Telegram Web Link
አዲስ የመኪና ዌብሳይት በአዲሱ አመት

ላለፉት ሁለት ሳምንታት ጠፍተናል ቪድዮ መልቀቅ አቁመናል :: የምናማክረውንም ላለፉት 3 ሳምንታት አቁመን ነበር :: አዎ ብዙ ስራዎች አምልጠውናል :: ግን ደግሞ ለእናንተ የተሻለውን ለማቅረብ ከአንድ የውጪ ድርጅት ጋር አንድ ላይ በመሆን እየሰራን ያለነው የመኪና ዌብሳይት ስላለ ነው :: በአዲሱ አመት ይጀምራል ብለን እናስባለን :: የብዙዎቻችሁን ጥያቄ ለመመለስ የተሰራ ዌብሳይት ነው :: ስለዚህ በትዕግስት እንድትጠብቁን እያልን የሚቀጥለውን አመት የምንቀበለውም በአዲስ ነገር መሆኑን ቀድመን ለማሳወቅ ነው ::

መልካም ምሽት ተመኘን
#Website
@OnlyAboutCarsEthiopia
Mercedes-Benz እና Rivian አንድ ላይ በመሆን ለአውሮፓ ገበያ የኤሌክትሪክ ቫን ለመስራት ስምምነት ላይ ደረሱ ::

የስታርት አፕ ካምፓኒው ሪቪያን እና የመርሴዲስ ቤንዝ ቫንስ ዲቪዥን ለአውሮፓ ገበያ ሁለት አዳዲስ ትላልቅ የኤሌክትሪክ የንግድ ቫኖች ለመገንባት አዲስ የጋራ ሥራ ሊጀምሩ ነው ። ለሁለቱም ወገኖች የማምረቻ ሥራን የማቃለል ዓላማ ያለው በመሆኑ ስምምነቱ ሁለቱ ኩባንያዎች በአዲሱ የአውሮፓ ህንጻቸው ውስጥ በተቻለ መጠን ብዙ የጋራ ወጪን በመቀነስ ለመስራት ምቹ የሆነ አካባቢን ይፈጥራል ። ስምምነቱ ገና ሙሉ በሙሉ አልተጠናቀቀም :: ነገር ግን አስቀድመው ማስታወቂያዎችን እየሰሩ ከሆነ እርግጠኛ መሆን አለባቸው።

ስለታቀደው ምርት እስካሁን ምንም የተነገረ ነገር የለም :: ነገር ግን "ሁለቱም ኩባንያዎች አለምን ወደ ንጹህ መጓጓዣ ለማሸጋገር የኤሌክትሪክ ቫኖችን በፍጥነት ለማምረት አቅደዋል :: ኩባንያዎቹ የትብብሩ ዋና ትኩረት ለደንበኛው በተመጣጣኝ ዋጋ መኪኖቹን ማቅረብ እንደሆነ ገልፀዋል :: ነገር ግን የዋጋ ዝርዝር መግለጫ አልተገለጸም ::

ሰላማዊ ምሽት ተመኘን
#Rivian #Mercedes #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሉሲድ 6 ከፍተኛ የስራ አስፈፃሚዎቻቸውን አባረዋል ::

ቴስላ በጣም ይቀናቀነዋል ተብሎ የሚታሰበው ሉሲድ ካምፓኒ በምርት ፍጥነት ምክንያት በተፈጠረው አስቸጋሪ የፋይናንስ ሁኔታ 6 ዋና ዋና አመራር ላይ ያሉ ሰራተኞችን አጥተዋል :: የምርታቸው መጠን ካቀዱት ከ 30-40% ስለቀነሱ እንደተቀነሱ ተናግረዋል :: ስለ Lucid Air የተብራራ ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ታገኛላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMNWW7YDq/

ግሩም ዋዜማ ተመኘን
#LucidAir #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ሰላም፣ ፍቅር ፣ደስታ ፣ ምስጋና ፣ ጤንነት ፣ በረከት፣ይቅርታ፣ ቅንነት ፣መትረፍረፍ ፣ስኬት፣መልካም አስተሳሰብ፤ የሞላበት ድንቅ እና ውብ ዓመት ይሁንልን! መልካም አዲስ ዓመት!!!🌼🌼🙏

ብዙ የመኪና ውድድር የምናይበት
የመኪናው ኢንደስትሪ የሚስፋፋበት
መኪና ያልገዛችሁ የምትገዙበት
በብዙ የምናተርፍበት አመት ይሁንልን

አሁን አሜን በሉ ከሆነ በሗላ ከምትሉ 😁
ፈገግ የምትሉበት አመት ይሁንላችሁ

@OnlyAboutCarsEthiopia
Only About Cars Ethiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን በአንድ ቻርጅ እቤታችን ውስጥ ምን ያህል ሰአት እና ወጪ አለው? ይህንን የማሳያችሁ በ VW ID.4 መኪና ነው :: VW ID.4 82 KWh Battery Pack ሲኖረው መኪናው የሚጠቀመው 77 KWh Battery Packun ነው :: ስለዚህ በአንድ ቻርጅ ወደ 110 ብር ይፈጃል :: በአንድ ቻርጅ ደግሞ 400 ኪሎሜትር ይጟዛል :: በቂ ነው ብዬ አስባለው :: ግን ችግሩ በ 2.3…
ቮልክስዋገን ኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት የገባውን ኤሌክትሪክ መኪና አሻሽሎ አቀረበ

ቮልስዋገን ID Xtreme ባሳለፍነው ሳምንት ለእይታ አቅርቧል :: ይህ Xtreme ጽንሰ-ሐሳብ የመጣው ከ ID.4 GTX ሞዴል ሲሆን ከ GTX ሞዴሉ 87 የበለጠ የፈረስ ጉልበት አለው ። 382 የፈረስ ጉልበት ነው ያለው ::
ሌሎች ማሻሻያዎቹ ሰፋ ያሉ ዊል አርቼች( የጎማ መሸፈኛዎች) ፣ የኤልኢዲ ባር ከላይ እና እንደገና የተነደፈ ባምፐር (ግጭት መከላከያ) ከቡል ባር ጋር እና ከስር ያለው የቦዲው ከቨር በአልሙኒየም የተሸፈነ ነው ። ID.4 ላይ ምን ያህል ሰአት ቻርጅ ለማድረግ እንደሚፈጅ እና ያሉትን ለየት ያሉ ነገሮች ከስር ያለውን ሊንክ በመንካት ማግኘት ትችላላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/nI6O9FXwQBI

ልዩ ምሽት ተመኘን
#VW #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
Pagani አዲሱን Utopia ሞዴሉን አውጥቷል

Pagani Utopia

AMG 6.0L V12 Twin ቱርቦቻርጅድ ሞተር ሲኖረው 852 የፈረስ ጉልበትም እንደሚኖረው ተናግረዋል :: በ ማንዋል ጊርቦክስ ብቻ የሚመጣ መሆኑንም አሳውቀዋል :: ይህንን ሞዴል 99 ብቻ የሚያመርቱ ሲሆን ዋጋው 2.5 ሚሊየን ዶላር ነው ::

ልዩ ምሽት ተመኘን
#Pagani #Manual
@OnlyAboutCarsEthiopia
Chrysler የመጨረሻውን 300C V8 ሞተር እንደሚያመርት አስታወቀ ::

ይህንን መኪና እኛ ሀገር በሊሞዚን አልያም ደግሞ ለሰርግ ሲጠቀሙበት አይታችሁ ሊሆን ይችላል :: የመጀመሪያው Chrysler 300 በ 1955 ሞዴል ነበር ለገበያ የቀረበው ። ሞተሩ ባለ 5.4 ሊትር hemi V8 ሲሆን ለዘመኑ ኃይለኛ ሞተር ያለው መኪና ነበር :: አዲሱም በተመሳሳይ V8 የሚገኝ ሲሆን ግን ባለ 6.4 ሊትር ሞተር ነው ::

300C ባለ ስምንት ፍጥነት ያለው አውቶማቲክ ትራንስሚሽን እና ማርሹን ለመቀየር 160 ሚሊሰከንዶችን ብቻ እንደሚፈጅበት ተናግሯል ። አዲሱን 300C ከ 0 እስከ 60 ማይል በሰአት (0-97 ኪሎ ሜትር በሰዓት) በ 4.3 ሰከንድ ውስጥ ይደርሳል ። ከፍተኛው ፍጥነት 160 ማይል በሰአት (278 ኪ.ሜ) ነው።

ምርጥ ከሰአት ተመኘን
#Chrysler #CarNews
@OnlyAboutCarsEthiopia
ይህ የ 2023 Toyota GR Corolla አሁን ለሽያጭ ቀርቧል ::

Toyota እስከዛሬ አይታችሁ ከምታውቁት ገራሚ እና የተሻለውን ኮሮላ እንደነበር ገልፀን ነበር ::
ይሄ ባለ 300 የፈረስ ጉልበት ያለው መኪና በ6 speed manual transmission እና በ AWD ብቻ ነው የሚገኘው :: ወደ ሞተሩ ስንመጣ ደግሞ 1.6 ሊትር 3 ሲሊንደር ያለው ሞተር ሲኖረው 300 hp ያመነጫል :: ይሄ በ Gazoo Racing የተሰራ ሲሆን በጣም ብዙ performance upgrade ተደርጎለታል :: ዋጋው ከ 37,000 የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ወደእኛ ሲቀየር የ 2022 Tucson ዋጋ ማለት ነው :: አንድ በ Gazoo Racing የተሰራ መኪና ኢትዮጵያ ውስጥ አለ :: እንዲሰራ የምትፈልጉ ከሆነ ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን ::

ሙሉውን ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZML9Qrqrn/

ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ 🙏
#GRCorolla #Toyota
@OnlyAboutCarsEthiopia
በተለይ አዳዲስ መኪኖች ላይ ይህንን በተን አታጡትም ::
Cruise Control
Cruise Control በጣም ጠቃሚ የሚያደርገው በፈለጋችሁት መካከለኛ ወይንም ከፍተኛ ፍጥነት ላይ በተመሳሳይ ፍጥነት መኪናው እንዲጟዝ ማድረግ ነው :: ይህ የሚጠቅመው በተለይ ለኛ ሀገር የፍጥነት ገደብ ወሰን ያለባቸው መንገዶች ላይ ስትነዱ በጣም ቀላል ያደርገዋል :: ግን እንዴት ነው እንዲሰራ ማድረግ የሚቻለው የሚለውን አጠር ያለ ቪድዮ ዩትዩብ ላይ ታገኛላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/2R6o7sWfdNs

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Cruisecontrol
@OnlyAboutCarsEthiopia
እነዚህን 4 አፖች ብትጠቀሙ በስልካችሁ ለቲክቶክ እና ለዩትዩብ ቪድዮ እንዲሁም ለቴሌግራም ፖስት አሪፍ የምንላቸው ናቸው ::

በተደጋጋሚ የተጠየቀ ጥያቄ ስለሆነ ነው ::
የመጀመሪያው PhotoRoom ሲሆን ይህንን የምንጠቀመው የሚያስፈልገን ፎቶ ላይ ባክግራውንዱ እንዲጠፋ ስንፈልግ ነው ::
ሁለተኛው ደግሞ CapCut ሲሆን እዚህ ላይ ቪዲዮዎቻችሁን ለቲክቶክ እንዲሁም ለዩትዩብ እንደምትፈልጉ ማስተካከል ያስችላችሗል ::
ሶስተኛው Snapseed ሲሆን ይሄ አፕ የሚጠቅመው ፎቶዎቻችሁን እናንተ በምትፈልጉት ዲዛይን መስራት ስለሚያስችላችሁ ነው :: ይህንን የምንጠቀመው በብዛት ለ Youtube Thumbnail ሲሆን ካገኘናቸው የስልክ አፖች ከ Photoshop ጋር በጣም ተቀራራቢ የሆነ የስልክ አፕ ነው ::
የመጨረሻው ደግሞ PhotoGrid ነው :: ይህ አፕ የሚጠቅመው የራሳችሁን Watermark ለማስቀመጥ ከላይ እንደምትመለከቱት እና ብዙ ፎቶ አንድ ላይ ሰብሰብ አድርጎ አንድ ፎቶ ለማድረግ የሚረዳ አፕ ነው ::
እነዚህን አፕሊኬሽኖች በ ios እና በ Android ላይም ታገኛላችሁ :: እንዴት መጠቀም እንችላለን ካላችሁ ብዙ ቪድዮዎች አሉ ዩትዩብ ላይ ግን በጣም ቀላል ናቸው ራሳቸው ጋይድ ስለሚያደርጉ ::

መልካም ቀን
#apps #editing
@OnlyAboutCarsEthiopia
በአጠቃላይ አሁን ላይ መኪኖች የሚሸጡበት ዋጋ በጣም እየጨመረ ያለው ለምን ይመስላችሗል?
Anonymous Poll
25%
ሻጮች ያለአግባብ በጣም እየጨመሩ ስለሆነ ነው
60%
ገንዘብ በጣም ዋጋ እያጣ ስለሆነ ነው
15%
ወይስ ደላሎች ሆን ብለው ነው እየጨመሩ ያሉት
ከውጭ የሚገቡ ሆነ ሀገር ውስጥ የሚመረቱ የኤሌክትሪክ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፣ የቤት አውቶሞቢሎችና የእቃ መጫኛ ተሽከርካሪዎች ላይ ዝቅተኛ የጉምሩክ ታሪፍ የሚጣልባቸው ሲሆን ከተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከኤክሳይዝ ታክስና ከሱር ታክስ ነፃ መደረጋቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

የታክስ ማሻሻያው በርካታ ዓላማዎች ያሉት ሲሆን ከዓላማው አንዱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲቀርቡ ለማስቻል ነው።

በታክስ ማሻሻያው መሰረት (የቤት አውቶሞቢሎች) ፦

1ኛ. ሙሉ በሙሉ ተበትነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ አውቶሞቢሎች ከጉምሩክ ቀረጥ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ ሙሉ በሙሉ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

2ኛ. በከፊል ተበትነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ የኤሌክትሪክ የቤት አውቶ ሞቢሎችን 5 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ብቻ የሚጣልባቸው ሲሆን ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ ሙሉ በሙሉ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

3ኛ. ሙሉ ለሙሉ ተገጣጥመው ያለቀላቸው የኤሌክትሪክ አውቶሞቢሎች ወደ ሀገር ሲገቡ 15 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ብቻ የሚጣልባቸው ሲሆን ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ ሙሉ በሙሉ ነጻ እንዲሆኑ ተወስኗል፡፡

Source: tikvahethiopia

ግሩም ከሰአት ተመኘን
#electric #Ethiopia
@OnlyAboutCarsEthiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቻይና ባቡሮቿ ላይ የምትጠቀመውን ቴክኖዎሎጂ መኪና ላይ እየሞከረች ነው ::

ቻይና ከማግሌቭ ባቡሮች ቴክኖዎሎጂ ተጠቅሞ በራሪ መኪና እየሞከረች ትገኛለች :: ይህ ቴክኖሎጂ እውን ከሆነ የጎማ እና የመንገድ ግጭት ስለሚወገድ መጓጓዣ ይበልጥ ቀልጣፋ ይሆናል። የአጠቃቀም ጉዳዮች ለመኪናዎች የበለጠ ክልል እና ምናልባትም ኢንዳክቲቭ ቻርጅ ለማድረግ እየነዳችሁ ስለሚሆን በጣም አሪፍ ያደርገዋል :: ስለዚህ ሙከራው አልቆ ቶሎ ቢጀምር ከወጪም አንፃር የተሻለ ነው ::

ፍክት ያለ ቀን ተመኘን
#China #EV #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Bugatti EB110 GT በሃይድሮሊክ የተገጠመ የኋላ ክንፍ እንደነበረው እና የሚነሳበት ብቸኛው መንገድ የመኪናው ሞተር ሲነሳ እንደሆነ ያውቃሉ? የBugatti EB110 ኦሪጅናል እና ያልተሻሻለው አንዱ ምልክት ይህ መኪናው በሚነሳበት ጊዜ ክንፉ ከፍ ይላል እና መኪናው በዘጋ ቁጥር ክንፉ ይወርዳል ::

ድንቅ ቀን ተመኘን
#Bugatti #CarFacts
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሴቶች በጣም የሚወዱት ይህንን መኪና ለምንድነው?
2022 Range Rover Sport

አዲሱ Range Rover Sport መኪና 3ኛው ጀነሬሽን ሲሆን መጀመርያ የተመረተው በ 2005 ላይ ነበር :: ዲዛይኑን በማሳመራቸው በ 2022 ገራሚ ከሚባሉ SUV መኪኖች አንዱ አድርገውታል :: የሚገርመው እዚህ መኪና ላይ የምታገኙትን ቴክኖሎጂ ትልቁ Range Rover መኪና ላይም አታገኙትም :: ግን ደግሞ ሬንጅ ሮቨር በአጠቃላይ እንደ ብራንድ በጣም ቶሎ ቶሎ የሚበላሹ እና ስፔር ፓርታቸውም በጣም ውድ የሆኑ መኪኖች ናቸው :: እንደዛ መሆኑን እያወቁ የሚገዙ ሰዎችም አሉ :: የሚገርመው እሱ ነው :: ምን ቢኖረው ይህንን ያህል ያስወደደው ስለ አዲሱ Range Rover Sport ማወቅ ያለባችሁን በሙሉ ከስር በምታገኙት ቪድዮ ላይ አለ ::
ሙሉውን ቪድዮ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/WP7hMR55sMA

ግሩም ምሽት ተመኘን
#RangeRover #RangeRoverSport
@OnlyAboutCarsEthiopia
የዳሲያ ማኒፌስቶ ኮንሴፕት መኪናቸውን ይፋ አደረጉ ::

ይህ የኤሌክትሪክ መኪና ውጫዊ ቦዲው በፕላስቲክ የተሰራ ሲሆን ፣ ሊታጠብ የሚችል የውስጥ ወንበሮች እና ተነቃይ የመቀመጫ መሸፈኛ እሱም እንደ መኝታ ቦርሳ የሚያገለግል ነው ::

ደስ የሚል ቀን ተመኘን
#Dacia #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/24 16:31:13
Back to Top
HTML Embed Code: