Telegram Web Link
የተለያዩ መኪኖች ላይ የሚገኙ ለየት ያሉ ማርሾች አሉ :: ከነሱም ውስጥ 8ቱ አሪፍ ዲዛይን ያላቸው ማርሾች

1. BMW 8 Series - የክሪስታል ማርሽ ሲሆን ከሌሎቹ የሚለየው እና አይን የሚስበው ተለቅ ስለሚል እና ውስጡ በደንብ ስለሚታይ ነው ::
2. Chevrolet Corvette - አሁን ላይ ብዙዎቹ አዳዲስ እና ኤሌክትሪክ መኪኖች በተን ማርሽ ይጠቀማሉ :: የዚህ መኪና ለየት የሚያረገው ከጎኑ ማርሽ የሚመስል ነገር መጨመራቸው ነው ::
3. Ford F-150 - የዚህን መኪና ማርሽ ለየት የሚያደርገው ታጥፎ ወደውስጥ መግባት በመቻሉ ነው :: ይህም የሆነው መሀል ላይ ያለውን ቦታ ለሌላ ነገርም መጠቀም እንዲቻል በማሰብ ነው ::
4. Genesis GV60 - በጣም ለየት ብለው ካገኘናቸው ማርሾች ውስጥ አንዱ ነው ::
5. McLaren 765LT - የዚህ መኪና ማርሽ ማርሽ አይመስልም :: ሌላ በተን ነው የሚመስለው ::
6. Pagani Huyara - ይሄ ውድ ከሚባሉ መኪኖች ውስጥ ሲሆን ማርሹም ትንሽ ለየት ይላል :: የውድድር መኪኖች ላይ ያሉ ማርሾችን ነው የሚመስለው ::
7. Rimac Nevera - ይህ ባለ 2000 hp ያለው ኤሌክትሪክ መኪና ሲሆን የሚሽከረከር ማርሽ ነው ያለው ::
8. Volvo XC90 - የመጨረሻው ደግሞ ከመጀመርያ BMW 8 Series ጋር ተመሳሳይ የክሪስታል ማርሽ ሲኖረው ይሄኛው አነስ ይላል ::

ብሩህ ቀን ተመኘን
#GearShifter
@OnlyAboutCarsEthiopia
ከላይ ከዘረዘርናቸው ለየት ያሉ የመኪና ማርሾች የቱን ወደዳችሁ?
Anonymous Poll
33%
BMW 8 Series
9%
Chevrolet Corvette
18%
Ford F-150
16%
Genesis GV60
8%
McLaren 765LT
7%
Pagani Huyara
3%
Rimac Nevera
6%
Volvo XC90
ይህ መኪና ኢትዮጵያ ውስጥ ገባ
2022 Nissan Navara Pro4X

ይህ የ 2022 Nissan Navara Facelift የተደረገለት ሲሆን የሚገርም ዲዛይን ነው ያለው :: ብዙ ጥቁር ፕላስቲኮችን የጨመሩ እዚህ Pro4X ሞዴላቸው ላይ ነው :: ግን ምን የተለየ ነገር ቢኖረው ነው ኒያላ እንደዚህ በትልቁ ያስመረቀው :: ሙሉ ቪድዮውን ዩትዩብ ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/jRHdsb67IeA

ልዩ ምሽት ተመኘን
#Nissan #NissanNavara
@OnlyAboutCarsEthiopia
Bentley የመጀመሪያውን Plug-in ሀይብሪድ መኪና አውጥቷል ::

ይህ Bentley Flying Spur በአለማችን ላይ ውድ ከሚባሉ ሴዳን መኪኖች አንዱ ሲሆን አሁን Plug-in ሀይብሪድ ሞዴል አማራጭ ጨምረዋል :: ይህ መኪና twin turbo V6 ሞተር ሲኖረው በአንድ ሙሉ ቻርጅ በኤሌክትሪክ ብቻ ከ 33 ኪሎሜትር በላይ መጟዝ ይችላል ::

ግሩም ምሽት ተመኘን
#Bentley
@OnlyAboutCarsEthiopia
መኪና መከራየት ፈልጋችሁ ያለ ሹፌርም በሹፌርም የት እንደምታገኙ ግራ ገብቷችሁ ያውቃል?

እኛም እስከአሁን ድረስ ይሄ አሪፍ የመኪና አከራይ ድርጅት ነው :: በቀላሉ እዚህ ዌብሳይት ላይ ማግኘት ትችላላችሁ የምንለውን አላገኘንም :: መኪና የሚያከራዩ በደንብ የተቀናጁ የምታውቋቸው ድርጅቶች አሉ? እስኪ ካሉ ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን ::

መልካም ቀን ይሁንላችሁ
#CarRent
@OnlyAboutCarsEthiopia
40ሺህ አልፈናል
ሁላችሁንም በጣም እናመሰግናለን 🎉🙏

ዩትዩብ ከጀመርን 2 አመት ሊሞላን ነው በዚህ ጊዜ ውስጥ የቻልነውን ለህብረተሰቡ የሚጠቅመውን ምክሮች የአዳዲስ መኪና ሪቪዎችን እና አስተማሪ ቪድዮ እየሰራን ቆይተናል :: የተለያዩ ጥያቄዎችን በመጠየቅ በተለያዩ ጊዜያት ከምንሰራቸው የቁልፍ መያዣዎች ስጦታዎችን ስንሰጥ ቆይተናል :: የቀረን መኪና ነው እሱም አይቀርም 😁 ዛሬ ማታ ለየት ያለ የመኪና ሪቪው የምንለቅ ይሆናል :: 50 ሺህ ስንደርስ ደግሞ ለየት ያለ ነገር ይዘን እንመጣለን ብለን እናስባለን :: ማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ጥያቄ እንዲሁም እንዲሰራላችሁ የምትፈልጉት ቪድዮ ካለ ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን :: በድጋሚ ሁላችሁንም እናመሰግናለን :: ማታ በአዲስ ቪድዮዩትዩብ ላይ እንገናኝ

ደስ እንዳሰኛችሁን ደስ የሚል ቀን ይሁንላችሁ ☺️
#youtube #yonathandesta
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለምን ይህንን መኪና ወደድኩት?

ይህ የ 2021 Nissan Juke N-Design ሲሆን ከበፊቱ ጋር በጣም ልዩነት አለው :: ከውጪ ዲዛይን ጀምሮ ውስጣዊ ገፅታው ያለው ቴክኖሎጂ እንዲሁም ያለው የውስጥ ስፋት በጣም ገርሞኛል :: ይሄ በሙሉ ተደምሮ ነው ዛሬ የዚህን መኪና ሪቪው የሰራነው :: ሙሉውን ቪድዮ ዩትዩብ ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/gzd3ObBesEw

ውብ ምሽት ተመኘን
#Nissan #NissanJuke
@OnlyAboutCarsEthiopia
Nissan Navara Pro4X

ውይ በቃን ስለዚህ መኪና ትሉ ይሆናል :: ግን ዩትዩብ ላይ ያልጠቀስነውን ነገር ቲክቶክ ላይ ለቀናል ለማለት ነው :: ከዚህ በሗላ ወደ ቲክቶክ ስለተመለስን በዛውም አጠር ያለ ቪድዮ እንዲሰሩላችሁ የምትፈልጉትን ሀሳብ ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን ::
የቲክቶክ ቪድዮ
👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMNp4y8wm/?k=1

ምርጥ ከሰአት ተመኘን
#NissanNavara #Tiktok
@OnlyAboutCarsEthiopia
የስፖኪዮ ስርቆት በአዲስ አበባ

በከተማችን በተለይ ባለፈው ወር በጣም ብዙ የመኪና ስፖኪዮ ተሰርቋል :: በተለይ ደግሞ መብራት ላይ እና የተጨናነቁ መንገዶች ላይ መኪናችሁ ውስጥ ብቻችሁን እንደሆኑ ካዩ በሗላ ትንንሽ ልጆች ለሁለት ወይም ለሶስት ሆነው ይሰርቃሉ :: መኪናችሁን አባራችሁ እንዳትይዙ ሌሎቹ ስትወጡ ጠብቀው ሌላ እቃ ይሰርቃሉ :: ስለዚህ ጠንቀቅ በሉ ለማለት ነው :: መፍትሄ ይሆናል ብለን ያሰብነውን ቲክቶክ ላይ ለቀናል
👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMNsJQubC/?k=1

ውብ ምሽት ተመኘን
#CarMirror #Spocio
@OnlyAboutCarsEthiopia
2023 Meyers Manx 2.0 ኤሌክትሪክ በጊ ለእይታ ቀርቧል ::

ይህ በ 1960ዎቹ Volkswagen ዲዛይን የተሰራው ሲሆን የመጀመሪያው ሙሉ በሙሉ በፋይበር ግላስ የተሰራ መኪና ነው :: ይህ ኤሌክትሪክ መኪና በሁለት የባትሪ አማራጮች የሚገኝ ሲሆን በ 20Kwh 241 ኪሎሜትር በ 40Kwh ባትሪ ፓክ ደግሞ 483 ኪሎሜትር ይጟዛል ተብሏል :: ዋጋው ይፋ አልተደረገም :: ግን የመጀመሪያዎቹ 50 መኪኖች በቅርቡ እንደሚያወጡ ይፋ አድርገዋል ::

ምርጥ ምሽት ተመኘን
#Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ከዚህ በፊት የጠየቅናቸውን መኪኖች አብዛኛዎቹን ሰርተናል :: በየሳምንቱ የምንለቅ ይሆናል :: መኪኖችን እንድንቀርፅ እየፈቀዳችሁልን ስለሆነ እያመሰገንን በተለይ ደግሞ መንገድ ላይ አስቁማችሁ እንድሰራ ቪድዮ እየጠየቃችሁኝ ስላላችሁ እጅግ አርጌ አመሰግናለሁ :: በቀጣይ ሪቪው ለመስራት ያሰብናቸው መኪኖች ከላይ የምትመለከቷቸው ናቸው :: እናም ከነዚህ ውስጥ አንዱ መኪና ያላችሁ ሰዎች የሚሸጥ ካልሆነ ቪድዮ ለመስራት ስለምንፈልግ ፈቃደኛ ከሆናችሁ በ @yonathandesta ላይ መልእክት በመላክ እንድትተባበሩን እንጠይቃለን ::
የመኪኖቹ ዝርዝር
- Hyundai Palisade
- Peugeot 5008
- FAW Bestune
- Suzuki Vitara
- Toyota Raize
- Toyota Corolla Cross
- Toyota Wigo/Agya
- Suzuki Celario
ከዘረዘርኳቸው ውጪ መኪኖችም ካሉሏችሁም በ @yonathandesta አናግሩን :: እናንተ እንዲሰራበት የምትፈልጉትም መኪና ካለ ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን :: የግድ የ 2022 ወይም የ 2021 ብቻ መሆን የለባቸውም :: መኪኖቹ ላላቸው ሰዎች ሼር አድርጉላቸው :: ቪድዮዎቹን የምታገኙት ዩትዩብ ላይ ነው ::
👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtube.com/c/yonathandesta?sub_confirmation=1

ልዩ ከሰአት ተመኘን
#CarReview
@OnlyAboutCarsEthiopia
የመኪናችንን ጎማ ከፍ ወዳለ ስናሳድግ ምን ለውጥ ይኖራል ?

ብዙዎቻችን እንደዚህ አይነት መኪኖችን ስናይ ምን ያህል መኪናችን ላይ ለውጥ እንዳለው አናውቅም :: ግን ትልቅ ለውጥ አለው :: ተለቅ ያለ ጎማ ስናደርግ ሙሉ የሰስፔሽን እና የፍሬን ሲስተሙን መቀየር ይኖርብናል :: ግን መኪናችን ላይ ምን ምኑ ላይ ለውጥ ይኖራል የሚለውን አጠር ያለ ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ለቀናል ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMNsq3oQk/

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#CarTires
@OnlyAboutCarsEthiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህንን ያውቃሉ?

እንደዚህ የሚታጠፉ መያዣዎች ያሏቸው መኪኖች ላይ ወርዶ እንዲቀር ማድረግያዎች አሏቸው :: ምን አልባት መኪናችሁ ላይ ካለ ይህንን ሞክሩት ::

ድንቅ ከሰአት ተመኘን
#Handle #AmazingStuff
@OnlyAboutCarsEthiopia
እስከ 2000 ኪሎሜትር የተነዳ መኪና ለሽያጭ ሲቀርብ እንድትገዙ የማልመክርበት ምክንያት ምንድነው?

በዚህ ፍጥነት የሚሸጡ መኪኖች አንድ ወይ መኪኖቹ በስርአት አልተያዙም ወይ ደግሞ መኪኖቹ ችግር ሊኖርባቸው ይችላል ::
ይህንን ያልኩበት ምክንያት መኪኖቹ በዚህ ፍጥነት ሲሸጡ በጥንቃቄ ስለማይዙት ነው ::
አብዛኛውን አዳዲስ መኪኖች የሚነዱ ሰዎች ለማጆች ስለሆኑ ብዙ መደረግ የሌለባቸውን ነገሮች ያደርጋሉ ::
ለማማከር የምትፈልጉ ቴሌግራም ላይ @YonathanDesta ብላችሁ ታገኙኛላችሁ ::
አጠር ያለ ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ለቀናል
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMNG71yxA/

ግሩም ምሽት ተመኘን
#NewCar
@OnlyAboutCarsEthiopia
2020 Hyundai Palisade

በ2020 ሞዴሉ 3 የ trim-levelኦች ሲኖሩት የSE ፤SEL እና Limited በ2021 እና 2022 ሞዴሎቹ ደግሞ ተጨማሪ 4ኛ Calligraphy Trim Level ጨምረዋል ። በ 2.2 ሊትር ናፍጣ ወይም በ 3.5 ሊትር 3.8 ሊትር V6 ሞተር እና 8-speed automatic transmission ሲኖራቸው
የ SE-trim-level በዋነኝነት የLane-safty, collision-avoidance-assist, Apple-carplay እና Android-Auto tools ሲኖሩት። የ SEL-trim-level ደሞ በ 4 አይነት አማራጮች ይመጣል :: እነሱም የ Convenience ,Premium ,Sunroof እና guidance packageኦች ናቸው።
• የSEL-convenience-package በዋነኝነት 20-inch-rims, power-seats, blind-spot-detection እና power-liftgate ሲኖረው በSEL-premium ደግሞ ተጨማሪ ሌዘር-ወንበሮች እና ብዙ የAC አማራጮች አለው። ሌላው ደግሞ የSEL-guidance-package የ navigation-tool ሲኖረው አንድላይም በSEL-premium-guidance-sunroof አማራጭ ማግኘት ይቻላል።
የlimited-trim-level ከSEL-fully-loaded በተጨማሪ ለየት ባለ የፊትለፊት-Grille እና ተጨማሪ sunroof ሲኖረው በመጨረሻም የ Calligraphy-trim-level ከlimitedኡ ብዙም ባይለይም አንዳንድ የluxury-መልክ የሚሰጡ aesthetic ለውጦች ተደርገውበታል ።
ቪድዮውን ቲክቶክ ላይ ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMNtMBa7f/

ልዩ ምሽት ተመኘን
#Hyundai #HyundaiPalisade
@OnlyAboutCarsEthiopia
Dodge አዲሱን የ 2023 Hornet ሞዴላቸውን ለእይታ አቅርበዋል ::

ይህ መኪና ለ Dodge የመጀመሪያው ኮምፓክት SUV ሲሆን ይወዳደራል ተብሎ የሚጠበቀውም ከ Toyota RAV4, Honda CR-V እና Nissan X-Trail ጋር ነው :: በሶስት ትሪም ሌቭል እንደአማራጭ ያቀረቡ ሲሆን በ GT, GLH እና R/T ሞዴል አቅርበዋል :: GT ላይ 2.0 ሊትር 4 ሲሊንደር 268 የፈረስ ጉልበት(HP) ሲኖረው ከ 0 እስከ 100 ኪሎሜትር በሰአት 5.6 ሰከንድ ብቻ ይፈጅበታል ብለዋል :: ከፍተኛ ፍጥነቱም 225 ኪሎሜትር በሰአት ነው ::
ወደ R/T ትሪም ሌቭል ስንመጣ ደግሞ Plug-in Hybrid ሞዴሉ ሲሆን 1.3 ሊትር 4 ሲሊንደር 288 የፈረስ ጉልበት(HP) ሲኖረው ከ 0 እስከ 100 ኪሎሜትር በሰአት 5.1 ሰከንድ ብቻ ይፈጅበታል ብለዋል :: ይሄ ለእኛ ሀገር ታክስ ሲስተም በጣም ተመራጭ ያደርገዋል ::
ለምን እንደሆነ ታክሱን እንዴት እንደሚሰራ የሰራሁትን ቪድዮ ከስር ታገኛላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/Ib9S7B59Mhw

ስለ ሀይብሪድ አይነቶች ደግሞ ለመመልከት
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/AhbvADJUeKg

መልካም ቀን ተመኘን
#Dodge #Hybrid
@OnlyAboutCarsEthiopia
ስለመኪናችሁ ቁልፍ የማታውቋቸው ነገሮች

የመኪና ቁልፍ አይነቶች በቁጥር ከ10 ቢበልጡም እኛ ግን ዋና ዋና የምንለውን 7 መርጠን በዛሬው የዩትዩብ ቪድዮ ይዘን ቀርበናል :: ስለእያንዳንዱ በደንብ የምንመለከት ይሆናል :: ምን አልባት የማታውቋቸውንም የቁልፍ አይነቶች ልታገኙ ትችላላችሁ :: ተመልከቱት ጋበዝናችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/61BuHk_eRkA

ድምቅ ያለ ምሽት ተመኘን
#CarKey
@OnlyAboutCarsEthiopia
የ Dodge በኤሌክትሪክ የሚሰራ Muscle መኪና ለእይታ አቅርቧል ::

በ ቻርጅ የሚሰራ Charger ሞዴል መኪናቸውን ከሰአታት በፊት ያወጡት ሲሆን ይህ Dodge Charger SRT Concept መኪና የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ Muscle Car ሆኗል ::
እውነቱን ለመናገር ዲዛይኑ የሚገርም ነው ::
3 ለየት ያሉ ነገሮችን ጨምረዋል ::
1. R Wing
2. Erupt
3. የተለየ ድምፅ
የመጀመሪያ ሁለቱ ምን እንደሆኑ ቲክቶክ ላይ ቪድዮ ለቀናል ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMNndbkc1/

ውብ ምሽት ተመኘን
#Dodge #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/24 20:31:24
Back to Top
HTML Embed Code: