Telegram Web Link
#ዜና

የቶዮታው Daihatsu ብራንድ ትኩረቱን ትናንሽ የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ አርጎዋል።


በToyota ስር የሚተዳደረው Daihatsu ከደህንነት ጋር ተያይዞ በገባበት ቅሌት የኩባንያውን ገጽታ ካበላሸ በኋላ ቶዮታ የዚህን ንዑስ ካምፓኒን መዋቅር በአዲስ መልክ እያደራጀ ነው።

ቶዮታ Daihatsu የአንዳንድ ለአለም አቀፍ ገበያ የሚውሉ የኮምፓክት መኪኖች የማምረቱን ስራውን ለቶዮታ እንደሚያስረክብ አስታውቋል።

የDaihatsu  አስተዳደርም በተለያዩ የልማት ቡድኖች መካከል ያለውን ግንኙነት እና ትብብር ለማሻሻል ሲል በአዲስ መልክ ተዋቅሯል። እናም ሰራተኞች ካምፓኒ ውስጥ ችግሮችን ካዩ እንዲናገሩ ይበረታታሉ።

ቶዮታም የDaihatsu ትኩረት ከንግድ ተሽከርካሪዎች ጀምሮ እስከ አነስተኛ ዋጋ እስካላቸው Mini የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ማምረት እንዲለውጥ እያደረገው ነው።

ቶዮታ በጃፓን የminicar ገበያ ላይ ከተቀናቃኞቹ Nissan እና Honda ኋላ እየቀረ ስላለ ይህንን ማድረጉ በሀገሪቱ ውስጥ በጣም ተፈላጊ ያደርገዋል።

#Toyota #Daihatsu
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የHyundai ግሩፕ በህንድ ሃገር ላይ የባትሪ ውል ተፈራረመ።


Hyundai እና Kia ህንድ ውስጥ ባትሪ ለማምረት ተፈራረሙ። ካምፓኒዎቹ Exide Energy ከተባለ የህንድ ሃገር በቀል ካምፓኒ ጋር lithium iron phosphate ወይም LFP ተብለው የሚጠሩትን የባትሪ አይነቶችን ለማምረት ተስማሙ። ባትሪዎቻችሁም እዛ የህንድ ገበያ ላይ የሚውሉ የHyundai እና የKia መኪኖች ላይ የሚገጠሙ ይሆናል።

ወደ ምርት መች እንደሚገቡ ወይም ምን ያህል መዋለ ንዋይ ፈሰስ እንደሚያደርጉ የተናገሩ ባይሆንም የህንድ የኤሌክትሪክ መኪና ገበያ በጣም ተስፋ ሰጪ የሆነ እና እነሱ በሃገሪቷ የኤሌክትሪክ መኪና ገበያ ላይ እራሳቸውን ግንባር ቀደም ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

#Hyundai #Kia #LFP
@OnlyAboutCarsEthiopia
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም በፍቅር በጤና አደረሳችሁ አደረሰን
ኢድ ሙባረክ!

መልካም በዓል ተመኘን 🙏
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BYD በአንድ መኪና ከ Ford በላይ እያገኘ ነው


የቻይና የመኪና አምራች ካምፓኒ የሆነው BYD ባለፈው አመት በአንድ መኪና ከ Ford በላይ ማግኘቱ ተገለፀ :: BYD የተጣራ ትርፉ 4.1 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ይህንንም ትርፍ ያገኘው በሸጣቸው 3 ሚሊየን መኪኖች ነው :: ስለዚህ በእያንዳንዱ መኪና 1,350 ዶላር ትርፍ አካባቢ ይሆናል ::

ነገር ግን BYD ከመኪኖችም ውጪ የተለያዩ እቃዎችን ስለሚያመርቱ ባወጡት መረጃ መሰረት በመኪና ወደ 1,250 ዶላር የሚጠጋ ትርፍ ማግኘታቸውን ነው የገለፁት :: ከ Ford ጋር ሲወዳደር 4.3 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ትርፍ ያገኙ ሲሆን የሸጡት መኪኖች ብዛት ግን 4.4 ሚሊየን መኪኖችን ነው :: ይህም በአንድ መኪና ያገኙት ትርፍ ከ 1,000 ዶላር ያነሰ ነው ::

BYD ከትልልቆቹ ማለትም ከ Volkswagen እና GM ብዙም አልራቀም :: ሁለቱም ድርጅቶች በአንድ መኪና ያገኙት ትርፍ ወደ 1,600 ዶላር የሚጠጋ ነው :: ሁሉም ግን ከ Tesla በጣም ይርቃሉ :: Tesla በአንድ መኪና 8,200 ዶላር ትርፍ ያገኛል :: ከላይ የተዘረዘሩት የመኪና አምራች ካምፓኒዎች የሚሸጧቸው መኪኖች ዋጋቸው አነስ ስለሚል ነው ::

ለምሳሌ BYD Seagull መኪናን ብናይ አሁን ቻይና ላይ ከ 10,000 ዶላር በታች እየተሸጠ ይገኛል :: ለዛም ነው BYD YangWang በሚል ስያሜ በዋጋ ከፍ ያሉ ሞዴሎችን ብዙ ትርፍ ለማግኘት እየሰራ ያለው ::

#BYD #Ford #Tesla #GM #VW
@OnlyAboutCarsEthiopia
Only About Cars Ethiopia
#ዜና BYD በአንድ መኪና ከ Ford በላይ እያገኘ ነው የቻይና የመኪና አምራች ካምፓኒ የሆነው BYD ባለፈው አመት በአንድ መኪና ከ Ford በላይ ማግኘቱ ተገለፀ :: BYD የተጣራ ትርፉ 4.1 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ይህንንም ትርፍ ያገኘው በሸጣቸው 3 ሚሊየን መኪኖች ነው :: ስለዚህ በእያንዳንዱ መኪና 1,350 ዶላር ትርፍ አካባቢ ይሆናል :: ነገር ግን BYD ከመኪኖችም ውጪ የተለያዩ…
#ዜና

BYD አዲስ የ Blade ባትሪ ላይ እየሰራ ይገኛል


BYD ከመኪኖች ትርፍም በተጨማሪ አዲስ በሚሰራቸው በዋጋ ቀነስ ያሉ የባትሪ ቴክኖዎሎጂዎች ትርፉን ለመጨመር እያሰበ ነው :: ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የካምፓኒው ሊቀመንበር እንዳሉት በስብሰባ ላይ ሁለተኛውን የብሌድ ባትሪ ጀነሬሽን ላይ እየሰሩ መሆኑን ተናግሯል ::

እንዳሉት ከሆነ አነስ ያለ, ክብደቱም ቀለል ያለ እና ሀይልም ቆጣቢ ሲሆን ግን ደግሞ ካሉት ባትሪ ጋር ተመሳሳይ የኪሎሜትር ሬንጅ እንደሚኖረው ገልጸዋል ::

በቁጥር ደግሞ አሁን ያለው ብሌድ ባትሪ 150 Wh/kg ሲሆን ቀጥዩ ጀነሬሽን ላይ ደግሞ 190 Wh/kg ነው :: ይህም በጣም (energy dense) የሆነ LFP (Lithium iron phosphate) ባትሪ ያደርገዋል ::

#BYD #Battery
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቻይና ስራ የፈቱ የመኪና ማምረቻዎችን እየዘጋች ነው


ከዚህ በፊት አቅርበንላቹ እንደነበረው ዜና ቻይና በጣም ብዙ መኪኖች ሚያመርቱ በጣም ብዙ የመኪና አምራች ካምፓኒዎች አሏት። ይሄም በሃገሪቷ ያለው የኤሌክትሪክ መኪና ገበያ ላይ የዋጋ ጦርነት እንዲፈጠር እና ብዙ ብዙ መኪኖች ኤክስፖርት እንዲሆኑ ምክንያት ሆኖዋል። ይሄም ጉዳይ አውሮፓዊያኑን እና የአሜሪካ ባለስልጣናትን ሀሳብ እንዲገባቸው አድርጎዋል። ነገር China Association of Automobile Manufacturers ለዚ ጉዳይ እልባት እያበጀሁ ነው ብሎዋል።

ያለፈው አመት የቻይና የመኪና አምራቾች ካላቸው የማምረት አቅም 70%ቱን ብቻ ነው እየተጠቀሙ ያሉት። እናም አሁን ላይ ስራ ፈተው የቆሙ ማምረቻዎች እየተዘጉ ነው።

በተጨማሪ የቻይና ባለስጣናት ለአዲን የኤሌክትሪክ መኪኖች ማምረቻ ካምፓኒ ፍቃድ ከመስጠታችን በፊት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እና ቅድመ ሁኔዎችን እንከተላለን ብለዋል።

ነገር ግን የሃገሪቷ የክልል መንግስታት ካምፓኒዎቹ የሚፈጥሩት የስራ እድል ላይ ጥገኞች ናቸው። ይሄም ለጉዳዩ እልባት የመስጠት ሂደቱን አዳጋች ያደርገዋል።

#china #EV_Market
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ሪቪው

Toyota አዲሱን 4Runner አስተዋወቀ


አዲሱ Toyota 4Runner በ Toyota Global Truck Platform TNGA-F ሲጠቀም ይህም በአዲሱ LandCruiser, Tacoma, Tundra እና Sequoia መኪኖች ጋር ተመሳሳይ ነው :: ዲዛይኑ አሁን ላይ ካለው 4Runner ጋር በጣም ተቀራራቢ ሲሆን ነዳጅ ለመቆጠብ ሲሉ የበፊቱን 4 ሊትር V6 ሞተሩን በባለ 2.4 ሊትር 4 ሲሊንደር ያለው ሞተር ቀይረውታል ::

አዲሱ ላይ 278 የፈረስ ጉልበት ሲኖረው የሀይብሪድ አማራጭ የሚያቀርቡት ላይ እስከ 326 የፈረስ ጉልበት ይደርሳል :: እንደዚህ በመሆኑ ከ 2,700 ኪሎግራም በላይ መጎተት ይችላል :: አሁን ካለው 4Runner ከ 450 ኪሎግራም በላይ ይጎትታል :: አዲስ Trailhunter ትሪም ጨምረዋል ::

ወደውስጥ ስንገባ አንዳንድ ሶፍት ማቴሪያል ያካተቱ ሲሆን አዲስ ተለቅ ያለ እስክሪን እና እቃ መያዣ አካተውበታል :: በቅርብ ወራት ውስጥ ወደ ሽያጭ እንደሚያቀርቡት ገልጸዋል ::

#Toyota #4Runner
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የፎርድ ሃች ባክ መኪና Focus አዲስ የፐርፎርማንስ ሞዴል ተሰራለት


Ford አውሮፓ ላይ Focus የተባለው የሃች ባክ ቦዲ ስታይል ያለው መኪናውን Focus ST (Sport Technologies) በሚል የሞዴል ስም በፐርፎርማንስ ቨርዥን አቅርቦታል።

Focus ST ማስተካከል የሚቻል የጥቅልል ሽቦ ሰስፔንሽን ሲስተም፣ ከፊት የ Brembo ፍሬኖች፣ ቀላል ክብደት ያለው ጎማ ያለው ሲሆን ትራንስሚሽኑ ማኑዋል ነው።
የተገጠመለት ባለ 2.3 ሊትር ቱርቦቻርጀር ያለው ሞተር ደግሞ 275 የፈረስ ጉልበትን ያመነጫል።

የእነዚህ ነገሮች ሁሉ ድምር የመኪናውን ፍጥነት በሰአት ከ 0 እስከ 100 ኪሎሜትር በሰአት በ 5.7 ሰክንድ ውስጥ እንዲገባ ያስችለዋል ። ውስጥ ላይም የስፖርት መኪናን ያማከለ መሻሻሎች ተደርገውበታል።

#Ford #FocusST
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Opel አና Vauxhall የድሮውን Frontera SUV ዳግም ነፍስ ሊዘሩበት ነው


ከ90ዎቹ ወጀመሪያ እስከ 2000 ወጀመሪያ ድረስ ለ10 አመታት ገበያው ላይ የነበረውን የVauxhall  SUV የሆነውን Frontera መኪና የጀርመኑ የመኪና አምራች Opel Vauxhall ጋር በጋራ በመሆን ዳግም  ሒወት ሊዘሩበት ነው።

ያኔ እንደ Isuzu Redeo እና Honda Passport ያሉ መኪኖች ይጠቀሙበት የነበረውን የIsuzu platform ይጠቀሙ የነበር ሲሆን የአሁነኞቹ ግን STAL-small ወይም STAL-medium platformን የሚጠቀሙ ይሆናል።

በመጀመሪያ ላይ ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ የሆነውን ቨርዥን ለገበያ የሚቀርብ ሲሆን ከተወሰኑ ጊዜያቶች ቡሃል ደግሞ በ48-ቮልት ሃይብሪድ አማራች ይኖረዋል።

ስለ መኪናው ዝርዝር መረጃ እስካሁን ይፋ አልሆነም።

#Opel #Vauxhall #Frontera
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Kia የመጀመሪያ ፒክ አፕ መኪናውን ለገበያ ሊያቀርብ ነው።


Kia የመጀመሪያው የሆነውን Tasman ብሎ የሰየመውን ፒክ አፕ መኪናውን በቀጣይ አመት ለገበያ ሊያቀርብ ነው።Kia እንዳለው C-segment ትራክ ሲሆን ሳይዙም ከHyundai Santa Cruz ጋር ተቀራራቢ ነው።

Tasman የሚለውን ስም ያወጡለት Tasmania ከተባለችው ደሴት በመነሳት ሲሆን ትርጉሙም "Evoke a spirit of adventure and exploration" ነው።

መኪናው እንደ ኮሪያ፣ አውስትራሊያ፣ አፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ ያሉ የፒክ አፕ መኪኖች የተለመዱባቸው ሐገራት ላይ ይሸጣሉ።

#Kia #Tasman
@OnlyAboutCarsEthipoia
#ዜና

Milano የመጀመሪያው የAlfa Romeo የኤሌክትሪክ መኪና።


የStellantis ግሩፕ አካል የሆነው Alfa Romeo አዲስ Milano የተሰኘ compact crossover መኪና ይዞ ቀረበ። መኪናው በሃይብሪድ እና በኤሌክትሪክ ሆኖ የቀረበ ሲሆን የካምፓኒው የመጀምሪያ የኤሌክትሪክ መኪናም ነው። የኤሌክትሪኩ Milano 54kwh ባትሪ ያለው ሲሆን በሁለት የጉልበት አማራጭ በ156 የፈረስ ጉልበት እና በ240 የፈረስ ጉልበት ሆኖ ነው የቀረበው። በአንድ ቻርጅም 410km ይጓዛል።

ሃይብሪዱ 1.2L ባለ 3 ሲሊንደር Engine ፣ 48 ቮልት Lithium-ion ባትሪ ፣21 kw ሞተር እና ባለ 6 የፍጥነት አማራች የሆነ Dual clutch ትራንስሚሺን አለው። ይሄ ሴት አፕም መኪናውን 136 የፈረስ ጉልበት እንዲያመነጭ ያስችለዋል።

Milano የ Alfa Romeo የመጀመሪያ የኤሌክትሪክ መኪናው ከመሆኑ ባሻገር ካምፓኒው በ1910 ከተመሰረተ ጀምሮ ከጣሊያን ሃገር ውጪ የሚመረተው የመጀመሪይው መኪና ነው። መኪናው Poland ላይ ከFiat 600 እና ከJeep Avenger ካሉ የStellantis ግሩፕ ስር ከሚመረት መኪኖች ጋር አብሮ ይመረታል።

Milanoን  Poland ውስት ለማምረት የተወሰነው ውሳኤ ጣሊያን ውስጥ ብዙ ተቀባይነት ያልገኘ ነገር ቢሆንም የStellantis Ceo የሆነው Carlos Tavares መኪናው ከፖላንድ ይልቅ በጣሊያን ውስጥ የሚመረት ከሆነ ተጨማሪ 10,000 ዩሮ ያሶጣል ሲል ሞግቶዋል።

#Alfa_Romeo #Milano #Stellantis
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

በአሜሪካ የናፍጣ መኪና ባለቤቶች ከሌላ አይነት የመኪና ባለቤቶች ይልቅ ብዙ ያሽከረክራሉ።


በአሜሪካ የሚገኙ የናፍጣ መኪና ባለቤቶች ከሌሎች የመኪና አይነት አሽከርካሪዎች ይበጥል ማሽከርከር ይወዳሉ ወይም የግድ ማሽከርከር ይጠበቅባቸዋል።

እንደ Energy.gov የ2022 National Household Travel Survey መረጃ መሰረት በአማካይ አንድ የናፍጣ የቤት ተሽከርካሪ 2022 ላይ 28,000 kmዎችን ተጉዞዋል። በሚገርም ሁኔታ ደግሞ ሁለተኛውን ደረጃ የፕለጊን ሃይብሪድ መኪና በአማካይ 26,000 kmዎችን በላይ በመጓዝ ይዘዋል።

ኖርማል ሃይብሪድ መኪናዎች ሳይቀር  ከቤንዚል መኪኖች የበለጠ ጉዞ ያረጉ ሲሆን በአማካይ አንድ የቤንዚል መኪና 22,500 kmዎችን ተጉዞዋል። የኤሌክትሪክ መኪኖች ደግሞ በአማካይ 20,000 kmዎቹን በመጓዝ የመጨረሻውን ደረጃ ይዘዋል።

#Diesel_car
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የጀርመን የመኪና አምራቾች ቻይና ላይ ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ እየተስተናገድን ነው አሉ።


እንደ በቻይና የሚገኘው  German Chamber of Commerce የዳሰሳ ጥናት መሰረት በቻይና የሚገኙ የጀርመን የመኪና  አምራቾች ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ እየተስተናገዱ እንዳሉ እየተሰማቸው ነው።

150 የመኪና ካምፓኒዎችን ከሚወክሉ መላሾች ምላሽ  ውስጥ 65%ቱ ፍትሃዊ ያልሆነ ፍክክር አንዳለ ተናግረዋል። የመንግስት ባለስልጣናትን ለማግኘት መቸገር፣ የግብር ማበረታቻ እና የገንዘብ ድጋፍ አለማግኘት የማሳሰሉ ችግሮች አሉባቸው።

የዳሰሳ ጥናቱ ላይ ያሉት በቀጥታ የጀርመን ካምፓኒዎች ብቻ ላይ ትኩረታቸውን ያረጉ ባይሆንም ጥናቱ ላይ ተካተዋል።

#German_Automakers #China
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Nio መኪኖቹ ላይ Generative AI ሲስተም እያካተተ ነው።


የቻይና የመኪና ሸማጮች ከሌላው አለም የመኪና ሸማቾች በተለየ ለአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ቅርብ የሆኑ እና በተቻለው ፍትነት መኪኖቻቸው ላይ ተካተው ሊያዩአቸው ይፈልጋሉ። አሁና ላይ በጣም ፍላጎት እያገኙ ካሉ የቴክኖሎጂ ግኝቶች መካከል አንዱ  አንደ ቻት ጂፒቲ(chatGpt) ያሉ Generative AI ናቸው።

በትኛውም ደረጃ ላዩ መኪኖች ላይ መካተት የሚችል ቴክኖሎጂ ሲሆን ከፍተኛ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት ደግሞ የኢንፎቴመንት ሲስተም ላይ ነው።

የቻይና የመኪና አምራቹ Nio ደግሞ የካቢን አሲስታንት የሆነችውን Nomi የተባለችው AI ሲስተሙ ላይ ማሻሻያ አረገ።
አሁን ላይ እደ የአየር ንብረት ሁኔታን እና የተለያዩ ቀልዶችን መናገር የምትችል ሲሆን አዲሷ Nomi GPT የተባለችው ቨርዥኗ ደግሞ መማር እና በጊዜ ሂደት የራሷን ማንነት መያዝ ትችላለች። Emotion እየኖራት እየመጣ ስለሆነ ከተጠቃሚዎች ጋር ሚኖራት ግኑኝነት ይበልጥ ተፈጥሮዋዊ እንዲመስል ሲረገው ከኢንተርኔት በይነ መረብ ጋር የተሳሰረች መሆኗ ደግሞ ስለየትኛውም ነገር እንድታውቅ ያስችላታል።

Nio ከNomi GPTን ማስጠቀም የሚችሉ መኪናዎች ላይ ማከትት ጀምሮዋል።

#Nio #NomiGPT
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የGAC Aion የቅንጡ ብራንዱ Hyper ላይ Solid State ባትሪዎችን ሊጠቀም ነው።


Solid State ባትሪዎች በባትሪው ቴክኖሎጂ ላይ  እንደ ቀጣዩ ትልቅ እርምጃ የሚታዩ ቢሆኑም እስካሁን ሙሉ በሙሉ Solid State ባትሪዎችን የተጠቀመ የመኪና አምራች የለም። የቻይናው የመኪና አምራች GAC Aionም ከጀማሪዎቹ አንዱ ሊሆን ይመስላል።

እንዳለው ከሆነ 2026 ላይ በቅንጡ የመኪና ብራንዱ Hayper ስር በሚመረቱ መኪኖች ላይ ሙሉ በሙሉ የSolid State ባትሪ የሚጠቀሙ መኪኖችን ለገበያ ያቀርባል።

Solid State : ባትሪዎች ውስጥ ያለውን የኤሌክትሮላይት አይነት የሚገልፅ ሲሆን በተለምዶ የlithium ion ባትሪዎች ላይ ከምንጠቀመው ፈሳሽ ኤሌክትሮላይት ይልቅ ጠጣር ፖሊመሮችን ይጠቀማል።

አድቫንቴጁ ከፍተኛ የሃይል እፍጋት፣ ለደህንነት የተሻለ መሆኑ እና በባትሪው ፐርፎርማንስ ላይ የአየሩ ሁኔታ ያን ያህል ተፅእኖ አለመኖሩ ነው።

GAC Aion እንዳለው የባትሪው የሃይል እፍጋት 400kw/kg ሲሆን ይህም ማለት ከተለመዱት አንዳንድ የlithium ion ባትሪዎች በ50% ብልጫ አለው። በአንድ ቻርጅም እስከ 1000kmዎች ይጓዛል።

እንደ መቆረጥ መበሳት ያሉ አደጋዎችን የሚቋቋም ሲሆን እስከ 200°c ባለ ሙቀት ውስጥም ያለምንም እክል ይሰራል።

#GAC_Aion #Hyper #Solid_State_Battery
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

አለም ላይ ላለው 80% የካርበን ልቀት ተጠያቂ የሚሆኑት 57 ካምፓኒዎች ናቸው


የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ 2016 ላይ ከተደረገው የፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነት በሗላ በአለም ላይ 80% ለሚሆነው የካርበን ልቀት ተጠያቂ የሆኑት እንደ ነዳጅ ዘይት፣ ጋዝ(Gas)፣ የድንጋይ ከሰል እና የግንባታው ሲሚንቶ አምራች የሆኑ 57 ካምፓኒዎች ናቸው።

እየተፈጠረ ላለው የአየር ንብረት መዛባት እንዲከሰት ከፍተኛውን ሚና የሚጫወቱ ሲሆን በፓሪሱ የአየር ስምነት ጊዜ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቁትን እነዚህን የግሪን ሃውስ ጋዞች እንዲቀንሱ ከስምምነት ተደርሶ የነበር ቢሆንም እነዚህ 57 ግዙፍ ካምፓኒዎች ግን ይባሱን ከስምምነቱ በሗላ ባሉት 7 አመታት ውስጥ ያላቸው የካርበን ልቀት ጨምሯል።

ከነዚህ ካምፓኒዎች መካከል ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስደው የአሜሪካው የነዳጅ አውጪ ካምፓኒ Exxon Mobil ሲሆን ባለፉት 7 አመታት ውስጥ 3.6 ጌጋ ቶን ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር ለቋል። ሌሎች ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው ካምፓኒዎች እንደ Shell፣ BP፣ Cheveron እና Total Energies ያሉ የነዳጅ አውጪ ካምፓኒዎች ናቸው።

#Climate_change #Paris_Climate_Agreement
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ማሳሰቢያ

በከተማችን አዲስ አበባ አሽከርካሪዎች በእግረኞች ላይ የትራፊክ አደጋ ከሚያደርሱባቸው መንገድች ውስጥ አንዱና ዋነኛው የእግረኞች መሻገሪያ ዜብራ ላይ ነው፡፡ በመሆኑም አሽከርካሪዎች ዘወትር በእግረኞች መሻገሪያ ዜብራ ላይ እግረኞች እስኪሻገሩ ቅድሚያ በመስጠት በእግረኞች ላይ የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ በከፍተኛ ደረጃ እዲቀንስ የበኩሎዎን ይወጡ፡፡
ምንጭ - TMA

@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Ford 43,000 SUV መኪኖችን ወደ ካምፓው ለጥገና Recall አደረገ።


Ford 43,000 ገደማ የሚሆኑ SUV መኪኖችን ጥገና ሊያረግባቸው ወደ ካምፓኒው recall ያረጋቸው ሲሆን ለዚህ ጥሪ ምክንያት የሆነውም መኪኖቹ ላይ ነዳጅ ከfuel Injector በመንጠባጠብ ሙቅ የሆነው የሞተር ክፍል ላይ አርፎ የእሳት አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል ነው።

ይሄ recallም የ2022 እና የ2023 ሞዴል Bronco Sport SUV መኪናዎች እና የ2022 ሞዴል Escape  SUV መኪናዎች ላይ ሲሆን ሁሉም ሞዴሎች ባለ 1.5 L Engine ነው ያላቸው።

Recallሉ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ታቅዶ የሆነ ቢሆንም አንዳንድ ሒስ ሰጪዎች "Recallሉ ችግሩን ለጊዜያዊነት ብቻ የሚፈታ የለበስ ለበስ ስራ ነው፤ ካምፓኒው fuel injectorዎቹ ለመቀየር የሚያወጣውን ወጪ እየሸሸ ነው !" ያሉ ሲሆን Ford ግን በዚ ጉዳይ ላይ በሙሉ ልብ የRecallሉ ጥገና ችግሩ እንዳይፈጠር የሚከላከል እና የደንበኞቼን ደህንነት የሚያስጠብቅ ነው ብሎዋል። በተጨማሪ ካምፓኒው የfuel injector የwarranty ጊዜን ያራዘመ ሲሆን ችግሩ የተፈጠረባቸው የመኪና ባለቤቶችም የFuel Injector ቅያሪ እንደሚያገኙ አሳውቆዋል።

#Ford #Recall #fuel_Injector
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የቴስላ በጣም ለየት ያሉ የዲዛይን ማሻሻያዎች።


የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ቴስላ ከተለምዶ የመኪና አሰራር ወጣ ያሉ ዲዛይኖችን በመስራት፣ የተለያዩ የእለት ተእለት ሂወታችንን የሚያቀሉልንን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች አበልፅጎ መኪናዎቹ ላይ በማካተት የሚታወቅ ሲሆን ከመኪናው የበር እጀታዎች አንስቶ እንስከ ውስጣዊ ሲስተሞቹ ድረስ አጠቃላይ ይአመኪናውን አጠቃቀም እንዲጨር የሚያረግ የዲዛይን ፍልስፍና ይከተላል።

ካረጋቸው ብዙ ለውጦች መካከል አንዱ የመኪና ማስነሻ Auxiliary ባትሪ ቴክኖሎጂው አንዱ ነው። በተለምዶ ብዙ የመኪና አምራቾች መኪኖቻቸው ላይ የሚጠቀሙት የሊድ አሲድ 12ቮልት axillary ባትሪ ሲሆን ቴስላ ግን ይሄንን የባትሪ ቴክኖሎጂ ከራሱ መኪኖች ጋር እንዲስማማ አድርጎ በሊቲየም አዮን የሚሰራ 24ቮልት ባትሪ አድርጎ ሰርቶታል።

የቴስላ የሊቲየም አዮን axillary ባትሪ ከተለምዶ የሊድ አሲድ ባትሪዎች በክብደቱ እና መጠኑ በጣም ትንሽ  የሆነ በመሆኑ በአንድ እጃችን መዳፍ ላይ ልናስቀምጠው እንችላለን። በመጠን እና በክብደቱ እነስ እንጂ ከሊድ አሲድ ባትሪዎች እጥፍ የሆነ 24ቮልት የኤሌክትሪክ ሃይልን ይይዛል።


#Tesla  #Auxiliary_Battery #Design_Evolution
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Chery ከአውሮፓ የቅንጡ መኪና አምራች ካምፓኒ ጋር ውል ሊፈራረም ነው።


የቻይናው የመኪና አምራች ካምፓኒ Chery የአውሮፓ የመኪና ገበያ ላይ ለመግባት ከፍተኛ ጥረት እያረገ ነው።በሃገረ ስፔን ላይ ተሽከርካሪዎቹን ማምረት መጀመር የሚያስችለውን ስምምነት ለማረግ እየተቃረበ ያለ ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ የካምፓኒው ፕሬዘዳንት ካምፓኒው ከአውሮፓ የቅንጡ የመኪና አምራች አጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት ሊያግ እንደሆነ አስውቆዋል።

ስምምነቱንም በዚ ሳምንት ውስጥ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ካምፓኒው ስምምነቱን ኬትኛው ብራንድ ጋር እንደሚያረግ የተናገረ ባይሆንም ከዚህ ቀደም እንድው Jaguar እና Land Rover ካሉ ብራንዶች ጋር  አጋርነትን በመፍጠር በቻይና መኪኖችን አምርቶዋል።

በተጨማሪ ፕሬዘዳንቱ ከአንድ ካምፓኒ ጋር ፕላትፎርም ሼር ለማረግ እየተነጋገረ ያለ ሲሆን ከሌላ ሁለት ካምፓኒዎች ጋር ደግሞ በጋራ ለመስራት እየተነጋገረ ያለ እንደሆነ አሳውቆዋል።

#Chery #Joint_Venture
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/22 20:28:52
Back to Top
HTML Embed Code: