Telegram Web Link
በሁለት ጎማዎች መኪናን ማሽከርከር

ባለ አራት ጎማ ያለውን መኪና በሁለት ጎማዎች እንዲሄድ ማድረግ በጣም ይገርማል :: ሞክሩት ለማለት ነው 😂
ይህንን ነገር አረቦች ሲያደርጉት አይታችሁ ይሆናል ብለን እናስባለን :: ለማድረግ ከባድ ቢመስልም እነሱ ቀለል አድርገው ሲያሽከረክሩ አይታችሁ ይሆናል :: ካላያችሁት እንድታዩት ጋበዝናችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMNnDRwWy/

ገራሚ ምሽት ተመኘን 🙏
#CarFacts #twowheel
@OnlyAboutCarsEthiopia
Nissan Qashqai ለምን ይመስላችሗል እንደሌሎቹ ዋጋው በጣም እየጨመረ የማይሄደው?

ከ 2014-2017 ያለው Qashqai በብዛት ስለገባ እነዚህን ችግሮች ታገኛላችሁ ::

1. Pipe በደንብ ፊት አያደርጉም ::
2. የጀርባ ካሜራችሁ ሊበላሽ ይችላል ::
3. ጎማችሁን በየ 20,000 ኪሎሜትር እንድትቀይሩ ያስገድዳችሗል :: ካልሆነ ግን Shock absorber እንዲቀየር ያደርጋችሗል ::
4. ዘይት ሊያፈስ ይችላል ::
5. ዝም ብሎ የመሞቅ ችግር እንዳለው ታስተውላላችሁ ::
በመጨረሻም የፍሬን መስመሩ ችግር ስላለበት በካምፓኒው ተጠርቶ ነበር ::
እነዚህን በሙሉ ነገሮች የምታገኙት ከ 40 ሺህ እስከ 50 ሺህ ኪሎሜትር እስክትደርሱ ነው :: ግን ዋናው ችግራቸውን ቲክቶክ ላይ ቪድዮ ሰርቼበታለሁ :: እንዲሁም ከ 2018 ወዲህ ያሉትንም ችግሮቻቸውን እዛው ቪድዮ ላይ ከስር አስቀምጫለሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMNnbUYWB/

ፈታ ያለ ምሽት ተመኘን
#Nissan #NissanQashqai
@OnlyAboutCarsEthiopia
ቪድዮ ላይ እንደምትመለከቱት ከ Bugatti Chiron ባለቤት በሞተር ሊሰርቁ ሲሞክሩ ነው :: እኛ ሀገርም ምንም እንኳን ቡጋቲ ባይሆንም ሌቦች በጣም እየበዙ ነው :: በተለይ ደግሞ የስፖኪዮ ሌቦች በየቀኑ የምንሰማው ነገር ነው :: ጠንቀቅ በሉ ::

መልካም ምሽት
#Bugatti
@OnlyAboutCarsEthiopia
ስለ መንሱር መኪና ቪድዮ እንድንሰራ በተደጋጋሚ ተጠይቀን ነበር ::
ይሀው ለቀናል :: እንዲሁም ሽልማት የሚያስገኙ ጥያቄዎችንም ያዘለ ቪድዮ ነው ::

የመንሱር 666 ሀመር መኪና | Mensur Jemal Hummer H3 Car
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/8RFfS8SGrwA

ውብ ምሽት ተመኘን
#Mensur #Hummer
@OnlyAboutCarsEthiopia
ቴስላ ሞዴል S Plaid ን የሚቀናቀን መኪና ይሄ ነው?

ይህም የሆነው አሁን የ Lucid Company CEO የ ቴስላ Model S ዲዛይነር ስለነበር ነው :: Lucid Air Dream, Grand Touring አሁን ደግሞ በቅርቡ Lucid Air Sapphire ሞዴላቸውን ለእይታ አቅርበዋል :: አዲሱ Lucid Air Sapphire 1,200 HP ሲኖረው ከቴስላ ከኳሊት ጀምሮ performanceum የተሻለ ነው :: ከ 0-100 ኪሎሜትር በሰአት ከ 2 ሰከንድ በታች እንደሚገባ አሳውቀዋል :: እስኪ ሲወጣ በደንብ የምናየው ይሆናል :: ዋጋው ግን ከ 249 ሺህ ዶላር የሚጀምር ይሆናል :: ከ Tesla Model S Plaid እጥፍ ይጨምራል :: ግን የሚቀንሱ ዋጋ ያላቸው ሞዴሎች ልክ እንደ Lucid Air Grand Touring ያሉ ሞዴሎች አሉ :: ስለሱ በደንብ የተብራራ ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ታገኛላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMNWW7YDq/

ውብ ምሽት ተመኘን
#LucidAir #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
Lamborghini Urus

መጪው Lamborghini Urus ቀድሞ በ2018 Bentley Bentayga ተይዞ የነበረውን የPikes Peak ሪከርድ በ17.9 ሰኮንድ በማሻሻል አዲስ ሪኮርድ ማስመዝገብ ችሏል።
ይህ August 19 ይፋ የሚደረገው አዲሱ Urus ሞዴል 4302m የሚረዝመውን የPikes Peak ተራራን በ10 ደቂቃ 32 ሰከንድ ጊዜ በመውጣት የPikes Peak production SUV ሪከርድን የራሱ አድርጎታል።

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#carnews
@OnlyAboutCarsEthiopia
Turbo charger እና Supercharger ልዩነታቸው ምንድነው?

ሁለቱም ሀይልን በመጠቀም የበለጠ አየር ወደ ሞተር በማስገባት የሞተሩን ጉልበት፣ ነዳጅ አጠቃቀም (fuel economy) ለመጨመር ይጠቅማሉ።

ዋና ልዩነታቸውን ምንድነው?

1.  የአሰራር መንገዳቸው - አየር ለማስገባት Turbo charger ከሞተሩ የሚወጣውን ጭስ የሚጠቀም ሲሆን Supercharger ደግሞ (ከcrankshaft ጋር በመገናኘት) የሞተሩን ጉልበት ነው የሚጠቀመው።

2. Supercharger የተፈለገውን ጉልበት ወዲያው የሚያደርስ ሲሆን Turbo charger ትንሸ ይዘገያል።

3. Turbo charger የሞተርን የፈረስ ጉልበት ከ30% እስከ 40% ሊጨምር ይችላል። ከሞተሩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው Supercharger ደግሞ ከ 50% እስከ 100% ጉልበት ሊጨምር ይችላል።

4. Turbocharger ከ Supercharger የበለጠ ጸጥ ያለ ነው።

ምርጥ ቀን ተመኘን
#Turbocharger #Supercharger
@OnlyAboutCarsEthiopia
አንጋፋዎቹ የደቡብ ኮሪያ ኩባንያዎች Hyundai እና Kia ከ2020 ጀምሮ ወደማርኬት አውጥተው ከሸጧቸው መኪኖች መካከል አብዛኞቹ በቆሙበት እሳት በመፍጠራቸው ምክንያት ባለፈው ሳምንት ጀምረው ካምፓኒዎቹ Recall ጠርተዋል።

ነገሩ እንዲህ ነው፤ Hyundai palisade እና Kia Telluride ግዙፍ እና ዘመናዊ SUV መኪናዎች ሲሆኑ በብዙዎች ዘንድም ተቀባይነትን ያፈሩ መኪኖች ናቸው በተለይ በሰሜን አሜሪካ ። ነገር ግን ከሰሞኑን የወጡት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አነዚህ ዘመናዊ መኪኖች ሰርኩት ቦርዳቸው ላይ በትንሽ እርጥበት ምክንያት በቀላሉ እሳት እንዲነሳ ምክንያት መሆናቸው ነው :: ለዚህም ነው እነዚህ ግዙፍ ኩባንያዎች ሞዴላቸው ከ2020 እስክ 2022 ያሉትን 245,000 Hyundai palisade እና 36,000 Kia Telluride መኪኖች እንደ አዲስ ወደ ካምፓኒው Recall የጠሩት ። በዛውም አክለው ወረፋውን ለሚጠባበቁ ባለንብረቶች ከጋራዣቸው ወይም ከቤታቸው አርቀው እንዲያቆሙ መክረዋል የሚሆነው ስለማይታወቅ።

ግሩም ቀን ተመኘን
#Recall #CarNews
@OnlyAboutCarsEthiopia
የአነጋጋሪው አንድሪው ቴት የመኪና ኮሌክሽን

ይሄ ለየት ያለ አስተሳሰብ ያለው ኢንተርፕለነር ከአስተሳሰቡም ውጪ ለየት ያሉ መኪኖች አሉት :: አምስት በጣም ለየት ያሉት መኪኖች እነዚህ ናቸው ::
1. Bugatti Chiron pur Sport
2. Aston Martin DBS Superlegerra
3. BMW M5 Competition
4. Ferrari 812 Superfast
5. Ferrari 458 Italia

ተጨማሪ ለየት ያሉ መኪኖችን ዩትዩብ ላይ ለቀናል :: ሊንኩን ከስር ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/WaoE5tRAeKQ

ፅድት ያለ ምሽት ተመኘን
#AndrewTate
@OnlyAboutCarsEthiopia
በፊልም ላይ የመጀመሪያው Car chase መቼ እንደጀመረ ያውቃሉ?

በፊልም ላይ የመጀመሪያው የመኪና ማሳደድ (Car chase) የመጣው ካሜራ እና አውቶሞቢል ከተፈለሰፈ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ነበር። እ.ኤ.አ. በ 1903 የባዮግራፍ ፎቶ ኩባንያ የመጀመሪያ የማሳደጃ(Chase) ትዕይንታችን ምሳሌ የሆነውን Runaway Matchን አዘጋጀ ። ምናልባት መኪናን ገና ያላዩ እና በጣም ያነሰ የሚነዳ መኪና ላላቸው ብዙ ሰዎች የልብ ህመም ነበር።
ነገር ግን በእያንዳንዱ አስር አመታት ውስጥ መኪኖቹ ፈጣን እየሆኑ እና የማሳደዱ ትዕይንቶች የበለጠ እየዘመነ መጣ ። ከ70ዎቹ የመኪና ማሳደጂያ(Car chase) ፊልሞች በኋላ፣ አንድ የሚታወቅ የማሳደድ ትዕይንት የተሞላ ፊልም The Blues Brothers በ 1980 ላይ ወጣ።
ከሃያ ዓመታት በኋላ፣ የተራቀቁ የፊልም ታዳሚዎች ከሚያሳድዱበት ትዕይንት የበለጠ የፈለጉት ከሃያ መኪና በላይ ፖሊሶች የሚያሳዱበትን ክፍል ነበር፤ ረሃባቸው የመኪና ማሳደድን(car chase) ብቻ ለመቅረጽ እስኪመስልም ድረስ ሄደው ነበር ከዛም እ.ኤ.አ በ2003 THE ITALIAN JOBS ለእይታ አበቁ ሌሎችም ልክ እንደ Fast and Furious ያሉ ፊልሞች እና በቅርቡ ደግሞ The Baby Driverንም መጥቀስ ይቻላል :: እነዚህ ሁሉ ውጣ ውረዶች ግን አሁን ላይ ላለንበት አጅግ ዘመናዊ የፊልም ኢንዱስትሪ ሚናው እጅግ የላቀ ነው። ያልጠቀስናቸው በጣም ብዙ አሉ :: እንድናያቸው የምትመክሩንን የመኪና ፊልሞች ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን ::

የሚመች ቀን ተመኘን
#CarChase #CarMovie
@OnlyAboutCarsEthiopia
ከዚህ በፊት መኪናዎችን ማሻሻጥ ስንሰራ የቆየን ሲሆን ካለፉት 4 ወራት ጀምሮ ግን እሱን በማቆም የማማከር አገልግሎት እና አዲስ መኪኖችን ቼክ እያረግን እንገኛለን :: አሁን ላይ ምን አልባት ካስተዋላችሁ እንደድሮ ቪዲዮ አንለቅም :: ይህም የሆነው አንድ ለየት ያለ የመኪና ዌብሳይት ከሚሰራ ካምፓኒ ጋር አብረን እየሰራን ስለሆነ ነው :: በተደጋጋሚ ስልክ ስትደውሉ ለነበራችሁ ይቅርታ ያልመለስንላችሁ ምክንያቱ እሱ ነው :: ለእያንዳንዳችሁ ከምንመልስበት ለሁላችሁም በቀላሉ የምንመልስበት ፕላትፎርም እየሰራን ነው :: የሚቀጥለው አመት ይጀምራል ብለን እናስባለን :: አብረናቸው ስለምንሰራ እንዲካተት የምትፈልጉትን ነገር ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን ::

ምችት ያለ ምሽት ይሁንላችሁ
#CarWebsite
@OnlyAboutCarsEthiopia
የBugatti "La Voiture Noire" 5 እውነታዎች።

1. "La Voiture Noire" የሚለው ቃል የፈረንሳይኛ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ጥቁሩ መኪና" ማለት ነው።

2. አለም ላይ አንድ "La Voiture Noire" ብቻ ነው ያለው ። ለዚህ ነው
ብቸኛነት Bugatti የምርት ስሙን ከሚጠብቅባቸው መንገዶች አንዱ የሆነው።

3. ዲዛይኑ ከ Bugatti Type 57SC Atlantic የተወሰደ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ሀሳቡን ለእይታ የቀረበው በ2019 Geneva motor show ላይ ነው።

4. ሙሉ አካሉ ከጥቁር carbon fiber ተሰራ ሲሆን 1500HP ያለው 8.0L quad-turbocharged W16 ሞተር አለው።

5. 19.8 ሚሊየን dollar ዋጋ ሲኖረው በጊዜው የአለማችን ውዱ መኪና ነበር። ( ገዢውም ማን እንደሆነ አይታወቅም)

ምርጥ ምሽት ተመኘን
#Carfacts
@OnlyAboutCarsEthiopia
ቶዮታ ለቻይና ገበያ የመጀመሪያውን ኤሌክትሪክ ሴዳን መኪና አውጥቷል ::

Toyota BZ3 የቶዮታ የመጀመሪያው ኤሌክትሪክ ሴዳን መኪና ነው :: FAW ከቶዮታ ጋር በጆይንት ቬንቸር የሚሰሩት መኪና ነው :: የሚጠቀሙት የ BYD Blade LFP ባትሪ ሲሆን በሁለት የሞተር አማራጮች ይመጣል :: 183 የፈረስ ጉልበት እና 244 የፈረስ ጉልበት ያላቸው ናቸው :: ከፊት ለፊት ገፅታው Toyota 86 የሚመስል ነገር አለው :: ከህዳር በሗላ ለሽያጭ እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል ::

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#Electric #Toyota
@OnlyAboutCarsEthiopia
2021 FORD BRONCO Review

ፎርድ ብሮንኮ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1965 የ 1966 ሞዴል አስተዋወቀ። የመጀመሪያው ብሮንኮ ከመንገድ ውጭ ችሎታው የላቀ ነበር። የመጀመሪያው ብሮንኮ በ10-አመታቱ ወቅት የተለያዩ አማራጮችን ይዞ ቀርቦ ነበር። በ 2021 ያወጡት BRONCO 6ኛው ጀነሬሽን ሲሆን በመኪናውም ላይ ብዙ ቴክ ፊቸሮችን ጨምረውበታል :: ከ Jeep-Wrangler ጋርም በጣም ይፎካከራል ። ብሮንኮን ልዩ ከሚያደርጉት ነገሮቶችም መኃል አመቺ ባልሆኑ መንገዶች ላይ እንደ ጭቃማ፣ ድንጋያማ ወይም ኮሮኮንች ፣ አሸዋማ እና ወዘት ባሉ ቦታዎች ላይ ያለችግር መሄዱ እና Off-road ይዘውት ሲወጡ የመኪናውን በሮች እና ጣራውን ከፈሉ ስለሚነቃቀሉም ነው።

በቀጣይ ክፍል ስለ ሞተር አማራጮቹ፣ ስለውስጣዊና ስለውጫዊዉ ገፅታዎቹ እንቃኛለን።

ልዩ ምሽት ተመኘን
#FordBronco
@OnlyAboutCarsEthiopia
ቶዮታ ከ 300 ቢሊየን ብር በላይ ለኤሌክትሪክ ባትሪ ኢንቨስት እንዳደረጉ ተናገሩ ::

ቶዮታ ምንም እንኳን ወደ ኤሌክትሪክ ገበያው አርፍዶ ቢገባም ያጣውን ነገር ለመመለስ በደንብ እየሰራ ይገኛል :: ቶዮታ አሜሪካ ውስጥ ላይ ብቻ ከ 130 ቢሊየን ብር በላይ ለኤሌክትሪክ ባትሪ ኢንቨስት ሲያደርጉ በአጠቃላይ ግን ከ 300 ቢሊየን ብር በላይ ለኤሌክትሪክ ባትሪ ኢንቨስት አድርገዋል :: ለውጡን የምናየው ይሆናል ::

ውብ ቀን ተመኘን
#CarNews
@OnlyAboutCarsEthiopia
FORD BRONCO Review Part 2

በ2021 BRONCO ለገዢዎች ከስድስት የተለያዩ የትሪም ደረጃዎች እንዲሁም ከባለ ሁለት እና ባለ አራት በር ስሪቶች መምረጥ እንዲችሉ አድርገዋል ። የትሪም ደረጃዎቹም Bronco Base, Big Bend, Black Diamond, Outer Banks, Badlands, እና Wildtrak ሲሆኑ በ2022 ደግሞ RAPTOR ብለው ጨምረዋል እሱን በሰፊው በቀጣይ የምናየው ይሆናል። የ2021 የብሮንኮ ቤዝ ሞተር በ2.3ሊትር ቱርቦ 275 የፈረስ ጉልበት አሊያም 300 የፈረስ ጉልበት ያቀረቡ ሲሆን ከፍ ላሉት ትሪም ደረጃዎች ደግሞ 2.7-ሊትር twin-turbo V6 315 የፈረስ ጉልበት ወይም 330 የፈረስ ጉልበት የሚያመነጩ ሞተሮች እንደ አማራጭ አቅርበዋል። ውስጣዊ ገፅታው እጅግ ማራኪ ሲሆን በ8.0inch ተችስክሪኑ ታጅቦ infotainment system፣ Apple CarPlay እና Android Auto ያካተተ ሲሆን ተነቃይ ጣራዎቹም እና በሮቹ እንደ እሪፍ ፊውቸር ይቆጠራሉ።

ልዩ ምሽት ተመኘን
#Ford
@OnlyAboutCarsEthiopia
የ2022 FORD BRONCO RAPTOR

በ2022 FORD BRONCO አዲሱ የትሪም ሌቭላቸውን ማለትም ራፕተርን ለገበያው እነሆ ብለዋል። ይህም ለየት የሚያደርገው ከቀደምቶቹ ይልቅ ስፖርታዊ ገፅታን ይበልጥ በመኪናው ማላበሳቸው ነው። በ2.7L እና 3.0L V6 EcoBoost Engine ከ10-Speed Automatic Transmission ጋር 315 የፈረስ ጉልበት የሚያመነጭ ሲሆን እጅግ ዘመናዊ የሚባልም FOX Suspension system ተገጥሞለታል :: ይህም አመቺ ባልሆነ ቦታ እንዲሄድ ያስችለዋል። በተጨማሪም በ16 ኢንች ወይም በ 17 ኢንች አልሙኒየም ቸርኬ የሚገኝ ሲሆን ከመሬት ያለውም ከፍታ ረዘም እንዲል አስችሎታል። በምቹ ሌዘር ወንበሮቹ ደምቆ በተጨማሪም Adaptive Cruise Control, Wireless Charging Pad, Remote Start System, Dual-Zone Automatic Climate Control እና አንዳንድ ተጨማሪ ነገሮችን አካቶ ይመጣል ። እዚህ ላይ ያልጠቀስናቸውን ነገሮች በ 2 ቲክቶክ ቪድዮዎች ላይ ታገኛላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMNT2q7Re/

https://vm.tiktok.com/ZMNT2D1bs/

ውብ ምሽት ተመኘን
#Ford
@OnlyAboutCarsEthiopia
Hilton Hotel has become the first hotel in Addis Ababa to install an electric car charging station.

ሒልተን ሆቴል የኤሌክትሪክ መኪና (EV) ቻርጅ መሙያ ጣቢያ በማስገጠም አዲስ አበባ ካሉ ሆቴሎች ቀዳሚ ሆኗል።

ሒልተን ሆቴል አዲስ አበባ ከግሪን ቴክ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የኢቪ ቻርጅ መሙያ ጣቢያ ባሳለፍነው ቅዳሜ አስመርቋል።

ግሩም ቀን ተመኘን
#Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
Rivian R1T Truck

Rivian የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ብቻ የሚያመርት የአሜሪካን ኩባንያ ሲሆን በፈረንጆንቹ 2021 R1T የተሰኘውን ኤልክትሪክ Pickup ሞዴላቸውን እነሆ ብለዋል። ይህ መኪና ከሞላ-ጎደል እጅግ ፊውቸርስቲክ ሲሆን፤ በ3 Trim ደረጃዎችም ይገኛል፤ እነሱም Explore, Adventure እና Launch Edition ሲሆኑ በሶስቱም ደረጃዎች ተመሳሳይ Single Speed Automatic Transmission እና All Wheel Drive (AWD) አማራጭ ይገኛሉ። የፈረስ ጉልበት(Horse Power)፣ የአልሙኒየም ቸርኬአቸው እና ውስጣዊ ገፅታቸው ግን ያለያያቸዋል። መኪናው ከሌሎች መኪናዎች ለየት የሚያደርገው መኪናውን ለመክፈት በአራት የተለያዩ አማራጫች ማለትም ስልክ፣ የእጅ አምባር፣ ካርድ እና በመደበኛ ቁልፍ መጠቀምን ማስቻሉ እና Gear tunnel ወይም ከጀርባው ክፍት ቦታ ባለፈ በመኪናው መሃል ለመሃል የሚያልፍ ሌላ እቃ ማስቀመጫ ኪስ መኖሩ ልዩ ያደርገዋል። አጠር ያለ ቪድዮ ቲክቶክ ላይ ከዚህ በፊት ለቀን ነበር ያላያችሁ ካላችሁ እንድታዩት ጋበዝናችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMNwhYnbh/

አስገራሚ ምሽት ተመኘን
#Electric #Rivian
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/24 22:32:18
Back to Top
HTML Embed Code: