Telegram Web Link
ቮልስ መኪናዎችን ከሰራን በሗላ ለምንድነው የድሮ መኪኖች ላይ ሪቪው የማትሰሩት ብላችሁ በተደጋጋሚ ትጠይቁናላችሁ

ይኸው
Peugeot 404

የፈረንሳይ መኪና ሲሆን የተሰራው ለአፍሪካ ታስቦ ነው ::
በጣም ነው የወደድኩት ካየሁት በሗላ
የጎን ማርሽ መሆኑ
ክላክሱ
ሰስፔንሽኑ
ብቻ ምን አለፋችሁ ቪድዮውን ካያችሁት በሗላ ትወዱታላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtube.com/shorts/pnb8kYQw344

ስለጠፋን ይቅርታ እየጠየቅን ዩትዩብ ላይ እንዲሁም ቲክቶክ ላይ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ የምንመለስ ይሆናል :: ባለፈው የጠየቅነውንም ጥያቄ የመለሱ 5 ሰዎች በዚህ ሳምንት ሪቪው ላይ የምንገልፅ ይሆናል ::

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ
#Peugeot404 #Classiccar
@OnlyAboutCarsEthiopia
የተሽከርካሪ መለያን (ታርጋ) በተመለከተ

ከክልል እና ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለሚመጡ ባለጉዳዮች ለተበላሸ ታርጋን ለመለወጥ የሚመጡ ደንበኞች ማሟላት የሚገባቸው

1. ሊብሬ ዋናና ኮፒ
2. የታደሰ መታወቂያ ዋናና ኮፒ
3. ውክልና ዋናና ኮፒ
4. የትራንስፖርት ቢሮ ደብዳቤ
5. ሊብሬ ባንክ የተያዘ ከሆነ የባንክ ደብዳቤና ሊብሬ ኮፒ
የጠፋ ታርጋን ለማውጣት የሚመጡ ደንበኞች ማሟላት የሚገባቸው
1. የትራንስፖርት ቢሮ ደብዳቤ
2. ሊብሬ ዋናና ኮፒ
3. የታደሰ መታወቂያ ዋናና ኮፒ
4. ውክልና ዋናና ኮፒ
5. የፖሊስ ደብዳቤ
6. ኘሬስ የተከፈለበት ዋናው ደረሰኝ
7. ሊብሬው ባንክ የተያዘ ከሆነ ከባንኩ ደብዳቤ እና ሊብሬ ኮፒ

ልዩ ምሽት ተመኘን
#CarPlate #Ethiopia
@OnlyAboutCarsEthiopia
ስንት አይነት የመኪና ቁልፎች አሉ?
ክፍል 1

የመኪና ቁልፍ አይነቶች በቁጥር ከ10 ቢበልጡም እኛ ግን ዋና ዋና የምንለውን 7 መርጠን ትንሽ ነገር እንበላችሁ ::

1. ሜካኒካል የመኪና ቁልፍ

የሜካኒካል የመኪና ቁልፍ ልክ እንደ መደበኛ የቤት ቁልፍ ይመስላል።
ይህ ቁልፍ ዛሬም ጥቅም ላይ የሚውል መሰረታዊ የመኪና ቁልፍ ነው። እነዚህ ቁልፎች ምንም አይነት የደህንነት ኢንኮዲንግ በሌላቸው አሮጌ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቅም ላይ ይውላሉ።

2. ሌዘር ከት የመኪና ቁልፍ

በሌዘር የተቆረጠ የመኪና ቁልፎች ከሌሎቹ የመኪና ቁልፍ ዓይነቶች የበለጠ ወፍራም ናቸው። ይህ ቁልፍ በሁለቱም በቁልፉ በኩል ጥርስ በሌዘር ስለሚወጣለት ቁልፉ በራሳችን ለመቅረጽ የበለጠ ከባድ ነው። በሌዘር የተቆረጡ ብዙ የመኪና ቁልፎች የRemote key አብሮ ሊኖራቸውም ይችላል። ከዋጋ አንጻርም ከ ሜካኒካል ቁልፎች የሚወደድ ይሆናል።

3. ማስተር የመኪና ቁልፍ

ልክ ስሙ እንደሚያመለክተው master ወይንም የዋና መኪና ቁልፍ በመኪኖች ወስጥ በሮችን እና የተለያዩ ተሽከርካሪዎች አካላት ማብራት ወይንም መክፈት አልያም የመጀመር ችሎታ አለው።

ማንኛውንም አይነት የመኪና ቁልፍ መቅረፅ እንዲሁም የመኪና ቁልፎችን ፕሮግራም ማድረግ ላይ የምትሰሩ ሰዎች ካላችሁ በ @Yonathandesta ላይ ኮንታክት አርጉን ::

እዚህ ላይ የጠቀስናቸው በጥቂቱ ነው :: ዩትዩብ ላይ ስለእያንዳንዱ በዝርዝር የሰራነው ቪድዮ ስላለ እሱን መመልከት ትችላላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/61BuHk_eRkA

ድምቅ ያለ ከሰአት ተመኘን
#CarKey
@OnlyAboutCarsEthiopia
በብዛት የምትጠቀሙት የራይድ ትራንስፖርት የቱን ነው?
Anonymous Poll
38%
Ride
57%
Feres
2%
ZayRide
2%
Rica
1%
ወይስ GreenTech
ስንት አይነት የመኪና ቁልፎች አሉ?
ክፍል 2

4. የ ሪሞት የመኪና ቁልፎች

እንደነዚህ ዓይነቶቹ ቁልፎች ብዙውን ጊዜ ለመሠረታዊ ተግባራት መኪናዎችን ከሩቅ ለመክፈት እና ለመቆለፍ ያገለላሉ። የ remote የመኪና ቁልፎች እንዴት እንደሚሰሩ ስንቶቻችን እናውቃልን ?
በ አጭሩ ለማስረዳት ያህል፤የደህንነት መሳሪያው የኢንፍራሬድ ሲግናል ወይም በተለምዶ የሬድዮ ማሰራጫ በመጠቀም በመኪናው ውስጥ ላለው ተቀባይ ኢንኮድድ መልእክት ለመላክ ይጠቀማል። ይህ ኢንኮድድ መልእክት በሩ እንዲከፈት ወይንም እንዲዝጋ ይነግረዋል።

5. የትራንስፖንደር መኪና ቁልፍ

ይህ ዓይነቱ ቁልፍ በቁልፍ መያዣው ውስጥ ማይክሮ ቺፕ ያለው ሲሆን ከባህላዊው የመኪና ቁልፍ የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው። ቺፕ ራሱ በባትሪ  አይሰራም። ነገር ግን ልክ ጥቅም ላይ ሲውል ኮድ ይልካል። ኮዱ ከመኪናው ጋር ተመሳሳይ ከሆነ መኪናው ይነሳል ማለት ነው። 

6. Smart የመኪና ቁልፎች

በአንጻራዊ በቅርብ ጊዜ የመጡት የ ስማርት የመኪና ቁልፎች ናቸው።
እነዚህ እንደለመድናቸው አይነት ቁልፎች አይደሉም። ስማርት ቁልፉ በመኪና ውስጥ ካለ የመኪናው ኢሞቢላይዘር ይጠፋል እና በአንድ በተን በመጫን መኪናው ይጀምራል። ስለዚህ ቁልፉን ወደ ignition ውስጥ መክተት አያስፍልገንም ማለት ነው።

ማንኛውንም አይነት የመኪና ቁልፍ መቅረፅ እንዲሁም የመኪና ቁልፎችን ፕሮግራም ማድረግ ላይ የምትሰሩ ሰዎች ካላችሁ በ @Yonathandesta ላይ ኮንታክት አርጉን ::

እዚህ ላይ የጠቀስናቸው በጥቂቱ ነው :: ዩትዩብ ላይ ስለእያንዳንዱ በዝርዝር የሰራነው ቪድዮ ስላለ እሱን መመልከት ትችላላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/61BuHk_eRkA

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#CarKey
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅር እና የጤና ይሁንላችሁ !

የሚገርም ምሽት ተመኘን 🙏
@OnlyAboutCarsEthiopia
ነዳጅ 📈

የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ ፦

- ቤንዚን በሊትር 57 ብር ከ05 ሳንቲም፣

- ነጭ ናፍጣ በሊትር 59 ብር ከ90 ሳንቲም

- ኬሮሲን በሊትር 59 ብር ከ90 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ ማስተከከያ ከመስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት 6:00 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

ሌሎች የነዳጅ ውጤቶች ማለትም የአውሮፕላን ነዳጅ ፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣና ከባድ ጥቁር ናፍጣ ባሉበት እንዲቀጥሉ መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል።

በሌላ በኩል አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተረዘጋው የታለመ ድጎማ አሠራር ታቅፈው ሕዝቡን እንዲያገለግሉ የተመረጡት የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽክርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ በ2ኛው ምዕራፍ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደገረም።

ሚኒስቴሩ እነዚህ ተሽከርካሪዎች በሐምሌ ወር በተወሰነላቸው ዋጋ ፦
- ቤንዚን በብር 41.26 በሊትር
- ነጭ ናፍጣን በብር 40.86 በሊትር እየገዙ እንዲቀጥሉ ብቻ ሳይሆን ከእጥፍ በላይ ያደገ ድጎማ ከመንግሥት እንዲያገኙ የተደረገ ስለሆነ በሚቀጥለው ጊዜ ዋጋ እስኪሻሻል ድረስ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ምንም ዓይነት ጭማሪ አይደረግም ብሏል።

ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር / ኢብኮ

@OnlyAboutCarsEthiopia
ምን ይሆን ለነዳጅ መኪና መፍትሄው 📈

ነዳጅ በጣም እየጨመረ ነው

የብር ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ በመምጣቱ የነዳጅ ዋጋ በየጊዜው መንግስት ማስተካከያ እያደረገ ነው :: ምንም እንኳን ከሌሎች ሀገሮች አንፃር የተሻለ የነዳጅ ዋጋ ቢኖረንም መንግስት እየደጎመም ቢሆን እስከአሁን ቆይቷል :: አሁንም እየደጎመም ቢሆን ግን ያለውን ጋፕ እያጠበበ ይገኛል :: በትላንትናው ጭማሪ ብቻ በአንድ የቤንዚን ሊትር ላይ ከ 9 ብር በላይ ጭማሪ ተደርጟል :: ስለዚህ ሰዉን ወደ ኤሌክትሪክ መኪኖች ሺፍት እንዲያደርጉ በተዘዋዋሪ መንገድ እየተናገረ ይመስላል :: ግን እውነት ኤሌክትሪክ መኪና ለእኛ ሀገር ይሆናል? የሚለው ሌላ ጥያቄ ነው :: አንዳንድ መረጃዎችን ሰብሰብ አድርገን በቅርብ ጊዜ በቪድዮ የምንለቅ ይሆናል :: ግን እናንተስ ምን ታስባላችሁ?

ውብ ቀን ተመኘን
#Fuel #Nedaj
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይሄ መኪና 10 ሚሊየን ብር ይገባዋል?
2022 Tesla Model Y Review

ቴስላ መኪና ሲባል በቃ በጣም አሪፍ መኪና እንደሆነ ይታወቃል :: በተለይ በጣም የሚታወቀው ባለው የኪሎሜትር ሬንጅ እና በቴክኖሎጂ ፊቸሩ ነው :: ቴስላ ሞዴል Y ላይ ምንም እንኳን ከ ሞዴል 3 እና ከ ሞዴል X መሀል ቢገኝም ግን በኪሎሜትር ከ ሞዴል 3 ያነሰ ነው :: ከኳሊቲ አንፃር ደግሞ ከሞዴል 3 የተሻለ ነው :: ግን በአንድ ቻርጅ ምን ያህል ይሄዳል? Long Range እና Performance ልዩነታቸው ምንድነው? ለዋጋው ተገቢውን ነገር ይሰጣል? የሚሉትን ያለንን ሀሳብ በዛሬው ቪድዮ ለቀናል ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/eNo_zm1Tdpo

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Tesla #TeslaModelY #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
Forwarded from Only About Cars News
Geely የመኪና ካምፓኒ የ Aston Martin የመኪና ካምፓኒ 7.6 % ሼር ገዛ

የቻይናው አውቶሞቲቭ ኩባንያ ዠይጂያንግ ጂሊ ሆልዲንግ ግሩፕ (GEELY.UL) አርብ ዕለት የብሪታንያ የቅንጦት መኪና አምራች አስቶን ማርቲን 7.6% አክሲዮን ገዝቷል :: ነገር ግን የስምምነቱን ዋጋ አልተገለጸም።

በሴፕቴምበር 28 የአስቶን ማርቲን የመዝጊያ ድርሻ ዋጋ ላይ በመመስረት፣ ድርሻው በ7.55 ቢሊዮን ፓውንድ (8.39 ቢሊዮን ዶላር) ይገመታል።

የዚጂያንግ ጂሊ መስራች እና ሊቀመንበር በሆነው ሊ ሹፉ የተገዛው አስቶን ማርቲን የቁጥጥር መዝገብ ላይ እንደገለፀው የቻይና ኩባንያ በብሪቲሽ የመኪና አምራች ውስጥ ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች አንዱ እንዲሆን አድርጎታል ተብሏል ::

በየቀኑ አዳዲስ የመኪና ዜናዎችን ለማግኘት
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
@OAC_News
Tata በጣም ርካሹን ኤሌክትሪክ መኪና በህንድ ለገበያ አቅርቧል ::

Tata Tiago EV በጣም ርካሹ የታታ ኤሌክትሪክ መኪና ሲሆን ዋጋውም 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ባለ 75 የፈረስ ጉልበት መኪናው በአንድ ቻርጅ 250 ኪሎሜትር መጟዝ ይችላል ተብሏል ::


በየቀኑ አዳዲስ የመኪና ዜናዎችን ለማግኘት
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽
@OAC_News

ልዩ ምሽት ተመኘን
#Tata #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
የወደድኩት የቻይና መኪና
Jetour X70 Plus Review

Jetour X70 Plus በ Chery ስር የሚገኝ መኪና ሲሆን ዲዛይኑም ካየሗቸው የቻይና መኪናዎች የተሻለ ነው :: ለዛም ይመስለኛል በብዛት እየገባ ያለው :: ይሄ መኪና በ 1.5 ሊትር እንዲሁም በ 1.6 ሊትር ሞተር አማራጭ ቢቀርብም እዚህ የምታገኙት 1.5 ሊትር ሞተር ያለውን ነው :: በሊትር ከ 10-13 ኪሎሜትር ይጟዛል :: የወደድኩት ዋናው ምክንያት እዚህ ዘርፍ ላይ ካሉ መኪኖች ዋጋው የተሻለ ነው :: ግን ደግሞ Dual Clutch Transmission ነው ያለው :: ይህንን ብቻ ነው እንደ ጉዳት የማየው :: የተቀረውን ደግሞ ዩትዩብ ላይ በዝርዝር ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/xAgJyld9gAA

ፍክት ያለ ምሽት ተመኘን
#Jetour #JetourX70Plus
@OnlyAboutCarsEthiopia
መኪና መግዛት መሸጥ ፣ የሚከራይ መኪና በቀላሉ ማግኘት ፣ የመኪናችሁን ስፔር ብዙ ሳትለፉ በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት ትፈልጋላችሁ? እንግዲያውስ @Hulemekina Join በማድረግ የምትፈልጉትን የመኪና እቃዎች እንዲሁም ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ታገኛላችሁ :: በቅርብ ቀን ስራ የምንጀምር ይሆናል :: በጣም የተለያዩ ተጨማሪ ነገሮችም አሉት :: ብቻ ምን አለፋችሁ ትወዱታላችሁ ::

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
#Hulemekina
@OnlyaaboutCarsEthiopia
የታክሲ እና የሜትር ታክሲ አገልግሎት ለሚሰጡ ሰዎች በጣም ጠቃሚ አፕ

ይህንን አፕሊኬሽን ምን አልባት ከዚህ በፊት ሰምታችሁት ሊሆን ይችላል
WAZE ይባላል :: ምንድነው የሚያረገው
በአካባቢያችሁ መንገድ ከተዘጋጋ ወይም ከተጨናነቀ ፣ እዛ አካባቢ ላይ ግጭት ካለ እና እንዲሁም ትራፊክ ካለ ይናገራል :: ግን ይህ የሚሆነው አፑን የሚጠቀመው ሰው በሚያስገባው መረጃ ነው :: አፑ ላይ ብዙ ተጨማሪ ነገሮች አሉት :: ስለዚህ በቪድዮ እንድንሰራላችሁ የምትፈልጉ ከሆነ ኮሜንት ላይ ሀሳባችሁን አጋሩንና የምሰራ ይሆናል :: አፕልኬሽኑን App Store እና play Store ላይ ታገኙታላችሁ ::

ውብ ምሽት ተመኘን 🙏
#Waze #app
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለነብዩ መሀመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም በዓል!

@OnlyAboutCarsEthiopia
@Hulemekina
በኤሌክትሪክ ሞተር ከሚሰሩት በስተቀር የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢሎች፣ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች እና የተገጣጠሙ ሞተር ሳይክሎችን ጨምሮ ሌሎች ተጨማሪ አንዳንድ እቃዎች ላይ እግዱ መጣሉን ያሳወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው።

ይኸው እግድ የተላለፈው የህገወጥ የምንዛሬ ገበያውን ይበልጥ ለማውረድ በማሰብ መሆኑ ተገልጿል።

የእግዱ መተግበር በአማካኝ ግማሽ ያህል የውጭ ምንዛሬን ሊያስቀር ይችላል ተብሏል።

ከሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው እገዳ የሚቆየው ላልተወሰነ ጊዜ  እንደሆነም የብሄራዊ ባንክ አሳውቋል።

@OnlyAboutCarsEthiopia
የ 2023 Volkswagen ID.4 AWD በተጨማሪ አማራጭ ፣ በአዲስ ቀለም ፣ በአዲስ ውስጣዊ ገፅታው ፣ በሚበራ ሎጎ እና ዋጋ በሚቀንስ አማራጭ መቷል ::

ይህ መኪና በከተማችን በብዛት ከሚሸጡ ኤሌክትሪክ መኪኖች አንዱ እና ዋናው ነው :: በ 2023 ሞዴሉ ላይ ግብ በ 2000$ የሚቀንስ ሌላ አማራጭ እንዳቀረቡ ገልፀዋል :: ተጨማሪ መረጃውን @OAC_News ላይ ታገኛላችሁ ::

እንዲሁም ብዙም የማይታወቀውን አንድ ለየት ስላለው ፊቸር Volkswagen ID.4 መኪና ላይ ቲክቶክ ላይ ታገኛላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMF6xL7BA/

ልዩ ምሽት ተመኘን
#Electric #ID4
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይሄ አፕሊኬሽን ትራፊክ እየቀጣ ላስቸገራችሁ ነው ❗️

WAZE ይባላል :: የጎግል አፕ ነው :: በተለይ ይህንን አፕ እንድትጠቀሙት ሪኮመንድ ስናደርግ በጣም ብዙ ጥቅም ስለምታገኙ ነው :: በተለይ የተዘጋጋ መንገድ ለማወቅ ፣ ትራፊክ የቱ ጋር እንዳለ ለማወቅ ፣ የሚሰራ መንገድ ካለ እና መሄድ የማይቻል መንገድ ከሆነ እዛው ላይ ተጠቃሚው ያስገባል :: ስለዚህ ሌላ ሰው በዛ በኩል ሲያልፍ ቀድሞ ምን ምን እንዳለ ያውቃል ማለት ነው :: ይሄ በተለይ ለራይድ እና የታክሲ ሹፌሮቹ እንዲሁም ደግሞ ሙሉ ቀን በመኪናችሁ የምትንቀሳቀሱ ከሆነ በጣም ይጠቅማችሗል :: አፑን ለመጠቀም ቀላል ነው :: ከ Google Maps ጋር ተመሳሳይ ሲሆን የዚህ የሚለየው የተጨመሩ ፊቸሮች ስላሉት ነው :: ግን አልገባንም በደንብ ካላችሁ ደግሞ ቪድዮ የምንለቅ ይሆናል አጠቃቀሙ ላይ ::

WAZE አፕ ለ IOS ስልኮች
👇🏽👇🏽👇🏽

https://apps.apple.com/us/app/waze-navigation-live-traffic/id323229106

WAZE አፕ ለአንድሮግድ ስልኮች
👇🏽👇🏽👇🏽

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.waze&hl=en&gl=US

አጠር ያለ የቲክቶክ ቪድዮ ስለ WAZE አፕ
👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMFMhy7QY/

ያልገባችሁ ማንኛውም አይነት ነገር ካለ ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን የቻልነውን እንመልሳለን ::

@Hulemekina ደግሞ Join ማድረግ እንዳትረሱ በቅርብ ቀን ስራ የሚጀምር ይሆናል :: በጣም ለየት ያሉ ነገሮች አሉት ::

ግሩም ከሰአት ተመኘን
#waze #app
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/24 14:24:36
Back to Top
HTML Embed Code: