ባደርግ ሰዎች ይፈርዱብኛል በማለት የሚያስደስቱንን ተግባራት ከማድረግ የምንገደብ ከሆነ(የማኅበረሰቡን እሴቶች በጠበቀ መልኩ) ጊዜያችንን ምንም ዓይነት ጥቅም በሌለው ጭንቀት እያባከንነው መሆኑን እናስተውል፡፡ ስለዚህ በህይወታችን ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የሚችለውን ብርቅ የሆነውን አቅምና ኃይላችንን በመሸርሸር ፈንታ እኛን በሚያስደስቱን ነገራት ላይ ትኩረት ልናደርግ ይገባል፡፡

7. የሚያውኩንን ነገሮች መለየት፡– ሌሎች ሰዎች አሉታዊ በሆነ መልኩ ይገመግሙናል/ይፈርዱብናል ብለን የምንጨነቀው ምናችንን በተመለከተ ነው? በስራችን ሁኔታ: ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት: ምናልባትም በክህሎታችንና ነገሮችን በመመርመር ባለን አቅም ሊሆን ይችላል:: ስለዚህ በውስጣችን መረጋጋት እንዳይኖር የሚቀሰቅሱ ነገሮችን መለየትና ማሻሻል ከቻልን ማሻሻል አሊያም እንዳሉ መቀበል ያስፈልጋል:: ምክንያቱም ከሁኔታዎች ጋር ሰላም መፍጠር ከቻልን የሰዎች አጸፋዊ ምላሽ አያስጨንቀንም ማለት ነው::

8. ራሳችንን መቀበል:– ፍጹም አለመሆናችንን፡ እንከንና ድክመቶች እንዳሉን መቀበል ነገር ግን አቻ የሌለን(ልዩ) በዓለም ላይ እኛን የሚመስል ሰብዕናና ተሰጥኦ የታደለ ሰው እንደሌለና ወደፊትም እንደማይኖር ልናስተውል ይገባል፡፡

9. አጸፋዊ ምላሾችን መጠበቅ/ተስፋ ማድረግ፡- በሰዎች ዘንድ የሚፈጠረውን አጸፋዊ መልስ በመፍራት ፈንታ ያ ምላሽ ሊፈጠር እንደሚችል አስቀድመን ተስፋ ማድረግ አለብን(የሰዎችን ስሜት ለመቀስቀስ መፍራት የለብንም) ምክንያቱም በሰዎች ዘንድ አሉታዊም ይሁን አዎንታዊ ምላሽ መፍጠር ካልቻልን ምናልባትም ራሳችንን የመሆን ድፍረቱን ልናጣ እንችላለንና፡፡

10. እየኮነኑን/እየፈረዱብን ነው ብለን ካሰብናቸው ሰዎች ጋር ማውራት፡- እንዲያው ሁኔታዎች ተመቻችተውልን ስለእኛ መጥፎነት ያስባሉ/እየፈረዱብን ነው ብለን ከምናስባቸው ሰዎቸ ጋር ተቀራርበን ብናወራ እስከምንገረም ድረስ ምንም ባለጠበቅነው ሁኔታ አዕምሯቸው በብዙ ጭንቀቶች እንደተሞላ ልናውቅ እንችላለን፡፡ ማን ያውቃል ልክ እኛ እንደምንጨነቀው እነሱም ሌሎች ሰዎች ስለእነሱ ምን ሊያስቡ/ሊሉ በሚችሉት ሃሳብ እየተጨነቁ ሊሆን ይችላል እኮ፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ግልጽ በማድረግ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ተቀራርበን ሃሳብ ማንሸራሸር ያስፈልጋል::

በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩትን ሃሳቦች ወደ ተግባረ ከቀየርናቸው እኛም መቀየር እንችላለን!

(በአለበል አዲስ)
©Zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
ዛሬ 1⃣5⃣0⃣0⃣0⃣ ቤተሰቦች ደርሰናል !

የዚህ ፔጅ አላማ ሰዎችን በማስተማር መለወጥ ፣ አዳዲስ ሃሳቦችን ማንሳት እንዲሁም የሚታወቁ ግን የተረሱትን ደግሞ ማስታወስ ነው ፡፡ ሁላችሁም በዚህ ፔጅ ጥሩ ነገር እንዳገኛችሁ አስባለሁ ፡፡

ለሁላችሁም ደስ የሚል መልካም ሕይወት እመኝላችኀለሁ ፡፡
ናሁ|Nahu
@Psychoet
ሳይኮቢዝ #2

ሰላም ፥ እንደምን አላችሁ !

ዛሬ ስለስራ ፈጠራ መሰረታዊ ሀሳቦች እናያለን ፡፡ በማንኛውም ቢዝነስ ላይ የተሰማሩ / ለመሰማራት ያሰቡ ሰዎች በዘርፋቸው ትልቅ ስኬት ለማግኘት የተጠቃሚዎቻቸውን ልብ መግዛት ፣ ተአማኒነት ማግኘት አለባቸው ፡፡ ለዚህ ደግሞ የስራ ፈጣሪዎቹ ስነልቦና ወሳኝ ነው ፡፡

ሥነልቦና ከሰዎች ባህሪ ጥናት ጋር በከፍተኛ ቁርኝት አለው ፡፡ ይሄም ለስራ ፈጣሪው 1. ራሱን ለስራው እንዲያዘጋጅ ይረዳዋል 2. የደንበኞቹን የመግዛት ባህሪይ ( Customer buying behavior ) እንዲያውቅ ያግዘዋል ፡፡

የሳይኮሎጂ እውቀት በስራ ፈጠራ ላይ 1. ምርታማነትን 2. ተነሳሺነትን 3. ቅልጥፍናን (ብልህነትን ) እንዲኖረን ያስችለናል ፡፡

በሚቀጥሉት ሳምንታት ወደ ቢዝነስ ሀሳቦችና እንዴት ባለንበት ስፍራ የራሳችንን ስራ መፍጠር እንደምንችል እንመለከታለን ፡፡

🎡@🎡መልካም ቀን
#Join #Join #Join
🔸🔹 ↘️💯💯💯↙️🔸🔹
🚗 www.tg-me.com/Psychoet 👍
🚕 www.tg-me.com/Psychoet 👍
መልካም ቀን ይሁንላችሁ ፣

አንድ ቀን አንድ አባት ከከተማ እየወጡ ሳለ ዲዮጋንን መንገድ ላይ ያገኙትና
👨‍🦳 "ከየት ነዉ የምትመጣው?" ሲሉት
👨"ከገሃነም" ሲላቸው በመደናገጥ

👨‍🦳"ደሞ! ምን ልትሠራ ሄድክ?" አሉት እሱም
👨"እሳት ፍለጋ...እሳት ልጭር"

👨‍🦳"ምነው ታዲያ ባዶ እጅህን ተመለስክ?" ሲሉት::
👱‍♂"እናንተ ራሳችሁ የምታመጡት እሳት እንጂ እዚህ እሳት የለም" ብለው መለሡኝ አላቸው ይባላል::

#ሰው_ሆኖ_አለመቻል_አይቻልም
©@temuabiy
#ሼር #ሼር #ሼር
#ክፍል_23
#አራቱ የወላጅ አይነቶችና በልጆች አስተዳደግ ላይ ያላቸው ተፅዕኖ
www.tg-me.com/psychoet
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

የወላጆች አስተዳደግ ሁኔታ በልጆቻቸው ከአካላዊ እስከ ሥነልቦናዊ ውቅር ተፅዕኖ ያደርግባቸዋል ፡፡ በመሆኑም ወላጆች ምን አይነት አስተዳደግ ሁኔታ መምረጥ እንዳለባቸው ሊወስኑ ይገባልጠ፡፡ ይሄም ለጤነኛ ለልጆች አስተዳደግ ጉልህ ሚና አለው ፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት 4 አይነት የወላጅ አይነቶች አሉ እነርሱም :-

Authoritarian ፦ ፈላጭ ቆራጭ

Authoritative ፦በልጆቻቸው እምነት የሚጥሉ

Permissive ፦ ልጆቻቸውን ሁሌ ነፃ የሚያረጉ (እሺ ባዮች)

Uninvolved ፦ ልጆቻቸው ህይወት ላይ በቂ ትኩረት የማያደርጉ (ዞር ብለው የማያዩ )

እያንዳንዱ የአስተዳደግ መንገድ የራሱ የሆነ መገለጫዎች ያሉት ሲሆን በልጆች ሁለንተናዊ ሕይወት ላይ የሚያመጣው አወንታዊና አሉታዊ ሚና አለው ፡፡

📌ፈላጭ ቆራጭ

እነዚህ ወላጆች ልጆቻቸውን አብዝተው የሚጨቁኑ ሲሆኑ የልጆችን ስሜት የማይረዱ ፣ ሀሳብ አስተያየት የማይቀበሉ ናቸው ፡፡ እኔ ባልኩት መንገድ ብቻ ሂድ ብለው ልጆችን የሚያሳድጉ ናቸው ፡፡

የዚህ አይነት ወላጅ ያሳደጋቸው ልጆች ብዙ ጊዜ የተግባቦት መጠናቸው የቀነሰ ፣ ሰው በተሰበሰበበት ማውራት የሚፈሩ ፣ በራሳቸው መተማመን የሌላቸው ይሆናሉ ፡፡ ነገር ግን የተሻለ ስርአት ያላቸው ናቸው ፡፡

📌በልጆቻቸው እምነት የሚጥሉ
እነዚህ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር የሚያስቀምጡት የጋራ ህግ ፣ ግብ ያላቸው ሲሆኑ ከልጆቻቸው ጋር ጥሩ ግንኙነት የሚፈጥሩ ናቸው ፡፡ የልጆቻቸውን ስሜት የሚረዱና ልጆቻቸውን በጥንቃቄ የሚጠብቁና ልጆቻቸው ያልተገባ ባህሪይ እንዳያዳብሩ ከጅምሩ የሚቆጣጠሩ ናቸው ፡፡ልጆቻቸውን በቅጣት ከማስተማር ይልቅ ጥሩ ነገር ሲሰሩ በመሸለምና በማበረታታት ለመቆጣጠር ይሞክራሉ ፡፡

በዚህ ቤተሰብ የሚያድጉ ልጆች ሀላፊነት የሚሰማቸውና ሀሳባቸውን የሚገልፁ ናቸው ፡፡

📌እሺ ባዮች

እነዚህ ወላጆች ልጆቻቸውን ከልክ በላይ አሞላቀው የሚያሳድጉ ፣ ልጆችን እንደ ልጆች ብቻ የሚያዩ ናቸው ፡፡ በተጨማሪም ከወላጅነት ይልቅ የጓደኛነት ባህሪ ለልጆቻቸው የሚያሳዩና የልጆችን ሁሉን ጥያቄ እሺ የሚሉ ናቸው ፡፡

በዚህ ቤተሰብ ውስጥ ያደጉ ልጆች ብዙ ጊዜ በትምህርታቸው ዝቅተኛ የመሆን እድላቸው የጨመረ ነው ፡፡

📌ልጆቻቸው ህይወት ላይ በቂ ትኩረት የማያደርጉ

እነዚህ ወላጆች ደግሞ ልጆች ራሳቸውን እንዲያሳድጉ የሚጠብቁ ናቸው ፡፡ የልጆቻቸው ፍላጎት ላይ ጊዜና ጉልበት የማያባክኑ ልጆቻቸውን የማይቆጣጠሩ ናቸው ፡፡ ትኩረታቸው የግል ስራቸው ፣ ሕይወታቸው ላይ ያረጋሉ ፡፡

በዚህ ቤተሰብ ያደጉ ልጆች ለራስ ያላቸው ግምትና ክብር ዝቅተኛ ነው ፡፡

🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
ሁሉም የወላጅ (የአስተዳደግ) አይነቶች የራሳቸው የሆነ አወንታዊና አሉታዊ ጎን ቢኖራቸውም ከሁሉም ለልጆች አስተዳደግ ተመራጭ የሚሆነው ሁለተኛው ነው ፡፡ ይህን አይነት የወላጅነት ሚና በመወጣት ቤተሰብን ብሎም ሀገርን በመልካም መገንባት ይቻላል ፡፡


በዩቲዩብ የምንለቃቸውን ትምህርቶች ለማግኘት ቻናላችንን Subscribe አድርጉ
youtube.com/thenahusenaipsychology
❖_____________________________❖
ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !

የሳምንት ሰው ይበለን!
❖__________________________________❖

ስለ ሳይኮሎጂ የበለጠ ለማወቅ ፔጁን ይከታተሉ ለወዳጆችዎ ያጋሩ

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
ለለውጥ መነሳሳት
Telegram : www.tg-me.com/psychoet

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

 8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

 10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡

መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ!
#Share #Like ማረግ ደስ ይላል
www.tg-me.com/psychoet

(በአንቶኒዮ ሙላቱ) ©Zepsychology
በዚህ ፔጅ በሚነሱ ሀሳቦች ላይ የበለጠ ለማወቅና ለመረዳት ፍላጎት ያላቸውን ጓደኞቻችሁን ጋብዙ ፡፡ የምፅፋቸው ሀሳቦችን በቀጥታ ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ ፡፡
www.tg-me.com/psychoet
www.tg-me.com/psychoet
www.tg-me.com/psychoet
ምስጋና እና ዘርፈ ብዙ ጥቀሞቹ
Telegram : www.tg-me.com/psychoet

በርካታ ጥናቶችም የምስጋና ባህል በተቻለ መጠን መዳበር እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡ ከእነዚህ ጥናቶች መካከል የ “Positive Psychology” መስራች ሴሊግማን 411 ሰዎች ላይ ያካሄደው ጥናት ቀዳሚ ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው የተለያዩ አዎንታዊ ሀሳቦች እና ድርጊቶች ያላቸውን ውጤት በመለካት (Testing) ሲሆን ምስጋና ከሁሉም የላቀ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ታውቋል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በሕይወታችን ትልቅ ቦታ አለው የሚሉትን እና በሚገባ አመስግነው ለማያውቁት ሰው የምስጋና ደብዳቤ ፅፈው በራሳቸው እጅ እንዲያደርሱ ከተደረገ በኋላ ውጤቱን ተጠንቶ ከፍተኛ የደስታ ስሜት ተሳታፊዎቹ ላይ ታይቷል፡፡ ለውጡ ይበልጥ አስደናቂ ሊሆን የቻለው የተፈጠረው የደስታ ስሜት ለብዙ ወራት መቆየት በመቻሉ ጭምርም ነው፡፡ በዚህ መሰረት ከየትኛውም ድርጊት በበለጠ መልኩ ምስጋና አመስጋኙን ደስተኛ የማድረግ ኃይል እንዳለው ታውቋል፡፡

የምስጋና ጥቅሞች

#ደስተኛ_ያደርገናል
በቀን ለአምስት ደቂቃ ያህል ማመስገን ከአማካይ ጤንነት በላይ 10% ሁለንተናዊ ጤንነትን ያሻሽላል፡፡

#ሰዎች_እንዲወዱን_ያደርጋል
በሁለት የተለያዩ ጥናቶች ከአብዛኘው ሰው 10 % በላይ የሚያመሰግኑ ሰዎች 17.5 % ከሌሎች የበለጠ የሰው መውደድ እንዳላቸው ታውቋል፡፡ ምስጋና ሰዎች እምነት እንዲጥሉብን፣ እንዲቀርቡን እና እንዲወዱን ያደርጋል፡፡

#በሥራ_ቦታ_ስኬታችንን_ይጨምራል
ምስጋና የተሻለ መሪ፣ ተግባቢ፣ የውሳኔ ሰው እና ስኬታማ እንድትሆኑ ያግዛል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ምስጋና ጤናማ ስሜት እንዲኖረን፣ ቁሳዊ አመለካከታችን (Materialism) እንዲቀንስ፣ ራስ ወዳድነት እንዲቀንስ፣ ለራሳችን ያለን አመለካከት እንዲሻሻል፣ ጥሩ እንቅልፍ እንድንተኛ፣ ረጅም እድሜ እንድንኖር ወዘተ ያደርጋል፡፡

ምስጋና ባህል እንደመሆኑ መጠን ደግመን ደጋግመን እስከተለማመድነው ድረስ ይሻሻላልም፡፡ ይህንን ለማድረግ የምስጋና ደብዳቤ መጻፍ፣ ጊዜ ቢታጣ እንኳ በልቦናችን ማመስገን፣ የምስጋና የግል ማስታወሻ መፃፍ፣ በረከቶቻችንን መቁጠር፣ ፀሎት የመሳሰሉት የምስጋና ባህላችንን ለማሻሻል የሚረዱ ልምምዶች ናቸው፡፡

_______________
ይህን ካነበባችሁ አይቀር የማመስገን ባሕልን ዛሬውኑ መለማመድ ጀምሩ ፡፡ ሕይወታችሁ ሲለወጥ ታዩታላችሁ ፡፡

አንድ ምሳሌ ልጨምርላችሁ ፦ አንድ ዳቦ ይዛችሁ ሶስት የተቸገሩ ሰዎችን ተመለከታችሁ ፡፡ ከዛ ዳቦውን እኩል ቦታ ቆርሳችሁ አካፈላችኀቸው፤ ሰዎቹም ሲበሉም ቆይተው ሲጨርሱ
#አንዱ ይሄ ምን ያጠግባል ፣ ደግሞ የማይጣፍጥ ዳቦ ነው ብሎ ተነስቶ ሄደ
#ሌላው ደግሞ ምንም ምላሽ ሳይሰጥ ሄደ
#የቀሪው ግን እጅግ አመስግኖ እያለቀሰ ምግብ ከበላሁ 1 ቀኔ ነበር በማለት ሰጪውን ደጋግሞ አመሰገነ

እናም በዚህ ሁኔታ ሰጪው ላይ ምን አይነት አስተሳሰብ የሚጎለብት ይመስላችኀል? ተቀባዮቹስ ላይ?

ሰጪው በጣም የሚያስደስተው የሰጠው ጥቂት ዳቦ ሳይሆን ያመሰገነንውና እሱ በሰጠው ጥቂት ዳቦ ከርሀብ የወጣው ሰው ታሪክ ነው ፡፡ አማሮ ለሄደው ሰው ግን ለወደፊቱ ሞልቶ ቢተርፈውም ላይሰጠው ያስባል ስለ ሶስተኛው ሰው ግን እንዴት ምንም ሳይል ይሄዳል በሚል ብዙ ጥያቄዎችን ያወጣል ያወርዳል፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ስንባል ምንም ነገር ስናደርግ ምላሽ እንጠብቃለን ፡፡

ስለዚህ ለመልካም ግንኙነት ስንል መልካም ነገር መናገር አማራጭ የሌለው ነገር ነው ፡፡ ካልተቻለ ግን መጥፎ ነገር ከመናገር ዝም እንበል ፡፡ መልካም ነገር የሚጀምረው ደግሞ ከቀላል ምስጋና ነው፡፡

Like & Share
fb.me/psychologyet
#ተሰሚነት
Telegram www.tg-me.com/psychoet
ብዙዎቻችን የሚጎለን ክህሎት ስለሆነ ሌሎችም እንዲማሩ አንብበን #Share እናርገው

“የሰው ውበቱ አንደበቱ ነው” ይላል አንድ ወዳጄ፡፡ አንደበት ውበት ብቻ ሳይሆን ሃብት፣ ስልጣን፣ እና ጉልበትም ነው፡፡ ሃሳባቸውን በሚገባ አደራጅተው አሳማኝ በሆነ መንገድ መግለጽ የሚችሉ ሰዎች ከሌሎች የበለጠ ተደማጭ ናቸው፡፡ ቢናገሩ ያምርባቸዋል፤ ጥሪ ቢያቀርቡ ተከታይ ያገኛሉ፤ በንግዱ ዓለምም ቢሆን የተሻለ አትራፊ ነጋዴ ናቸው፡፡ ለዚህ ይመስለኛል መጽሐፍ ቅዱስም “ሰው የአንደበቱን ፍሬ ይበላል”የሚለው፡፡

ይህንን ክህሎት የተወሰኑ ሰዎች ሲፈጥራቸውም የታደሉት ሊሆኑ ይችላል፡፡ በሌላ መልኩ ግን በልምምድ እና ውስን ስልቶችን ጠንቅቆ በማወቅ አንደበተ ርቱዕ ሰው መሆንም ይቻላል፡፡የተወሰኑ ጠቃሚ የምላቸውን ስልቶችን ላጋራችሁ፡፡

ቅለት

ማስተላለፍ የምትፈልጉትን መልዕክት ቀላል፣ ግልጽ እና አጭር አድርጉ፡፡ የተራዘመ መልዕክት በአንድ በኩል አሰልቺ ነው፡፡ የሚፈለገውን ግብም አይመታም፡፡ አጥብቆ ለሚጠራጠረም ይህ ሁሉ እኔን ለማሳመን የሚደረግ ጥረት ከጀርባው ሌላ የተሸፈነ ፍላጎት አለ ወይ የሚል ሃሳብም እንዲያድርበት በር ሊከፍት ይችላል፡፡የዓለማችን ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል መስራች ስቲቭ ጆብስ “አንድን ነገር ቀላል በሆነ መንገድ መግለጽ መቻል ትልቅ ጥበብ ነው” (Simplicity is the ultimate sophistication) ይላል፡፡

ሌሎች ሊያገኙ የሚችሉት ጥቅም ላይ ትኩረት ማድረግ

“እኔ ምን አገኝበታለሁ?(What’s in it for me?) ”የተለመደ ጥያቄ ነው፡፡ ሰዎች ባይናገሩ እንኳን በውስጣቸው ይህንን ስሌት ከመስራት ወደ ኋላ አይሉም፡፡ በመሆኑም ለዚህ ወሳኝ ጥያቄ በቂ ማብራሪያ ማቅረብ መቻል በቀላሉ ሃሳባችንን ሰዎች እንዲገዙን ያደርጋል፡፡

በራስ መተማመን

አንዳንዴ እውነታው ከምናስተውለው የተለየ እንደሆነ ውስጣችን እያወቀ የተናጋሪው በራስ መተማመን ውሳኔያችንን ሊያስለውጥ፣ ሃሳባችንን ሊያስቀይር ወዘተ ይችላል፡፡ የምንናገረውን ነገር እንደምንተማመንበት ሁለመናችን ሊያስረዳ ይገባል፡፡ በሰዎች መካከል በሚደረግ የእርስ በእርስ ግንኙነት ውስጥ ቃላዊ ባልሆነ መንገድ የሚተላለፉ መልዕክቶች በቃል ከሚተላለፉት ያልተናነሰ ጉልበት አላቸው፡፡

በሌሎች ዓይን ማየት

ከሚመስሉን ሰዎች ጋር መስራት እንፈልጋለን፡፡ የጋራ ታሪክ አለን ብለን የምናስብ ከሆነ፣ ሃሳባችን ከተመሳሰለ፣ ምርጫች ከገጠመ ወዘተ ውስጣችን ፍላጎት በቀላሉ ይፈጠራል፡፡ ስለዚህ ይህንን የአንድነት መንፈስ ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮችን ማድረግ የማሳመን ኃይላችንን ከፍ ያደርጋል፡፡ በቀጥታ የዓይን ግንኙነት መፍጠር፣ በትኩረት ማዳመጥ፣ ግንባርን አልፎ አልፎ ዝቅ ከፍ ማድረግ የመሳሰሉት ስልቶች እየተባለ የሚገኘው ነገር እየገባን እንደሚገኝ የሚጠቁሙ ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን የማሳመን አቅማችንንም እንዲሁ በዛው ልክ ከፍ እንዲል ያደርጋሉ፡፡በወደደው ሰው ተጽእኖ ጥላ ስር በቀላሉ ያልወደቀ መቼም አይጠፋም፡፡

ያለማቋረጥ ጥረት ማድረግ

ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ትምህርት ቤት እያለሁ አንድ መጽሔት ዝግጅት ውስጥ ተሳትፎ አደርግ ነበር፡፡ አንዱን ዕትማችንን በምናዘጋጅበት ወቀት አንድ ቢሮ በተደጋጋሚ መሄድ ነበረብኝ፡፡ በወቅቱ ሳላስተውል፣ይህ ስልት ሰዎችን ሊያሳምን እንደሚችል ሳላስብበትም ነበር አደርገው የነበረው፡፡ በስተመጨረሻ የመስሪያ ቤቱ ኃላፊ የስፖንስርሺፕ ደብዳቤያችን ላይ ከመራበት በኋላ “ይህንን ያደረጉት ተስፋ አልቆርጥ ስላልከኝ ነው”እንዳለኝ ትዝ ይለኛል፡፡ እንደየ ሁኔታው ያለ ማቋረጥ ጥረት ማድረግም ሰዎች ሃሳባችንን ሃሳባቸው እንዲያርጉ ይረዳል፡፡

እጥረትን መፍጠር

ዋልያ የሀገር ኩራት ምንጭ፣ የንግድ ስያሜ መጠሪያ፣ የብሔራዊ ቡድናችን አርማ ወዘተ መሆን የቻለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ በመገኘቱ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ብርቅዬ በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ በተለያየ መልኩ መሸጥ የምንፈልገው ሃሳብም ይሁን ቁስ ከሌላው በምን መልኩ እንደሚለይ፣ በምን እንደሚሻል ወዘተ ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ እዚህም እዚያም እንደ ልብ ለሚገኝ ነገር ፍላጎታችን እምብዛም ነው፡፡

ዝግጅት

ስለምንናገረው ነገር ጠንቅቀን ማወቅ፣ አስቀድመን የቤት ሥራችንን በሚገባ መስራት ማሳመን የምንፈልገውን አካል ለማሳመን ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በራስ መተማመናችንንም ይገነባል፡፡

ለምሳሌ እነዚህን በሙሉ ክህሎቶች ዶ/ር ምህረት ላይ እናገኛለን ፡፡ የመሰማቱ አንዱ ሚስጢር ይሄ ነዉ ፡፡ ሲያስተምር አይታችሁ ከሆነ የሚያስተምረውን ነገር ቀለል አርጎ ፣ በራስ መተማመን ለአድማጭ በሚስብ መልኩ ያደርጋል ፡፡ ይህ በሁላችን አድማጮቹ ዘንድ ተሰሚነትን ፈጥሮለታል ፡፡ በሌላ በኩል አንድ ሰፈር /ስራ ቦታ የምናውቀውን ሳያቋርጥ የሚያወራ ፣ ንግግር የማያስጨርስ ሰው ስናስብ እንኳን ለመስማት ከሱ ጋር ለማውራት ይቀንቀናል ፡፡ እንግዲህ ሚስጥሩ ይሄው ነው ፡፡

በሰዎች ዘንድ ለመሰማት በዕውቀትና በጥበብ እናውራ !
(በነጋሽ አበበና ናሁሰናይ ፀዳሉ)
©zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
#Share & #Like oue page - fb.com/psychologyet
_________________________
👉ጠቃሚ ምክሮች👈

1. ከአለስፈላጊ ክርክሮች ጭቅጭቆች እና እሰጣገባዎች ራቅ።

2. ራስህን ገንቢ ሃሳብ ከሌላቸው (negative) ሰዎች አርቅ። ምክንያቱም አንተን ራሱ ሳትፈልገዉ እንደነሱ እንድታስብ ትገደድ ይሆናል፡፡

3. መቀበል የምትፈልገውን ስጥ።

4. ገንቢ ያለሆኑ ጎጂ አስታያየቶችን ከመስጠት ተቆጠብ።

5. ለሰዎች ፍቅርና አክብሮት ይኑርህ።

6. ይህ መቼም በእኔ አይደርስም አትበል፣የሕይወትን አቅጣጫ ሁሌም ቢሆን ማወቅ አንችልምና።

7. የመኪና የፊት መስታወት ትልቅ ሆኖ የኋላ መመልከቻውዠ መስታወት ግን ለምን ትንሽ የሆነ ይመስልሃል....ምክንያቱም የፊቱ ካለፈው ይልቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ስለዚህም የኀላዉን ሳትዘነጋ በትልቁ የሕይወት መስታወት ወደፊት እያየህ ተጓዝ::

#መልካም_ቀን !
#Share #Like
@Psychoet
ከጭንቀት ነፃ የሆነ «ደስተኛ ሕይወት» ለመኖር ወሳኝ የሆኑ አሥር የሕይወት መርሆች አውቅ ከሆኑ የሳይኮሎጂ መፅሀፍቶች የተወሰደ እና ከሳይኮሎጂ ባለሞያዎች/አማካሪዎች የተገኘ መረጃ!

#ሼር ማድረግ ደስ ይላል፡፡ የዛሬ ደስታዎን #ሼር በማድረግ ይጀምሩ፡፡

1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው።

2. አትኩሮትህ በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ ይሁን፡- ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፡፡

4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።

5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ ሲሆን እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፣ አላማችንና ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዘን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበትም ነው፡፡

6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦ ሰዎችን አትና፤ በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡

7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ/ለፈጣሪህ ስጠው።

8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ራስህን መውደድ ተለማመድ፤ የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን ሲያጠፋ ይቅር በማለት፣ ሲደክም በማበርታት፤ ሲሳካለት በማሞካሠት ተንከባከበው፡፡

9. መልካም አስብ መልካም ተናገር፦ በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።

10. ለምን እንደምትኖር እወቅ፦ ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱን ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይቀየራል፡፡

11. የአዲስ መረጃ ቤተሰቦች፣ ሼር ማድረግ ምን ያህል ደስ እንደሚያሰኝ ስለሚያውቁ ቀናቸውን የሚጀምሩት የኛን መረጃ ሼር በማድረግ ነው፡፡

ደስተኛ ህይወትን ለሁላችንም ይስጠን ! መልካም የጤና ጊዜ!!!

----------------------

ምንጭ - (ቶማስ እንደፃፈዉ፣ ፅሁፉ ከዶክተር አለ የተወሰደ)
©ጽሑፎን ከFacebook Sci-tech page ነው ያገኘሁት ጥሩ ነገር ስለሚለጥፉ Like አርጓቸው

Join My Telegram Channel www.tg-me.com/Psychoet
እንደምን አመሻችሁ
ነገ ጠዋት ቅዳሜ ከ 2:10 ጀምሮ በፋና 98.1 ላይ "እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ " በሚል የቀጥታ ውይይት ስላለ በመደወል ሀሳብ አስተያየቶቻችሁን መስጠት ትችላላችሁ ፡፡ ውይይቱ ሲያልቅ እኔም ከሥነልቦና አንፃር ማብራሪያ እሰጣለሁ ፡፡

መልካም ምሽት !
#ተሰሚነት
Telegram www.tg-me.com/psychoet
ብዙዎቻችን የሚጎለን ክህሎት ስለሆነ ሌሎችም እንዲማሩ አንብበን #Share እናርገው

“የሰው ውበቱ አንደበቱ ነው” ይላል አንድ ወዳጄ፡፡ አንደበት ውበት ብቻ ሳይሆን ሃብት፣ ስልጣን፣ እና ጉልበትም ነው፡፡ ሃሳባቸውን በሚገባ አደራጅተው አሳማኝ በሆነ መንገድ መግለጽ የሚችሉ ሰዎች ከሌሎች የበለጠ ተደማጭ ናቸው፡፡ ቢናገሩ ያምርባቸዋል፤ ጥሪ ቢያቀርቡ ተከታይ ያገኛሉ፤ በንግዱ ዓለምም ቢሆን የተሻለ አትራፊ ነጋዴ ናቸው፡፡ ለዚህ ይመስለኛል መጽሐፍ ቅዱስም “ሰው የአንደበቱን ፍሬ ይበላል”የሚለው፡፡

ይህንን ክህሎት የተወሰኑ ሰዎች ሲፈጥራቸውም የታደሉት ሊሆኑ ይችላል፡፡ በሌላ መልኩ ግን በልምምድ እና ውስን ስልቶችን ጠንቅቆ በማወቅ አንደበተ ርቱዕ ሰው መሆንም ይቻላል፡፡የተወሰኑ ጠቃሚ የምላቸውን ስልቶችን ላጋራችሁ፡፡

ቅለት

ማስተላለፍ የምትፈልጉትን መልዕክት ቀላል፣ ግልጽ እና አጭር አድርጉ፡፡ የተራዘመ መልዕክት በአንድ በኩል አሰልቺ ነው፡፡ የሚፈለገውን ግብም አይመታም፡፡ አጥብቆ ለሚጠራጠረም ይህ ሁሉ እኔን ለማሳመን የሚደረግ ጥረት ከጀርባው ሌላ የተሸፈነ ፍላጎት አለ ወይ የሚል ሃሳብም እንዲያድርበት በር ሊከፍት ይችላል፡፡የዓለማችን ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል መስራች ስቲቭ ጆብስ “አንድን ነገር ቀላል በሆነ መንገድ መግለጽ መቻል ትልቅ ጥበብ ነው” (Simplicity is the ultimate sophistication) ይላል፡፡

ሌሎች ሊያገኙ የሚችሉት ጥቅም ላይ ትኩረት ማድረግ

“እኔ ምን አገኝበታለሁ?(What’s in it for me?) ”የተለመደ ጥያቄ ነው፡፡ ሰዎች ባይናገሩ እንኳን በውስጣቸው ይህንን ስሌት ከመስራት ወደ ኋላ አይሉም፡፡ በመሆኑም ለዚህ ወሳኝ ጥያቄ በቂ ማብራሪያ ማቅረብ መቻል በቀላሉ ሃሳባችንን ሰዎች እንዲገዙን ያደርጋል፡፡

በራስ መተማመን

አንዳንዴ እውነታው ከምናስተውለው የተለየ እንደሆነ ውስጣችን እያወቀ የተናጋሪው በራስ መተማመን ውሳኔያችንን ሊያስለውጥ፣ ሃሳባችንን ሊያስቀይር ወዘተ ይችላል፡፡ የምንናገረውን ነገር እንደምንተማመንበት ሁለመናችን ሊያስረዳ ይገባል፡፡ በሰዎች መካከል በሚደረግ የእርስ በእርስ ግንኙነት ውስጥ ቃላዊ ባልሆነ መንገድ የሚተላለፉ መልዕክቶች በቃል ከሚተላለፉት ያልተናነሰ ጉልበት አላቸው፡፡

በሌሎች ዓይን ማየት

ከሚመስሉን ሰዎች ጋር መስራት እንፈልጋለን፡፡ የጋራ ታሪክ አለን ብለን የምናስብ ከሆነ፣ ሃሳባችን ከተመሳሰለ፣ ምርጫች ከገጠመ ወዘተ ውስጣችን ፍላጎት በቀላሉ ይፈጠራል፡፡ ስለዚህ ይህንን የአንድነት መንፈስ ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮችን ማድረግ የማሳመን ኃይላችንን ከፍ ያደርጋል፡፡ በቀጥታ የዓይን ግንኙነት መፍጠር፣ በትኩረት ማዳመጥ፣ ግንባርን አልፎ አልፎ ዝቅ ከፍ ማድረግ የመሳሰሉት ስልቶች እየተባለ የሚገኘው ነገር እየገባን እንደሚገኝ የሚጠቁሙ ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን የማሳመን አቅማችንንም እንዲሁ በዛው ልክ ከፍ እንዲል ያደርጋሉ፡፡በወደደው ሰው ተጽእኖ ጥላ ስር በቀላሉ ያልወደቀ መቼም አይጠፋም፡፡

ያለማቋረጥ ጥረት ማድረግ

ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ትምህርት ቤት እያለሁ አንድ መጽሔት ዝግጅት ውስጥ ተሳትፎ አደርግ ነበር፡፡ አንዱን ዕትማችንን በምናዘጋጅበት ወቀት አንድ ቢሮ በተደጋጋሚ መሄድ ነበረብኝ፡፡ በወቅቱ ሳላስተውል፣ይህ ስልት ሰዎችን ሊያሳምን እንደሚችል ሳላስብበትም ነበር አደርገው የነበረው፡፡ በስተመጨረሻ የመስሪያ ቤቱ ኃላፊ የስፖንስርሺፕ ደብዳቤያችን ላይ ከመራበት በኋላ “ይህንን ያደረጉት ተስፋ አልቆርጥ ስላልከኝ ነው”እንዳለኝ ትዝ ይለኛል፡፡ እንደየ ሁኔታው ያለ ማቋረጥ ጥረት ማድረግም ሰዎች ሃሳባችንን ሃሳባቸው እንዲያርጉ ይረዳል፡፡

እጥረትን መፍጠር

ዋልያ የሀገር ኩራት ምንጭ፣ የንግድ ስያሜ መጠሪያ፣ የብሔራዊ ቡድናችን አርማ ወዘተ መሆን የቻለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ በመገኘቱ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ብርቅዬ በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ በተለያየ መልኩ መሸጥ የምንፈልገው ሃሳብም ይሁን ቁስ ከሌላው በምን መልኩ እንደሚለይ፣ በምን እንደሚሻል ወዘተ ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ እዚህም እዚያም እንደ ልብ ለሚገኝ ነገር ፍላጎታችን እምብዛም ነው፡፡

ዝግጅት

ስለምንናገረው ነገር ጠንቅቀን ማወቅ፣ አስቀድመን የቤት ሥራችንን በሚገባ መስራት ማሳመን የምንፈልገውን አካል ለማሳመን ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በራስ መተማመናችንንም ይገነባል፡፡

#SHARE #LIKE
2024/09/30 09:33:38
Back to Top
HTML Embed Code: