Telegram Web Link
መኪኖቻችሁን በደስታ ሰታችሁን ሪቪው እንድንሰራ ፈቃደኛ ስለሆናችሁ በጣም እናመሰግናለን :: በዚህ ሳምንት በህመም ምክንያት ሪቪው መስራት ስላልቻልኩ እና ቀጠሮ ስለሰረዝኩኝ ይቅርታ እየጠየኩ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የምንጀምር ስለሆነ ከላይ የምትመለከቷቸውን መኪኖች ያላችሁ እና አስመጪ ያልሆናችሁ ሰዎች ለሪቪው ስለምንፈልጋቸው እንድትተባበሩን እንጠይቃለን :: በብዙዎቻችሁ ጥያቄ መሰረት ያገለገሉ መኪኖች ላይ ሪቪው በቅርቡ የምጀምር ይሆናል :: ዩትዩብ ከቀናት በሗላ ቁጥሩ የሚበራ ይሆናል :: ስለዚህ 40 ሺህ ልንሞላ ስለሆነ ሰብስክራይብ ያላደረጋችሁ ማድረግ እንዳትረሱ ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtube.com/c/yonathandesta?sub_confirmation=1

የተለየ ከሰአት ተመኘን
#CarReview #Youtube
@OnlyAboutCarsEthiopia
ምን ልዩነት አለው ከድሮ ሞዴል ጋር?
2023 Honda Civic Type R

ከውጪ ገፅታው ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ነው ሪዲዛይን ያደረጉት :: የሚሰሩ ቬንት ያ ማለት የምትመለከቱት በሙሉ Functional ናቸው :: ውስጡ ከፊት ያሉት ወንበሮች ቀይ ናቸው :: እና ደግሞ እዚህ ሞዴል ላይ በማንዋል ብቻ ነው የሚገኘው :: ቢሆንም ሞተራቸው ተመሳሳይ ነው :: ውስጡ ላይ የተለዩትን እንዲሁም የጨመሯቸውን ነገሮች አንድ ላይ ዩትዩብ ቪድዮ ለቀናል ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/UjjjugkAEjU

በጣም እናመሰግናለን VPN አብርታችሁ እያያችሁ ስላላችሁ :: ቪድዮዎቹን በVPN እንድታዩ ያልነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያላችሁትን ተከታታዮቻችንን ብቻ ነው ::

አርብ ነው እያያችሁ ፈታ በሉ
#Honda #HondaCivic
@OnlyAboutCarsEthiopia
መኪና ለመግዛት ስትሉ የመኪና መሸጫ ዌብሳይት ላይ እንዲካተቱ የምትፈልጓቸው ነገሮች ምንድናቸው? እስኪ ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን :: እኛ ሀገር ላይ ብዙውን ጊዜ ስለመኪናችን ዝርዝር ነገር ስለማናውቅ ስንሸጥም ዘርዘር ያለ ነገር አናስቀምጥም :: ይህንን የሚፈታው ምንድነው ብላችሁ ታስባላችሁ? አመሻሹ ላይ በአዲስ የመኪና ሪቪው እንገናኛለን

ውብ ቀን ተመኘን
#CarWebsite
@OnlyAboutCarsEthiopia
ምኑ ነው ከ Hyundai Creta የሚሻለው?
2022 Kia Seltos Review

ከ Hyundai Creta በሳይዝ በዲዛይን እና በግራውንድ ክሊራንስ ወይም ከመሬት ባለው ከፍታ የተሻለ ነው :: 1.6 ሊትር 4 ሲሊንደር ሲኖረው Dual Clutch Transmission ነው የሚጠቀመው :: ግን ለምንድነው Dual Clutch Transmission (DCT) የሚጠቀመው? ለምንድነው DCT በጣም እየበዛ የመጣው? እነዚህንን እና አንዳንድ ተጨማሪ ነገሮችን በዛሬው ቪድዮ የምናይ ይሆናል :: ቪድዮውን ከስር ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/AevxUrB3FOc

በጣም እናመሰግናለን VPN አብርታችሁ እያያችሁ ስላላችሁ :: ቪድዮዎቹን በVPN እንድታዩ ያልነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያላችሁትን ተከታታዮቻችንን ብቻ ነው ::

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#KiaSeltos #DCT
@OnlyAboutCarsEthiopia
መኪና መግዛት ፈልጋችሁ ግን ምን መኪና መግዛት እንዳለባችሁ ግራ ከገባችሁ ይህ መረጃ ለእናንተ ነው

እኛ መኪና አፈላልገን አናሻሽጥም ወይም ከአስመጪዎችም ጋር አንሰራም :: የምንሰጠው አገልግሎት መኪና መግዛት ለምታስቡ የትኛው መኪና ባላችሁ ዋጋ ማግኘት እንደምትችሉ እናማክራለን እንዲሁም አዲስ መኪናውን ከመግዛታችሁ በፊት መኪናውን ሙሉ ቼክ እናደርጋለን :: ከውጪ መኪናም ማስመጣጥ የምትፈልጉ የትኛው ለእናንተ የተሻለ እንደሆነ እናማክራለን :: እኛን ለማግኘት በ @YonathanDesta ወይም በ ኢሜል [email protected] ላይ መልእክት በመላክ ቢሮአችን ድረስ በመምጣት ለመነጋገር ቀጠሮ ማስያዝ ትችላላችሁ :: ስልክ ደውላችሁ ላላነሳንላችሁ ይቅርታ እየጠየቅን ከዚህ በሗላ በመልእክት ብቻ የምንመልስ ይሆናል ::

መልካም ሰኞ ተመኘን
#Consultant #YonathanDesta
@OnlyAboutCarsEthiopia
በከተማችን አዲስ አበባ ብቻ በአማካይ ምን ያህል መኪና የሚሸጥ ይመስላችሗል?
Anonymous Quiz
31%
እስከ 100 መኪኖች
18%
ከ 100 እስከ 150 መኪኖች
13%
ከ 151 እስከ 200 መኪኖች
14%
ከ 200 እስከ 300 መኪኖች
24%
ከ 300 በላይ መኪኖች
የመኪና ሽያጭ በከተማችን ውስጥ ትልቁ ገበያ ነው

ይህንን ስንል በመረጃ ነው :: ኢትዮጵያ በብዛት ከሚገቡት እቃዎች ዋነኛው መኪና ነው :: ኢትዮጵያ ውስጥ ከፈለጋችሁት የአለማችን ክፍል መኪና ማስገባት ትችላላችሁ :: እሱ ብቻ ሳይሆን እንደሌሎች ሀገሮች በአየር ብክለት ምክንያት ተብለው የሚከለከሉ መኪኖች የሉም :: ቀረጣቸው እየጨመረ ይመጣል የሞተራቸው መጠን ሲጨምር :: ለዛም በጣም ብዙ መኪኖች በየቀኑ የሚገቡት :: የሱን መረጃ ማግኘት ትንሽ ከባድ ስለሆነ ያለን አማራጭ የነበረው በሚወጡት አዲስ ታርጋ ነበር :: ለሪሰርች ለመጠቀም በወሰድነው መረጃ ባለፉት 6 ወራት ከ 30,000 በላይ ታርጋዎች ተሰተዋል :: እንዲሁም የታርጋ ችግር እንዳለም አስተውለናል :: እንደዛም ሆኖ በቀን ከ 165 በላይ መኪኖች ይሸጣሉ በአማካይ :: ያገለገሉ መኪኖች ሲጨመሩ ወደ 200 ይጠጋሉ ብለን ገምተናል :: ይህንን ቁጥር አልጠበቅንም ነበር በጣም ገርሞናል :: እናንተስ ምን ታስባላችሁ?

ግሩም ምሽት ተመኘን
#NewCars #AddisAbaba
@OnlyAboutCarsEthiopia
ማራቶን ሞተርስ ቅርብ ጊዜ መገጣጠም የጀመረው ኤሌክትሪክ መኪና መንገዶች ላይ መታየት ጀምሯል ::
Hyundai Kona Electric

ስለዚህ የማውቃቸው አንዳንድ ነገሮች ልንገራችሁ :: Electric ያልሆነውን ኮና በአካል ሄጄ አንዳንድ ነገር አሳይቻችሁ ነበር :: ይሄ የሚለየው ግን ሙሉ በሙሉ Electric ነው ::
በሁለት Electric battery pack አማራጮች የሚገኝ ሲሆን በ 39 እና በ 64 kWh ሬንጃቸውም ይለያያል :: ከ 303 km እስከ 484 km በአንድ ቻርጅ መጏዝ ይችላሉ :: ካሳያሗችሁ ኮና ከ 0-100 km በሰአት በ 2.2 ሰከንድ ይፈጥናል :: ተጨማሪ ነገሮችን ነገ በቲክቶክ ቪድዮ የምለቅ ይሆናል ::

ልዩ ምሽት ተመኘን
#Electric #HyundaiKona
@OnlyAboutCarsEthiopia
Job Title: Short Script writer / Content Creator for tiktok and telegram

Company: OnlyAboutCarsEthiopia

Job Type: Freelance

Description: we need young content creator who can write about new car stuff and can make short amharic scripts on daily basis. The intern will mostly work from home and will work daily during the internship. No payment on the internship period. At the end of the internship, 1-2 interns will be selected for continuing work.

Internship Qualifications:
-knowledge about cars
-know how to write amharic script
-Strong Amharic proficiency


Internship Application Requirements:
-Submit your personal information @yonathandesta
-Age 17-25
-Sample to your previous work if you have one

#ContentCreator

From: @OnlyAboutCarsEthiopia
Hyundai Kona Electric

ምንም እንኳን አጠቃላይ ቅርፁ የነዳጁን ቢመስልም ከፊት ያለው ገፅታ ትንሽ ለየት ይላል :: ይህም የሆነው የነዳጅ ሞተው ስለማይጠቀም ነው :: ግን ይህ ብቻ አይደለም የሚለያቸው ሌላ ልዩነትም አላቸው :: እነሱን ለመመልከት ቲክቶክ ላይ ቪድዮ ለቀናል
👇🏽👇🏽👇🏽

https://vm.tiktok.com/ZMN4Gnsmb/?k=1

ረጋ ያለ ምሽት ተመኘን
#Electric #HyundaiKona
@OnlyAboutCarsEthiopia
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሱፐርቻርጀሮች 2019 Dodge Challenger, 2016 Jaguar F-Type, 2016 Chevy Corvette, Range Rover Sport እና Velar በጥቂቱ እነዚህ ናቸው :: የውድድር መኪኖች እንዲሁም እኛ ያልጠቀስናቸው ይኖራሉ :: ግን ሱፐርቻርጀር ምንድነው? እንዴት ነው የሚሰራው? ስንት አይነት ሱፐርቻርጀሮች አሉ የሚለውን በዛሬው ዩትዩብ ቪድዮ ላይ ታገኛላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/mos53LXIgZ8

40,000 ሰብስክራይበርስ ልንሞላ በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች ስለቀሩን ሰብስክራይብ ማድረግ እንዳትረሱ ::

Photo Credit- Exotic Ethiopian Cars

ግሩም ምሽት ተመኘን
#SuperCharger
@OnlyAboutCarsEthiopia
የመኪና አደጋ በየጊዜው እየጨመረ ያለ ትልቅ ችግር ነው :: ምንም እንኳን አዳዲስ መኪኖች ላይ ያሉት ቴክኖዎሎጂዎች አደጋን ለመቀነስ ቢሰሩም እኛ ሀገር በብዛት የሚነዱት መኪኖች 10 አመት እና ከዛ በላይ የሆናቸው መኪኖች ናቸው :: ግን አደጋ በሚደርስበት ሰአት መኪኖቻችንን ወደነበረበት ለመመለስ ምን ምን ነገሮች ናቸው የሚሰሩት? ምን ምን ማሽኖችን ይጠቀማሉ? ሌሎችም እናንተም መጠየቅ የምትፈልጉትን ጥያቄ አንድ ላይ ባለሙያ የሆነ ሰው ስለምንጠይቅ ማወቅ የምትፈልጉትን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን

ነገ የ 40ሺ ሰብስክራይበርስ ቪድዮ ይለቀቃል በዩትዩብ ይጠብቁን
ሰብስክራይብ ማድረጉን አትርሱ

https://youtube.com/c/yonathandesta?sub_confirmation=1

ርሃ የሆነ ቀን ተመኘን
#CarAccident #CarRepair
@OnlyAboutCarsEthiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Dodge ቀጣዩን ጀነሬሽን Charger እና Challenger ኤሌክትሪክ እንደሚያደርግ አረጋገጠ❗️

Dodge በመስል መኪኖቹ Charger እና Challenger በአለም ዙርያ የሚታወቅ ሲሆን በጣም ትልልቅ horsepower (የፈረስ ጉልበት) ያላቸው መኪኖችም ናቸው :: አሁን ግን ወደ ኤሌክትሪክ ሊቀይሯቸው እንደሆነ አረጋግጠዋል :: እነዚህ በ Supercharger ሞተራቸው በድምፃቸው የሚለዩ መኪኖች ኤሌክትሪክ ሲሆኑ ምን እንደሚመስሉ እኔንጃ :: እስኪ ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን

የምታርፉበት እሁድ ተመኘን
#Dodge #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
ሰላም ዛሬ ልንለቅ የነበረውን የ 40 ሺህ ሰብስክራይብ ስላልሞላልን ሲሞላ የምንለቅ ይሆናል :: ስለዚህ እስከዛው ግን የተለያዩ የመኪና ቪድዮዎችን በቲክቶክ እንዲሁም በኢንስታግራም የምንለቅ ይሆናል :: ፎሎ ማድረጉን እንዳትረሱ ::
Tiktok:
https://vm.tiktok.com/ZMNV3Gw39/
Instagram:
https://Instagram.com/yonathan_desta

ውብ ምሽት ተመኘን
#Tiktok #Instagram
@OnlyAboutCarsEthiopia
Timing Belt መቼ ነው መቀየር ያለበት?

Timing Belt የመኪናችሁን ክራንክ ሻፍት እና ካም ሻፍት ዙራቸውን ተመሳሳይ ማድረግ ነው :: ይህ ማመሳሰል ከፒስተኖች አቀማመጥ አንጻር የሞተሩ ቫልቮች በትክክለኛው ጊዜ እንዲከፈቱ እና እንዲዘጉ ያደርጋል። መቼ መቀየር አለበት ብለን ስንመለከት ከ 60,000 ኪሎሜትር አንዳንዶቹ ላይ እስከ 170,000 ኪሎሜትር ይደርሳል :: ስለዚህ የመኪናችሁ ማንዋል ላይ እያያችሁ ብትቀይሩት የተሻለ ነው ::

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#TimingBelt
@OnlyAboutCarsEthiopia
መኪናችሁ ውሀ ውስጥ ቢገባ ምን ማድረግ አለባችሁ?

1. መኪናችሁ ውስጥ ውሀ እየገባ እንደሆነ ካወቃችሁ የመኪናችሁን ሞተር ማጥፋት አለባችሁ ::
2. መኪናችሁን እየገፋችሁ ወይም በ መኪና ማንሻ ከዛ ቦታ ማንቀሳቀስ ይኖርባችሗል ::
3. ውሀ ሞተር ውስጥ አለመግባቱን ማረጋገጥ አለባችሁ ::
ግን ቢገባስ እንዴት አድርገን ነው ማውጣት የምንችለው የሚለውን ዩትዩብ ላይ ቪድዮ ለቀናል ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/j-jYeaTzPJg

ድምቅ ያለ ምሽት ተመኘን
#FloodedCars
@OnlyAboutCarsEthiopia
እስከ 2017 ድረስ ያለው Nissan Qashqai ለምንድነው ዋጋው ከሌሎች መኪኖች የሚቀንሰው?

ይህንን ጥያቄ ኢንስታግራም ላይ ተጠይቄ ስለነበር ነው:: Nissan Qashqai አንድ ዋና ችግር ስላለበት ነው :: እሱም የ CVT ትራንስሚሽኑ ወይም (Continuous Variable Transmission) ችግር ስላለበት ነው :: ለዛ ነው ዋጋው የቀነሰው :: በብዛት የገባው እሱ መኪና ስለሆነ ነው እንጂ አብዛኛው ከ 2008-2017 ድረስ ያመረቷቸው የኒሳን ሞዴሎች ልክ እንደ Juke, Versa, Sentra, Altima, Maxima, Xtrail እና Murano ይሄ ችግር አለባቸው :: ታድያ መፍትሄው 2 ነገር ነው ይሄን መኪና የገዛችሁ ካላችሁ :: በየ 40,000 ኪሎሜትር የትራንስሚሽኑን ዘይት መቀየር እና የነዳጅ ፔዳሉን ሙሉ በሙሉ አለመርገጥ መኪናው ያለምንም ችግር ለረዥም ጊዜ እንዲቆይ ያደርገዋል :: በየሳምንቱ ኢንስታግራም ላይ ጥያቄዎቻችሁን ፈታ ባለ መልኩ እየሳቅን እየተጫወትን ስለምንመልስ ፎሎ ማድረጉን እንዳትረሱ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://Instagram.com/yonathan_desta

ግሩም ቀን ተመኘን
#NissanQashqai #Nissan
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/24 22:26:34
Back to Top
HTML Embed Code: